Monday, November 22, 2010

በእርሱ ፈቃድ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! 


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



በእርሱ ፈቃድ ስለሆነልን ሁሉ ክብርና ምስጋና ለልዑል እግዚሀብሔር ይሁንልን። አሜን። ሀሳብ እንጂ የመሳካቱን እምነት ለእርሱ ለታላቁ መላእከ ሚካኤል በመተዋችን በአለፈው ዕለተ አርብ የእለቱን ስራችንን ጨርሰን የአየር መሳፈሪያ ቲኬትን እንዳገኘን፣ የአውቶሞቢል አከራዮችንም ዳላስ ስንደርስ እንደሚያቀርቡልን ካረጋገጥን በኃላ ነበር የማደሪያ ሆቴላችንም እንደዚያው የቀናን። ምሽቱን በረን ፣ መኪናውንም ተቀብለን፣ ሆቴልም ላፍታ ገብተንና ተጸዳድተን ፣ ለባብሰን ከእኩለ ሌሊት በኃላ የቅዱስ ሚካኤል በክንፉ አቅፎና ደግፎ ከገልፉ የአሜሪካን ሀገረ ክፍል አንስቶ በጋርላንድ ቴክሳስ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በሥርዐተ ማህሌት አጋማሽ አብቅቶ፣ ንግሠ በዓሉን ከናንተ ጋር እንድናከብር ያበቃን። እናንተንም እንኳን ለዚህ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ለዚሁም የእርሱ ፍቃድ አሁንም ይክበር ይመስገን። አሜን።


ከእርሱ ምስጋና በመለጠቅ ዘርዝረን የማንዘልቃችሁ ለዚህ በዓል መሳካት ጉልበትና እውቀታችሁን እንዲሁም በንዋይ የተሳተፋችሁ፣ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ተሰብስባችሁና ከደብሩም ተወጣጥታችሁ አገልግሎት የሰጣችሁ ሁሉ እርሱ ቅዱስ ሚካኤል አገልግሎታችሁን ይቀበልላችሁ። በተለይም ሁለት የአስተዳደር ቦርድ አባላት ሚስቶች የጀርባ አጥንት አድርጎ ጥንካሬን ስለሰጣችሁ እርሱ ይክፈላችሁ። አንደኛዋ እህት በረጅም ጊዜ አገልግሎታቸው የእማሆይ ተቀጥያ ስም ያተረፉት እህት ከመቅደሱና ከአስተዳደር ቦርድ ውጪ ባለው ማንኛውም ክንውን ተሰጥቶ ያላቸው ሀቀኛ የቅዱስ ሚካኤል ባሪያ ናቸው። ሁላችንን የገረመን ቢኖር፣ ታቦቱ ወደ መንበሩ እንደገባ የወንበር እጥረት ኖሮ ከጀርባ ካለው ተንቀሳቃሽ መጋዘን ለማውጣት ስንራዳ፣ የበሩን መዘወሪያ ለመክፈት ወደ 15 የምንሆን ወንዶች የተሳነን እኚሁ ሴት እህታችን ነበር ተጠርተው መጥተው አከፋፈቱን ያሳዩን። ሌላዋ እህት ደግሞ የኮምፒተር ችሎታ ያላቸውና ከወጣቱ ዲያቆን አስተማሪ ጋር እየታገዙ ሌሊት ተቀን ለፍተው በኤሌክትሮኒስ ቅዳሴና መዝሙር ለምዕመናኑ መገልገያ እንዲሆንና የተቋረጠ አገልግሎቱን እንዲቀጥል ያበቁ።


እንደተረዳነው ከሆነ ይህ ወጣት መምህር በርቀት ላለነው ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመላው ዓለም የዕምነቱ ተከታዮች ቅዳሴውን live በኢንተርኔት ለማስተላለፍ እቅድ እንዳለ ነው። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አዲስ እየገባ ያለውን የ security system upgrade የstate of art ደረጃ በጠበቀ እየተካሄደ መሆኑን ስንረዳ አንዳንድ ውይይቶችንም ከተኮናታሪ ሰራተኞች ጋር ተለዋውጠናል። ይህም አንድ መሰረታዊ ስራን አስተዳደሩ እያከናወነ መሆኑን ተረድተናል። ሌላው አዲስ ያየነው ለዘማሪዎች የመልበሻ ክፍል የተባለውን ባንወደውም ጊዜዊ በመሆኑ አይከፋም። ይህን በተመለከተ የህንጻ ኮሜቴና ምዕመኑ በቅርቡ ደረጃውን የጠበቀ ህንጻ ይገነባሉ የሚል እምነት አለን። በተጨማሪም ለልጆች የትምህርት ክፍል ችግር እንዳለና ይህም ተጠንቶ በቅርቡ ይቀረፋል የሚል እምነት አለን።


ወደ በዓሉ በመመለስ ፤ የሱን ተዐምር ለማየት በመብቃታችን ከውስጣችን የሚደቀደቀው አልፎ ወጥቶ በፈታችን የወረደው ዕንባ አብረን ለተጋራነው የክርስትና ፈተና ምስክር ነበር። ዛሬ ሁልም ነገር አልፏል ብለን መቀመጥ የሌለብናን በምንችለው ሁሉ ቤተ ክርስትያናችንን ነቅተን መጠበቅ የግድ ነው። በዓሉ እጅግ ያማረና የደመቀ ሲሆን የአስተዳድደር ጠሀፊው እንደጠቆመው ደብሩ ከሌሎች እህት ደብሮች ጋር ያለውን ቅርርብ በተግባር ያሳየ ሲሆን፣ ወደፊትም በህብረት እንዴት እንደሚተሳሰሩ ጠቁሟል። እንዲሁም እስካሁን ሰራን የምንለው ያነሰ መሆኑንና እርስ በእርሳችን መናቆር አቁመን ለተተኪው ትውልድ መሰረት መጣል እንዳለብን አሳስቧል። እንግዲህ ልብ ያለው ይገነዘበው ዘንድ። ከዚሁ ሳንርቅ ሰሞኑን ለእስር የተዳረገውና በመካከካችሁ የረዥም ጊዜ ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ለሁለተኛ ጊዜ በሕግ ወጥ ተግባር ላይ መገኘቱን መረጃዎች ይጠቁሟሉ። ሌሎችም እንደሚሉት በመጀመሪያው ጥፋት እንዳልሆነ ሲሆን ቤተ ክርስትያኑም ስለእርሱ እርዳታ ስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ መናገሩ በኛ ተገቢ አይመስለንም። ባለፈው በደብሩ ውስጥ ብጥብጥ ያነሳሱ የክህነት ግዴታቸውንም ያልተወጡት ከነጥቂት ግብረአበሮቻቸው ጋር ከቅዱስ ሚካኤል አጥር ውጪ በሚገኘው የተለየ እምነት ተከታዮች ህንጻ ውስጥ መግባታቸውንና ይኸውም ነገር ፍለጋ መሆኑንን ቀደም ብለን መጣፋችን ይታወቃል። የራሳቸውን ቤት አጥፍተውና የፈጠራቸውንም አስቀይመው ራሳቸውን ሲያገሉ ራቅ ቢሉ መልካም ነበር። በእውነት አንድ ዕምነትና ሀይማኖት ካለን ለምን እናከራለን የሚለውን ለአንባቢያን በመተው፣ ክርስትናውን ለማስፋት ሲባል ላዘጋጁት መንፈሳዊ ጉባኤ ሲሆን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳደርን አዳራሽ በአነስተኛ ክፍያ መጠየቅ ፣ ይህም ባይሆን አንድ አይነት ዕምነት ያላቸው እስከሆኑ ድረስ ጉባኤቸውን አስመልክቶ ማስታወቂያ እንዲያስቀምጡና እንዲነገርላቸውም ማድረግ ሲቻላቸው ፤ እነርሱ ግን ሆነ ብለው ከመውጫው አጥር ትክክል ፊት ለፊት ከመንገዱ ባሻገር የተከሉትን ማስታወቂያቸውን አይተን ዛሬም ቅዱስ መንፈስ እንደራቃቸውና ከተሳሳተ መንገድ መውጣት እንደተሳናቸው ከተግባራቸው አረጋግጥልናል።  እንደዚሁም የምስክርነት ዝማሬ ያቀረቡት የደብሩ የወላጅ መዘምራን ልባችንን የነካው ሲሆን፣ ከምዕመኑ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ፊት የሚወርደው ዕንባ ባለፈው ጥቂት ወራቶች በደብሩ የነበረውን የክርስትና ፈተና የሚያስታውስና ፤ ሳይረዱ በሌላ ጎን ቆመው የነበሩትን፣ በተፈጠረውም አዝነውና ቆስለው የነበሩትን እንዲሁም መስዋዕት የከፈሉትን ሁሉ ወደ ምንጩ አምጥቶና በአጸደ መስቀሉ ፊት አቁሞ አንድ ያደረገበት ዕለት መሆኑ ነበር። 


የነበርነው ሁሉ ሌሊቱን በሙሉ ከኢትዮጵያና ከዚሁ ሀገር የተለያዩ አድባራት በመጡ ካህናት አባቶችና ደብሩ በቅርቡ በአገኛቸው መነኩሴ ካህን እየተመራ የተካሄደው ስርዐት ወደር የሌለው ለመሆኑ፣ የህጻናቱ ፣ የወጣቶቹ ፣ የእህቶችና ወንድሞች ዝማሬን ጨምሮ እንደ ኤሌክትሪክ በውስጣችን ሲያነዝረን ያራፈደን መንፈስ ምን ግዜም የማይረሳ በረከት ነበር። በወጣቱ አስተማሪ እየተገነቡ ያሉት ህፃናት ያቀረቡትን ስንመለከት በዚሁ ከቀጠሉ ተተኪነታቸውን አንጠራጠርም። በማግስቱም የተደረገው ስረዐተ ቅዳሴና ዝማሬ እንዲሁም የወጣቱ መምህር ትምህርት ውብ ነበረ።


ከቀትር በኃላ በዕለተ ሰንበት ወደ አየር ማረፊያ ስንጓዝ እድሉ ገጥሞን የመረዳጃ ማህበር የሬዲዮ ዝግጅት ለማዳመጥ በቅተን ነበር። እንደተሰማው ከሆነ ረጅም ጊዜውን የወሰደው ባለፈው ሳምንት በከተማችሁ ተደርጎ ስለነበረው በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ለሚመራው የኢሕአዴግ መንግስት  ስብሰባ የተቀዳውን ነበር። ሲፈልግ ተቃዋሚ እራሱን የሚያስመስለው የኢሕአዴግ መንግስት ቅጥረኛ የሆነው መረዳጃ ማህበር አመራር አቋም በገሀድ የጀመረ ለመሆኑ በዚህ ቀን broadcasting ስብሰባውን ላልነበሩት በስርጭቱ ሲያስተጋባ ነበር። የሬዲዮ ስርጭቱን በሀላፊነት የያዘው የመረዳጃ ማህበሩ የተመዘገበበትና የሚንቀሳቀስበት ሕጋዊ ፈቃዱ ውጪ የባዕድ ሀገር መንግሥት የፖለቲካ ሥራ መጠቀሚያ ሆኖ መስማታችን በጣሙን አሳዝኖን አምሽቷል። የሚያሳየውም እነዚሁ ቅጥረኞች እንዴት ሰርገው ሬዲዮኑን እንደሚጠቀሙበት ብቻ ሳይሆን ነዋሪውም በስሙ ሲጠቀሙበት ፈዞ ተመልካችነቱ ያሳፍራል። ሊያው ወንዱ ሁሉ ሱሪውን ያወለቀ ወይንም ህሊናውን የሸጠ ሆኖ ነው በዳላስ የተቀመጠ። በድርጅቱ ብለው በኃይማኖቱ  ገብተውበት ሲቀልዱበት ከጎናችሁ ተነስታ የምታበራይ የሴት ጀግና በመውጧቷ ወንዱ ሁላ ወደማጀት አሰኝታዋለች። ከትውልድ ሀገራችሁ ይዛችሁ የመጣችሁትን የወንድ ትምክህተኝነት በአንዲት ኢትዮጵያዊት ላይ ለወገኗ በመቆሟ እነምናምንቴዎች የፈጸማችሁት በደል አሁን በመረጃ እያሳደዳቹ ነውና የት ትገቡ? 

እኛና ገጻችንን በመካከላችሁ እንድንገባ ያበቃችሁን በኃይማኖታችን ስትመጡ ቢሆንም ማንነታችሁንና ስትፈጽሙ የኖራችሁትን ሕገ ወጥ ድርጊትና በወገኖቻችን ላይ የፈጸማችሁትን በደል እንደ ወይዘሮዋ ገጽ ጥያቄ ወገኖቻችሁን ሁሉ ይቅርታ ጠይቃችሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከድርጊታችሁ ካልተገታችሁ ከኪሮስ እጣ ፈንታ የማታመልጡ መሆኑንና የሚያስፈልገው መረጃ ሁሉ ከሚመለከተው ክፍል ጋር እንደምንለዋወጥ ደጋግመን እንዳስገነዘብነው እንደምንቀጥልበት ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። በትላንትናው ዕለት እርሱን ለማስፈታት የተባበራችሁ ሁሉ  ዛሬ ብታስፈቱትም የእርሱ ጉዳይ ቅድሚያ የተሰጠበትን ምክንያት የብሔራዊ ጸጥታና ጥቅም ጎጂነቱ በማየሉ ቢሆንም የተቀራችሁ ባለተሮች መዝገባችሁ የተከፈተ ቢሆንም ለማወፈር የማንግደረደር መሆናችንን እያሳወቅን የወይዘሮውን ጥያቄ መፈጸሙ እንድንራራ ያዳዳናል።

ሌላው በወይዘሮዋ ገጽ ውስጥ አዲስ የወጣውን መረጃ እንድታዩትና እንድትገነዘቡት ስንጠቁም፤ በመረዳጃ ማህበሩ አመራር ላይ ካሉት ውስጥ የኮንስትራክሽን መሀንዲስ ነኝ የሚለው ግለስብ በሰፊው የዳላስ ወገኖቻችንን እያጭበረበረና ገንዘብ እየቀማ ያለ ግለሰብ ሰለባ የሆናችሁ ቁጥራችሁ እየበዛ በመምጣቱ ከየአቅጣጫው  የምታሰሙት እሮሮ ደርሶናል። እንደዚህ ያሉ ግለስቦች አረአያዊ ምግባር የጎደላቸው ስለሆኑ ቤቱ የመጥራት ግዴታ ይገባዋል። በተለይም ከቀዳዳው ሙላው ጋር ተጣብቆ ያለና ወደ ከፍ ያለ ጥፋት ውስጥ እየገባ ለመሆኑ ጥርጥር የለንም።

እርሶስ ምን ይላሉ?

3 comments:

Anonymous said...

ዳላሶች እንዴት ከረማችሁ፤ ስለአገልግሎታችሁና ስለመቆርቆራችሁ የቆማችሁለት አንድዬ ይክፈላችሁ።
እንዳላችሁት የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በአል ከአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት በመጡ ካህናት፤ ዲያቆናት፤ ምእመናንና ምእመናት ተካፋይነት በከፍተኛ ደረጃ ተከብሮ ውሏል። እግዚአብሔር አምላካችንን ካህናት በቅዳሴና በማህሌት፤ ዘማርያን ከሂውስተን መድሃኒአለም፤ ከሂውስተን ኃመር ኖህ ቅድስት ማርያም፤ ከኧርቢንግ ማርያም፤ ከዳላስ ሚካኤል፤ ወዘተ (የልጆች፤ የወጣቶች፤ የእናትና የአባት መዘምራን) እንዲሁም ምእመናን በሚጣፍጥ ዜማ፤ በእልልታና በደስታ እንባ ፊታቸው እየታጠበ ሲያመሰግኑት አድረው ውለዋል። ላደረግልን ውለታ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተባረከና የተቀደሰ ይሁንልን። ከሩቅም ከቅርብም በአሉን ለማክበር ለመጡት ሁሉ እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ይስማላቸው፤ ስለታቸውን ይቀበላቸው፤ በረከቱንና ምህረቱን ያብዛላቸው እንላለን።
እንኳንስ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች፤ በፍርድ ቤት የከሰሱትም፤ ቤቱን ሊያዘጉና ሊያፈርሱ ዛሬም በመሯሯጥ ላይ የሚገኙትም በቦታው ተገኝተው ከቡራኬው ሲካፈሉ ተመልክተናል። እግዚአብሔር ታላቅ፤ ኃያልና የሁሉንም ልብ መርምሮ የሚያውቅ ስልሆነ እንደየስራቸው ብድራቸውን አይንፈጋቸው። ቸር አምላክ ስለሆነ እድሉን ሰጥቶ በአይናቸው እንድያዩ አድርጓቸዋል። በአንድ ወቅት አንዱን የቦርድ ተወካይ ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር። እነዚህ ከሳሽ፤ አፍራሽ፤ በጥባጭ የሚባሉትን ጣዖት አምላኪዎች ለምንድን ነው ከዚህ የማታባርሯቸው? እኛንም ቤተክርስቲይናችንንም እንዲበጠብጡ አንፈልግም፤ ይኸ እኮ አሜሪካን አገር ነው፤ ቤተክርስቲያን ለአባሎቿ ብቻ ነው አገልግሎት መስጠት ያለባት ብንላቸው። የሰጡን መልስ፤ ግድ የላችሁም ታገሱ እግዚአብሔር እኮ እነሱንም ማስተማር ይፈልጋል፤ እነዚህ ስዎች የት እንዳሉም የሚያውቁ አይመስለኝም፤ በቤተክርስቲያን ቆመው በሃሰት ስሚሉና ሲገዘቱ፤ ሲሳደቡ፤ ሲያሙ፤ አለማዊ ህይወታቸውን በሙሉ ሲያንጸባርቁ እግዚአብሔርን መድፈራቸውን የተገነዘቡ አይመስለኝም። ሞኝነታቸው እንጂ በነሱ አቅም የእግዚአብሔር ቤት ሊፈርስ አይችልም፤ እንደውም እነሱ የእግዚአብሔርን ቤት ለማፍረስ ሲሯሯጡ እግዚአብሔር ደግሞ የነሱን ቤት ያፈርሰዋል የሚል ነበር።
እኛም ይኸንን አነጋገር እንደትንቢት ወስደነው የእያንዳንዳቸውን የህይወት ታሪክ ስንመረምር፤ በእውነት እግዚአብሔር ምን ያህል ታጋሽና መሃሪ እንደሆነ ተገንዝበናል። እነዚህ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት ስራዬ ብለው የተያያዙትንና ደጋፊዎቻቸውን ስንመለከትና ታሪካቸውን ስንመረምር እንኳንስ ህያው በሆነ ሁሉን በሚችል፤ ሁሉን በሚያውቅና በሁሉም ስፍራ በሚኖር በእግዚአብሔር አምላክ ፊት ቀርቶ በኛም በደካሞቹና በሃጢአተኞቹ ፊት ለመቆም የማይገባቸው ምናምንቴዎች እንደሆኑ በጥናት አስደግፈን ደርሰንበታል። በእውነትም እግዚአብሔር ቤታቸውንና ህይወታቸውን በማፍረስ ላይ እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። ዳላሶችም በተደጋጋሚ እንደጻፋችሁት እንዚህ እኩያን ንስሃ ገብተው እግዚአብሔርን ይቅርታ ቢለምኑ ይቅር ይላቸው ዘንድ የመዳን ቀን ዛሬ ነውና።

Anonymous said...

