Friday, July 16, 2010

ጥሩ ቀን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



እንደምን ከረማችሁ? ለናንተም ለኛም መልካሙን እየተመኘን በትላንትናው እለት መሪያችን ብራክ ኦባማ ‘ጥሩ ቀን‘ ያሉት ወግ ያለው አባባል ነው እኛንም ደስ ብሎናልና እናንተንም ደስ ይበላችሁ እንላለን።

በአካል በመካከላችሁ ባንሆንም እዚህ እስከ እሁድ የምንጠብቀው የግፊት ንባብ ማረጋገጫው የመጨረሻው እለት እንዲሳካልን በጸሎታችሁ አትርሱን ፣ በዚህም አጋጣሚ የ11ዱን ሕይወታቸው ያልፉትንና ቤተሰቦቻቸውን እያሰብን አሁንም እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ሌሊትና ቀን በተለያየ ሥራ ላይ ለሚሰሩት ሁሉ ብርታቱን እንመኛለን። ኦባማም ሁሉም ቫልቮች በመዘጋታቸውና ሰኔቱም የባንኩን አዲስ ሕግ በማጽደቁ ነበር ጥሩ ቀን ያሉት። እኛም ከዳላስ ከመውጣታችን በፊትና እዚህ ገልፈ ከገባን ጊዜ ጀምሮ በአፕሪል 28 አደጋ የፈነዳውን በገልፍ ባሕር ውስጥ ከማይል በታች ዝቅታ የሚገኘውን ባለቤትነቱ የእንግሊዙ ቢፒ የዘይት ድርጅት ወደ ባሕር ውስጥ የሚተፋውን ጋዝና ዘይት መቆለፍና መዝጋት ከዚያም የተፈጠረውን የአካባቢ ብክለት መቆጣጠርና ማስወገድ ላይ ያተኮረ ስራ ነው።

ከዚህ በፊት በሰው ሰራሽነቱ ተፈጽሞ የማያውቅና ከተለያየ ሙከራና ጥናት በኃላ የተገኘ ውጤት በመሆኑ የሚያስደስትና የሚያኮራ ውጤት ነው። የኛ ክፍል ግምገማ ይህ ዘዴ 60 ደቂቃ እንደፈለግነው ከሰራ ይሰራል ስለዚህ ሌላ መስመር ግፊቱን ካልቻለና ሌላ ቦታ ላይ እንዳይፈነዳብን ፣ ከሆነስ እንዴት የሚለው መላምት ላይ ነበርን። እንደ ቆብ የተሰራው ክዳን ቫልቩ ከመዘጋቱ በፊት በከፍትኛ ደረጃ መፈቀድ ስላለበት ለጊዜው ቢዘገይም በመጨረሻው በመሆኑና በምናየውም ውጤት በመደሰታችን ደስታው የሁላችንም ዜጎች ብቻ ሳይሆን ለአለምም አዲስ ውጤት ነው። በአሁን ሰአት በናፍቆት የተጠበቀው የሶስቱ ቫልቮች መዘጋትና አዲሱ ክዳን ግፊት የመቆጣጣር አቅምና የዚህ የነዳጅ ጉድጓድ ጋር የተያያዙት ማንኛውም የነዳጅ መስመር ጤንነት አስተማማኝነት ከተረጋገጠ ትልቁና ዋናው ችግር በቁጥጥር ስር ዋለ ማለት ነው። 2ኛው ተግባር ይህንን ጉርጓድ መግደል ወይንም መድፈን ነው። ከዚህ ጎን እየተካሄደ ያለው የብክለቱን ጽዳት ስራ ነው። አሁንም በየደረጃው የሰው ኃይል ፍላጎቱ ያለ ሲሆን ብዙ አሳ አጥማጆች የነበሩት በተለያየ ስራ ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ነው። እስካሁን ከሁለት የኢትዮጵያ ተወላጆች ውጭ ሌላ አላየንምና ወደዚህ አካባቢ መሰራት ለሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ የቢፒ ነዳጅ ድርጅትን ድህረ ገጽ ደጋግመው ይጎብኙ ዘንድ እንጠቁማለን።

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር በነገው እለት ጠቅላላ የአባለት ስብሰባ የጠራ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ስብስብ ያለፈባቸውን ድክመትና ጥንካሬ ይገመገማል ። በተለይ ትኩረቱ የተመዘበረውን የደብሩን ገንዘብ የሚመለከት መሆኑን ቀደም ሲባል ተገልጣል። በርግጥ ገንዘብ ጎድሏል። የሚሰራ ሁሉ ይሳሳታልና በስህተት የተፈጸመ ከሆነና አጠፉ የተባሉት አምነው ይቅርታ ከጠየቁ ይቅርታ ሊደረግላቸው ይገባል ስንል ፣ የሚክዱትን ግን አስፈላጊው እርምጃ ቢወሰድባቸው ቅሬታ አይገባንም ክርስትያኖች ነንና።

ሌላው የአመራር አባሎች በቁርጥና ወሳኝ ሰአት ላይ ፌርማታችን እዚ ነው ብልው ኃላፊነታቸውን ጥለው በወረዱት ብናዝንም ፤ ደብሩ ከመዘጋት ወደ አለመዘጋት ፣ ከወንጀል መድረክ ወደ ቅድስና መቅደስ ፣ አባላትና ምእመናን ከመበታተን ወደ አንድነት ፣ ወዘተ……. ያመጡ የአመራር አባሉ፣ ካሕናቱ፣ አባላቱና ምእመናኑ ሁሉ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ፣ አሁንም በርቱ ፣ጽኑ፣ በምህላውንና በጸሎቱ ቀጥሉ እንላለን ።

ሌላው ከዳላሱ ወዳጃችን የሰማነው ቢኖር የቤተ ክርስትያኑ ከሳሾች ስለኛ ብሎግ ወይም ድኅረ ገጽ ቤተ ክርስትያኑን በሕግ የዲስከቨሪ ወይንም የማስረጃ ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው። በግርግር መነኩሴው ገዘቱ እንጂ ነገሩ ከወዲያ ነበር። እኛም በቁጣ ለጻፍነው ሁሉ ይቅርታ እየጠየቅን አሁንም በኛ ገጽ ቦርዱ እንደማንም ያነበው እንደሆን እንጂ ከደሙ ንጹህ ነው። ከሳሾቹማ ዘግቶባቸው ነው የሚገርመው እነሱን የወከለው የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ተብዬው ነው ይህን የመሰለ ጽፎ መጠየቁ ። ብሎግ ምን እንደሆነ የማያውቅ ከሆነ እንደነ እንቶኔ የተጠራጠረውን አሊያም የደበረውን ሁሉ አንተ ወይም አንቺ ናችሁ እኔን በተመለከተ ነቀፌታ የጣፋችሁብኝ ፣ ማሉልኝ አለ እያሉ የከተማው መተረቻ አደረጉት ያሉት ቢጤ የሆነ ጠበቃ።

ከሳሽና አስከሳሾችም ምንም መብት የላቸውም ደብሩን ለመክሰስ። የየዋህነት ይሁን ድንቁርና ከእምነት ውጭ ደብሩን በፈለጉት መንገድ ባለመሄዱ እንደ ህጻን ያኮረፉ ብቻ ሳይሆን የስነ አእምሮ ችግር እንዳይሆን እንጂ፤ ለደብሩ ቫን፣ ቲቪ ፣ መጋረጃ ፣ መብራት ፣ ገንዘብ ፣ ወዘተ……. በመቸር የፈለጉትን ተጽእኖ ለማድረግ ወይንም የእግዚሐብሔርን ቤትና መንግሥት በአዱኛ ለመግዛት ነውን? እኛ የፈለግነውን ለማግኘት ደብሩን በሕግ በመክሰስ የገንዘብ አቅሙን በማዳከም ፣ ምእመናን ገንዘብ እንዳይሰጡ መቀስቀስ ፣ ምእመናንና አባላት መካከል ብሎም ቀሳውስቱን መከፋፈል ነውን? ሁሉም ከሸፈባቸው ፣ ፈረሰባቸውም ፣ ሁሉም የሰይጣን ስራ ነው ፣ የኛን ኦርቶዶክስ እምነት ከሌላችሁ ከኛ የተለያችሁ ናችሁ አላችኃቸው ፣ ከማህበር ሁሉ ለያችዋቸው ፣ ትመለሱ ይሆን ብሎ ታገሳችሁ ፣ አስመከራችሁ ፣ አልተቀበሏኣችሁም።
 እንግዲህ ደብሩ ቢተዋችሁም ፤ የሚቀጥለውን ጥሪ ለደብሩ አባላት እናቀርባለን።

ለቅዱስ ሚካኤል ደብር አባላትና ምእመናን ሁሉ፡- ቦርዱ ከሳሾቹን እስካሁን ስላልከሰሰና ወደፊትም የሚከስ ስለማይመስል፤ እያንዳንዳችሁ የደረሰባችሁ የስነ ልቦና፣ የሶሻል፣ የባሕልና የሀይማኖት ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ፤ እነዚሁ ግለሰቦች ያለማቋረጥ በአምልኮት ጊዜዎቻችሁ ሁሉ ከቤተ ክርስትያናችሁ ከጎናችሁ በመሆን የእንቅፋት ተጽኖ በመሆን፤ አባል ሳይሆኑ ቤተ ክርስትያናችሁንና የመረጣችኃቸውን ኃላፊዎችን በመክሰስ፣ ስም በማጥፋት ፣ ምእመናን አባል እንዳይሆኑ በመቀስቀስ ፣ ምእመናን ገንዘብ እንዳይሰጡ ዘመቻ በማድረግ፣ ወዘተ…….የተወሰናችሁ በፌደራል ፍርድ ቤት ደረጃ ከሳሽ በመሆንና የተቀራችሁት ደግሞ የገንዘብ እርዳታ በማድረግ፤ ይህንም ተግባር እንዲሆን ቦርዱ እንዲተባበር በነገው ስብሰባችሁ ላይ እንድታነሱትና በሚያመች መንገድ ሁሉ እርምጃ በመውሰድ እንድትገብሩት በአክብሮት  ክርስታናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

ከዚህ የሚቀጥለው ደግሞ ከዚህ በፊት እንደጠየቅነው ሁሉ ጥሩ ውጤት እያመጣ ያለው የዳላስ የኢትዮጵያ ቀን አከባበርን በተመለከተ ነው። ይህ በወያኔ ሎሌዎች የሚቀነባበርው ዝግጅት የተደጋገመ እክል እያጋጠመው መሆኑን የዳላስ ምንጮቻችን አልሸሸጉንም። ዝግጅቱም ይሰረዝ ይሆናል የሚል ግምትም አለ። አሁንም የኛ አቋም አልተለወጠም። የኮሚኒቲውም አመራሮች ወያኔዎችን ሙጥኝ እንዳሉ ስልሆነ በዚህ ዙርያ ለአምዳችን የገለጹት የለም። ስለዚህ በዳላስና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ተወላጆች ሁሉ አቋሟቸውን አንድ እያደረጉ በማንኛውም ዘርፍ እንደማይሳተፉ ከሚደርሱን ጽሑፎች እየተገነዘብን ነን። በየትኛውም አለም ውስጥ ተሰምቶ የማይታወቅ 99.6% አሸንፌ ነው ስልጣን የያዝኩት የሚለው ወያኔ በትውልድ ሀገራችን ውስጥ የሚፈጽመውን ሰቆቃ የዳላስ ነዋሪ ሕብረተሰብ ዘንድ እንዳይጋለጥ አንዱ መሳሪያ ያደረገው ይህንኑ መረዳጃ ማህበርን ነው። ከዚህ ቀደም ባሉት ጽሑፎቻችንም ብዙ ብለናል። አሁንም የዳላስና ፎርትወርዝ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማሕበር ከወያኔ ሎሌዎች ይጽዳ !  እንዲጸዳም ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽዎ እንወጣ ዘንድ እየጠየቅን ከመጪው ‘የኢትዮጵያ ቀን በአል“ እራሳችንን የማግለል የትውልድ ግዴታችን መሆኑን እናስገነዝባለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

ይድረስ ለዳላስ ኢኦቲስ ብሎግ፡
ያለፉትን ጽሁፎቻችሁን ወይም እናንተ እንደምትሉት መጣጥፎቻችሁን ስንገመግም አንዳንድ ልብ ያልናቸው ለናንተ ላይጥሙ የሚችሉ አስተያየቶች ፈልቀውብናል።
1.ጽሁፎቻችሁ ከግማሽ በላይ ቦርዱን የሚደግፉ ሆነው አግኝተናቸዋል።
2.ለቤተክርስቲያን እንደምትቆረቆሩና እንደውም ለሃይማኖታችሁ ስትሉ ሰማእት ለመሆን እንደምትሹ ይነበባል።
3.ከዋያኔ ጋር ለመደራደር የምትሹም ትመስላላችሁ።
4.ከሉዘር ተኩላም ጋር ቅርበት ሲኖራችሁ ግን በሩቁ ልትገፈትሩት እንድምትፈልጉ ይታያል።
5.የህብረተሰቡን የማንበብና የመረዳት ችሎታ የገመገማችሁ አይመስልም።
6.ነባር የቤተክርስትያን አባል ከሆናችሁ የቤተክርስቲያኗን ታሪክ በቅደም ተክተል ብትዘግቡ።
7.ሚካኤል የሰራቸውን ተአምራትና የእግዚአብሔርን ሃይል የናቁና ቤተክርስትያኑን ያረከሱ ሁሉ ምን እንደሚጠብቃቸው ያውቁ እንደሁ ቢጠየቁ።
8.6ዘረፋ……ዘረፋ……ዘረፋ፤ እነማን? ከነኢዩኤል፤ መላኩ፤ አራጋው፤ ክነግብረአበሮቻቸው ልታጣሉን ነው? ወይስ? ከተዋበች አቤት አቤት ሞኝ መስላ ድምጿን አጥፍታ ዘረፈች ጋር ልታውዳጁን?
9.ወቸ ጉድ!! ለምን ይኸ ሁሉ ጦርነት ተፈጠረ? የተደራጀ የሕዝብ ቤተክርስትያን ነጥቆ ለጳውሎስ/ለወያኔ ለማስረክብ? ወይስ የዘረፍነው የሕዝብ ገንዘብ ሳይታወቅብን በሁሉም መንገድ ችግር እንፍጠር፤ እንክሰስ፤ አመጽ እናስነሳ፤ ቢላችንን እንሳል፤ መውዜራችንን እናጸዳዳ…ወዘተ።
10.ኧረ ለመሆኑ አለማየሁ የሚባል ሌባ እምን ገባ? እሱን የበላ ዥብ አልጮህ አለሳ? ያችስ ከአቡነ ይስሃቅ የሰረቃት አንድ መቶ አምሳ ሺህ ብር እምን ገባች? እነሻምበልስ ያውቁ ይሆን? ነው ወይስ? እነተኩላ? እነእንቶኔስ?
11.ይኸን ቦርድ አዚማቸውን አዞሩበት ይሆን? ኧረ በአዛኚቷ ሁላችንም ይኸን ቦርድ እንርዳ!!
12.መውጫ ቀዳዳ ጠፍቶአቸው እነወያኔና እነሆድ አምላኩ፤ እነጭራሮ እግር፤ እነሚዳቋ ወዘተ… እንዳአይጥ መርመስመስ ሲጀመሩ፤ ሃፍረት የማያውቁ ሌቦች እንታረቅ እያሉ የአንዳንዱን ቦርድ ሆድ አባብተውታል ይባላል።
አይ ሰይፈ ሚካኤል ስንቱን ጉድ ችለህ አሳለፍክ? አሁንስ እንዴት ጨከንክ?
ገና ገና ገና የእግዚአብሔር ስራ መች አለቀና!!

Anonymous said...

እስቲ ለዚህ መጣጥፍቻሁ ይረዳ እንደሁ ይኽው ባለ 99.6% ተመራጭ ነኝ ባይ ወያኔ ከዚህ በፊት 90 ሚሊዮን ዶላር በጀት መድቦ ዳያስፖሮውን ልበትን፤ ልበጥብጥ፤ ቤተክርስቲያንን ላፍርስ ብሎ እነዚህን ሆዳሞች ሲመለምል ያወጣውን 52 ገጽ መመሪያ ለዚህ ሕዝብ አቅርቡለት እና እነዚህ የበግ ለምድ ለብሰው በመሀከላችን የሚሽሎከለኩት ተኩላዎች የታሪክ አተሎች ወያኔ ወንድሞቻቸውንና፤ ሃይማኖታቸውን እንደይሁዳ አገራቸውን ሳይቀር ለገንዘብ እንዲሽጡ እንዴት በብር እንደባሪያ እንደገዛቸው እስቲ ለሕዝቡ ተንትናችሁ አስረዱላቸው። ሕዝቡም ወዳጅና ጠላቱን ለይቶ ይወቅ፤ በግ ከአራጁ ጋር ይውላል እንደሚባለው አብሮ እየበላ እየጠጣ ከሚታረድ ይወቀውና ይለይለት!! 52ቱን ገጽ ከዚህ ታገኙታላችሁ፦

http://ethiomedia.com/carepress/document.pdf