Monday, November 8, 2010

ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ፺፯ን አስመልክቶ በተፈጠረው ሕይወታቸው የተቀጩት ዜጎችን ለመዘከር በዳላስ ከተማ በግንባር ሀላፊነቱን ወስዶ የተንቀሳቀሰው ግለሰብና አበሮቹ፣ ዝግጅቱን አስመልክቶ ይደረግ በነበረው ሳምንታዊ የቴሌኮንፍረስ ላይ ከእውነት የራቀ መረጃዎችን ሲያዘግቡ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው። በከተማው የረጅም አመታት ነዋሪነትና የነዋሪ ወገኖቻችንን አመኔታና ድጋፍ ይዘናል የሚሉ እነዚሁ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች በፖለቲካው አሪና ፖለቲከኛ፣ በቤተ ክርስትያንም ሆነ መስጊድ ሀይማኖተኛ፣ በመረዳጃ ማህበሩም ውስጥ ለወገን ሀሳቢና ደራሽ አድርገው እርስ በራሳቸው ሲመራረጡና ሲሿሿሙ፤ የሀቀኛ ተጋይ ወገኖች መካከል በመስረግ ትግላቸውን በተለያየ ስልት ማኮሏሸት ላይ ብቻ የተካኑ ግለሰቦች ናቸው።

የማይወክሉትና እነሱ የሌሉበት የዳላስ የሙያም ሆነ የግብረሰናይ ድርጅት የለም። በወገኖቻችን ስም የማይመዘብሩትና ለግል ጥቅም የማያውሉትን አለ ለማለት ያዳግታል። ከመረዳጃ ማህበሩ ይዞ የሬዲዮ ክፍሉንም ጨምሮ ያ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው ዛሬ ቤተ ክርስትያን የሚተናወጡ ወዳጆች ነው እናንተም እያተረፋችሁ ያላችሁት።  እንግዲህ የናንተ መመሪያ ይኼንን ሁሉ ያካትት እንደሆነ ባይገባንም ለናንተ የሰጡት ቃል ግን ፍጹም ከዕውነት የራቀ መሆኑንና በትላንት ዕለት ያዘጋጁት ስብሰባ የሚገባውን ያህል የቅስቀሳ ስራ ላለመደረጉ ምላሹ እነሱን፣ የነርሱን ቤተሰብና ወዳጆችን ጨምሮ ከነ ተናጋሪዎቹ በቁጥር ከ፵ በታች የሆኑ ብቻ እንደነበሩ በማስረጃ ተደግፎ የተቀመጠ ሆኖ ይገኛል።

ወደፊትም እናንተ ማወቅ ይገባችኃል በማለት የምናሳስበው ቢኖር፤ ይህ ወይም ሌላው ትግላችሁ በእንደዚህ አይነት ደካማና አፍራሽ ግለሰቦች ሰለባ ሆኖ እንዳይኮላሽ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድትወስዱ ነው።

No comments: