Monday, November 8, 2010

አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ


ሰሞኑን እነ ቀዳዳው ሙላው ከትግሬ ተወላጅነት ወጥተው የወያኔ መንግስት በለጠፈው የአማራ ድርጅት በዳላስ አመራር ለመጨበጥ ፲ የማይሞሉ ላይና ታች ሲሉ ከርመዋል። ከሆነላቸውም ዲሲ ካለው ኤምባሲ ጽ/ቤትም ለመጋበዝ ይፍጨረጨራሉ። በዳላስ ካቀፉዋቸውም ውስጥ ደብራችሁን የከሰሱና ያስከሰሱ ይገኙበታል። ከነዚሁ የወያኔ ቅጥረኞች ውስጥ ተኩላው (ተኮላ) ጓደኛው ሽኮኮ የመሰለ እስስት (ፀሀይጽድቅ) እንደዚሁም ቀዩ ሰይጣን ይገኙበታል።

እኛን መነካካት የተጠናወተው ተኩላው ለእርሱና ቢጤዎቹ ለምንሰጠው ባህሪ በጣሙን እንደቆሰለ ዘወትር በብዕሩ አጣጣል እየገለጠው ይገኛል። እኛም እንዳንጨምርበት የሚችል ልብ የለውምና በአንድ በኩል እናዝንለታለን። እሱንና ቢጤዎቹ እግዚሀብሔርን አውቀውና ንስሀ ገብተው እንዲሞቱ እንጂ ይህቺ ፫ጊዜ በድንገተኛ ልብ ድካም የመነመነች ልቡ ጧኣ ብላ እንድትቀር ፈጽመን አንሻምና እናዝንልሀለን። ቅዱስ ሚካኤል ግን እንዳያፈርጥህና እንዳታርፈው። በሞትና በሕይወት አፋፍ አጣብቂኝ ያለህ መሆንህን የረሳህ፣ ከታቦት ጋር ፍርድ ቤት የቆምክ ፣ ጭራሹን ሀይማኖት የሌለህና ለወያኔ ያደርክ፣ ይህንኑ ለማስፈጸም የምትሯሯጥ ለመሆንህ የምትገኝባቸውና የተሳተፍክባቸው በሎሌዎቹ የሚጠራው ስብሰባ ያንተን ባንዳነት ማስረጃ ናቸውና፤ ቤተክርስትያን ውስጥ ፖለቲካና የንጹሀንን አግልጋዮችን ስም መቀባት የጀመርክ ራስህ ነህና አሁን ሌላ መኮነንህን ለራስህ አድርገው።

እኛ በእርግጥ ሀይማኖትታችንን ፣ ወገኖቻችንን ብሎም ይቺን ሀገራችን አርገን የምንኮራባትን አሜሪካንን የምንወዳትንና የምንሰፈሰፍላትን ያህል ያላነሰ ለትውልድ ሀገራችን ኢትዮጵያም እንቆረቆራለን፣ መልካም አስተዳደርና ብልጽግናዋን ማየት የምንግዜም ምኞታችን ብቻ ሳይሆን በምንችለው ሁሉ በጎውን እናደርጋለን። ይህ ሀቅ ነው። አንተም የፈለከውን የፖለቲካ አቋም መውሰድና መደገፍ መብት አለህ። ነገር ግን የውጭ መንግሥትና አላማ አምጥተህ በመካከላችንና ብለህም በሀይማኖታችን ውስጥ ጣልቃ ማስገባት ወይንም በምንም አይነት መልኩ ማስረግ በሕጋዊም ሆነ በሞራልም በኩል ተቀባይነት የሌለው አጀንዳ ነው የምንልህ። ዛሬ ሸፈፈፍ ብለህ ከፍርድ ቤቱ ስትቻኮል እንደ ድል ቆጥረህ ሻምባይ ይዘህ ትጥፋለህ ብለን ነበር። ለምን እንደዘገየህ ባይገባንም ከማጅራትህ ላይ ቆመን የምንተነፍስብህ መስሎህ እውነቷን ለማስረገጥ በመሞከርህ በዚሁ እውነት ለመናገር ያበረታህ ወደ እውነተኛው መንገድም በመምራት የሰፈረብህን አጋንንት ያውጣልህ ነው የምንል። ረዳት ዳኛዋ የሰጠችው ትዕዛዝ ገና ለድል የሚያበቃ ስላልሆነ ረጋ በል፣ ለሳሳችዋ ልብህ አስብላት።

በተረፈ ያጀቡህ ካንተም የማይሻሉ በመሆናቸው አሁንም አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሆኑት ውስጥ ገነት ከበደ (እብዶ/ቀጮ)፣ መስፍን ወልደየስ (በበጎ አድራጎት ስም ገንዘብ ከደብሩ የመዘበረ) ጓደኛህ ሽኮኮ እስስት ፀሀይጽድቅ፣ እንደዚሁም የነገር አባታችሁና ጠሀፊያችሁ እነ ምናምንቴ እንደ ሆነስ ለምን አላወሳህም? ከጥሁፍ እንዳየነው ከሆነ አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ አስምረህበታል። ማለፊያ ነጥብ ነው የጣፍከውን መልሰህ ካነበብከው። አንተና ቢጤዎችህ ማን እንዳሳደጋችሁማ ራሳችሁ በተግባር እያሳያችሁን አይደል እንዴ? እንግዲህ ምትሀት አሊያም የምትወስዱት የልብም ሆነ ለሌላ መድሀኒት ካልሆነ ፤ ህሊናን የሚያስት አደንዛዥ እጽዋት ወይንም ልክፍት እንበለው ወይስ በዘር የሚመጣ በሽታ፤ይህም ካልሆነ መረንና ልቅ አስተዳደግ ይሆን ወይስ ከዚያ የከፋ ብልግናና አስነዋሪ እንዲሁም ማፈሪያ ያደረጋችሁ? በውን እናንተ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አላችሁ? እሱንም የወረሳችሁት ካሳደጎቻችሁ ነውን? እነሱም ደብር እየከሰሱ ነው ያሳደጋችሁ? እንዲያ ከሆነ ቀጥሉበትና በርቱ! ለዚህም ነው ከወላጆቻችሁ የወረሳችሁትን እናንተም እየደገማችሁ ያላችሁ? ከዚህስ ያቺ በእንጥልጥል ላይ ያለች ልብህ ትፋረድህ የምንል። እኛ የቅዱሳን ልጅ ቅዱስ ወይንም የሰይጣን ልጅ አጋንንት የምንል ስለዚህ የስራህን እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ይፍረድ።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

No comments: