Wednesday, November 3, 2010

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የሰሞኑ የዳላስ አየር ዝናብና ቅዝቃዜ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበሩንም ሆነ ቤተክርስትያናችሁ ውስጥ ውስጡን የነካካውንና የገባው አዲስ አየር የአንዳንዶችን ጎራ ጠአሙን እየለወጠ ይገኛል። በተለይም የወይዞሮዋ ጦመር ያስበረገጋቸው የሀሳብ ድውያኖች የመጣባቸው ቀዝቃው አየር ሳይሆን ሀፍረትና ክስረት ከየአደባባዩ እያሸሻቸው ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? በእርሱ ፀጋና ምህረት ለዚህ ያደረሰን እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱና ለገናና ስሙ ይሁን። አሜን።

ያለውንና ያለፈውን የዳላስ ኢትዮጵያ ተወላጆችን ስናስታውስ ፤ እንኳን ከዳላስ እራቅን ብለን ለመዳዳት ቢፈታተነንም፣ ላለን የወገን ክብርና ፍቅር ግን ምነው ገለባውን ሳንለይ አፋጥነህ ያወጣኸን የሚል ወኔን ያገሳናል። ይኹንና ካለንበት እርቀቱ ሳይገታን ሀዘንና ደስታችሁን እንድንካፈል ለተቀደሰውም ትግላችሁ በፀሎትም ሆነ በሀሳብ አብረናችሁ በመጓዝ ከቀን ወደቀን የምትከፍሉትን መስዋዕትና ፍሬ በማየት በውስጣችን ያበራችሁትን ተስፋ ወሰን የሌለው በመሆኑ ለሠራዊት ሁሉ ጌታና ፈጣሪ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ከንቅቡ ተንገዋለው ከወደቁት ውስጥ እንደ ክፈተው ነጋ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፊርማቸውና ፎቶግራግ ታሪካቸው ተጠርዞ ገበያ ላይ ረክሶ ወድቆ ይገኛል። ከሩሲያዊያን ዘንድ ሲጀመር ያልነበረው እንደነበረ በሞቀበት ሁሉ እየገባ ሙሾ ማውጣት የሚወደው ክፈተው ዛሬ ደግሞ የነእስስቱ አለቅላቂ እንደዚሁም ጭፍራ ሆኖ መገኘትና ደብሩን በተለያየ መንገድ መውጋት ስራዬ ብሎ የያዘው፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን ይዞ መነኩሴ ካህኑን ለመደለል ከስውር ወደ ገሀድ ገብቶበታል። ከ፩፪ አመት በፊት ደብሩ እንዳይቀጥራቸው ከወሰኑት ውስጥ አንዱ የነበረና በወቅቱ የሕግ ወጥ ቁማር በማጫወት ተዳዳሪ የነበረው ክፈተው ነጋ (ኢዮኤል) ከሳምንት በፈት በዋለው ሰንበት አርፍዶ ወደ ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ወደ ፊት ዘልቆ የተቀመጠው፣ እንደምዕመናኑ ተባርኮ እንደመውጣት፣ እርሱ ግን እስከመጨረሻው ቆይቶ መነኩሴው ጨርሰው ሲወጡ ጠብቆ ሲጠቀጥቃቸው የተመለከቱ ሁሉ ግርሞታቸው በፈታቸው እንደሚነበብ ፤ መነኩሴውም ቤሆን ሲሸሹት እንደከረሙና ቀንና ሰአቱን ተጠቅሞ የእልህ ድርጊትና መንፈሳዊነት የጎደለው አቀራረብ እንደነበር፣ እንደዚሁም የእርሳቸው ችኮላ ፈቃደኛ አልመሆናቸውን እንደሚያሳይ በቦታው የታዘቡትን አካፍለውናል።

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያን ድርጊታቸውን የጀመሩት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትና አድገውም በዳላስ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር ውስጥ ቢሆንም፤ በደበሩ ውስጥም በነበረው ችግር ዘው ብለው ሲገቡ ለሀይማኖታቸው በቆሙ ተገተው አሁን ለመበርከክ በቅተዋል። እነሱ መጀመሪያ ሸማቸው ከመቆሸሹ በፈት የራሳቸው ጭቅቅት ወደ ሸማቸው የተላለፈ መሆኑን ዛሬም አልገባቸውም። ብዙዎቹም በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ወደ ውጭው አለም ተልከው እስከ ዶክተርነት ማዕረግ ትምህርት የደረሱና ያስተማራቸውንም ሕዝብ የካዱ፣ ዕውቀታቸው የከፈተላቸውን ብርሀን ከመጠቀምና ለሀገራቸው ዕድገትን ከማምጣት ይልቅ ከስርዐቱ ጋር ተቆላልፈው አብረው የወደቁ ቅድመ አብዮትና የነሱ ጸር ሆነውም ገሚሱ አብዮተኛ ሌላው ተቃራኒ ሆነው ሀገርና ያጠፉ ብለውም በንጹህ የወገን ደም የታጠቡ፤ ዛሬ ደግሞ በሰከነ እድሜና ወደ ሞት በመጠሪያ ዋዜማቸው ንስሀ ገብተው በጎ እያደረጉ መጠሪያ ሰአታቸውን ከመጠባበቅ ይልቅ፤ በከተማችሁ የወያኔ ሎሌነትን መርጠውና ታዛዥ ሆነው በሱ መመሪያ ለሱ ስጋት የሆኑትንና ወደፊትም ስጋት ይሆነኛል ብሎ የሚያስባቸውን በራሱ ቅጥረኛ መቆጣጠር ካልሆነም ማጥፋት በሚለው የተሰማሩ ሆነው ተገኝተዋል። በቅርቡ ቅንጅት የተባለውን የከተማችሁን ድርጅት እንዴት ለሁለት እንደከፈሉትና እንዳከሰሙት። ከዚያም ደጀን ብለው የወያኔ ምርኮኛ እንዳደረጉት እናንተው ምስክሮች ናችሁ።

የማይበራ ባትሪ የሚሉት የተገንጣዩ ቅንጅት ደጀኔ ለአምስተኛው አመት የምርጫ ፱፯ ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰውትን ለመዘከር የበተነውን  በራሪ የላኩልን ተባባሪያችንን እያመሰገንን እንደ ሞኝ የራሱን ቁጥር አክሎበታል። እኛ ግን ከኃላው ያሉትን እነ ኪዳኔ አለማየሁ፣ በትሩ ግ/እግዚሀብሔር፣ ተፈራወርቅ አሰፋና ወዘተ ….. እንድሆኑና እነርሱም ይህንኑ ቀን በማስመልከት በዳላስ ስም ሰፋ ያለ ጊዜ በቴሌ ኮንፍረስ ያሳለፉና ይህንንም በተመለከተ ነዋሪው ግንዛቤ እንዳይጨብጥ አፍነው ይዘው የከረሙ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ለወያኔ መረጃ አስተላላፊ እንደነበሩ ያገኘነው መርጃ ያረጋግጣል። በተለይ እነዚህ ፫ ግለሰቦች ዳላስ የገቡት አላማናተልዕኮ ይዘው ነው። ለዚህም ነው ከዳላስ በፊት የነበረው ሕይወታቸው፤ ሸማቸው ላይ ውኃ በማፍሰስ የሚጠራ አይደለምና በተለይ የአሜሪካውን ለመቃኘት ጉግልም ይበቃል የሚያሰኝ።

አንዳንድ የዋህ የሆኑ በመረዳጃው ማህበር ስር የተቋቋመውን እድር በተለየ መልኩ ሲመለከቱት ታይተዋል። ሀቁ ግን የተለየ ነው። የመረዳጃው ማህበር አገልግሎቱና ሕጋዊ ፈቃዱ ፈፅሞ ከእድር ጋር በማንኛውም መንገድ የማይገናኝ በሕግ ወጥ መንገድ የተለጠፈ ድርጅት ነው፤ የ አይ አር ኤስ ህግን ያልተከተለና የተላለፈ ነው። ያለ ውዴታ በግዴታ በአመት ፵ ዶላር ከእድር አባሎች የሚነጠቀው ገንዘብ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው። መረዳጃውም ይቀበል ከሆነ ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ሕግን በተጻረረ መንገድ ለእድሩ ጃንጥላ መሆኑ በራሱ ሕግን ተላልፎ ተጠያቂ ያደርገዋል። ሰሞኑን ምርጫ ተብሎ በእድሩ ስም የተጠራውና የሚካሄደው ማን ያቦካውንና የጋገረውን ማን ሊቋደስ እንደሆነና ማን ላይ ለመላከክ እንደሆነ ባይገባንም፤ እንደ ጀመሩትና እንደ አደራጁት እድሩ ከማህበሩ ተነጥሎ ራሱን እንደ ክለብ አሊያም የንግድ ድርጅት አድርጎ በትርፋማነት ለመንቀሳቀስ ባስቸኳይ ካልሆነ ፤ ነገ እስከነ አካቴው መረዳጃ ማህበሩንም ያጠፋዋል። የማይሆንም ከሆነ የቀረውን ገንዝብ ተከፋፍሎ ወይንም ለመረዳጃው ማህበር አሊያም ለተመሳሳይ ግብረ ሰናይ ተሰጥቶ መዘጋት የሚገባው ነውና። ይህንን የማይቀበል ወይንም ጥርጣሬ ላለው የራሱን የሕግ ባለሙያ ምክር መሻቱ ተገቢ ነው ስንል፤ የቀብር መድህን ዋስትና ግን በአይነቱም ሆነ በጥራቱ እንዲሁም በዋጋው አሁን አባላቱ ከሚከፍለው ጋር ማስተያየቱ ልዩነቱን ለማወቅ አያውክም።

ለመቛጫ ወደ ደብሩ ስንመለስ ቀደም ብለው ከቤተ ክርስትያኑ እርቀው የነበሩትና ቅያሜ አላቸው የሚባል አሉባልታ የሚናፈስባቸው የነበሩት ሁሉ ዛሬ ወደ ምንጩና ወደ ቤታቸው ተመልሰው ይገኛሉ። እንደ ምንጮቻችን አጠያየቅ የተረዱትን ሲያካፍሉን ፤ እነዚህ ወገኖቻችን እኛ ወደ ድብራችን የምንመጣው አብረን በህብረት ፈጣሪያችንን ለማመስገንና በሁላችንም ደስ እንዲለው ነው። ነገር ግን በእርሱ ቤት እርሱንም እኛንም የሚያሳዝነን ልናይ ስላልፈቀድን ፣ እዚህም በህብረት ባልጸለይንበት ጊዜ መጥተን ከውጭ ተሳልመንና ጸልየን ከመሄድና በያለንበት ተመሳሳይ የግል ጸሎታችንን ስላላቋረጥን መልሱን ስናገኝ ይኸው ተመልሰናል ብለው የነገሯቸውን ለኛም አካፍለውናል። እግዚሀብሔር አሁንም ይስማችሁ ነው የምንል። በሌላ በኩል አዲስ አባልነት ለመመዝገብ ጥያቄዎች እየበዙና እየተስተናገዱ ሲሆን አሁንም ቅሬታ አለን ብለው ከከሳሾች ጋር የወገኑና ራሳቸውን የቅዱስ ሚካኤል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው የሚጠሩና የቦደኑ አሁንም በአባልነት ያሉ ፲ የማይጠጉ ግለሰቦች ናቸው። እንደሚታወቀው ሁሉ የከሰሱም ሆነ በዚህ ቡድን የታቀፉት በሙሉ የደብሩ አባላት ያልሆኑ መሆናቸውን ለማንም የተሰወረ አይደለምና። እነዚህም ጥቂት ግለሰቦችም ቢሆኑ አላማና አጀንዳ ያላቸውና ዘወትር እንደ ውዳሴ የሚሉት የወያኔ የ፶፪ ገጽ ሎሌ እንጂ ምንም አይነት የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ዕምነት የሌላቸውና መተግበሩንም ለማስመሰል እንኳን አልሆን ያላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያንና እንደዚሁም ጸረ መረዳጃ ማህበር መሆናቸውን በተግባር ያስመዘገቡ ናቸው። በተለይም መለከት በተባለው ገጻቸው በሴብተምበር 25 የቃዡትን በትላንቱ ዕለት በተደረገው የውስጥ ስብሰባ ላይ ቅዠት ተብሎላቸው ተደምድሟል። እነሱ የተከሏቸውና አስርገው ያስገቧቸውም እነፍቅረማርያም ሚስጥሩ ደርሷቸው ባይገኙም የበላይ መሪና አማካሪያቸው የሆነውና በሌላ ቡድን ያሰረጉት መልዕክቱን በሚገባ የተረዳው መሆኑን ተቀብሎታል ሲል የሚካኤል ሰይፍ ወኪል ካዛገበን ተረድተናል። በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት በሙሉ የዕምነቱ አማኞችና ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ከስራቸው የሚመራቸውና ያቀፏቸው በጎሳና በዘር የታቀፉ፣ በማህበር ፣ጥዋና በመሳሰለው በተለያየ  ከሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ የተመረጡትን አቅፎና ተደራጅቶ የያዘ የደብሩ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጨምሮ አስገንዝቦናል። በዚሁ ስብስባ ላይም ደብሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ፣ የአባላትም ተሳትፎ ከፍ ያለ፣ የሚያኮራ ውጤት ላይ መድረሱንና አስተዳደር ቦርዱም ዕቅዶቹን ለመተግበር እያደረገ ያለው አመርቂ መሆኑን ተገልጧል። የምዕመናኑም እጅ ተከፍቶ ለደብሩና ለቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት የሚያደርገው እርዳታ እያደገ ይገኛል ፤የተጨማሪ የትምህርት ክፍል ጥያቄ ወሳኝነት ደረጃ ላይ መድረሱም ተወስቷል።

በሚቀጥለው ጥሁፋችን በቸርነቱ እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኃለን።


እርሶስ ምን ይላሉ?    

2 comments:

Anonymous said...

ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ? እንደው ለመሆኑ ይኸ ክፈተው ነጋ የምትሉት ወንበዴ ማን ነው? ያ ድሮ ግሪን ፌስ የምንለው ወንጀለኛ በፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ ላይ ስናነበው የነበረው ነው? ወይስ ሌላ? ደሞስ የታልቦትንና የፍልውሃውን ታሪክ ጭምር የሚያስታውሰን ብዙ የሚጣፍ ታሪክ ያለው እኮ ነው። የናቡቴው መክለፍለፍና ማምታታትማ ዛሬ አዲስ የተጀመረ ሳይሆን ከጥንት ነው። ሁለት መጽሀፍ የሚወጣውን የታሪክ ማህደሩን ከስር ከመሰረቱ መጀመሩና መዘገቡ፤ ለሱም ቢከርሙ የተረሱ የመሰሉትን የወንጀል ትዝታዎች ማስታወሻ፤ ለሌላውም ሰው ታሪኬን ማንም አያውቀውም ብሎ ሲመጻደቅ የቆየበትን የእግዚአብሔር ቤት እንዴት አድርጎ እንደቀለደበትና እንዳራቆተው፤ የሃይማኖቱም ልክ እስከምን ድረስ እንደሆነ ማስገንዘቡ የታሪክ ግዴታና ሂደት ስለሆነ ዘገባው በተከታታይ ይቀርባል። ባህር ስለተሻገርን ታሪካችን አይፋቅም። እውነት ምንም ቢሆን ትዘገይ እንደሁ እንጂ አደባባይ መውጣቷና ብርሃን ማብራቷ አይቀርም። ጭለማው ሲገፈፍ ነው የያዘን አባዜ ለቆን የሚጠፋው። ለእውነት የቆማችሁ ሁሉ አንድ፤ አንድ እያላችሁ ብቅ ብቅ እያላችሁ ስለሆነ እግዚአብሔርን እያመሰገንን ለቀራችሁትም ብርሃኑን ያብራላችሁ እንላለን።

Anonymous said...

የሆለታ 33ተኛው ዙር ምሩቅ የሆኑት ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አስፋው ሰሞኑን ወደ አዲስ አበባ ሄደው ወይዘሮ እጅጋየሁ በየነ መምበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ በኢትዮጵያው ሲኖዶስ የተወሰነባቸውን ውሳኔ እንዴት በፍርድ ቤት ከሰው ማሳገድ የሚያስችሉ በዚሁም ተግባር በቂ ለምምድ ያላቸው ታጋይ መሆናቸውን ለማስረዳትና የክሱ ዋና አማካሪ እንደሚሆኑ አንዳንድ ጓደኞቻቸው ሰሞኑን አስረዱ።
በዚህም ተግባር ከተቀጠሩ የነ ተኮላንና የነ ጸሃይ ጽድቅን ጠበቃ አዲስ አበባ ሆነው እንደሚያስጠሩ ይታመናል።የሚያስገርመው ዋናው ተዓምር ግን በዳላስ ሚካኤል ላይ የፈጸሙትን በጣም አሳፋሪ ተግባር እንዴት ወደ አገር ቤት ይዘው እንደሚሄዱ ነው።
ወ/ሮ እጅጋየሁም በዚሁ አኳያ አገር ውስጥ ያለውን ሲኖዶስ እንደማይስማሙበትና እንደማያምኑበት November 4 2010 http://www.dejeselam.org/2010/11/blog-post_04.html እትም ላይ ደጀሰላም አውጥቶታል።