Thursday, November 25, 2010

ለጥያቄዎ መልስ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንደምን ከርማችኃል? እንኳን ለምስጋና ቀን አደረሳችሁ። ዛሬ በደብራችሁ ለልጆች በተዘጋጀው መርሀ ግብር ልጆቻችሁን ወደ ቤተ ክርስትያኑ እንድታደርሱ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውሳችኃለን።

ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁት መሰረት ያለንን የማካፈል ኃላፊነት ስለተሰማን ዳላስ ካሉት ምንጮቻችን ውስጥ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ያካፈለንን ልናቀብላችሁ ስለወደድን የሚቀጥለውን እንላለን።

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ፈደሬሽን የቀድሞ አመራር አባል የነበረው የኤርትራ ተወላጅ ኪሮስ ወልደስላሴ እርድታ ለማሰባሰብ በግምባር ቀደምትነት የሚሯሯጡት ውስጥ ኢዮኤል ነጋ aka ክፈተው ነጋ እንዲሁም ኢልያስ ድንበሩ የተባሉ ሲሆን እንዴት የቅዱስ ሚካኤል ደብር ከቅዳሴ በኃላ ማስታወቂያ ተናገረ የሚለውን መልስ ያገኘነው እንደሚከተለው ነው። የደብሩ ቦርድ አመራር ተነጋግሮ ያሳለፈው ውሳኔ መሰረት ያደረገው ግለሰቡ ለኮሚኔቲውና ለቤተ ክርስትያኑ ላበረከተው እንጂ የታሰረበትን የወንጀል ደብሩ እንደማይደግፍ ነው። አላደረጉም ተብለን ከምንወቀስ አደረጉ ተብለን ትችቱን መቀበሉን መርጠናል ብለው ማለታቸውን ነበር።

እኛም ወንጀለኛ ነው ብለን ከፍርድ አሰጣጥ ስርዐት አንቀድምም ነገር ግን የኛ ተቅዋሞም ሆነ አቋም ለሁሉም በእኩልነት መሆን አለበት። ያለአግባብ የተወነጀለ ከሆነ በምንችለው ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን ነገር ግን ሆዳችን እያወቀ ደጋግሞ ሕግን ለተላለፈ እንዲሁም ሀይማኖታችንን የሚጻረርና ሀሰት ለሰራ ደብሩ “ከዚህ ስፍራ በዚህ ቀንና ሰአት ገንዘብ መዋጮ ለእከሌ እንዲደረግ ቤተሰቦቹ ጥያቄ አቅርበዋል“ ተብሎ በጠሀፊው መነገሩ የተለያየ ነጥቦችን አላካተተም። ለምሳሌ እንደተለመደው ሁሉ የትኛው የቤተሰቡ ተወካይ ማስታወቂያው ሲነገር ነበረ? ለተመሳሳይ ማስታወቂያ ባለጉዳዩ ወይንም ተወካዩን በግልጽ ሲያስተዋውቁ እኛም ዋቢ አልነበርንምን ፣ ዛሬ ለምን አልነበረም? በተለያየ ጊዜ ወገኖቻችን በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ሲውሉ ለምን ለነርሱስ አልተደረገም? በቅርቡ የቀዳዳው ሙላው ወዳጅ (ውሽማ) አብረኸት አብርሃ በቁጥጥር ስር አልነበረችምን? ወዳጇም ሆነ እርሷም ለደብሩ ያደረጉት ምንም በጎ ስራ የላቸውምን? ወዘተ…… ማለት ይቻላል።

እኛ የምንለው ደብሩ standard ወይንም አንድ አይነት አቋም ይኑረው ነው የምንል። የዘር ፣ የጉሳ ፣ የጾታ ወይንም የፖለቲካ አመለካከት ሳይዝ ለሁሉም በእኩልነት ያስተናግድ ነው የምንል። ከሁሉም በላይ ሕግን በተለይም የከፋ ወንጀል የተመሰረተበትን ግለሰብ ለማስፈታት ለሚደረግ የገንዘብ መዋጮ አስተባባሪ መሆን ወይንም በማንኛውም ደረጃ ቤተ ክርስትያን ያን  የመሰለ ማስታወቂያ ማድረግ የተለየ መልዕክት ማስተላለፍ መሆኑን ልናሰምርበት እንወዳለን።
ከዚሁ ጋር በማያያዝ ደብሩ አጭር ማስታወቂያ አደረገ እንጂ ከዚያ ውጭ ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ ይኸው በግልጽ መታወቅ አለበት። ነገር ግን የደብሩን ስም በመጠቀም ከፈደሬሽንና ከሌላም ወገን ገንዘብ ለማግኘት አስተባባሪ ነን የሚሉት ግለሰቦች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ስለስማን ፣ የዳላሱን የቅዱስ ሚካኤልን ስም በሀሰት መጠቀማቸውን እንዲያቆሙና ደብሩም ለወደፊቱ እንዲጠነቀቅ እንጠቁማለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: