Tuesday, November 16, 2010

የቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን 

ሰሞኑን የናንተ ዳላስ እናንተኑ አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ባሉት ወገኖቻችን እንደገና መወያያ ሆናችሁ ነው ያላችሁት። እኛም ምንም ዕድሉን አግኝተን ተቺም ሆነ አድናቂ ባንሆንም የተቻለንን ያህል ሳንመለከተው አልቀረንም። ጋሼ Looser ተኮላ መኮንን AKAተኩላው የእንጀራ ጉዳይ እንዳለው ሰሞኑን እኛንም እድገት በሚሉት መልክ ከአንድ ክፍል አንስተውን ትርፍ ጊዜአችንን ሳይቀር ወደሚነጥቀን ኃላፊነት ስለገባን አንዳንዴ ብዕራችን የደረቀ እንዳይመስላችሁ እያስገነዘብን፤ ፈቃዱ ሆኖ አሁንም መልሶ በዚህ ጦመር ላገናኘን የሠራዊት ሁሉ ጌታ እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

በኢንተርኔት እያስተማረን ያለው ወጣቱ ወንድማችን ከ80 በላይ ፈቃደኛ የሆኑ የወላጆች እርዳታ በመታገዝ ለሚሰጠን መንፈሳዊ ትምህርት የምናቀርበው ልባዊ ምስጋና ለእርሱና ለሚረዱት ወላጆች ጭምር ይድረስልን። ይህም ይሳካ ዘንድ እርሱንም ለመቅጠር የትምህርት ክፍሉና የአስተዳደር ቦርድ ለፈጸማችሁት ተግባር ቅዱስ ሚካኤል ደርቦ ይክፈላችሁ።

የፊታችን ቀዳሚት ለሚከበረው የኅዳር ሚካኤል አመታዊ ንግሥ ሁላችሁን በሰላም አድርሶ የበዐለ ንግሡ ተሳታፊ አድርጎ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስጨርሳችሁ። ለዚሁ በዐል አከባበር ከርቀት የምትጓዙትንም ሚካኤል በሰላም አድርሶ በሰላም ይመልሳችሁ። ለበዐሉ መሳካት በምትችሉት ሁሉ የምትሳተፉ፣ ማለት በተለያየ አገልግሎት እንዲሁም ዝግጅቱ እንዲሳካ በንዋይ የደጎማችሁ ሁሉ ቅን ሥራችሁን እርሱ መድሀኒተ ዓለም እየሱስ ክርስቶስ ይቁጠርላችሁ። ሳንጠቅስ የማናልፈው የቀድሞ የደብሩ መዘምራን የነበሩትና በአድማ የተለዩት እራሳቸውን ይመረምሩ ዘንድ ስንጠቁም፤ ቤቱን የሚጠብቀው ታጋሹ ሚካኤል ግን እህቶቻችንን የእናት መዘምራን አቅርቦ አወደሰ፤ ለጥቆም ንጹህና ነገር የማያውቁትን ታዳጊ ወጣቶችን እየባረከበት ከስራቸውም ህጻናትን እያበዛበት ላለውና ምንም ለማይሳነው ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።

በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ በዚህ ሀገር አብረን ለምናከብረው ታላቁ የምስጋና ዕለተ ሐሙስ በሰላም ከወዳጅ ዘመድና ቤተሰብ ጋር እንዲያደርሳችሁ ምኞታችን ነው። ምንም እኛ ኦርቶዶክሶች ዘወትር ፈጣሪያችንን ሳናመሰግን ውለን ባናድርም ይህንን ዕለት ግን እንደኛ ላልተሟላላቸው በአካባቢያችን ለሚገኙ ችግረኞች የተቻለንን ሁሉ በማድረግ በዚህ ዕለት መከወን ቀኑን የተለየ ያደርገዋል። ለምሳሌ በኛ ቤተሰብ ውስጥ ቀደም ሲል ከርቀትና ከቅርበት ያለን በዚህ ዕለት በመገናኘት አብረን የምናሳልፈው ተለውጦ በቅርብ ያለው ብቻ ለእራት ስንገናኝ ቀኑን ግን በፈቃደኝነት ባካባቢያችን በሚገኙ የተለየ ዕምነት ተከታዮች፣ የሳልቬሽን አርሚ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ቅርንጫፍ፣ መጠለያ ማዕከሎችና ይህን በመሳሰሉት ተመዝግበንና የምንችለውን የንዋይ ድጋፍ በማድረግ በዕለቱ የችግረኞችን ምግብ በማዘጋጀትና በመመገብ እናከብራለን። ይህንን አይነቱን ልምድ የከተማችሁ መረዳጃ ማህበርና ቤተክርስትያኖች በማስተባበር ቢከውኑ በምንኖርበት ሕብረተሰብ ውስጥ ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ስለእኛ ማንነት ባሕልና ሀይማኖት ለሀገሬው የማስተዋወቅን መንገድ በቀላሉ ይከፍታል የሚል እምነት አለን። እኛ በፍላጎት ልጆቻችን ግን በመወለድ የተቀበልነው ዜግነት ብቻ ሳይሆን ባሕሉንም ጭምር ነውና በጎ የሆነውን ሁሉ አብረን የመካፈሉን ልምድ እንጨብጥ ለማለት ነው።

በማከል የምንለው አንድ ነገር ቢኖር በሀሳብ መለያየት በዚያም መተቻቸት መልካም ሲሆን፣ መስመር በማለፍ ግን በአካል ጉዳት አንዱ በሌላው ላይ መቃጣት ተገቢ አይደለም። ይህን ለማለት ያበቃን የኛንም ይህን ጦመር ጨምሮ ብዙ ጊዜ ወያኔ በሚል ቃል ተጠቅመን መጣፋችን የሚታወስ ነው። ቃሉ ግን አንባቢዎቻችንን ግንዛቤ በሚያስጨብጥ መልክ በማለት እንጂ ለቦታው ትክክለኛ ቃል ስላልሆነ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እንጠይቃለን። ትውልድ ሀገራችን ወያኔ ወይንም የወየነ መንግሥት ኖርዋትም አታውቅም። ያለው በትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት የተቁዋቋመ የኢሕአዴግ መንግሥትና አመራር ነው። ወያኔ የሚለውን ስም ማን እንደሰጠው በቦታው ስለሌለን ባናውቅም በአማርኛው ቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን ቃሉን ላለመጠቀም እንሞክራለን

የኢሕአዴግ መንግሥት ካቋቋማቸው በዘርና በጎሳ ድርጅት ውስጥ ያልታቀፉና ለመታቀፍና ዕውቅናን ለማግኘት ሲሉ በዳላስ ከተማ ለግል ጥቅማቸው የሚንቀዠቀዡት ጥቂት ግለሰቦች የከሰረ ማንነት አደባባይ የወጣው ዛሬ አይደለም። የኢሕአዴግ ድርጅት የበታች አመራሮችም ቢሆኑ እነዚህን የመሳሰሉ ግለሰቦችን ለቆሻሻ ምግባር መጠቀሚያ እንጅ እንኳን ደጋፊ ለተባባሪነት እንደማይዘግቧቸው እሙን ነውድርጅቱም እንደነዚህ ያሉ ትምህርት የሌላቸውን collateral damage አያቅፍም፣ ስልት መፈተሻ cannon folder እንዲሆኑ እንጂ። ባለፈው እንዳስነበብናችሁ በከተማችሁ  በነዚሁ ጥቂት ግለሰቦች በታቀደው ያለፈው ቀዳሚት ከቀትር በኃላ የተጠራው ስብስብ  ደገፊ ነን ብለው የተገኙ አዘጋጅና የክብር እንግዳቸውን ጨምሮ ከ15 የመይበልጡ ነበሩ።

የክብር እንግዳው ታየ የሚሉት የኢሕአዴግ cannon folder የስም አምባሳደር ሲሆን አዘጋጆቹ አልማ በሚል ስም የተዋቀሩ ሌሎች የኢሕአዴግ cannon folder እንዲሁም አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሆኑት ሙሉጌታ ወራሽ aka ቀዳዳው ፣ Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው፣ፀሀይጽድቅ ቤተማርያም aka እስስቱ እና ቢጤዎቻቸው ሲሆኑ ሁሉም ታክሲ ነጂና ትምህርት የሌላቸው መሀይምነታቸው ከድርጊትና ባሕሪያቸው፤ማንነታቸውን ለማወቅ ብዙ ምርምር የማይጠይቅ ነው። ከዚህም በፊት እነዚህ ኢሕአዴግ ላወጣው ባለ52 ገፅ መመርያ አስፈጻሚ ለመሆንና ለዚህም ጥቅማጥቅም ለማግኘት የተነሱ ሲሆን ማን ማንን ቀድሞ እንደሚጥል ባናውቅም፣ ቀዳዳው እንደሚለው አባቱን ኢሕአዴግ እንደ ገደለበት በዚያም ምክንያት ሱዳን እንደገባ ነው። Looser ተኩላውም ቢሆን እንደ ውዳሴ ማሪያም ለአመታት የኢሕአዴግ  ተቁዋሚ ነኝ ሲል የኖረ ቢሆንም እስስቱ ጋደኛቸውም ቢሆን በደርግ ዘመን ወንጀል የሰራና ኢሕአዴግ  ሥልጣን ሲይዝ ወደ አሜሪካን በመምጣት ጥገኝነት በሀሰት ጠይቆ የሚኖር ሌላው የኢሕአዴግ cannon folder ሲሆኑ ፤ ስንኮንን የከረምነውን ተግባራቸውን ባደባባይ ያረጋገጡ ቅጥረኞች ናቸው። ይሁን እንጂ አሜሪካ መብታቸው የተጠበቀና ማንኛውንም አይነት ሰላማዊ ስብሰባ የማድረግ መብታቸውን ሕግ የሚያከብረው ሲሆን በሌላው በኩል ተቁዋሚው ወገን የተቁዋሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከስብሰባ ውጪ ባለው ቦታ 30 በማይሞሉ ግለሰቦች ተካሂዷል። ይህ በዚህ እንዳለ ተቃዋሚው ወደ ስብሰባው ክፍል ድረስ ዘልቆ በመግባት ስብሰባውን ለማደናቀፍ የተደረገውን እንቅስቃሴ ፣ ደጋፊ ያለውን ያህል እንደኛ አባባል ሥርዐት የሌሽለትን ያሳያል። ምንም ድርጊታቸውን ብንጸየፍምና ብንታገላቸውም ለሁሉም ቦታና ገደብ አለው። የተቃዋሚው መብት ያለውን ያህል እነርሱም በሰላማዊ መንገድ የግላቸውን ስብሰባ የማድረግ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው። አሁንም በዚህ የጠራ አቋማችን ወቀሳና ትችቶቻችሁን እንቀበላለን።

በተለያየ ድኅረ ገጾች የተበተነው ቪዲዮ ሁላችንም ስላየነው እዚህ አላወጣነውም። ነገር ግን ከደጋፊው ጎራ የሚሰነዘረው ቃላትና ለዱላ መጋበዝ  እንዲሁም አዘጋጂ የሆኑት ማንነት ለኢሕአዴግ የከተማው ተወካይም ሆነ ለድርጅቱ ታላቅ የፖለቲካ ኪሳራ አድርሰውበታል። ከዚሁ በማያያዝ ተቃዋሚ ነን ባዮች በተቻላቸው ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲገልጡ እያሳሰብን ማንኛውንም ሕግ የማይደግፈውን እንቅስቃሴዎች እንዲያጤኑ እናሳስባለን።

ከዚሁ ሳንወጣ እንግዲህ ቅንጅትም ሆነ በወቅቱ ተቅዋሚ ሆናችሁ የተገኛችሁ ሚስተር ዴቪድ የተባለውና ባንድ ወቅት ከዳላስ ዝቅ ብላ ባለችና ደሴቶ እየተባለች በምትጠራ አዋሳኝ ከተማ በዳኝነት ተመርጦ ሳለ በስነ ምግባር እክል የተባረረውና የቀዳዳው ሙላው የግል ጠበቃ ብቻ ሳይሆን ለነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ግለሰቦችን የወከለና ብቸኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር በዳላስ ያልውን በሀሰት በተለያየ መንገድ ከሶ ያለውን አሁን ደግሞ እናንተን ስብሰባ ረበሻችሁ ብሎ መጥሪያ እንዳይልክላችሁ። ቀዳዳው ሰይጣን የሰፈረበት ከአባቱ ሞት ጋር አንድ ቀን ነው የሚሉት የቀዬው አደጎች ይናገራሉ። ስለዚህ ሆዳቸውን የሚያመልኩና ለንዋይ ያደሩ ሁሉ ትብይ ሆነው መርገርፋቸው እሙን ነው።

ሌላው ሳንገልጽ የማናልፈው ቢኖር በእስስቱ ተፈራወርቅ የተቋቋመው አጽራረ ቤተ ክርስትያን በከፈተው መለከት ገጽ ከመቃብር ያለ አስከሬን ሕይወት ሊቀጥል የሚሞክር ይመስል፣ ለኛ ምላሽ ለመስጠት ሲል ከዚህ በፊት ያልዘገበውን የግለሰብ ስም በመጥቀስ ሀሰት ዘግቧል። ወይንም በቅዠት አለም ዛሬም እየዋኘ ይገኛል። እንግዲህ አባሎቹም ህሊና የሌላቸውና በቅዠት ውስጥ የሚልከሰከሱ ስለሆነ የሰፈረባቸውን የክህደት ሰይጣን ይልቀቃችሁ፣ ከገባችሁትና ከያዛችሁ ምናምንቴ ተላቀቁ ነው የምንል።

ዛሬም አስተያየቶቻችሁን እንቀበላለን።




እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: