Tuesday, November 30, 2010

ለመከረንና ላስተማረን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
__________________________________________________________________________________ከዚህ በታች ያለውን አስተያየት በዋናው ገጻችን ያወጣነው ባጋጣሚ ካላዩት እንዲያነቡት ነው። አስተያየት ሰጪዎቹን ከልብ እናመሰግናለን። መልዕክታቸው በተለይ እኛን ከልባችን ገብቶ የቀጠቀጠን ስለሆነና ስለመከረን፣ ለናንተም የሚላመጥ ፍሬ ካለው በማለት ስለሆነ ልናካፍላችሁ ወደድን። አስተያየቶቻችሁ ይቀጥሉ። የእነዚህ ወገኖቻችንን ብዕር ተጠቅሞ ለመከረንና ላስተማረን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።


Anonymous said...
ዳላሶች እንዴት ከረማችሁ፤ ስለአገልግሎታችሁና ስለመቆርቆራችሁ የቆማችሁለት አንድዬ ይክፈላችሁ። እንዳላችሁት የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል ከአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት በመጡ ካህናት፤ ዲያቆናት፤ ምእመናንና ምእመናት ተካፋይነት በከፍተኛ ደረጃ ተከብሮ ውሏል። እግዚአብሔር አምላካችንን ካህናት በቅዳሴና በማህሌት፤ ዘማርያን ከሂውስተን መድሃኒአለም፤ ከሂውስተን ኃመር ኖህ ቅድስት ማርያም፤ ከኧርቢንግ ማርያም፤ ከዳላስ ሚካኤል፤ ወዘተ (የልጆች፤ የወጣቶች፤ የእናትና የአባት መዘምራን) እንዲሁም ምእመናን በሚጣፍጥ ዜማ፤ በእልልታና በደስታ እንባ ፊታቸው እየታጠበ ሲያመሰግኑት አድረው ውለዋል። ላደረግልን ውለታ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተባረከና የተቀደሰ ይሁንልን። ከሩቅም ከቅርብም በአሉን ለማክበር ለመጡት ሁሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ይስማላቸው፤ ስለታቸውን ይቀበላቸው፤ በረከቱንና ምህረቱን ያብዛላቸው እንላለን። እንኳንስ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች፤ በፍርድ ቤት የከሰሱትም፤ ቤቱን ሊያዘጉና ሊያፈርሱ ዛሬም በመሯሯጥ ላይ የሚገኙትም በቦታው ተገኝተው ከቡራኬው ሲካፈሉ ተመልክተናል። እግዚአብሔር ታላቅ፤ ኃያልና የሁሉንም ልብ መርምሮ የሚያውቅ ስልሆነ እንደየስራቸው ብድራቸውን አይንፈጋቸው። ቸር አምላክ ስለሆነ እድሉን ሰጥቶ በአይናቸው እንድያዩ አድርጓቸዋል። በአንድ ወቅት አንዱን የቦርድ ተወካይ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። እነዚህ ከሳሽ፤ አፍራሽ፤ በጥባጭ የሚባሉትን ጣዖት አምላኪዎች ለምንድን ነው ከዚህ የማታባርሯቸው? እኛንም ቤተክርስቲይናችንንም እንዲበጠብጡ አንፈልግም፤ ይኸ እኮ አሜሪካን አገር ነው፤ ቤተክርስቲያን ለአባሎቿ ብቻ ነው አገልግሎት መስጠት ያለባት ብንላቸው። የሰጡን መልስ፤ ግድ የላችሁም ታገሱ እግዚአብሔር እኮ እነሱንም ማስተማር ይፈልጋል፤ እነዚህ ስዎች የት እንዳሉም የሚያውቁ አይመስለኝም፤ በቤተክርስቲያን ቆመው በሃሰት ስሚሉና ሲገዘቱ፤ ሲሳደቡ፤ ሲያሙ፤ አለማዊ ህይወታቸውን በሙሉ ሲያንጸባርቁ እግዚአብሔርን መድፈራቸውን የተገነዘቡ አይመስለኝም። ሞኝነታቸው እንጂ በነሱ አቅም የእግዚአብሔር ቤት ሊፈርስ አይችልም፤ እንደውም እነሱ የእግዚአብሔርን ቤት ለማፍረስ ሲሯሯጡ እግዚአብሔር ደግሞ የነሱን ቤት ያፈርሰዋል የሚል ነበር። እኛም ይኸንን አነጋገር እንደትንቢት ወስደነው የእያንዳንዳቸውን የህይወት ታሪክ ስንመረምር፤ በእውነት እግዚአብሔር ምን ያህል ታጋሽና መሃሪ እንደሆነ ተገንዝበናል። እነዚህ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ስራዬ ብለው የተያያዙትንና ደጋፊዎቻቸውን ስንመለከትና ታሪካቸውን ስንመረምር እንኳንስ ህያው በሆነ ሁሉን በሚችል፤ ሁሉን በሚያውቅና በሁሉም ስፍራ በሚኖር በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ቀርቶ በኛም በደካሞቹና በሃጢአተኞቹ ፊት ለመቆም የማይገባቸው ምናምንቴዎች እንደሆኑ በጥናት አስደግፈን ደርሰንበታል። በእውነትም እግዚአብሔር ቤታቸውንና ህይወታቸውን በማፍረስ ላይ እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። ዳላሶችም በተደጋጋሚ እንደጻፋችሁት እንዚህ እኩያን ንስሃ ገብተው እግዚአብሔርን ይቅርታ ቢለምኑ ይቅር ይላቸው ዘንድ የመዳን ቀን ዛሬ ነውና።
Anonymous said...
እንደተባለው የበአሉ ዝግጅት ከማንኛውም ጊዜ በተሻለና በተቀነባበረ መልኩ በአባላቱ ትብብር እጅግ በጣም ያማረ ሊሆን ችሏል። ትብብር ላደረጋችሁ ሁሉ ቅዱስ ሚካኤል ይቁምላችሁ እያልን። ከሁሉም በላይ ገናናው ስሙ የተከበረው አምላካችን ስላደረገልን ሁሉ የተመሰገነ ይሁን። እነዚህ ሁሉ የምታይዋቸው ለውጦች፤ ደስ የሚል በዓል መከበር፤ የልጆች ትምህርት መጀመር፤ የአስተማሪው መቀጠር፤ ወዘተርፈ እንዲሁ ዝም ተብሎ የመጡ ለውጦች እንዳልሆኑ ብዙዎቻችን እናውቃለን የማታውቁ የቤተክርስትያን ተቆርቋሪዎች ካላችሁ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለባቸው መሆኑን በግልጽ እንድታውቁ ያስፈልጋል፤ ይህን ለመረዳት የምትፈልጉ ከሆነ የምታውቋቸውን ለቤተክርስቲያኑ እድገት ሌሊትና ቀን የሚደክሙትን ብታነጋግሩ በግልጽ ሊያስረዷችሁ ይችላሉ። ይኸ በየመንደሩና በየመሸታ ቤቱ እየዞረ የሚያወራውን ብትጠይቁት የሚነግራችሁ አሉባልታና ውሸት ከመሆኑም በላይ ወይ ዘራፊ አሊያም ጥቅም የጎደለበት አስዘራፊ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። በአሁኑ ወቅት እንደምታዩት ቤተክርስቲያኑን እያራቆቱ ኪሳቸውን ሲያዳብሩ የነበሩት እነኢዩኢልና ግብረአበሮቹ የቤተክርስቲያኑ እድገትና የተሻለ ነገር ለልጆችና ለወላጆች በአጠቃላይ ለአባላቱም ሆነ ለቤተክርስቲያን መምጣቱ የእግር እሳት ሆኖ እያቃጠላቸው ነው። በፊት መዝረፍ ለምን ይቀርብናል፤ ቦታችንን አንለቅም! በማለት እውስጥ ሆነው አመጸኞችን በማስተባበር ለመቆየት ሞከሩ፤ ሲዘርፉት የኖሩትን ቤተክርስቲያን ጉዳቸው እንዳይወጣ ሲሉ ያልጎደለውን ገንዘብ ጎሏል በማለት ህዝቡን አደናግረው ምርጫ በማደናቀፍ ሂሳብ እስኪጣራ አንወጣም አሉ አልሆነም። ሚካኤል ገፍትሮ ካስወጣቸው በኋላ ደግሞ እቦታችን መመለስ አለብን በማለት ታገሉ አልሆነም፤ አስከሰሱ፤ አስበጠበጡ፤ ህዝቡን ፕሮፓጋንዳና ውዥንብር በመንዛት ትክክለኛውን የቤተክርስቲያኑን ሂደት እንዳያውቅ ለማድረግ ሞከሩ ያም አልሆነም። አሁን ደግሞ በነሱ አለመኖር የተሰራው ጥሩ ነገር እንዳጋለጣቸው ሲያዩ በከፍተኛ ደረጃ በመደራጀት ላይ ይገኛሉ። ምን ለማድረግ እንደሁ ካለፈው የስራ ፍሬያቸው ስለሚታወቅ ሁላችንም በተጠንቀቅ በአይነ ቁራኛ መጠበቅ ግድ ነው። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ አወናባጅ ወንበዴዎች ለዘረፋቸው እንዲያመቻቸው ማህበረ ሰይጣን የሚባል የወንበዴ ጥርቅም አምጥተው በቤተክርስቲያኑ ላይ እንደመቅሰፍት በመዝራት ላንድ ሁለት አመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ዘረፉ ሲነቃና የሚያስቆማቸው ኃይል ሲመጣ፤ ከስም ማጥፋት ጀምሮ እስከ ማስፈራራት ብሎም ላቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ልጆቻቸውን በማሰማራት እስከ መደባደብ ደረሱ። ያ ሁሉ አልሰምር ሲል ወደክስ አምሩ ክሱም አልሆን ሲል የወያኔን የወንበዴ ጥርቅም አደራጅተው እንደገና ቤተክርስቲያንን ለመንጠቅ ጉልበታቸውን ፈተሹ ሚካኤል ወግዱ ብሎ እንደውሻ ጭራቸውን ቆልፈው እንዲጠፉ ቢያደራጋቸውም በየስርቻው በመልከስከስ አሁንም ሽምግልና፤ እርቅ፤ ፍቅር፤ ሰላም በማለት ለማጭበርበር ቢጥሩም የስራ ፍሬያቸው ስለሚታወቅ ሴራው አልሰራ አለ፤ ከሸፈ። አሁን ደግሞ ደብዛው ጠፍቶ የነበረውና ታይቶ የማይታወቀው ሌባ ሁሉ ከየተደበቀበት ጉድጓድ እየወጣ ወደ ሚካኤል ሰይፍ በመቅረብ መልአኩን በመፈታተን ላይ ይገኛል። የሚያሸንፈውን ለሚካኤል እንተወው። በኛ በኩል ሰዎቹም ሆኑ ስራቸው በግልጽ የሚታወቅ ስለሆነ በዝርዝር ተጽፎ ለህዝብ መበተን አለበት እንላለን። ለመንደርደሪያ ያህልም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ህዝቡ እንዲወያይበት አቅርበናል። 1ኛ፡ በጎአድራጎት እየተባለ ሲጠራ የነበረ የማህበረ ሰይጣን ቀኝ እጅ ሀ. መቼ እንደተመሰረተ ለ. እነማን ይመሩት እንደነበረ፤ አሁን የት እንዳሉ፤ አድራሻ፤ ስራ፤ ሐ. የተዘረፈው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ፤ የሚታወቀው ማስረጃ ያለው፤ የማይታወቀው በግምት መ. እንዴት ሊዘረፍ እንደቻለና አባሪ ተባባሪ እነማን እንደነበሩ 2ኛ፡ ሟች አባታችን ነፍሳችውን ይማርልን አቡነ ይስሃቅ በስማቸው የህይወት ኢንሹራንስ ተገዝቶ እንደነበረና ሲሞቱም እንሹራንስ እንደተበላ በሰፊው ይነገራል። ሀ. የኢንሹራንሱ ገንዘብ ምን ያህል እንደነበረ ለ. ማን ፈርሞ እንደተቀበለ ሐ. ገንዘቡ የት እንደደረሰ መ. በአንድ ወቅት በአለማየሁ እጅ $150,000 ከየት የመጣ ነበር ከኢንሹራንሱ ገንዘብ የአለማየሁ ድርሻ መሆኑ ነው ወይስ? 3ኛ፡ ስላለፈ ነገር መነጋገር አይገባንም፤ ያለፈ ሂሳብም ወደኋላ ሄደን ማስመርመር የለብንም የሚል መፈክር ሲያሰሙን የኖሩት ሲበዘብዙን የኖሩት የትናንት ቦርድ አባላት የዛሬ … ስለሆኑ። የትናንት የዛሬ ሳይባል ሂሳባችን ሲሆን ቤተክርስቲያኑ ከተመሰረተ ጀምሮ አልያም ላለፉት 10 አመታት አስመረምረናል የሚሉትን ጭምር በውጭ ኦዲተር ካልሆነም በአይ አር ኤስ በደንብ እንዲመረመርና ውጤቱ ለህዝብ በግልጽ እንዲታወቅ። የጎደለ ካለም ያጎደሉ በህግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ። 4ኛ፡ በቤተክርስቲያናችን ላይ በተለያየ ምክንያት ችግር በመፍጠር ገቢው እንዲቀነስ፤ አባላት እንዳይከፍሉ፤ ህዝቡ እንዲበጣበጥ በማድረግና ረብሻ በመፍጠር ቤተክርስቲያኑ ኪሳራ ደርሶበት እንዲዘጋ እናደርጋለን በማለት የፎከሩ፤ የከሰሱ፤ የተለያየ ቅስቀሳ በማድረግ እስከዛሬ በቤተርስቲያናችን ውስጥ ቁጭ ብለው ከኛው ጋር እየበሉ እየጠጡ የሚያርዱንን የእያንዳንዳቸው ስም፤ አድራሻቸው፤ በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱት ጥፋት፤ በገንዘብ ተተምኖ ሀ. ታሪካቸው ለህዝቡ በግልጽ እንዲነገርና ማንና ምን መሆናቸው እንዲታወቅ ለ. በህግ ተከሰው በቤተክርስቲያኑ ላይ ያደረሱትንም ሆነ የዘረፉትን ገንዘብ እንዲከፍሉ ሐ. በማንኛውም በቤተክርስቲያኑ ኮሚቴም ሆነ አግልግሎት እንዳይሳተፉ መ. አዋጥተናል የሚሉት ገንዘብ ካላቸው ማስረጃቸውን ለፍርድ ቤት እንዲያቀረቡ ይኸ እንግዲህ ከኛ የሚጠበቀውን እንስራ ለማለት እንጂ እግዚአብሔርን ንቀው ቤቱን ደፍረው ለሚያደረጉትማ ክፍያቸውን በእጥፍ ድርብ ከመላእክት አለቃ ከራሱ እንደሚቀበሉ ሙሉ እምነት አለን።
Anonymous said...
የያዕቆብ ወንድም የይሁዳ መልእክት ምዕራፍ 1 1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤ 2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ። 3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ። 4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። 5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ። 6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል። 7 እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል። 8 እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ። 9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም። 10 እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ። 11 ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል። 12 እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥ 13 የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው። 14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ። 16 እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል። 17 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ 18 እነርሱ። በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና። 19 እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው። 20 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ 21 ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። 22 አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ 23 አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። 24 ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው 25 ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።

Thursday, November 25, 2010

ለጥያቄዎ መልስ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንደምን ከርማችኃል? እንኳን ለምስጋና ቀን አደረሳችሁ። ዛሬ በደብራችሁ ለልጆች በተዘጋጀው መርሀ ግብር ልጆቻችሁን ወደ ቤተ ክርስትያኑ እንድታደርሱ በዚሁ አጋጣሚ እናስታውሳችኃለን።

ብዙዎቻችሁ በጠየቃችሁት መሰረት ያለንን የማካፈል ኃላፊነት ስለተሰማን ዳላስ ካሉት ምንጮቻችን ውስጥ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ያካፈለንን ልናቀብላችሁ ስለወደድን የሚቀጥለውን እንላለን።

የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያን እግር ኳስ ፈደሬሽን የቀድሞ አመራር አባል የነበረው የኤርትራ ተወላጅ ኪሮስ ወልደስላሴ እርድታ ለማሰባሰብ በግምባር ቀደምትነት የሚሯሯጡት ውስጥ ኢዮኤል ነጋ aka ክፈተው ነጋ እንዲሁም ኢልያስ ድንበሩ የተባሉ ሲሆን እንዴት የቅዱስ ሚካኤል ደብር ከቅዳሴ በኃላ ማስታወቂያ ተናገረ የሚለውን መልስ ያገኘነው እንደሚከተለው ነው። የደብሩ ቦርድ አመራር ተነጋግሮ ያሳለፈው ውሳኔ መሰረት ያደረገው ግለሰቡ ለኮሚኔቲውና ለቤተ ክርስትያኑ ላበረከተው እንጂ የታሰረበትን የወንጀል ደብሩ እንደማይደግፍ ነው። አላደረጉም ተብለን ከምንወቀስ አደረጉ ተብለን ትችቱን መቀበሉን መርጠናል ብለው ማለታቸውን ነበር።

እኛም ወንጀለኛ ነው ብለን ከፍርድ አሰጣጥ ስርዐት አንቀድምም ነገር ግን የኛ ተቅዋሞም ሆነ አቋም ለሁሉም በእኩልነት መሆን አለበት። ያለአግባብ የተወነጀለ ከሆነ በምንችለው ሁሉ ከጎኑ እንቆማለን ነገር ግን ሆዳችን እያወቀ ደጋግሞ ሕግን ለተላለፈ እንዲሁም ሀይማኖታችንን የሚጻረርና ሀሰት ለሰራ ደብሩ “ከዚህ ስፍራ በዚህ ቀንና ሰአት ገንዘብ መዋጮ ለእከሌ እንዲደረግ ቤተሰቦቹ ጥያቄ አቅርበዋል“ ተብሎ በጠሀፊው መነገሩ የተለያየ ነጥቦችን አላካተተም። ለምሳሌ እንደተለመደው ሁሉ የትኛው የቤተሰቡ ተወካይ ማስታወቂያው ሲነገር ነበረ? ለተመሳሳይ ማስታወቂያ ባለጉዳዩ ወይንም ተወካዩን በግልጽ ሲያስተዋውቁ እኛም ዋቢ አልነበርንምን ፣ ዛሬ ለምን አልነበረም? በተለያየ ጊዜ ወገኖቻችን በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ሲውሉ ለምን ለነርሱስ አልተደረገም? በቅርቡ የቀዳዳው ሙላው ወዳጅ (ውሽማ) አብረኸት አብርሃ በቁጥጥር ስር አልነበረችምን? ወዳጇም ሆነ እርሷም ለደብሩ ያደረጉት ምንም በጎ ስራ የላቸውምን? ወዘተ…… ማለት ይቻላል።

እኛ የምንለው ደብሩ standard ወይንም አንድ አይነት አቋም ይኑረው ነው የምንል። የዘር ፣ የጉሳ ፣ የጾታ ወይንም የፖለቲካ አመለካከት ሳይዝ ለሁሉም በእኩልነት ያስተናግድ ነው የምንል። ከሁሉም በላይ ሕግን በተለይም የከፋ ወንጀል የተመሰረተበትን ግለሰብ ለማስፈታት ለሚደረግ የገንዘብ መዋጮ አስተባባሪ መሆን ወይንም በማንኛውም ደረጃ ቤተ ክርስትያን ያን  የመሰለ ማስታወቂያ ማድረግ የተለየ መልዕክት ማስተላለፍ መሆኑን ልናሰምርበት እንወዳለን።
ከዚሁ ጋር በማያያዝ ደብሩ አጭር ማስታወቂያ አደረገ እንጂ ከዚያ ውጭ ምንም ያደረገው ነገር ስለሌለ ይኸው በግልጽ መታወቅ አለበት። ነገር ግን የደብሩን ስም በመጠቀም ከፈደሬሽንና ከሌላም ወገን ገንዘብ ለማግኘት አስተባባሪ ነን የሚሉት ግለሰቦች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ስለስማን ፣ የዳላሱን የቅዱስ ሚካኤልን ስም በሀሰት መጠቀማቸውን እንዲያቆሙና ደብሩም ለወደፊቱ እንዲጠነቀቅ እንጠቁማለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Happy Thanksgiving!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

Monday, November 22, 2010

በእርሱ ፈቃድ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



በእርሱ ፈቃድ ስለሆነልን ሁሉ ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚሀብሔር ይሁንልን። አሜን። ሀሳብ እንጂ የመሳካቱን እምነት ለእርሱ ለታላቁ መላእከ ሚካኤል በመተዋችን በአለፈው ዕለተ አርብ የእለቱን ስራችንን ጨርሰን የአየር መሳፈሪያ ቲኬትን እንዳገኘን፣ የአውቶሞቢል አከራዮችንም ዳላስ ስንደርስ እንደሚያቀርቡልን ካረጋገጥን በኃላ ነበር የማደሪያ ሆቴላችንም እንደዚያው የቀናን። ምሽቱን በረን ፣ መኪናውንም ተቀብለን፣ ሆቴልም ላፍታ ገብተንና ተጸዳድተን ፣ ለባብሰን ከእኩለ ሌሊት በኃላ የቅዱስ ሚካኤል በክንፉ አቅፎና ደግፎ ከገልፉ የአሜሪካን ሀገረ ክፍል አንስቶ በጋርላንድ ቴክሳስ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በሥርዐተ ማህሌት አጋማሽ አብቅቶ፣ ንግሠ በዓሉን ከናንተ ጋር እንድናከብር ያበቃን። እናንተንም እንኳን ለዚህ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ለዚሁም የእርሱ ፍቃድ አሁንም ይክበር ይመስገን። አሜን።


ከእርሱ ምስጋና በመለጠቅ ዘርዝረን የማንዘልቃችሁ ለዚህ በዓል መሳካት ጉልበትና እውቀታችሁን እንዲሁም በንዋይ የተሳተፋችሁ፣ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ተሰብስባችሁና ከደብሩም ተወጣጥታችሁ አገልግሎት የሰጣችሁ ሁሉ እርሱ ቅዱስ ሚካኤል አገልግሎታችሁን ይቀበልላችሁ። በተለይም ሁለት የአስተዳደር ቦርድ አባላት ሚስቶች የጀርባ አጥንት አድርጎ ጥንካሬን ስለሰጣችሁ እርሱ ይክፈላችሁ። አንደኛዋ እህት በረጅም ጊዜ አገልግሎታቸው የእማሆይ ተቀጥያ ስም ያተረፉት እህት ከመቅደሱና ከአስተዳደር ቦርድ ውጪ ባለው ማንኛውም ክንውን ተሰጥቶ ያላቸው ሀቀኛ የቅዱስ ሚካኤል ባሪያ ናቸው። ሁላችንን የገረመን ቢኖር፣ ታቦቱ ወደ መንበሩ እንደገባ የወንበር እጥረት ኖሮ ከጀርባ ካለው ተንቀሳቃሽ መጋዘን ለማውጣት ስንራዳ፣ የበሩን መዘወሪያ ለመክፈት ወደ 15 የምንሆን ወንዶች የተሳነን እኚሁ ሴት እህታችን ነበር ተጠርተው መጥተው አከፋፈቱን ያሳዩን። ሌላዋ እህት ደግሞ የኮምፒተር ችሎታ ያላቸውና ከወጣቱ ዲያቆን አስተማሪ ጋር እየታገዙ ሌሊት ተቀን ለፍተው በኤሌክትሮኒስ ቅዳሴና መዝሙር ለምዕመናኑ መገልገያ እንዲሆንና የተቋረጠ አገልግሎቱን እንዲቀጥል ያበቁ።


እንደተረዳነው ከሆነ ይህ ወጣት መምህር በርቀት ላለነው ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የዕምነቱ ተከታዮች ቅዳሴውን live በኢንተርኔት ለማስተላለፍ እቅድ እንዳለ ነው። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አዲስ እየገባ ያለውን የ security system upgrade የstate of art ደረጃ በጠበቀ እየተካሄደ መሆኑን ስንረዳ አንዳንድ ውይይቶችንም ከተኮናታሪ ሰራተኞች ጋር ተለዋውጠናል። ይህም አንድ መሰረታዊ ስራን አስተዳደሩ እያከናወነ መሆኑን ተረድተናል። ሌላው አዲስ ያየነው ለዘማሪዎች የመልበሻ ክፍል የተባለውን ባንወደውም ጊዜዊ በመሆኑ አይከፋም። ይህን በተመለከተ የህንጻ ኮሜቴና ምዕመኑ በቅርቡ ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ ይገነባሉ የሚል እምነት አለን። በተጨማሪም ለልጆች የትምህርት ክፍል ችግር እንዳለና ይህም ተጠንቶ በቅርቡ ይቀረፋል የሚል እምነት አለን።


ወደ በዓሉ በመመለስ ፤ የሱን ተዐምር ለማየት በመብቃታችን ከውስጣችን የሚደቀደቀው አልፎ ወጥቶ በፈታችን የወረደው ዕንባ አብረን ለተጋራነው የክርስትና ፈተና ምስክር ነበር። ዛሬ ሁልም ነገር አልፏል ብለን መቀመጥ የሌለብናን በምንችለው ሁሉ ቤተ ክርስትያናችንን ነቅተን መጠበቅ የግድ ነው። በዓሉ እጅግ ያማረና የደመቀ ሲሆን የአስተዳድደር ጠሀፊው እንደጠቆመው ደብሩ ከሌሎች እህት ደብሮች ጋር ያለውን ቅርርብ በተግባር ያሳየ ሲሆን፣ ወደፊትም በህብረት እንዴት እንደሚተሳሰሩ ጠቁሟል። እንዲሁም እስካሁን ሰራን የምንለው ያነሰ መሆኑንና እርስ በእርሳችን መናቆር አቁመን ለተተኪው ትውልድ መሰረት መጣል እንዳለብን አሳስቧል። እንግዲህ ልብ ያለው ይገነዘበው ዘንድ። ከዚሁ ሳንርቅ ሰሞኑን ለእስር የተዳረገውና በመካከካችሁ የረዥም ጊዜ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ለሁለተኛ ጊዜ በሕግ ወጥ ተግባር ላይ መገኘቱን መረጃዎች ይጠቁሟሉ። ሌሎችም እንደሚሉት በመጀመሪያው ጥፋት እንዳልሆነ ሲሆን ቤተ ክርስትያኑም ስለእርሱ እርዳታ ስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ መናገሩ በኛ ተገቢ አይመስለንም። ባለፈው በደብሩ ውስጥ ብጥብጥ ያነሳሱ የክህነት ግዴታቸውንም ያልተወጡት ከነጥቂት ግብረአበሮቻቸው ጋር ከቅዱስ ሚካኤል አጥር ውጪ በሚገኘው የተለየ እምነት ተከታዮች ህንጻ ውስጥ መግባታቸውንና ይኸውም ነገር ፍለጋ መሆኑንን ቀደም ብለን መጣፋችን ይታወቃል። የራሳቸውን ቤት አጥፍተውና የፈጠራቸውንም አስቀይመው ራሳቸውን ሲያገሉ ራቅ ቢሉ መልካም ነበር። በእውነት አንድ ዕምነትና ሀይማኖት ካለን ለምን እናከራለን የሚለውን ለአንባቢያን በመተው፣ ክርስትናውን ለማስፋት ሲባል ላዘጋጁት መንፈሳዊ ጉባኤ ሲሆን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳደርን አዳራሽ በአነስተኛ ክፍያ መጠየቅ ፣ ይህም ባይሆን አንድ አይነት ዕምነት ያላቸው እስከሆኑ ድረስ ጉባኤቸውን አስመልክቶ ማስታወቂያ እንዲያስቀምጡና እንዲነገርላቸውም ማድረግ ሲቻላቸው ፤ እነርሱ ግን ሆነ ብለው ከመውጫው አጥር ትክክል ፊት ለፊት ከመንገዱ ባሻገር የተከሉትን ማስታወቂያቸውን አይተን ዛሬም ቅዱስ መንፈስ እንደራቃቸውና ከተሳሳተ መንገድ መውጣት እንደተሳናቸው ከተግባራቸው አረጋግጥልናል።  እንደዚሁም የምስክርነት ዝማሬ ያቀረቡት የደብሩ የወላጅ መዘምራን ልባችንን የነካው ሲሆን፣ ከምዕመኑ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ፊት የሚወርደው ዕንባ ባለፈው ጥቂት ወራቶች በደብሩ የነበረውን የክርስትና ፈተና የሚያስታውስና ፤ ሳይረዱ በሌላ ጎን ቆመው የነበሩትን፣ በተፈጠረውም አዝነውና ቆስለው የነበሩትን እንዲሁም መስዋዕት የከፈሉትን ሁሉ ወደ ምንጩ አምጥቶና በአጸደ መስቀሉ ፊት አቁሞ አንድ ያደረገበት ዕለት መሆኑ ነበር። 


የነበርነው ሁሉ ሌሊቱን በሙሉ ከኢትዮጵያና ከዚሁ ሀገር የተለያዩ አድባራት በመጡ ካህናት አባቶችና ደብሩ በቅርቡ በአገኛቸው መነኩሴ ካህን እየተመራ የተካሄደው ስርዐት ወደር የሌለው ለመሆኑ፣ የህጻናቱ ፣ የወጣቶቹ ፣ የእህቶችና ወንድሞች ዝማሬን ጨምሮ እንደ ኤሌክትሪክ በውስጣችን ሲያነዝረን ያራፈደን መንፈስ ምን ግዜም የማይረሳ በረከት ነበር። በወጣቱ አስተማሪ እየተገነቡ ያሉት ህፃናት ያቀረቡትን ስንመለከት በዚሁ ከቀጠሉ ተተኪነታቸውን አንጠራጠርም። በማግስቱም የተደረገው ስረዐተ ቅዳሴና ዝማሬ እንዲሁም የወጣቱ መምህር ትምህርት ውብ ነበረ።


ከቀትር በኃላ በዕለተ ሰንበት ወደ አየር ማረፊያ ስንጓዝ እድሉ ገጥሞን የመረዳጃ ማህበር የሬዲዮ ዝግጅት ለማዳመጥ በቅተን ነበር። እንደተሰማው ከሆነ ረጅም ጊዜውን የወሰደው ባለፈው ሳምንት በከተማችሁ ተደርጎ ስለነበረው በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ለሚመራው የኢሕአዴግ መንግስት  ስብሰባ የተቀዳውን ነበር። ሲፈልግ ተቃዋሚ እራሱን የሚያስመስለው የኢሕአዴግ መንግስት ቅጥረኛ የሆነው መረዳጃ ማህበር አመራር አቋም በገሀድ የጀመረ ለመሆኑ በዚህ ቀን broadcasting ስብሰባውን ላልነበሩት በስርጭቱ ሲያስተጋባ ነበር። የሬዲዮ ስርጭቱን በሀላፊነት የያዘው የመረዳጃ ማህበሩ የተመዘገበበትና የሚንቀሳቀስበት ሕጋዊ ፈቃዱ ውጪ የባዕድ ሀገር መንግሥት የፖለቲካ ሥራ መጠቀሚያ ሆኖ መስማታችን በጣሙን አሳዝኖን አምሽቷል። የሚያሳየውም እነዚሁ ቅጥረኞች እንዴት ሰርገው ሬዲዮኑን እንደሚጠቀሙበት ብቻ ሳይሆን ነዋሪውም በስሙ ሲጠቀሙበት ፈዞ ተመልካችነቱ ያሳፍራል። ሊያው ወንዱ ሁሉ ሱሪውን ያወለቀ ወይንም ህሊናውን የሸጠ ሆኖ ነው በዳላስ የተቀመጠ። በድርጅቱ ብለው በኃይማኖቱ  ገብተውበት ሲቀልዱበት ከጎናችሁ ተነስታ የምታበራይ የሴት ጀግና በመውጧቷ ወንዱ ሁላ ወደማጀት አሰኝታዋለች። ከትውልድ ሀገራችሁ ይዛችሁ የመጣችሁትን የወንድ ትምክህተኝነት በአንዲት ኢትዮጵያዊት ላይ ለወገኗ በመቆሟ እነምናምንቴዎች የፈጸማችሁት በደል አሁን በመረጃ እያሳደዳቹ ነውና የት ትገቡ? 

እኛና ገጻችንን በመካከላችሁ እንድንገባ ያበቃችሁን በኃይማኖታችን ስትመጡ ቢሆንም ማንነታችሁንና ስትፈጽሙ የኖራችሁትን ሕገ ወጥ ድርጊትና በወገኖቻችን ላይ የፈጸማችሁትን በደል እንደ ወይዘሮዋ ገጽ ጥያቄ ወገኖቻችሁን ሁሉ ይቅርታ ጠይቃችሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከድርጊታችሁ ካልተገታችሁ ከኪሮስ እጣ ፈንታ የማታመልጡ መሆኑንና የሚያስፈልገው መረጃ ሁሉ ከሚመለከተው ክፍል ጋር እንደምንለዋወጥ ደጋግመን እንዳስገነዘብነው እንደምንቀጥልበት ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። በትላንትናው ዕለት እርሱን ለማስፈታት የተባበራችሁ ሁሉ  ዛሬ ብታስፈቱትም የእርሱ ጉዳይ ቅድሚያ የተሰጠበትን ምክንያት የብሔራዊ ጸጥታና ጥቅም ጎጂነቱ በማየሉ ቢሆንም የተቀራችሁ ባለተሮች መዝገባችሁ የተከፈተ ቢሆንም ለማወፈር የማንግደረደር መሆናችንን እያሳወቅን የወይዘሮውን ጥያቄ መፈጸሙ እንድንራራ ያዳዳናል።

ሌላው በወይዘሮዋ ገጽ ውስጥ አዲስ የወጣውን መረጃ እንድታዩትና እንድትገነዘቡት ስንጠቁም፤ በመረዳጃ ማህበሩ አመራር ላይ ካሉት ውስጥ የኮንስትራክሽን መሀንዲስ ነኝ የሚለው ግለስብ በሰፊው የዳላስ ወገኖቻችንን እያጭበረበረና ገንዘብ እየቀማ ያለ ግለሰብ ሰለባ የሆናችሁ ቁጥራችሁ እየበዛ በመምጣቱ ከየአቅጣጫው  የምታሰሙት እሮሮ ደርሶናል። እንደዚህ ያሉ ግለስቦች አረአያዊ ምግባር የጎደላቸው ስለሆኑ ቤቱ የመጥራት ግዴታ ይገባዋል። በተለይም ከቀዳዳው ሙላው ጋር ተጣብቆ ያለና ወደ ከፍ ያለ ጥፋት ውስጥ እየገባ ለመሆኑ ጥርጥር የለንም።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Tuesday, November 16, 2010

የቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን 

ሰሞኑን የናንተ ዳላስ እናንተኑ አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ባሉት ወገኖቻችን እንደገና መወያያ ሆናችሁ ነው ያላችሁት። እኛም ምንም ዕድሉን አግኝተን ተቺም ሆነ አድናቂ ባንሆንም የተቻለንን ያህል ሳንመለከተው አልቀረንም። ጋሼ Looser ተኮላ መኮንን AKAተኩላው የእንጀራ ጉዳይ እንዳለው ሰሞኑን እኛንም እድገት በሚሉት መልክ ከአንድ ክፍል አንስተውን ትርፍ ጊዜአችንን ሳይቀር ወደሚነጥቀን ኃላፊነት ስለገባን አንዳንዴ ብዕራችን የደረቀ እንዳይመስላችሁ እያስገነዘብን፤ ፈቃዱ ሆኖ አሁንም መልሶ በዚህ ጦመር ላገናኘን የሠራዊት ሁሉ ጌታ እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

በኢንተርኔት እያስተማረን ያለው ወጣቱ ወንድማችን ከ80 በላይ ፈቃደኛ የሆኑ የወላጆች እርዳታ በመታገዝ ለሚሰጠን መንፈሳዊ ትምህርት የምናቀርበው ልባዊ ምስጋና ለእርሱና ለሚረዱት ወላጆች ጭምር ይድረስልን። ይህም ይሳካ ዘንድ እርሱንም ለመቅጠር የትምህርት ክፍሉና የአስተዳደር ቦርድ ለፈጸማችሁት ተግባር ቅዱስ ሚካኤል ደርቦ ይክፈላችሁ።

የፊታችን ቀዳሚት ለሚከበረው የኅዳር ሚካኤል አመታዊ ንግሥ ሁላችሁን በሰላም አድርሶ የበዐለ ንግሡ ተሳታፊ አድርጎ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስጨርሳችሁ። ለዚሁ በዐል አከባበር ከርቀት የምትጓዙትንም ሚካኤል በሰላም አድርሶ በሰላም ይመልሳችሁ። ለበዐሉ መሳካት በምትችሉት ሁሉ የምትሳተፉ፣ ማለት በተለያየ አገልግሎት እንዲሁም ዝግጅቱ እንዲሳካ በንዋይ የደጎማችሁ ሁሉ ቅን ሥራችሁን እርሱ መድሀኒተ ዓለም እየሱስ ክርስቶስ ይቁጠርላችሁ። ሳንጠቅስ የማናልፈው የቀድሞ የደብሩ መዘምራን የነበሩትና በአድማ የተለዩት እራሳቸውን ይመረምሩ ዘንድ ስንጠቁም፤ ቤቱን የሚጠብቀው ታጋሹ ሚካኤል ግን እህቶቻችንን የእናት መዘምራን አቅርቦ አወደሰ፤ ለጥቆም ንጹህና ነገር የማያውቁትን ታዳጊ ወጣቶችን እየባረከበት ከስራቸውም ህጻናትን እያበዛበት ላለውና ምንም ለማይሳነው ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።

በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ በዚህ ሀገር አብረን ለምናከብረው ታላቁ የምስጋና ዕለተ ሐሙስ በሰላም ከወዳጅ ዘመድና ቤተሰብ ጋር እንዲያደርሳችሁ ምኞታችን ነው። ምንም እኛ ኦርቶዶክሶች ዘወትር ፈጣሪያችንን ሳናመሰግን ውለን ባናድርም ይህንን ዕለት ግን እንደኛ ላልተሟላላቸው በአካባቢያችን ለሚገኙ ችግረኞች የተቻለንን ሁሉ በማድረግ በዚህ ዕለት መከወን ቀኑን የተለየ ያደርገዋል። ለምሳሌ በኛ ቤተሰብ ውስጥ ቀደም ሲል ከርቀትና ከቅርበት ያለን በዚህ ዕለት በመገናኘት አብረን የምናሳልፈው ተለውጦ በቅርብ ያለው ብቻ ለእራት ስንገናኝ ቀኑን ግን በፈቃደኝነት ባካባቢያችን በሚገኙ የተለየ ዕምነት ተከታዮች፣ የሳልቬሽን አርሚ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ቅርንጫፍ፣ መጠለያ ማዕከሎችና ይህን በመሳሰሉት ተመዝግበንና የምንችለውን የንዋይ ድጋፍ በማድረግ በዕለቱ የችግረኞችን ምግብ በማዘጋጀትና በመመገብ እናከብራለን። ይህንን አይነቱን ልምድ የከተማችሁ መረዳጃ ማህበርና ቤተክርስትያኖች በማስተባበር ቢከውኑ በምንኖርበት ሕብረተሰብ ውስጥ ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ስለእኛ ማንነት ባሕልና ሀይማኖት ለሀገሬው የማስተዋወቅን መንገድ በቀላሉ ይከፍታል የሚል እምነት አለን። እኛ በፍላጎት ልጆቻችን ግን በመወለድ የተቀበልነው ዜግነት ብቻ ሳይሆን ባሕሉንም ጭምር ነውና በጎ የሆነውን ሁሉ አብረን የመካፈሉን ልምድ እንጨብጥ ለማለት ነው።

በማከል የምንለው አንድ ነገር ቢኖር በሀሳብ መለያየት በዚያም መተቻቸት መልካም ሲሆን፣ መስመር በማለፍ ግን በአካል ጉዳት አንዱ በሌላው ላይ መቃጣት ተገቢ አይደለም። ይህን ለማለት ያበቃን የኛንም ይህን ጦመር ጨምሮ ብዙ ጊዜ ወያኔ በሚል ቃል ተጠቅመን መጣፋችን የሚታወስ ነው። ቃሉ ግን አንባቢዎቻችንን ግንዛቤ በሚያስጨብጥ መልክ በማለት እንጂ ለቦታው ትክክለኛ ቃል ስላልሆነ በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እንጠይቃለን። ትውልድ ሀገራችን ወያኔ ወይንም የወየነ መንግሥት ኖርዋትም አታውቅም። ያለው በትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት የተቁዋቋመ የኢሕአዴግ መንግሥትና አመራር ነው። ወያኔ የሚለውን ስም ማን እንደሰጠው በቦታው ስለሌለን ባናውቅም በአማርኛው ቋንቋ አካዳሚያን የሆኑት እስኪያስረዱን ቃሉን ላለመጠቀም እንሞክራለን

የኢሕአዴግ መንግሥት ካቋቋማቸው በዘርና በጎሳ ድርጅት ውስጥ ያልታቀፉና ለመታቀፍና ዕውቅናን ለማግኘት ሲሉ በዳላስ ከተማ ለግል ጥቅማቸው የሚንቀዠቀዡት ጥቂት ግለሰቦች የከሰረ ማንነት አደባባይ የወጣው ዛሬ አይደለም። የኢሕአዴግ ድርጅት የበታች አመራሮችም ቢሆኑ እነዚህን የመሳሰሉ ግለሰቦችን ለቆሻሻ ምግባር መጠቀሚያ እንጅ እንኳን ደጋፊ ለተባባሪነት እንደማይዘግቧቸው እሙን ነውድርጅቱም እንደነዚህ ያሉ ትምህርት የሌላቸውን collateral damage አያቅፍም፣ ስልት መፈተሻ cannon folder እንዲሆኑ እንጂ። ባለፈው እንዳስነበብናችሁ በከተማችሁ  በነዚሁ ጥቂት ግለሰቦች በታቀደው ያለፈው ቀዳሚት ከቀትር በኃላ የተጠራው ስብስብ  ደገፊ ነን ብለው የተገኙ አዘጋጅና የክብር እንግዳቸውን ጨምሮ ከ15 የመይበልጡ ነበሩ።

የክብር እንግዳው ታየ የሚሉት የኢሕአዴግ cannon folder የስም አምባሳደር ሲሆን አዘጋጆቹ አልማ በሚል ስም የተዋቀሩ ሌሎች የኢሕአዴግ cannon folder እንዲሁም አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሆኑት ሙሉጌታ ወራሽ aka ቀዳዳው ፣ Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው፣ፀሀይጽድቅ ቤተማርያም aka እስስቱ እና ቢጤዎቻቸው ሲሆኑ ሁሉም ታክሲ ነጂና ትምህርት የሌላቸው መሀይምነታቸው ከድርጊትና ባሕሪያቸው፤ማንነታቸውን ለማወቅ ብዙ ምርምር የማይጠይቅ ነው። ከዚህም በፊት እነዚህ ኢሕአዴግ ላወጣው ባለ52 ገፅ መመርያ አስፈጻሚ ለመሆንና ለዚህም ጥቅማጥቅም ለማግኘት የተነሱ ሲሆን ማን ማንን ቀድሞ እንደሚጥል ባናውቅም፣ ቀዳዳው እንደሚለው አባቱን ኢሕአዴግ እንደ ገደለበት በዚያም ምክንያት ሱዳን እንደገባ ነው። Looser ተኩላውም ቢሆን እንደ ውዳሴ ማሪያም ለአመታት የኢሕአዴግ  ተቁዋሚ ነኝ ሲል የኖረ ቢሆንም እስስቱ ጋደኛቸውም ቢሆን በደርግ ዘመን ወንጀል የሰራና ኢሕአዴግ  ሥልጣን ሲይዝ ወደ አሜሪካን በመምጣት ጥገኝነት በሀሰት ጠይቆ የሚኖር ሌላው የኢሕአዴግ cannon folder ሲሆኑ ፤ ስንኮንን የከረምነውን ተግባራቸውን ባደባባይ ያረጋገጡ ቅጥረኞች ናቸው። ይሁን እንጂ አሜሪካ መብታቸው የተጠበቀና ማንኛውንም አይነት ሰላማዊ ስብሰባ የማድረግ መብታቸውን ሕግ የሚያከብረው ሲሆን በሌላው በኩል ተቁዋሚው ወገን የተቁዋሞ ሰላማዊ ሰልፍ ከስብሰባ ውጪ ባለው ቦታ 30 በማይሞሉ ግለሰቦች ተካሂዷል። ይህ በዚህ እንዳለ ተቃዋሚው ወደ ስብሰባው ክፍል ድረስ ዘልቆ በመግባት ስብሰባውን ለማደናቀፍ የተደረገውን እንቅስቃሴ ፣ ደጋፊ ያለውን ያህል እንደኛ አባባል ሥርዐት የሌሽለትን ያሳያል። ምንም ድርጊታቸውን ብንጸየፍምና ብንታገላቸውም ለሁሉም ቦታና ገደብ አለው። የተቃዋሚው መብት ያለውን ያህል እነርሱም በሰላማዊ መንገድ የግላቸውን ስብሰባ የማድረግ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው። አሁንም በዚህ የጠራ አቋማችን ወቀሳና ትችቶቻችሁን እንቀበላለን።