እንደተባለው የበአሉ ዝግጅት ከማንኛውም ጊዜ በተሻለና በተቀነባበረ መልኩ በአባላቱ ትብብር እጅግ በጣም ያማረ ሊሆን ችሏል። ትብብር ላደረጋችሁ ሁሉ ቅዱስ ሚካኤል ይቁምላችሁ እያልን። ከሁሉም በላይ ገናናው ስሙ የተከበረው አምላካችን ስላደረገልን ሁሉ የተመሰገነ ይሁን።
እነዚህ ሁሉ የምታይዋቸው ለውጦች፤ ደስ የሚል በዓል መከበር፤ የልጆች ትምህርት መጀመር፤ የአስተማሪው መቀጠር፤ ወዘተርፈ እንዲሁ ዝም ተብሎ የመጡ ለውጦች እንዳልሆኑ ብዙዎቻችን እናውቃለን የማታውቁ የቤተክርስትያን ተቆርቋሪዎች ካላችሁ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለባቸው መሆኑን በግልጽ እንድታውቁ ያስፈልጋል፤ ይህን ለመረዳት የምትፈልጉ ከሆነ የምታውቋቸውን ለቤተክርስቲያኑ እድገት ሌሊትና ቀን የሚደክሙትን ብታነጋግሩ በግልጽ ሊያስረዷችሁ ይችላሉ። ይኸ በየመንደሩና በየመሸታ ቤቱ እየዞረ የሚያወራውን ብትጠይቁት የሚነግራችሁ አሉባልታና ውሸት ከመሆኑም በላይ ወይ ዘራፊ አሊያም ጥቅም የጎደለበት አስዘራፊ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም።
በአሁኑ ወቅት እንደምታዩት ቤተክርስቲያኑን እያራቆቱ ኪሳቸውን ሲያዳብሩ የነበሩት እነኢዩኢልና ግብረአበሮቹ የቤተክርስቲያኑ እድገትና የተሻለ ነገር ለልጆችና ለወላጆች በአጠቃላይ ለአባላቱም ሆነ ለቤተክርስቲያን መምጣቱ የእግር እሳት ሆኖ እያቃጠላቸው ነው።
በፊት መዝረፍ ለምን ይቀርብናል፤ ቦታችንን አንለቅም! በማለት እውስጥ ሆነው አመጸኞችን በማስተባበር ለመቆየት ሞከሩ፤ ሲዘርፉት የኖሩትን ቤተክርስቲያን ጉዳቸው እንዳይወጣ ሲሉ ያልጎደለውን ገንዘብ ጎሏል በማለት ህዝቡን አደናግረው ምርጫ በማደናቀፍ ሂሳብ እስኪጣራ አንወጣም አሉ አልሆነም። ሚካኤል ገፍትሮ ካስወጣቸው በኋላ ደግሞ እቦታችን መመለስ አለብን በማለት ታገሉ አልሆነም፤ አስከሰሱ፤ አስበጠበጡ፤ ህዝቡን ፕሮፓጋንዳና ውዥንብር በመንዛት ትክክለኛውን የቤተክርስቲያኑን ሂደት እንዳያውቅ ለማድረግ ሞከሩ ያም አልሆነም። አሁን ደግሞ በነሱ አለመኖር የተሰራው ጥሩ ነገር እንዳጋለጣቸው ሲያዩ በከፍተኛ ደረጃ በመደራጀት ላይ ይገኛሉ። ምን ለማድረግ እንደሁ ካለፈው የስራ ፍሬያቸው ስለሚታወቅ ሁላችንም በተጠንቀቅ በአይነ ቁራኛ መጠበቅ ግድ ነው።
እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ አወናባጅ ወንበዴዎች ለዘረፋቸው እንዲያመቻቸው ማህበረ ሰይጣን የሚባል የወንበዴ ጥርቅም አምጥተው በቤተክርስቲያኑ ላይ እንደመቅሰፍት በመዝራት ላንድ ሁለት አመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ዘረፉ ሲነቃና የሚያስቆማቸው ኃይል ሲመጣ፤ ከስም ማጥፋት ጀምሮ እስከ ማስፈራራት ብሎም ላቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ልጆቻቸውን በማሰማራት እስከ መደባደብ ደረሱ። ያ ሁሉ አልሰምር ሲል ወደክስ አምሩ ክሱም አልሆን ሲል የወያኔን የወንበዴ ጥርቅም አደራጅተው እንደገና ቤተክርስቲያንን ለመንጠቅ ጉልበታቸውን ፈተሹ ሚካኤል ወግዱ ብሎ እንደውሻ ጭራቸውን ቆልፈው እንዲጠፉ ቢያደራጋቸውም በየስርቻው በመልከስከስ አሁንም ሽምግልና፤ እርቅ፤ ፍቅር፤ ሰላም በማለት ለማጭበርበር ቢጥሩም የስራ ፍሬያቸው ስለሚታወቅ ሴራው አልሰራ አለ፤ ከሸፈ። አሁን ደግሞ ደብዛው ጠፍቶ የነበረውና ታይቶ የማይታወቀው ሌባ ሁሉ ከየተደበቀበት ጉድጓድ እየወጣ ወደ ሚካኤል ሰይፍ በመቅረብ መልአኩን በመፈታተን ላይ ይገኛል። የሚያሸንፈውን ለሚካኤል እንተወው።
በኛ በኩል ሰዎቹም ሆኑ ስራቸው በግልጽ የሚታወቅ ስለሆነ በዝርዝር ተጽፎ ለህዝብ መበተን አለበት እንላለን። ለመንደርደሪያ ያህልም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ህዝቡ እንዲወያይበት አቅርበናል።
1ኛ፡ በጎአድራጎት እየተባለ ሲጠራ የነበረ የማህበረ ሰይጣን ቀኝ እጅ
ሀ. መቼ እንደተመሰረተ
ለ. እነማን ይመሩት እንደነበረ፤ አሁን የት እንዳሉ፤ አድራሻ፤ ስራ፤
ሐ. የተዘረፈው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ፤ የሚታወቀው ማስረጃ ያለው፤ የማይታወቀው በግምት
መ. እንዴት ሊዘረፍ እንደቻለና አባሪ ተባባሪ እነማን እንደነበሩ
2ኛ፡ ሟች አባታችን ነፍሳችውን ይማርልን አቡነ ይስሃቅ በስማቸው የህይወት ኢንሹራንስ ተገዝቶ እንደነበረና ሲሞቱም እንሹራንስ እንደተበላ በሰፊው ይነገራል።
ሀ. የኢንሹራንሱ ገንዘብ ምን ያህል እንደነበረ
ለ. ማን ፈርሞ እንደተቀበለ
ሐ. ገንዘቡ የት እንደደረሰ
መ. በአንድ ወቅት በአለማየሁ እጅ $150,000 ከየት የመጣ ነበር ከኢንሹራንሱ ገንዘብ የአለማየሁ ድርሻ መሆኑ ነው ወይስ?
3ኛ፡ ስላለፈ ነገር መነጋገር አይገባንም፤ ያለፈ ሂሳብም ወደኋላ ሄደን ማስመርመር የለብንም የሚል መፈክር ሲያሰሙን የኖሩት ሲበዘብዙን የኖሩት የትናንት ቦርድ አባላት የዛሬ … ስለሆኑ። የትናንት የዛሬ ሳይባል ሂሳባችን ሲሆን ቤተክርስቲያኑ ከተመሰረተ ጀምሮ አልያም ላለፉት 10 አመታት አስመረምረናል የሚሉትን ጭምር በውጭ ኦዲተር ካልሆነም በአይ አር ኤስ በደንብ እንዲመረመርና ውጤቱ ለህዝብ በግልጽ እንዲታወቅ። የጎደለ ካለም ያጎደሉ በህግ እንዲጠየቁ እንዲደረግ።
4ኛ፡ በቤተክርስቲያናችን ላይ በተለያየ ምክንያት ችግር በመፍጠር ገቢው እንዲቀነስ፤ አባላት እንዳይከፍሉ፤ ህዝቡ እንዲበጣበጥ በማድረግና ረብሻ በመፍጠር ቤተክርስቲያኑ ኪሳራ ደርሶበት እንዲዘጋ እናደርጋለን በማለት የፎከሩ፤ የከሰሱ፤ የተለያየ ቅስቀሳ በማድረግ እስከዛሬ በቤተርስቲያናችን ውስጥ ቁጭ ብለው ከኛው ጋር እየበሉ እየጠጡ የሚያርዱንን የእያንዳንዳቸው ስም፤ አድራሻቸው፤ በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱት ጥፋት፤ በገንዘብ ተተምኖ
ሀ. ታሪካቸው ለህዝቡ በግልጽ እንዲነገርና ማንና ምን መሆናቸው እንዲታወቅ
ለ. በህግ ተከሰው በቤተክርስቲያኑ ላይ ያደረሱትንም ሆነ የዘረፉትን ገንዘብ እንዲከፍሉ
ሐ. በማንኛውም በቤተክርስቲያኑ ኮሚቴም ሆነ አግልግሎት እንዳይሳተፉ
መ. አዋጥተናል የሚሉት ገንዘብ ካላቸው ማስረጃቸውን ለፍርድ ቤት እንዲያቀረቡ
ይኸ እንግዲህ ከኛ የሚጠበቀውን እንስራ ለማለት እንጂ እግዚአብሔርን ንቀው ቤቱን ደፍረው ለሚያደረጉትማ ክፍያቸውን በእጥፍ ድርብ ከመላእክት አለቃ ከራሱ እንደሚቀበሉ ሙሉ እምነት አለን።

Anonymous said...

የያዕቆብ ወንድም የይሁዳ መልእክት
ምዕራፍ 1
1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤
2 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።
3 ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
5 ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።
6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።
7 እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።
8 እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ እያለሙ ሥጋቸውን ያረክሳሉ ጌትነትንም ይጥላሉ ሥልጣን ያላቸውንም ይሳደባሉ።
9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።
10 እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።
11 ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።
12 እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥
13 የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።
14-15 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።
16 እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።
17 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
18 እነርሱ። በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
19 እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
20 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
21 ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
22 አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
23 አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
24 ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
25 ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።