Friday, September 17, 2010

ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ከምንጩ ሁነው ያላገኙትን ከውጪ ይረካሉን?

ከብዙ ውጣና ውረድ በኃላ የዘገየው ከባሕር በታች ያለውን የጥልቅ ውቅያኖስ የነዳጅ ሀብት ውጤት ማምረቻ ጉርጓድ ዛሬ ፻፶ ቀናት በላይ ያስቆጠረውንና በሜክሲኮ ጎልፍ የሚገኘው እንደዚሁም እኛንም ከዳላስ የመልቀቂያ ምክንያት የሆነን፤ ይህንኑ ጉርጓድ ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት (ለመግደል) ከቀናት ባሻገር በመድረሳችን ተደስተናል። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ሰነበታችሁ? የምትልኩልንን አስተያየቶችን ይደርሱናል። የምንለጥፋቸው ጥቂቶቹን ብቻ ነበር ነገር ግን አንዳንዱ አስተያየት የግል ፍላጎቶችን ብቻ የሚያንጽባርቁና ያነጣጠሩበትን አላማ እስክንገነዝብ መያዝን እየመረጥን ስለመጣን በዚህ እንደማትከፉብን እርግጠኞች ነን።

ወደ እርዕሳችን ስንመለስ፤ ከምንጩ ሆነው ያረኩትን ወይንም ምንጩን ረግጠው የሄዱትን ለመገንዘብ ስንሞክር የራሳችንን ግምገማ እንዲያስከፋቸው ፈጽመን አንሻም። ምንጩ ደርቆም አያውቅም፣ በጥባጭ ካለ እንደሚሉት ሆነና በጥባጩ ሆነና መንፈሱን ያልለበሰ፣ የበጠበጠውን እንኳን ማጥራት ያቃተው፣ ከፈጣሪ ይሆን መንፈሱን የተገፈፈው? ስልጣኑን ያላበሰው ልዑል እግዚሀብሔር ከሆነ ፤ አደራ የተሰጠውን የእረኛ ሀላፊነት በፈቃዱ ጥሎ፣ እንደርሱ ቢሆን ምንጩንም አድርቆ ፣ ባትሪዬን ጨረስኩኝ ማለት ምንኛ ፈጣሪንመክዳት ይሆን? ምንኛ አሳዛኝና አስለቃሽ ይህን? ከምንጩ ሳሉ ድፍርሳቸውን ችሎ ከልቡ ፈጣሪን አምኖና ተቀብሎ የነበረው ፤ ዛሬ የበርከቱ ትሩፋትን የበዛላቸውና ምንጫቸውን አጥርተው እየጠጡ የሚጠብቁት ምንኛ የተመረጡና የተመሰገኑ ናቸው።

በሌላ በኩል ምንጩን ያደፈረሱት የተጠናወታቸውን መጥፎ ምግባር እርሱ መዳህኒተ ዓለም ያስተምራቸው፣ ለነሱም ልቦና ይስጣቸው እንጂ አሁንም ከምንጩ ማደፍራስ ተግባር አላሰለሱም። ምንጩ እንዲደርቅ ወይንም ከመጀመሪያ በመግቢያችን እንዳሰፈርነው የጥልቅ ውቃያኖሱ የነዳጅ ጉርጓድ እስከመጨረሻው ለማዘጋት በቡድን በመሆን በተለያየ አቅጣጫ ቢዳክሩም፤ እርሱ ራሱ በደሙ የዋጃትን የእነቶኔ ሴራ በየደረጃው እየከሸፈ ተንኮላቸውም እጅጉን እያራቃቸውና እያረከሳቸው ይገኛል። በረከቱንና ሰላሙን ስለነሳቸው በምንጩና በዙሪያው ተሰልፈው ለማደፍረስ የመጨረሻ ምዕራፋቸው ላይ ናቸው። እውነትም መንገድም እኔ ነኝ ያለውንና ምንጩንም ባርኮ ያከበረውን ፈጣሪ ስራ የማን ፍጡር እውቀት፣ ሀብት ወይስ ልብ ነው የሚያሸንፍ? ምንኛ ትዕቢት ያለው ነው በፈጣሪው ላይ የሚጠራራ? እውነትስ ፈጣሪውን ያውቃልን? እውነትስ ከልቡ አምኖ የተጠመቀና ልዑል እግዚሀብሔርን የተቀበለ ነውን? ስንትስ ጌዜ ነው እየወደቀ የሚነሳ? ስንትስ ጌዜ ነው በይቅርታ የሚመለከተው? መቼ ነው ለስራው መጥፎ ተግባርና ምንጩን እያወከ የሚቀጥል? አቤቱ ከቁጣህና ከቅጣትህ ሰውረን ምህረትህን ስጠን።

በዳላሱ የቅዱስ ሚካኤል ደብር ላይ ቦድነው ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ከሳሽና አስከሳሽ ብቻ አይደሉም፣ እኛ ካልመራነው (እኔ ከሞትክ ያለችው አህያ) ፣ እግዚሀብሔር የፈቀደውን እንዳስቀመጠ ሁሉ የእርሱን የማንሳት ሀይል የሳቱ፣ እርስ በራሳቸው ተመራርጠውና ተሻሽመው የጠነሰሱት ፣ እሱን ከማስቀደም ይልቅ እራሳቸውን ለግል ፍላጎታቸው ያስቀደሙ፣ የተለያየ ክሶች በተለያየ ጊዜ በቤተ ክርስትያኑ ላይ እንዲከፈቱና በዚያም ባለው ወጪ እንዲዳከም ብሎ እንዲዘጋ ፣ የሀሰት የሰላም ዘንባባ አንግበናል የሚሉና አመራሩን አምባ ገነን ብለው የሚቀቡ፣ እነሱ ተክለው ካሳደጓቸው የቤተ ክርስትያን ከሳሾች ጋር ክሳቸው እልባት ሳያገኝ እንዲነጋገሩ የቆሙ፣ ወዘተ…….. ደጋግመው በገጾቻቸው የሚያወጣቿው በቂ ማስረጃዎች ናቸው። ለምን አርዮስ እንዲለይ ተደረገ ብለን እራሳችንን ጠይቀን ለመረዳት መሻት ይገባናልና ለነዚህም እርሱ ልቦናቸውን ለውጦ መክሮና አስትምሮ ከምንጩ ይመልሳቸው፣ የተትረፈረፈውንም ከምንጩ የሞላውን እውቀትና በረከት ለመሳተፍ ያብቃቸው እንላለን።

በሌላ በኩል ገንዝብና ስልጣን ማምለክ የተያያዙት ከፈጣሪያቸው መራቃቸውን እንዴት ይረዱት ስንል ከነዚሁ ውስጥ ቀዳዳ ዋሾች በቅርቡ ከማን አንሼ ብሎ ለኮሚኒቲው ማእከል ቃል የገባውን ግለሰብ እውነቱን ከሆነቃሉን በአስቸኳይ እንዲፈጽም በዚህ አጋጣሚ ለሚመለከታቸው ስናሳስብ፣ ዋሾን ማመንና ጉም መጨበትን አንድ ነው እንዳያባብል ከመጦቆም ወደ ኃላ አንልም።


እርሶስ ምን ይላሉ?

3 comments:

Anonymous said...

Anonymous said...
Dallaseotc.blogspot.com ገጽን የምትከታተሉና በሚወጡት ስድቦች የምታዝኑ ምእመናን፦ እኔ ሲመስለኝ የዚህ ብሎግ ባለቤት ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ የሌለው፣ የእግዚአብሔርን ቃል የናቀ፣ ፀረ ሰላም፣ የካህን ውግዘት የማይፈራ፣ ቤተክርስቲያኗን እያረጋጉ ያሉትን ካህን የናቀ ፀረ ከርስትና ወይም ሌላ አላማ ያለው አለያም ህይወቱ በስድብና ..... የተጥለቀለቀ አለማዊ፣ ፖለቲከኛ ብቻ የሆነ ሰው ሊሆን ስለሚችል ናቅ አድርጋችሁ ብታልፉት በእርግጥ በነሱ ጎራ ያሉትን ሰዎችን ማሳያ ናሙና መሆኑ እርግጥ ነው ይሁንና ሀሰት ኖረም አልኖረ እውነት መፍካቷ ብርሀን ጨለማን መግለጡ አይቀሬ ነው:: ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳን እንጂ የተሳዳቢያን ተከራካሪ ሊኖራት አይችልም፣ በቅዱሳን ፀሎት እንጂ በሀጥያተኞች እርግማን አትጠበቅም አትገለገልም ምን አልባት ወንድም መካሪ ካላቸው ከፅሁፎቻቸው ውስጥ ስድቦቹን ለቅመው እያወጡ እንዲለጥፉ ብትመክሯቸው ከዚህ በተረፈ ተሰደብን ብላችሁ የምታስቡ ሀይማኖተኞች አይድነቃችሁ just ignore
it ይህንን ጽሁፍ በገጻቸው ላይ ካወጡት ብዬ ለመለጠፍ ሞክሬ ስላላወጡልኝ ነው እዚህ ጎራ ያልኩት። እግዜር ይስጥልኝ።

September 8, 2010 11:22 PM

እውነታችሁን ነው እያረማችሁ ጻፉ ብለን ብንመክራቸውም በጭራሽ እውነትዋ ካልሆነች አንጽፍም። ለውሸትና ለማጭበርበርማ ከመረዋ እነ ወልሻሻውና ወሸከሬው ተኩላና የአሜሪካንን መንግስት በማጭበርበር በነጻ ህክምና፤ ቤትኪራይ፤ ፉድስታምፕ እየተቀበሉና ታክሲና ልዩ ልዩ ንግድ እያካሄዱ የሚኖሩ ግብረአበሮቹ፤ ከሰላም ተዋህዶ ደግሞ የሌቦች መሪ እነኤፍሬም እሸቴ፤ እነቄስ ነኝ ባይ መስፍን አሉላችሁ፤ ለምን ተጨማሪ ሌባና አጭበርባሪ ቀዳዳ ፈለጋችሁ እያሉ ቀለዱብን። (አይነጋ መስሉአት በቅዋት … ) እንደተባለው ለንጋት አንዲት ሰአት እንደቀረቻቸው ቢያውቁዋት ኖሮ ሚካኤልን ለመክሰስ ባልተነሱ ነበር። ቀኑ እሩቅ አይደለም ሁሉሽም ሌባ ሁሉ ተለቃቅመሽ ትገቢያታለሽ። የእናንተን የሃይማኖተኞቹን ያህልም ባይሆን ከፍልውሃው ታልቦትና ከወዳጁ ከሌቦች መሪ ከግሪን ፌስ ጥቂት የተማርናት ብልጠት ስላለችን ቤተክርስቲያናችንን እንክዋን የማህበረ ሰይጣን እኩያን የወያኔውም ከይሲዎች ቢሆኑ ለሃጫቸው እንደተዝረበረበ እንዲሁ እንዳማራቸው ይቀርዋታል እንጂ ለጳውሎስ የሚያስረክቡትማ እዛው ገሃነም ሲገናኙ እንጂ እዚህማ ሱሚ ነው።

Anonymous said...

የዚህችን ቤተክርስቲያን ጠላቶች ሴራና እኩይ አላማ ከነተግባራቸው በግልጽ ሕዝቡ እንዲያውቅ ለማድረግ ስናስብ ይፋ የሚወጡበትን እና እርቃናቸውን የሚቀሩበትን ወቅት በራሳቸው ጥያቄ ስላመጡት ለሕዝቡ ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ አግኝተነዋል። እስከመቼ ተለባብሰው እሹሩሩ እየተባሉ ይኖራሉ? ሕግ በሌለበት አገር ወንጀል ሲፈጽሙ ኖረው፤ ከዛ አምልጠው እዚህ ሕግ ያለበት አገር መጥተው ደግሞ የሚያውቀን የለም በሚል በየቤተክርስቲያኑ መሽገው ኖሩ።

የወንጀለኛው ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር በሽታቸው እያገረሸ ስለመጣ የተለመደውን ተግባራቸውን በእግዚአብሔር ቤት መለማመድ ቀጠሉ። ሃይ የሚላቸውም ስለጠፋ ጎለበቱ። ጠያቂ ሲነሳም የሌለውን ታሪክ ሰጥተው አዋርደውና አበሻቅጠው ያባርሩታል። ይኸም ድርጊት ያለቁጥጥር የወንጀል መረባቸውን እንዲዘረጉና ተዝናንተው ይህችን ቤተክርስቲያን እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን እንዲመጡ እድል ሰጥቷቸዋል። ሆኖም በማንአለብኝነት ስለታበዩ ጥጋቡ ገፈተራቸውና ሕዝቡን ከመናቅ አልፈው እግዚአብሔርን መዳፈር ጀመሩ። ስለዚህም ነው ጉዳቸው የአደባባይ ምስጢር እየሆነ የመጣው። የእግዚአብሔርን ቤት ስላረከሱና ሰይጣናዊ ተግባራቸውን ሃይማኖተኛ በመምሰል በመቅደስ ሳይቀር በመተግበር በእግዚአብሔር መንፈስ ላይ ስለቀለዱ፤ ስሙን በከንቱ ከሚጠሩት ከሰራዊት ጌታ የእጃቸውን መቀበያው ወቅት ተቃረበ። ታድያ ከእግዚአብሔር መደበቅ ይቻል ይሆን?

ሕዝቡንስ እንደበግ ስትነዱ፤ ገንዘቡን ስትዘርፉ፤ ቤቱን ስታፈርሱ፤ ስሙን ስታጎድፉ ቅር ሳይላችሁ ተኩራርታችሁ ኖራችሁ። ዛሬ ታዲያ በእናነተው እጅ የሞተው ቤተሰብም፤ የቆሰለውም፤ ያበደውም፤ የተመረዘውም፤ ሁሉም ከያለበት ወጥቶ ቀንም ሆነ ሌሊት ከየገባችሁበት ጉድጓድ እየፈለፈለ ሊያወጣችሁ ዝግጁ ነው። እናንተስ ተዘጋጅታችኋል??

“አላርፍ ያለች ጣት ኩስ ጠንቁላ ትወጣለች” እንደሚባለው እናንተ ያላፈራችሁበትን የሌብነትና የወንጀል ህይወት ሕዝቡ እስከዛሬ ሸፍኖ ከነገ ዛሬ ይሻላችኋል በማለት ቢታገሳችሁ የፈራችሁ ስለመሰላችሁና በየሰንበቴው ቤት ከምታደርጉት ሀሜትና በቤተክርስቲያን ውስጥ ከምታደርጉት ጸያፍ የሆነ የአፍ እላፊ አልፋችሁ የንጹሀን ግለሰቦችን ስም ለማጉደፍ ሰይጣናዊ የሃሰት መርዛችሁን በድረገጽ መርጨት ጀመራችኋል። እስከ አሁን ድረስ ማንነታችሁን እያወቀ ገመናችሁን ሸፍኖ የተሸከማችሁን ህዝብ በአለም መድረክ በሀሰት ስሙን ማጥፋት ወግ ከመሰላችሁ የየአንዳንዳችሁን ማንነትና የተዝጎረጎረ ታሪካችሁን ለአለም መድረክ ማውጣት አይገድም። የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ እንዳላችሁት በእንቁላሏ ጊዜ ብናስቆማችሁ ኑሮ ከእጅ ሌብነት ወደአፍ ሌብነት ባልተሸጋገራችሁ ነበር። ፈርንጅ ሲተርት “ውሸትን መልሰህ መልሰህ ከተናገርክ እውነት ይመስላል” እንደሚለው፤ ሃሳዊ መሲሆች ፈጥራችሁ የምትጽፉትን ክርፋት፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አለና፤ ቅመሱት!

Anonymous said...

ይድረስ ለ ዳላሰ ኢ. ኦ. ቲ. ሲ ደራሲ፤
ይህቸን በሚካኤል በቤተክርስቲያናቸን ዉስጥ የሚደረገውን ተንኮል በማየት የተሰማኝንና
የተገነዘብኳቸውን አንዳንድ ዘገባዎች ከዚህ ከ (Comment) ቦታ አውጥተው ወደ በዋናው
መድረክ ላይ ያስገቡልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ።
እምን ጊዜ ደረስን !!!!
ስምንተኛው ሽህ የሚባለው ጊዜ እየደረሰ ይሆን ???
ክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄደው ለመጸለይ ! የመንፈሳዊ ትምህርት ለመማር !
ጥፋት ሰርቶም እንደሆነ ንስሃ ለመግባት !.... ነበር ። በአሁኑ ጊዜ ግን የምናየው ብዙዎቹ
የሚመጡት ለመጸለይ ስይሆን፤ ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ምን ጥፋት ይሰራ ያሆን? ምን
ይነገር ይሆን? ምን ይባል ይሆን? እነማን ይመጡ ይሆን? ሄደን እናደናግር እንጅ በልባችን
ያለውን ቂምና በቀል “ይቀር በለን እኛም የበደሉንን ይቀር እንል ዘንድ” የሚለውን ጸሎት
ልንጸልይ እንዳልሆነ በዛኛው እሁድ (August 29,2010) የነበረው የህዝብ ብዛት ያሳይ ነበር።
ከነበሩት አዛውንት መካከል! ሁለተኛ እዚህ ቤተክርስቲያን እልደርስም ያሉት! ቤተክርስቲያን
የከሰሱት! በሰላም ቀን ቤተክርስቲያን ይማይሄዱ ግር ግር አለ ሲባል ብቻ ካሜራቸውን ይዘው
ብቅ የሚሉ! እነሱ የኛ ነው የሚሉት ቄስ ከሌለ ቀሳውስት ሲያስተምሩም ሆነ ሃሌ ሉያ ሲል
እጆሮዋቸው ውስጥ ስፒከር ወትፈው መንፈሳዊ ያልሆነ መጽሃፍ የሚያነቡና ቄስ የሚዘልፉ!
በሃሰት ፍርድ ሸንጎ ላይ ቀርበው በመሃላ የሚዋሹ! ባይ ሎው ለመለውጥ ብዙ ጊዜ አባክነን፤
እንዳንለውጥም ተከለከልን በዚህ ምክንያት ቤተክርስቲያኑን ማፍረስ አለብን ብለው የተነሱ
ወንዶችና ሲቶች! የሸማቸውን ዘርፍ በግራና በቀኝ ትካሻቸው የለበሱ ተሳዳቢወችና ዘላፊውች!
ቤተመቅደሱን ሞልተውት ማየት ትልቅ ትይንት እንደነበረ የማይካድ ሃቅ ነበር።
ድሮ አገራቸን በነበርንበት ወቅት ሃይማኖትህ ምንድነው? ሲባል! የምንሰማው እስላም ውይም
ክርስቲያን ነኝ ይሚለውን መልስ ለመጠበቅ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ጥያቄ ነበር።
ክርስቲያን ነኝ ካለ ጥያቄው ያቆም ነበር በዚህ በዳላስ አካባቢ ግን ክርስቲያንነት ሌላ ጥያቄ ይዞ
እንደቀረበ የምናየው ነው። ሲኖዶስ እንደ ሃይማኖት ተቆጥሮ የየትኛው ሲኖዶስ ክርስቲያን ነህ
ወይም ነሽ? መባል ተጀምሯል። በበኩሉም አሜሪካ ያለ ክርስቲያን ቄስ ልጆችን ድቁና ከሰጠ
እንደ ትልቅ ሃጢአት ተቆጥሮ በየ ብሎጉና በአፍ ድቁና በተቀበሉት ልጆች ላይ ውርጅብኝ
መከናውኑ ይሚያስገርም አስጠያፊ ድርጊት መሆኑን የማያውቅ ምእመን ካሉ ንስሃ ግቡ መባል
ይገባል።
በመጨረሻው ሰንበቴ ብሎግ እንድተገለጸው የሚካኤልን ቤተክርስቲያን በቦርድና፤ ባስተናጋጅነት
ሲያገለግሉ የነበሩት ባልና ሚስት ከኢትዮጵያ መንግስት ይዘው የመጡትን የሚካኤልን
ቤተክርስቲያን መውረስ ባይሆንም ማዘጋት ዘዴና ተንኮል ለ ከሳሾችና ተባባሪዎች ለማስተላለፍ
እቤታቸው ውስጥ የደረጉትን የማስተባበሪያ ግብዣ! ይሄን ቤተክርስቲያን አዘጋለሁ ትልቅ ቂም
አለኝ! በህይዎቴ ለስልጣን ተዎዳድሬ ወድቄ አላውቅም! የሚካኤል ምእመን ግን ሳይመርጠኝ
ቀርቶ አዋረዶኛል! የሚሉት ሻለቃ ለጋባዧ የላኩትን ኢማል ሳታነቡት የቀራችሁ ካላችሁ
እንደገና አንብቡትና የሚካሄደውን ደባ ሁሉ ተረዱ።
በነገራችን ላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ በመሃላ ያነሳሁትን ቪዲዮ አልቆራረጥኩም (Edit ) አላደረግሁም
ቪድዮ የማነሳው ክልጅነቴ ጀምሮ ነው በማለት የዋሸው ግለሰብ በ ጋርላንድ ፖሊስ የ ኢምግሬሽን
አቋሙ እየተጠና መሆኑን ሰምተናል።
ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ ይባላልና በጥያቄን መልስ ጊዜ ከመዋረዱና ከመታሰሩ በፊት አገሩን ጥሎ
ቢጠፋ ይሻለዋል ምንም አይነት ችግር እንዳይደርስበት ስለምንፈልግ ምክራችንን
እናስተአልፋለን።
የቀዳሐውን ኦሪጂናል ቪዲዎ አቅርብ ሲባል ምን ያቀርብ ይሆን? የለኝም ካለ በሃሰት መሰከርክ
ሊባል ነው። ካቀረበ ቪዲዎው ሊፈተሽ ነው። በሁለቱም አቅጣጫ ጥፋት ላይ መውደቁ የማይቀር
ስለሆነ ቢያስብበት ይሻላል። በልጅነቱ ኢትዮጵያ በነበረበት ጊዜ አባቱ ወይም ዘመዱ የገዙለት
ቪዲዮ ማንሻ ምን የሚባል ነበር ሲባል አላስታውሰውም ሊል ነው ወይም ዋሸሁ?
በማንኛውም ኢትዮጵያዊ መጥፎ ነገር እንዳይደርስበት መመኘት አግባብ ስለሆነ ይሄ ምክር
ይድረሰው።
መረዋ በተባለው ብሎግ “ ይህ ቤተክርስቲያን በአሜሪካ የሚገኙትን ጳጳስ ከተከተለ ደሜ
ይፈሳል” የሚለውን አነጋገር አሁን ብቻ ሳይሆን ገና ሲጀመር ጀምሮ “የአሜሪካውን ሲኖዶስ
ከተከተለ እንጋደላለን! ያለንን መሳሪያ ቡጢም ቢሆን ይዘን እንቀርባለን” ሲል የነበረውን
ማስታወስ ይገባል!
ደራሲው በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኑ በኢትዮጵያው ጳጳስ መተዳደር አለበት እያለ መጻፉን
የማያውቅ ምእመን ይኖር ይሆን! ለምን ይሆን? ምን አጀንዳ አለው? ቤቱን አሽጦ ኮሚሽን
ለማግኘት ይሆን? ወይስ ለጳጳሱ ከሚላከው ከገቢው 20% ለሱ ምናልባት 5%ቱ ቃል ተገብቶለት
ይሆን።
ሰሞኑን የሚነፍሰው ሌላው የተረመረዘ ዎሬ በማዎቅም ይሁን ባለ ማወቅ የተጻፈው፤ የቦርድ
አመራረጥ ዘዴ ሲሆን ቤተክርስቲያንን በነጻ ማገልገል ለተማረና ላውቀ እንጅ ያልተማረ ወይም
እንግሊዝኛ በደንብ ያላወቀ አይመረጥ፤ ሊቀ መንበርም አይሁን የሚል የተሳሳተ አስተያየት በዚሁ
ብሎግ ማንበቤ አሳዝኖኛል። እነዚህ ግለሰቦች ትቂት ቆይተው ያልተማረ እቤተክርስቲያኑ
አይድረስ ይሉ ይሆን ብየ ፈራሁ።
ያለነው አሜሪካ ነው ፍርድ ቤት የቀረበ ሁሉ እንግሊዝኛ ካላወቀ አስተርጓሚ ይሰጠዋል።
ቤተክርስቲያን የሚያገለግል በታማኝነት በትህተኝነት በመልካም ፈቃድነት እንጅ በመማር ወ
ይም ባለመማር አይደለም። በዚሁ አጋጣሚ እንድታውቁት ያህል ያሁኑ ሊቀ መንበር ከማንም
ያላነሰ እውቀት ብቻ ሳይሆን ትምህርትም ያለው መሆኑን ተረዱ። ከማንም የበለጠ ትህትና እና
አስተያየት እንዳለው ለማሳየት የማይፈልግ የተቆጠበ አገልጋይ ለመሆኑ ማስረጃ አያስፈልገውም።
እግዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ።
የሄን ጽሁፍ በብሎግዎ ካቀረቡልኝ፡ በሚከተለው ጊዜ የአሜሪካውን ሲኖዶስ መከተል
ለቤተክርስቲያናችን ጥቅሙንና ጉዳቱን በዝርዘር እጽፋለሁ።
እግዚአብሄር ይስጥለኝ።
ለሁላችንም መልካም ቀን ይሰጠን ዘንድ አጸልያለሁ!!!!
አሜን!.