Monday, July 19, 2010

መጣጥፎዎቻችሁ ይቀጥሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንዴት ሰንብታችሁኃል? እኛ ከስራ ውጥረት በቀር ጥሩ ነው ያለነው። እንደሚታወቀው ሁሉ ካለንበት ስራ ስለናንተ ማሰብ አላቆምንም ። ባለፈው እንዳስጨበጥናችሁ ፤ እንደፈለግነው የግፊቱ ንባብ ባይደርስምና ዘይቱም ወደ ባህር መትፋቱ ቢቆምም፣ ከቆቡ ጋር በተያያዘ መጋጠሚያ ላይ የሚሾልክ የጋዝ ትነት አስመልክቶ ቀጣዩን ስራ በማገት ከትላንት እሁድ የጀመርው እስከ ነገ ማክሰኞ በመራዘሙ ውጤቱን እየጠበቅን ነው ። የማስተንፈሻና የመድፈኛ ቀዳዳ ቁፋሮውም እንደቆመ ነው። ሌላው ደግሞ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ሊስማሙ የሚችሉበትን ምን ያህል ዘይትና ጋዝ አካባቢና ባሕሩን ብክለት የፈጸመውን መጠን ፣ የአሀዝ ስሌት ማግኘትና በዚያም የወንጀሉን መጠን መገመት እንዲያስችል ማድረግ ።

በተቃራኒውም የግፊቱ ንባብ ዝቅታ ካመጣ በአስቸኳይ ሎጀስቲኩን አደራጅቶ የተዘጋውን ቫልቭ ከፍቶ ነዳጁን ማውጣት የሚለው ሲሆን ፣ የት ቦታ ላይ ችግሩ እንደተፈጠረ ማረጋገጥ፣ ከዚሁ የሚፈሰውን እንዴት መቆጣጠርና መዝጋት የሚሉት አበይት ትኩረቶች ናቸው ። ካለንበት ገልፍ ደግሞ ወጣ ስንል ወደ ዳላስ ደግሞ ልንቃኝ እንወዳለን ።

ያለፈው ቀዳሚት የተካሄደውን የደበሩን አባላት ስብሰባ ከማለቁ የወሬ ቁራችን የተኩላው ብሎግ ጫፍ ይዞ እንደተለመደው ቀበዣዥሮ ተንፍሷል ። የሽኮኮውም ሆነ የመስፍን ድኅረ ገጽ አልሞትንም ቢሉም፣ እጃቸውን የሰጡ ወይም ንስሐ የገቡ ቢመስሉም፣ ማኅበረ ሰይጣነዊነታቸው (ማኅበረ ቅዱሳን) የቀበሮ ባሕታዊ መሆናቸው ወደውን አይደለም ፣ ማንም አይሞኝላቸውምና ። እንደምንሰማው ከሆነ በሜይ ሁለቱ ምክንያት ደብሩና የሚመለከታቸው ሁሉ በጋርላንድ የሚካሄደውን የተቀናጀና የተደራጀ ወንጀል ሴራ ምርመራ የተገባደደ ሲሆን ፤ የሚቀጥለው ምርመራ የሚያተኩረው በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ወደ ወንጀለኞቹ ላይ ነው ። ቪዲዮ ማንሳት መዝናኛዬ ፣ አሊያም ለመብቴ ነው የከሰስኩት የምትሉ አሁን ሁኔታው ከወገኖቻችሁ ጋር ሳይሆን የፈጠራችሁን አምላካችሁን ጭምር ነው ያሳዘናችሁት ፣ ወይንም የኃይሉ ብር ወይንም የቀዳዳው ሙላው ጠበቃ አያድናችሁም ። የሚደርሰን ወሬ እውነት ከሆነ ወዮ ለናንተ !

ሌላው በስብሰባችሁ የተነሳው የአባላት ቁጥር ጥያቄ አስመልክቶ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤት ያገደውን የስም ዝርዝር የማይሰጥ እንጂ እንደ አባልነት ማየት እንደሚቻል ነው ። ስለዚህ ጉዳይ አንተን ስለማይመለከት ተኩላው ዝጋ እንልሀለን !  አንተ ባጠቃላይ ስለዚህ ቤተ ክርስትያን መብት እንደሌለህ በምን ቋንቋ እንግለጽልህ? መፃፍም የምትችለው ገና እልምህ እውን ሆኖ በከሰስከው ጉዳይ ረተህ መብትህን ስታረጋግጥ ነው ፣ ሊያውም ከስር ቤት ከተረፍክ ነው ። አንተ ብቻ ሳትሆን ገና ብዙ ሰዎች የሚጋሩህ ስለሆነ በናፍቆት ጠብቀው ። ሽማግሌ ተብዬዎችም ስለስላም ተነፈሳችሁ ፣ ፊርማ ሰብሳቢዎችም የምትሉትን ለፈለፋችሁ ፣ ወዘተ….. እኛን የገረመንና እንደዚህ ለሁለት የከፈላችሁን ነገር በእውነት ማየት ወይም መቀበል ለምን አቃታችሁ?
1ኛ/ ፖለቲካን ከመካከላችሁ አርቁ
2ኛ/ዘርኝነትንና ጎጠኝነትን  ከራሳችሁ ለዩ
3ኛ/ እምነታችሁን መርምሩ ፣ ሀይማኖታችሁን እወቁ

በዚህ ከተስማማችሁ በመካከላችሁ ያለው ልዩነት በኖ ይጠፋል ። እኔ ብቻ ወይንም የኔ የሚለው የህጻን አስተሳሰብ ጠፍቶ እኛ ወይንም የኛ ማለት ሲጀመር መተሳሰብና መከባበር ይጀመራል፣ እንደ ክለብ ቤት መሆኑ ቀርቶ እንደ ቤተ እግዚሐብሔር ሆኖ ይከበራል ። እስቲ ሕሊናችሁን ሰብስባችሁ ሀይማኖት ማለት ምን እንደሆነ ለመገንዘብ ሞክሩ መልሱን ታገኛላችሁ። የናንተ ችግሩ ቦርዱ አይደለም። ቦርዱ ቢለወጥ ያለው ሒደት አይለወጥም፣
ከአንድ በላይ የተደራጀ ወገን ያለበት ምን ጊዜም ሰላም አይኖረውም፣ ዛሬ ይኼ ቢያሸንፍ ነገ ሌላኛው ተራ ሊያገኝ ይችላል፣ እስከመቼ? ለቀጣዩ ትውልድ ምን እየተዋችሁ ነው? እንግዲህ ይህን ለመረዳት የመንኮራኩር ጠበብት አያሻም እንዲሉ !  እራሳችሁን መርምሩ? የኦርቶዶክስ እምነታችሁን ተገንዘቡ ? ነው የምንለው ። በተለይም አሁን ገናችሁ ያላችሁትም የቦርዱም ደጋፊዎች በቅርቡ ከተቃዋሚዎች ጋር ንግግር መጀመራችሁን ሰምተን ነበር የት እንደቆመ ባናውቅም ጥሩ ጅምር ነበር ። እንደኛ ግን ውይይቱ ግዳጃቸውን እየተወጡ ካሉ አባላት ጋር ብቻ ቢሆን ጥሩ ነው እንላለን ። ከሳሾቹም ቢሆኑ ቤተ ክርስትያኑ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆን ያስታወቀው በቀድሞው ቦርድ ጊዜ ነው ። አቋሙ ዛሬም አልተለወጠም ። ከውይይት በፊት የሕጉ መስመር መዘጋት አለበት ይኽ ደግሞ የሁለቱም ወገን የሕግ አማካሪ የሚስማማበትና ጠበብት መሆን የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለምና ሁለቱም ወገኖች ፈሪሀ እግዚሐብሔርን ያስቀድሙ እንላለን።

ባለፈው ጽሁፋችን እንዳሳሰብነው ቦርዱ ካፋችን የነጠቀን ቢመስልም የክስ ክስ ጉዳይን በአጀንዳው  ላይ ለተሰብሳዊ ማቅረቡን ይግፋበት ስንል አባላት ሙሉ ድጋፍ ትሰጡት ዘንድ አሁንም ክርስትያናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን? ሌላው የቤተ ክርስትያኑ  የሒሳብ ሰራተኛ ድርጊት ብዙዎች እያዘኑበት የፃፉልንን አንበናል ግን ቦርዱ በአሁኑ ሰአት ሊያሰናብተው ያልፈቀደበት ምክንያት ሊኖረው ይችላልና ታገሱ እንላለን ምክንያቱም ከሲደልል ጉዳይ እንማር ። እንደዚሁም ስለ ፀሐፊዋም ባል ያላችሁት ከተጀመረው ምርመራ በኃላ ወይም እራሱ አሊያም ለቦርዱ ለጊዜው መተውን እንመርጣለን። በተረፈ መጣጥፎዎቻችሁ ይቀጥሉ እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

1 comment:

Anonymous said...

ኧረ ለመሆኑ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እንዲሉ ይኸ ሂሳብ ሰራተኛ ምን ያህል ገንዘብ ቢዘርፍ ነው እንዲህ ህይወቱን እስኪስት ድረስ የሚወራጨው? እሱና አጎቶቹ ያመጡት ኦዲተር ሳያሞካሻቸው ለምን ሄደ ነው? ወይስ ሚካኤል እንደተለመደው ሰይፉን እያሳያው ነው? ቦርዱ የወንጀለኛ ጥርቅሙን የፈራ ይመስላል። ባይፈራስ ክስ፤ ይግባኝ፤ ሌላ ክስ፤ ወዘተ.. እንዴት ይሁን? በቤተክርስቲያን ውስጥ ሌቦች የሚሞገሱበት ደህናዎች የሚሰደቡበትና የሚረገጡበት ዘመን ደረስን፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ይፍረድ እንላለን። እንዳበደች ውሻ እየተራወጠ ብሎግ አልጻፍንም ብላችሁ ማሉ ሲል የከረመው ማፈሪያ ስብሰባው እንዳለቀ ጅሪውን ሰብስቦ ቦርዱን ሲያነጋግር አይተን ጉድ ስንል፤ ቦርዱን ሲያሳቅል የከረመው ሁሉ ሚዳቋ እንኳ ሳይቀር ከቦርዶች ጋር ውይይት መያዛቸው እንኳን አባላቱን ሚካኤልንስ ሳይገርመው ቀረ ብላችሁ ነው? በመጨረሻ ሰርጎ የገባውስ ከሳሽ እንዴት ሊገባ ቻለ? እንዴትስ የመናገር እድል ተሰጠው? አጠያያቂ ጉዳይ ነው። ክርስቶስ ቤቴ የሌቦች ምሽግ አይደለችም እንዳለው ሁሉ፤ ሌቦች ከቤተክርስቲያን ራቁ ወደሚሰረቅበት ሂዱ። አሁን ያለውን ቦርድ እውስጡ የተነከረው መዝገብ ያዥም ሊያታልለው አልቻለም እንኳን እናንተ።