በተለያየ ድኅረ ገጾች የተበተነው ቪዲዮ ሁላችንም ስላየነው እዚህ አላወጣነውም። ነገር ግን ከደጋፊው ጎራ የሚሰነዘረው ቃላትና ለዱላ መጋበዝ  እንዲሁም አዘጋጂ የሆኑት ማንነት ለኢሕአዴግ የከተማው ተወካይም ሆነ ለድርጅቱ ታላቅ የፖለቲካ ኪሳራ አድርሰውበታል። ከዚሁ በማያያዝ ተቃዋሚ ነን ባዮች በተቻላቸው ሁሉ በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲገልጡ እያሳሰብን ማንኛውንም ሕግ የማይደግፈውን እንቅስቃሴዎች እንዲያጤኑ እናሳስባለን።

ከዚሁ ሳንወጣ እንግዲህ ቅንጅትም ሆነ በወቅቱ ተቅዋሚ ሆናችሁ የተገኛችሁ ሚስተር ዴቪድ የተባለውና ባንድ ወቅት ከዳላስ ዝቅ ብላ ባለችና ደሴቶ እየተባለች በምትጠራ አዋሳኝ ከተማ በዳኝነት ተመርጦ ሳለ በስነ ምግባር እክል የተባረረውና የቀዳዳው ሙላው የግል ጠበቃ ብቻ ሳይሆን ለነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ግለሰቦችን የወከለና ብቸኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር በዳላስ ያልውን በሀሰት በተለያየ መንገድ ከሶ ያለውን አሁን ደግሞ እናንተን ስብሰባ ረበሻችሁ ብሎ መጥሪያ እንዳይልክላችሁ። ቀዳዳው ሰይጣን የሰፈረበት ከአባቱ ሞት ጋር አንድ ቀን ነው የሚሉት የቀዬው አደጎች ይናገራሉ። ስለዚህ ሆዳቸውን የሚያመልኩና ለንዋይ ያደሩ ሁሉ ትብይ ሆነው መርገርፋቸው እሙን ነው።

ሌላው ሳንገልጽ የማናልፈው ቢኖር በእስስቱ ተፈራወርቅ የተቋቋመው አጽራረ ቤተ ክርስትያን በከፈተው መለከት ገጽ ከመቃብር ያለ አስከሬን ሕይወት ሊቀጥል የሚሞክር ይመስል፣ ለኛ ምላሽ ለመስጠት ሲል ከዚህ በፊት ያልዘገበውን የግለሰብ ስም በመጥቀስ ሀሰት ዘግቧል። ወይንም በቅዠት አለም ዛሬም እየዋኘ ይገኛል። እንግዲህ አባሎቹም ህሊና የሌላቸውና በቅዠት ውስጥ የሚልከሰከሱ ስለሆነ የሰፈረባቸውን የክህደት ሰይጣን ይልቀቃችሁ፣ ከገባችሁትና ከያዛችሁ ምናምንቴ ተላቀቁ ነው የምንል።

ዛሬም አስተያየቶቻችሁን እንቀበላለን።




እርሶስ ምን ይላሉ?

Friday, November 12, 2010

Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው 

በዚህ ገጽ ከምናቀርበው መጣጥፍ ምክንያት ከሚደርሱን አስተያየቶች ውስጥ የአማርኛውን አሀዝ ለማንበብ የተቸገራችሁ እንዳላችሁ ነው። ይህን ችግር ይቃለል ዘንድ የቁጥር አጣጣላችንን ለማሻሻል እንሞክራለን ፣ ለሰጣችሁንም አስተያየቶች ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? ክብር ምስጋናው የማያልቅበት ቸር ፈጣሪያችን ዳግመኛ ፈቃዱ ሆኖ በዚች ጦመር ስላገናኘን አሁንም ወሰን የሌለውን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን።

ከተጉለት ነኝ የሚለውና ተረትን የሚያበዛው Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው ለትውልድ ሀገሩ በውትድርና ሲቀጠር እንደማንኛውም ወታደር ሳይሆን እንደባለሟል የጓዳ ውስጥ አሽከር ሆኖ ማዕረግ ላለው መኮንን ያደረ ነበር። አድርባይ እንጂ ታማኝና ሀቀኛ እንዲሁም ለተቀበለው ኃላፊነትና ለገባው ቃል ኪዳን የቆመ አልነበረም። እርሱም አበረከትኩኝ የሚለው አንዳችም የለውም። የበላይ አለቃውንም አሳልፎ የሰጠና እርምጃ ሲወሰድበትም የተመለከተ ለመሆኑ በወቅቱ የነበሩ ይናገራሉ። ከዚያም በኃላ ነበር እንደወታደር ተመድቦ ከሠራዊቱ ጋር እንዲቀላቀልና ወታደራዊ ግዳጁን እንዲወጣ ሲመደብ ነበር ሽንቱን መልቀቅ የጀመረው። ለትውልድ እናት ሀገሩ የተቀበለውን ኃላፊነትና የገባውን ቃል ኪዳን ሰብሮ፣ ከተመደበበት ክፍልና ከሠራዊቱ ተነጥሎ ሀገሩንና ሕዝቡን ክዶ ፣ በወሳኝ ሰአት ሸሽቶ የተሰወረ ፤ እንደ ተጉለቴ ሳይሆን ማኅተሙን የበጠሰ፣ የታሪክ ዝቃጭ በነካው ሁላ የማይሳካለት Looser ግለሰብ ነው።

እንግዲህ ለመብቴ ነው የቆምኩት ማለት የማይሰለቸው Looser የራስን መብት ከመጠየቅ አኳያ የሌላውንም መብት የመጠበቅ ግዴታን ታውቀዋለህን? ስለ ሀይማኖትስ ምን የምታውቀው አለህ? ማኅተምህን የበጠስክ ከሀዲ እንጂ። አባል ባልሆንክበት ደብር መብቴ ብለህ በፍርድ ቤት የምትጠይቀው ነጻ መብት ስጦታ የምታገኝ መስሎህ ከሆነና ልክስክስ ሕግ አማካሪህም የቻለውን ቢፍጨረጨር ፣ ሀቅን እንደማይለውጥ በገባህና ከሰይጣናዊ መንገድ በወጣህ ነበር። ገንዘቡን እስከሰጣችሁት እርሱም የማይፈነቅለው ድንጋይ ባይኖርም የማታ ማታ አንተና የወያኔ ሎሌዎች መቅለል የማይሰለቻችሁ የLooser ጽዋችሁን የምትቃመሱበት ሰአት እየቀረበባችሁ ይገኛል። ባለፈው ባለጌ ያሳደገው መባልን የማትፈልግ ሆነህ እራስህን ለመለወጥና ለመሸፈን ያደረከው ሁሉ ማንነትህን መደበቅ እንደማትችል ብታውቅ እንደዚሁም አንተን የመለመሉህና የነሱን አጸያፊ ቆሻሻ ተግባር እንድትሰራላቸው ያደረጉህም ጭምር የወያኔን መንግስት እያስመታችሁት ነው የምትገኙት።

እንግዲህ ያልከው 3 ቀን አለፈ። ታዲያ በግፍ የከሰስከው ደብር ይግባኝ ማስገባቱንም ሆነ አለማስገባቱን ምነው አላካፈልከን? አንተ እንድንሰማልህ የምትፈልገውን ብቻ አጀንዳ ሳታደርግ ማቅረብ ይገባሀል። አንተ የምትሸሽበትንማ ሳትወድ እራሱ በወቅቱ ይሰማብኃል ስለዚህ የሚያመዛዝን አዕምሮ ሰጥቶህ ከሰው እኩል እስክታስብ።

ባለፈው አነበብኩኝ ያልከውን የቀድሞ መሪያችንን የነበሩትን ቢል ክሊንተን መጽሀፍ እስካሁን ጨርሰህ ከሆነ ባናውቅም ግምገማህን አላካፈልከንምና ምንድን ገጠመህ? መቼም አነበብን ካልን ጥሩና ጠቀሜታውን ወይንም ተቃራኒውን ግምገማችንን ማካፈል ይጠበቃልና በቶሎ አካፍለን፣ ዋሽተህም ከሆነ አላነበብኩም ማለቱ ይቀላል። የናንተ የቀድሞ ቴክሳስ ገዢ በኃላም የሁላችን መሪ የነበሩት እናንተው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ቡሽ አዲስ መጽሀፍ ማውጣታቸውን ሰማን እንግዲህ በጉርብትናህ ቀድሞ ደርሶህ ከሆነ ስለዚህ መጽሀፍ የምትለንን ለማንበብ እንጠብቃለን።  

እርሶስ ምን ይላሉ?

Wednesday, November 10, 2010

HAPPY VETERANS DAY 2010

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


US MARINE CORPS 235th BIRTHDAY and VETERANS DAY 2010


United States Joint Service Color Guard on parade at Fort Myer in Arlington County, Virginia.

Service branches

U.S. Army
U.S. Marine Corps
U.S. Navy
U.S. Air Force
U.S. Coast Guard

Good Morning!

From one Marine veteran to all veterans of all branches of the services, Thank you!

For all of our men and women in uniform protecting our rights and freedoms today, Thank You!

My prayers are with each warrior and their families.

Take time to thank a veteran for his or her service to our nation, for without their sacrifice and willingness to give their lives in our defense, America would be a far different place today.

A football game, the American Flag, the National Anthem  and a flyover. What more could one ask?


For your enjoyment please go to http://www.youtube.com/watch?v=UL03ko7T3o4  for a short video.

 God Bless America!


Semper Fi!!

እርስዎ እድሉን ባያገኙም ፣ ሌሎች በከፈሉትና እየከፈሉ ባሉት መስዋዕትነት እነኾ ለዚህ በቅተዋልና ለዚች ታላቅ ሀገር የበኩልዎን አስተዋጾ በቅን እንዲወጡ እያሳሰብን፤ ለልጆ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ አሊያም ለሚያውቁትም ሆነ ለማያውቁት ፤ አሁን በአገልግሎት ላይ ያለ/ያለችና ቀደም ብለው አገልግሎታቸውን የሰጡትን ላፍታ የክብር ምስጋና እንድታቀርቡላቸው ስንጠይቅ፤ በሕይወት የተለዩንም እንድታስቧቸው በአክብሮት እንጠይቃለን?

እርሶስ ምን ይላሉ?

Monday, November 8, 2010

አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ


ሰሞኑን እነ ቀዳዳው ሙላው ከትግሬ ተወላጅነት ወጥተው የወያኔ መንግስት በለጠፈው የአማራ ድርጅት በዳላስ አመራር ለመጨበጥ ፲ የማይሞሉ ላይና ታች ሲሉ ከርመዋል። ከሆነላቸውም ዲሲ ካለው ኤምባሲ ጽ/ቤትም ለመጋበዝ ይፍጨረጨራሉ። በዳላስ ካቀፉዋቸውም ውስጥ ደብራችሁን የከሰሱና ያስከሰሱ ይገኙበታል። ከነዚሁ የወያኔ ቅጥረኞች ውስጥ ተኩላው (ተኮላ) ጓደኛው ሽኮኮ የመሰለ እስስት (ፀሀይጽድቅ) እንደዚሁም ቀዩ ሰይጣን ይገኙበታል።

እኛን መነካካት የተጠናወተው ተኩላው ለእርሱና ቢጤዎቹ ለምንሰጠው ባህሪ በጣሙን እንደቆሰለ ዘወትር በብዕሩ አጣጣል እየገለጠው ይገኛል። እኛም እንዳንጨምርበት የሚችል ልብ የለውምና በአንድ በኩል እናዝንለታለን። እሱንና ቢጤዎቹ እግዚሀብሔርን አውቀውና ንስሀ ገብተው እንዲሞቱ እንጂ ይህቺ ፫ጊዜ በድንገተኛ ልብ ድካም የመነመነች ልቡ ጧኣ ብላ እንድትቀር ፈጽመን አንሻምና እናዝንልሀለን። ቅዱስ ሚካኤል ግን እንዳያፈርጥህና እንዳታርፈው። በሞትና በሕይወት አፋፍ አጣብቂኝ ያለህ መሆንህን የረሳህ፣ ከታቦት ጋር ፍርድ ቤት የቆምክ ፣ ጭራሹን ሀይማኖት የሌለህና ለወያኔ ያደርክ፣ ይህንኑ ለማስፈጸም የምትሯሯጥ ለመሆንህ የምትገኝባቸውና የተሳተፍክባቸው በሎሌዎቹ የሚጠራው ስብሰባ ያንተን ባንዳነት ማስረጃ ናቸውና፤ ቤተክርስትያን ውስጥ ፖለቲካና የንጹሀንን አግልጋዮችን ስም መቀባት የጀመርክ ራስህ ነህና አሁን ሌላ መኮነንህን ለራስህ አድርገው።

እኛ በእርግጥ ሀይማኖትታችንን ፣ ወገኖቻችንን ብሎም ይቺን ሀገራችን አርገን የምንኮራባትን አሜሪካንን የምንወዳትንና የምንሰፈሰፍላትን ያህል ያላነሰ ለትውልድ ሀገራችን ኢትዮጵያም እንቆረቆራለን፣ መልካም አስተዳደርና ብልጽግናዋን ማየት የምንግዜም ምኞታችን ብቻ ሳይሆን በምንችለው ሁሉ በጎውን እናደርጋለን። ይህ ሀቅ ነው። አንተም የፈለከውን የፖለቲካ አቋም መውሰድና መደገፍ መብት አለህ። ነገር ግን የውጭ መንግሥትና አላማ አምጥተህ በመካከላችንና ብለህም በሀይማኖታችን ውስጥ ጣልቃ ማስገባት ወይንም በምንም አይነት መልኩ ማስረግ በሕጋዊም ሆነ በሞራልም በኩል ተቀባይነት የሌለው አጀንዳ ነው የምንልህ። ዛሬ ሸፈፈፍ ብለህ ከፍርድ ቤቱ ስትቻኮል እንደ ድል ቆጥረህ ሻምባይ ይዘህ ትጥፋለህ ብለን ነበር። ለምን እንደዘገየህ ባይገባንም ከማጅራትህ ላይ ቆመን የምንተነፍስብህ መስሎህ እውነቷን ለማስረገጥ በመሞከርህ በዚሁ እውነት ለመናገር ያበረታህ ወደ እውነተኛው መንገድም በመምራት የሰፈረብህን አጋንንት ያውጣልህ ነው የምንል። ረዳት ዳኛዋ የሰጠችው ትዕዛዝ ገና ለድል የሚያበቃ ስላልሆነ ረጋ በል፣ ለሳሳችዋ ልብህ አስብላት።

በተረፈ ያጀቡህ ካንተም የማይሻሉ በመሆናቸው አሁንም አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሆኑት ውስጥ ገነት ከበደ (እብዶ/ቀጮ)፣ መስፍን ወልደየስ (በበጎ አድራጎት ስም ገንዘብ ከደብሩ የመዘበረ) ጓደኛህ ሽኮኮ እስስት ፀሀይጽድቅ፣ እንደዚሁም የነገር አባታችሁና ጠሀፊያችሁ እነ ምናምንቴ እንደ ሆነስ ለምን አላወሳህም? ከጥሁፍ እንዳየነው ከሆነ አሳዳጊ የበደለው መባልን እንደማትሻ አስምረህበታል። ማለፊያ ነጥብ ነው የጣፍከውን መልሰህ ካነበብከው። አንተና ቢጤዎችህ ማን እንዳሳደጋችሁማ ራሳችሁ በተግባር እያሳያችሁን አይደል እንዴ? እንግዲህ ምትሀት አሊያም የምትወስዱት የልብም ሆነ ለሌላ መድሀኒት ካልሆነ ፤ ህሊናን የሚያስት አደንዛዥ እጽዋት ወይንም ልክፍት እንበለው ወይስ በዘር የሚመጣ በሽታ፤ይህም ካልሆነ መረንና ልቅ አስተዳደግ ይሆን ወይስ ከዚያ የከፋ ብልግናና አስነዋሪ እንዲሁም ማፈሪያ ያደረጋችሁ? በውን እናንተ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አላችሁ? እሱንም የወረሳችሁት ካሳደጎቻችሁ ነውን? እነሱም ደብር እየከሰሱ ነው ያሳደጋችሁ? እንዲያ ከሆነ ቀጥሉበትና በርቱ! ለዚህም ነው ከወላጆቻችሁ የወረሳችሁትን እናንተም እየደገማችሁ ያላችሁ? ከዚህስ ያቺ በእንጥልጥል ላይ ያለች ልብህ ትፋረድህ የምንል። እኛ የቅዱሳን ልጅ ቅዱስ ወይንም የሰይጣን ልጅ አጋንንት የምንል ስለዚህ የስራህን እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ይፍረድ።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ይድረስ ለነአምን ዘለቀና ለታማኝ በየነ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ፺፯ን አስመልክቶ በተፈጠረው ሕይወታቸው የተቀጩት ዜጎችን ለመዘከር በዳላስ ከተማ በግንባር ሀላፊነቱን ወስዶ የተንቀሳቀሰው ግለሰብና አበሮቹ፣ ዝግጅቱን አስመልክቶ ይደረግ በነበረው ሳምንታዊ የቴሌኮንፍረስ ላይ ከእውነት የራቀ መረጃዎችን ሲያዘግቡ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው። በከተማው የረጅም አመታት ነዋሪነትና የነዋሪ ወገኖቻችንን አመኔታና ድጋፍ ይዘናል የሚሉ እነዚሁ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች በፖለቲካው አሪና ፖለቲከኛ፣ በቤተ ክርስትያንም ሆነ መስጊድ ሀይማኖተኛ፣ በመረዳጃ ማህበሩም ውስጥ ለወገን ሀሳቢና ደራሽ አድርገው እርስ በራሳቸው ሲመራረጡና ሲሿሿሙ፤ የሀቀኛ ተጋይ ወገኖች መካከል በመስረግ ትግላቸውን በተለያየ ስልት ማኮሏሸት ላይ ብቻ የተካኑ ግለሰቦች ናቸው።

የማይወክሉትና እነሱ የሌሉበት የዳላስ የሙያም ሆነ የግብረሰናይ ድርጅት የለም። በወገኖቻችን ስም የማይመዘብሩትና ለግል ጥቅም የማያውሉትን አለ ለማለት ያዳግታል። ከመረዳጃ ማህበሩ ይዞ የሬዲዮ ክፍሉንም ጨምሮ ያ ሁሉ አልበቃ ብሏቸው ዛሬ ቤተ ክርስትያን የሚተናወጡ ወዳጆች ነው እናንተም እያተረፋችሁ ያላችሁት።  እንግዲህ የናንተ መመሪያ ይኼንን ሁሉ ያካትት እንደሆነ ባይገባንም ለናንተ የሰጡት ቃል ግን ፍጹም ከዕውነት የራቀ መሆኑንና በትላንት ዕለት ያዘጋጁት ስብሰባ የሚገባውን ያህል የቅስቀሳ ስራ ላለመደረጉ ምላሹ እነሱን፣ የነርሱን ቤተሰብና ወዳጆችን ጨምሮ ከነ ተናጋሪዎቹ በቁጥር ከ፵ በታች የሆኑ ብቻ እንደነበሩ በማስረጃ ተደግፎ የተቀመጠ ሆኖ ይገኛል።

ወደፊትም እናንተ ማወቅ ይገባችኃል በማለት የምናሳስበው ቢኖር፤ ይህ ወይም ሌላው ትግላችሁ በእንደዚህ አይነት ደካማና አፍራሽ ግለሰቦች ሰለባ ሆኖ እንዳይኮላሽ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድትወስዱ ነው።

Sunday, November 7, 2010

የኮብራ እባቡን ያዙልንና እንለፍ ለሚሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የኮብራ እባቡን ያዙልንና እንለፍ ለሚሉ

በዚህ አገር የኮብራ ዘር የሆኑት የእባብ አይነቶች አደገኛ ገዳይ ሀይል ያላቸው በመሆናቸው እጅጉን የተፈሩ መርዛሞች ናቸው። የኛም ገጽ እነዚህን መርዛም እባቦችን ለይተን ስናሳውቃችሁ አብረን ከርመናል።እንግዲህ የነቃችሁባቸውና እያደበያችሁ የጣሏችኃቸው ብዙዎች ናችሁ። ነገር ግን ዛሬም እነዚህን መርዛም እባቦችን ያዙልንና እንለፍ የምትሉ ቂላቅሎች ደግሞ እኛ መርዛም እባቦችን እናንተው ሞክሩና ከመርዙ ካመለጣችሁና ከተረፋችሁ፣ ብላችሁም ከልባሞቹ ጎራ ከገባችሁ እንያችሁ ነው የምንል። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? የእርሱ ፈቃድ ሆኖ ለዚህ ጊዜ ላደረሰን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።

በተለያየ ጊዜ አስረግጠን በደብራችሁና በመረዳጃ ማህበራችሁ ላይ የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ሂደት በሚገባ እያስጨበጥናችሁ አብረን ከርመናል። በየጊዜውም አዲስ አበባ እየደረሱ ለሚዘግቡት መረጃ ካሳ ጥቅማጥቅም ከሚደለሉት ውስጥ ብዙዎቹ ባለ መሬት ሆነዋል። መቃብር ቦታን ሳይቀር እያፈራረሰ እንዲሁም የገጠር መሬት ሳይቀር ለውጭ ባለ ሀብቶች በነጻ ለማለት በሚያስደፍር ዋጋ እየቸበቸበ ያለ መንግሥት፤ ምንም አይነት ለነዋሪው ዜጋ፣ ለአካባቢው አየርም ሆነ መሬት ብክለት ደንታ እንደሌለው ባለፉት ጥቂት አመታት ከአበባው እርሻ ሂደት የጨበጥነውን ዋቢ በማድረግ ስንተች ለወደፊቱ የተሻለ አቀራረብ እንዲሰነጽ ለሚመለከተው አካል የመጠቆም የትውልድ ግዴታችንን ለመወጣት በማሰብ ነው። ካካባቢው ከሚወጡት ዘገባዎች፣ በአበባው ምርት ምክንያት ካካባቢው ለተፈናቀሉት ዘለቄታዊነት የጎደለው የአኗኗር ልውውጥ (ትራንስፎርሜሽን) ፤ በምርቱ ምክንያት የተፈጠረው የተፈጥሮና የአካባቢ ብክለት ያስከተለው ፤ ባምራች ሰራተኞች ላይ የደረሰው የጤና ችግርና በምድረ ከርሱ ላይ ያተረፈው ብክለት በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

ቤተ ክህነቱ ባለው የአስተዳደር ብልሹነትና የውስጥ ምዝበራ የተነሳ እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ደብር ለንዋይ የሚያደርገው ሩጫ ወደ ሌላውም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዳይሰራጭ እየተሰጋ ያለ ችግር ነው። አጽማቸው እየወጣ ያሉት ብዙዎቹ ለዚያ ቤተ ክርስትያን በዚያ ቦታ ከምስረታው እስከ ህልውናው በሕይወታቸው የከፈሉት የሚዘነጋ አይደለም። የመሬት ችግር የለብንም የሚል መንግሥት ተርፎት ለባእድ የሚቸረችር እንዴት ይህንን ጉዳይ በዝምታ ያየዋል። እኛ ሀገር አይሰልጥን አንልም ነገር ግን ሁሉም በአግባቡ ቢሆንና ለቀጣዩም ትውልድ በማስተዋል ይሁን ነው የምንል።

በመረዳጃ ማህበራችሁ ስር በሕገወጥ መንገድ የተለጠፈውን እድር በማደራጀት የያዙት የጴንጤ እምነት ካላቸው ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ጎራ እያሉ መረጃ ባቀረቡ ቁጥር በጥቅማ ጥቅም እየተደለሉ የሚመለሱትን እያዩ ከእስልምና ሀይማኖት የያዙትም እሽቅድድም እየገቡ ነው የሚል ዘገባ በማየታችን ብዙም አልተገረምንም። አዲስ የሚመረጡ ከተገኙ ፣ እድሩን በፍጹም ከመረዳጃው ማፋታት የቅድሚያ አጀንዳቸው መሆን የሚገባ ነው። በአሁኑ ሰአት ህብረተሰቡ ሁኔታዎችን በሚገባ አላምጦ የጨረሰ በመሆኑ ተግባራዊ ያደርገዋል የሚል ተስፋ እየታየ ነው። በተለይም በአሁኑ ሰአት ለሁለት ተከፍሎ ያለው የመረዳጃው ማህበር አመራር በቅርቡ ራሱን እየቀረጸ ይመጣል የሚል ተስፋ እየታየ ነው። አንዳንዶች አመራር ላይ ያሉት አንጃ እየሆኑባቸው የመጡት በወንጀል ደም እጃቸውን ከታጠቡት ጋር ላለመስራት እራሳቸውንም ለመለየት ወስነዋል። አሁንም በነ ይልማ ፈለቀ የሚመራው የወያኔ ቡድን ቀስ እያለ መሬት እየከዳው ይገኛል። አዲሱ ምርጫም በፊት እራሳቸውን ያገላሉ ተብሎም ይጠበቃል። በሌላ በኩል ከወይዘሮዋ ጦመር እየተጋለጡና እየተመቱ ያሉት ፤ በህብረተሰቡ ስም በብዙ ሺህ ዶላር ሲዘርፍ የነበሩት የነ በትሩ ገ/እግዚሀብሔር ጉድ በማስረጃ እየተቀነባበረ እየተሰራ ለመሆኑ እንደዚሁም የመንግሥትም እጅ በቅርቡ ይገባበታል የሚባልም መረጃዎች ለመመዝገብ በቅተናል።

በሌላ በኩልም የእስስቱ ተፈራወርቅ ቡድን የተከላቸው እነ ፍቅረማሪያም ደረሰ ቡድን በመጋለጡና አዋቀርን ያሉትም ቡድን በመፍረሱ እነ ግርማቸው አድማሴ የጤና ቀውስ ውስጥ ከቶአቸው ይገኛል። እነዚህን መርዛም እባቦች የዳላስ ሕዝብ አንቅሮ ከተፋቸው እንግዲህ ከርሟልና መቃብራቸውን እየተመኙ ናቸው። ሰይጣናዊ ስራቸውን በመልካም ስም ለመሸፈን ሲሉ መለከት ያሉትም ገጻቸው እንደ በረዶ ከደረቀ ከርመ፣ ሀሰታቸው ሁሉ ተጋለጠ፣ እርቃናቸውን መቅረታቸውን ሀገር አወቀው። መሪዎቻቸው የሆኑት በቤተክርስትያኑና በዳላስ ነዋሪ በሆነ የኢትዮጵያ ተውላጆች ስም መነገዱን እንዲያቆሙ የሁላችሁም ግዴታ መሆን ያለበት፣ ባቆሙዋቸው የሀሰት ግብረ ሰናይና የባለሙያዎች ድርጅቶች ስም በሚንቀሳቀሱበት ሁሉ እየተገኛችሁ እናንተን እንደማይወክሉ ማጋለጥ ከሁላችሁም የሚጠበቅ ትግል ነው። በተለይም የወይዘሮዋ ጦመር ባለፈው ባወጣው መልዕክት ላይ በየሳምንቱ በሚካሄደው የቴሌኮንፍረስ የፓለቲካ ውይይት ላይ በመመዝገብ እየተሳተፋችሁ እነዚህን መርዛም እባበቦችን ማጋላጥ ግዴታችሁ ነው።

ፓለቲካው ውስጥም ፓለቲከኛ፣ ቤተ ክርስትያን ውስጥም ሀይማኖተኛ፣ በመረዳጃ ማህበር ውስጥም የወገን አሳቢ በመምሰል ለግልና ለወያኔ ጥቅም ማደሪያው ጊዜ አብቅቷልና ጥፉ በሏቸው። ከናንተ በተለያየ መንገድ የሚሰበስቡት ገንዘብ የት እንደሚገባ ታውቃላችሁን? እነሱና ቢጤዎቻቸው ኪስ ውስጥ ነው። ለምሳሌ የቅንጅቱ ብርሀኑ ነጋ በቅርቡ በጥሬ ገንዘብ ፩ ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት መግዛቱ፤ የማይበራ ባትሪ የሚሉት የናንተው የዳላሱ ደጀኔ ወይንም ፍቅረማሪያም ስንት ደርሷቸው ይሆን?

ለመሆኑ በደብራችሁ ቅዱስ ሚካኤል አዲስ የተቀጠረው መምህር ስለ ልጆቻችሁ የሚሰራውን ጎብኝታችሁ የጣላችሁልን ባይኖርም፤ እኛም የሱ የርቀት ተማሪ ሆነን ጀምረናል። ይህ በኢንተርኔት የምናገኘው ትምህርት አጀማመሩን ብንወደውም ለምስጋና ገና አልደረስንም። የሚነቅፉንን መነኩሴ አባትንም አዲስ አበባ ኮሌጅ ውስጥ እንዳስተማራቸውም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። እርሳቸው ግን እርሱ ባገኘው ተወዳጅነት ብዙም ተደሳች ባይሆኑም የስራ ቅጥራቸው እንዲፈረም በጣም የቸኮሉ ሆነው ተገኝተዋል። እንደሚደርሰን ዘገባ ከሆነ በጣሙን ከነክፈተው (ኢዮኤል) ነጋ ቡድን ጋር እጅና ጓንት እንዲሉ የዕለት ጎብኜ ወዳጆቻቸውና አማላጆቻቸው ሆነዋል። ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ካንድም ሁለቴ አውግዘዋችሁ አልፎ እርግማን ስለጣሉባችሁ ነው ትሉን ይሆናል! ያ ለኛ አይደለም። እኛ ዕውነትን ዕውነት፣ ሀሰትንም ሀሰት እንደምንል ሁሉ ለሳቸው ወዳጆች የሰጠነው ዕውነተኛ ባሕሪያቸውን ነው እንጂ ፈጥረነው እንዳልሆነ በግልጽ የተቀመጠ ነው። እኛም የግለሰቡን መብትና ነጻነት ስለምናከብር ከመሰላቸው ሁሉ የመወዳጀት መብታቸውን በድጋሚ እናከብራለን። የነሱንም ተጽዕኖ ተቀብለው ቢያራምዱም እንዳመጣጡ በጊዜው የደብሩን ህልውና በማስቀደም እናስተናግደዋለን።    

ከዚህ ባለፈ እንግዲህ ለልጆቻችሁ ትምህርት በተመለከተ የምታደርጉት አስተዋጾ በጣሙን ከማስኮራት አልፎ የሚያስቀና ሆኖ አግኝተነዋል። በደብሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ፹ በላይ ፈቃደኛ ሆነው ለልጆቻችሁ የትምህርት ክፍል ለመርዳት የተመዘገቡ ተገኝተዋል። ልዑል እግዚሀብሔር ምስጋና ይግባው። አሜን። እንደምንሰማው ከሆነ አስተዳደሩ የተቀሩትንም ንዑሳን ክፍሎችን ሁሉ በሚገባ ማደራጀት ስለጀመረ የምትችሉ ሁሉ በሚመስላችሁ ንዑሳን ክፍል እየተመዘገባችሁ አገልግሎት በመስጠት እንድትባረኩ በዚህ አጋጣሚ ከሚካኤል ሰይፍ ተወካይ የቀረበውን ጥሪ እናስተላልፋለን። እየተዋቀሩ ካሉት ውስጥ የአባት መዘምራን፣ የመስተንግዶ ክፍል ተጨማሪ የሰው ኃይል፣ እንደዚሁም የበዐል ቀን ዝግጅት የመሳሰሉ ሲገኙ ፤ ለመጪው የቅዱስ ሚካኤል በዐለ ንግሥ የገንዘብና የሁለቱንም ጾታ የሰው ኃይል ፈቃደኞችን ስለሚያስፈልግ የተቻላችሁን ሁሉ እንትተባበሯቸው በቅዱስ ሚካኤል ስም ጥሪ እናቀርባለን?

እርሶስ ምን ይላሉ?

Wednesday, November 3, 2010

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የሰሞኑ የዳላስ አየር ዝናብና ቅዝቃዜ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበሩንም ሆነ ቤተክርስትያናችሁ ውስጥ ውስጡን የነካካውንና የገባው አዲስ አየር የአንዳንዶችን ጎራ ጠአሙን እየለወጠ ይገኛል። በተለይም የወይዞሮዋ ጦመር ያስበረገጋቸው የሀሳብ ድውያኖች የመጣባቸው ቀዝቃው አየር ሳይሆን ሀፍረትና ክስረት ከየአደባባዩ እያሸሻቸው ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? በእርሱ ፀጋና ምህረት ለዚህ ያደረሰን እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ለእርሱና ለገናና ስሙ ይሁን። አሜን።

ያለውንና ያለፈውን የዳላስ ኢትዮጵያ ተወላጆችን ስናስታውስ ፤ እንኳን ከዳላስ እራቅን ብለን ለመዳዳት ቢፈታተነንም፣ ላለን የወገን ክብርና ፍቅር ግን ምነው ገለባውን ሳንለይ አፋጥነህ ያወጣኸን የሚል ወኔን ያገሳናል። ይኹንና ካለንበት እርቀቱ ሳይገታን ሀዘንና ደስታችሁን እንድንካፈል ለተቀደሰውም ትግላችሁ በፀሎትም ሆነ በሀሳብ አብረናችሁ በመጓዝ ከቀን ወደቀን የምትከፍሉትን መስዋዕትና ፍሬ በማየት በውስጣችን ያበራችሁትን ተስፋ ወሰን የሌለው በመሆኑ ለሠራዊት ሁሉ ጌታና ፈጣሪ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ከንቅቡ ተንገዋለው ከወደቁት ውስጥ እንደ ክፈተው ነጋ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ፊርማቸውና ፎቶግራግ ታሪካቸው ተጠርዞ ገበያ ላይ ረክሶ ወድቆ ይገኛል። ከሩሲያዊያን ዘንድ ሲጀመር ያልነበረው እንደነበረ በሞቀበት ሁሉ እየገባ ሙሾ ማውጣት የሚወደው ክፈተው ዛሬ ደግሞ የነእስስቱ አለቅላቂ እንደዚሁም ጭፍራ ሆኖ መገኘትና ደብሩን በተለያየ መንገድ መውጋት ስራዬ ብሎ የያዘው፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን ይዞ መነኩሴ ካህኑን ለመደለል ከስውር ወደ ገሀድ ገብቶበታል። ከ፩፪ አመት በፊት ደብሩ እንዳይቀጥራቸው ከወሰኑት ውስጥ አንዱ የነበረና በወቅቱ የሕግ ወጥ ቁማር በማጫወት ተዳዳሪ የነበረው ክፈተው ነጋ (ኢዮኤል) ከሳምንት በፈት በዋለው ሰንበት አርፍዶ ወደ ቤተ ክርስትያኑ ውስጥ ወደ ፊት ዘልቆ የተቀመጠው፣ እንደምዕመናኑ ተባርኮ እንደመውጣት፣ እርሱ ግን እስከመጨረሻው ቆይቶ መነኩሴው ጨርሰው ሲወጡ ጠብቆ ሲጠቀጥቃቸው የተመለከቱ ሁሉ ግርሞታቸው በፈታቸው እንደሚነበብ ፤ መነኩሴውም ቤሆን ሲሸሹት እንደከረሙና ቀንና ሰአቱን ተጠቅሞ የእልህ ድርጊትና መንፈሳዊነት የጎደለው አቀራረብ እንደነበር፣ እንደዚሁም የእርሳቸው ችኮላ ፈቃደኛ አልመሆናቸውን እንደሚያሳይ በቦታው የታዘቡትን አካፍለውናል።

ውኃ ስላፈሰሱበት ብቻ የለበሱት ሸማ ንጹህ የሚመስላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያን ድርጊታቸውን የጀመሩት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትና አድገውም በዳላስ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማህበር ውስጥ ቢሆንም፤ በደበሩ ውስጥም በነበረው ችግር ዘው ብለው ሲገቡ ለሀይማኖታቸው በቆሙ ተገተው አሁን ለመበርከክ በቅተዋል። እነሱ መጀመሪያ ሸማቸው ከመቆሸሹ በፈት የራሳቸው ጭቅቅት ወደ ሸማቸው የተላለፈ መሆኑን ዛሬም አልገባቸውም። ብዙዎቹም በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ ወደ ውጭው አለም ተልከው እስከ ዶክተርነት ማዕረግ ትምህርት የደረሱና ያስተማራቸውንም ሕዝብ የካዱ፣ ዕውቀታቸው የከፈተላቸውን ብርሀን ከመጠቀምና ለሀገራቸው ዕድገትን ከማምጣት ይልቅ ከስርዐቱ ጋር ተቆላልፈው አብረው የወደቁ ቅድመ አብዮትና የነሱ ጸር ሆነውም ገሚሱ አብዮተኛ ሌላው ተቃራኒ ሆነው ሀገርና ያጠፉ ብለውም በንጹህ የወገን ደም የታጠቡ፤ ዛሬ ደግሞ በሰከነ እድሜና ወደ ሞት በመጠሪያ ዋዜማቸው ንስሀ ገብተው በጎ እያደረጉ መጠሪያ ሰአታቸውን ከመጠባበቅ ይልቅ፤ በከተማችሁ የወያኔ ሎሌነትን መርጠውና ታዛዥ ሆነው በሱ መመሪያ ለሱ ስጋት የሆኑትንና ወደፊትም ስጋት ይሆነኛል ብሎ የሚያስባቸውን በራሱ ቅጥረኛ መቆጣጠር ካልሆነም ማጥፋት በሚለው የተሰማሩ ሆነው ተገኝተዋል። በቅርቡ ቅንጅት የተባለውን የከተማችሁን ድርጅት እንዴት ለሁለት እንደከፈሉትና እንዳከሰሙት። ከዚያም ደጀን ብለው የወያኔ ምርኮኛ እንዳደረጉት እናንተው ምስክሮች ናችሁ።

የማይበራ ባትሪ የሚሉት የተገንጣዩ ቅንጅት ደጀኔ ለአምስተኛው አመት የምርጫ ፱፯ ተያይዞ ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰውትን ለመዘከር የበተነውን  በራሪ የላኩልን ተባባሪያችንን እያመሰገንን እንደ ሞኝ የራሱን ቁጥር አክሎበታል። እኛ ግን ከኃላው ያሉትን እነ ኪዳኔ አለማየሁ፣ በትሩ ግ/እግዚሀብሔር፣ ተፈራወርቅ አሰፋና ወዘተ ….. እንድሆኑና እነርሱም ይህንኑ ቀን በማስመልከት በዳላስ ስም ሰፋ ያለ ጊዜ በቴሌ ኮንፍረስ ያሳለፉና ይህንንም በተመለከተ ነዋሪው ግንዛቤ እንዳይጨብጥ አፍነው ይዘው የከረሙ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ ጊዜ ለወያኔ መረጃ አስተላላፊ እንደነበሩ ያገኘነው መርጃ ያረጋግጣል። በተለይ እነዚህ ፫ ግለሰቦች ዳላስ የገቡት አላማናተልዕኮ ይዘው ነው። ለዚህም ነው ከዳላስ በፊት የነበረው ሕይወታቸው፤ ሸማቸው ላይ ውኃ በማፍሰስ የሚጠራ አይደለምና በተለይ የአሜሪካውን ለመቃኘት ጉግልም ይበቃል የሚያሰኝ።

አንዳንድ የዋህ የሆኑ በመረዳጃው ማህበር ስር የተቋቋመውን እድር በተለየ መልኩ ሲመለከቱት ታይተዋል። ሀቁ ግን የተለየ ነው። የመረዳጃው ማህበር አገልግሎቱና ሕጋዊ ፈቃዱ ፈፅሞ ከእድር ጋር በማንኛውም መንገድ የማይገናኝ በሕግ ወጥ መንገድ የተለጠፈ ድርጅት ነው፤ የ አይ አር ኤስ ህግን ያልተከተለና የተላለፈ ነው። ያለ ውዴታ በግዴታ በአመት ፵ ዶላር ከእድር አባሎች የሚነጠቀው ገንዘብ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው። መረዳጃውም ይቀበል ከሆነ ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ሕግን በተጻረረ መንገድ ለእድሩ ጃንጥላ መሆኑ በራሱ ሕግን ተላልፎ ተጠያቂ ያደርገዋል። ሰሞኑን ምርጫ ተብሎ በእድሩ ስም የተጠራውና የሚካሄደው ማን ያቦካውንና የጋገረውን ማን ሊቋደስ እንደሆነና ማን ላይ ለመላከክ እንደሆነ ባይገባንም፤ እንደ ጀመሩትና እንደ አደራጁት እድሩ ከማህበሩ ተነጥሎ ራሱን እንደ ክለብ አሊያም የንግድ ድርጅት አድርጎ በትርፋማነት ለመንቀሳቀስ ባስቸኳይ ካልሆነ ፤ ነገ እስከነ አካቴው መረዳጃ ማህበሩንም ያጠፋዋል። የማይሆንም ከሆነ የቀረውን ገንዝብ ተከፋፍሎ ወይንም ለመረዳጃው ማህበር አሊያም ለተመሳሳይ ግብረ ሰናይ ተሰጥቶ መዘጋት የሚገባው ነውና። ይህንን የማይቀበል ወይንም ጥርጣሬ ላለው የራሱን የሕግ ባለሙያ ምክር መሻቱ ተገቢ ነው ስንል፤ የቀብር መድህን ዋስትና ግን በአይነቱም ሆነ በጥራቱ እንዲሁም በዋጋው አሁን አባላቱ ከሚከፍለው ጋር ማስተያየቱ ልዩነቱን ለማወቅ አያውክም።

ለመቛጫ ወደ ደብሩ ስንመለስ ቀደም ብለው ከቤተ ክርስትያኑ እርቀው የነበሩትና ቅያሜ አላቸው የሚባል አሉባልታ የሚናፈስባቸው የነበሩት ሁሉ ዛሬ ወደ ምንጩና ወደ ቤታቸው ተመልሰው ይገኛሉ። እንደ ምንጮቻችን አጠያየቅ የተረዱትን ሲያካፍሉን ፤ እነዚህ ወገኖቻችን እኛ ወደ ድብራችን የምንመጣው አብረን በህብረት ፈጣሪያችንን ለማመስገንና በሁላችንም ደስ እንዲለው ነው። ነገር ግን በእርሱ ቤት እርሱንም እኛንም የሚያሳዝነን ልናይ ስላልፈቀድን ፣ እዚህም በህብረት ባልጸለይንበት ጊዜ መጥተን ከውጭ ተሳልመንና ጸልየን ከመሄድና በያለንበት ተመሳሳይ የግል ጸሎታችንን ስላላቋረጥን መልሱን ስናገኝ ይኸው ተመልሰናል ብለው የነገሯቸውን ለኛም አካፍለውናል። እግዚሀብሔር አሁንም ይስማችሁ ነው የምንል። በሌላ በኩል አዲስ አባልነት ለመመዝገብ ጥያቄዎች እየበዙና እየተስተናገዱ ሲሆን አሁንም ቅሬታ አለን ብለው ከከሳሾች ጋር የወገኑና ራሳቸውን የቅዱስ ሚካኤል መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው የሚጠሩና የቦደኑ አሁንም በአባልነት ያሉ ፲ የማይጠጉ ግለሰቦች ናቸው። እንደሚታወቀው ሁሉ የከሰሱም ሆነ በዚህ ቡድን የታቀፉት በሙሉ የደብሩ አባላት ያልሆኑ መሆናቸውን ለማንም የተሰወረ አይደለምና። እነዚህም ጥቂት ግለሰቦችም ቢሆኑ አላማና አጀንዳ ያላቸውና ዘወትር እንደ ውዳሴ የሚሉት የወያኔ የ፶፪ ገጽ ሎሌ እንጂ ምንም አይነት የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ዕምነት የሌላቸውና መተግበሩንም ለማስመሰል እንኳን አልሆን ያላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያንና እንደዚሁም ጸረ መረዳጃ ማህበር መሆናቸውን በተግባር ያስመዘገቡ ናቸው። በተለይም መለከት በተባለው ገጻቸው በሴብተምበር 25 የቃዡትን በትላንቱ ዕለት በተደረገው የውስጥ ስብሰባ ላይ ቅዠት ተብሎላቸው ተደምድሟል። እነሱ የተከሏቸውና አስርገው ያስገቧቸውም እነፍቅረማርያም ሚስጥሩ ደርሷቸው ባይገኙም የበላይ መሪና አማካሪያቸው የሆነውና በሌላ ቡድን ያሰረጉት መልዕክቱን በሚገባ የተረዳው መሆኑን ተቀብሎታል ሲል የሚካኤል ሰይፍ ወኪል ካዛገበን ተረድተናል። በዚህ ስብሰባ ላይ የተገኙት በሙሉ የዕምነቱ አማኞችና ተከታዮች ብቻ ሳይሆን ከስራቸው የሚመራቸውና ያቀፏቸው በጎሳና በዘር የታቀፉ፣ በማህበር ፣ጥዋና በመሳሰለው በተለያየ  ከሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ የተመረጡትን አቅፎና ተደራጅቶ የያዘ የደብሩ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጨምሮ አስገንዝቦናል። በዚሁ ስብስባ ላይም ደብሩ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያለ፣ የአባላትም ተሳትፎ ከፍ ያለ፣ የሚያኮራ ውጤት ላይ መድረሱንና አስተዳደር ቦርዱም ዕቅዶቹን ለመተግበር እያደረገ ያለው አመርቂ መሆኑን ተገልጧል። የምዕመናኑም እጅ ተከፍቶ ለደብሩና ለቅዱስ ያሬድ ትምህርት ቤት የሚያደርገው እርዳታ እያደገ ይገኛል ፤የተጨማሪ የትምህርት ክፍል ጥያቄ ወሳኝነት ደረጃ ላይ መድረሱም ተወስቷል።

በሚቀጥለው ጥሁፋችን በቸርነቱ እስክንገናኝ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኃለን።


እርሶስ ምን ይላሉ?