Saturday, December 25, 2010

በመኃላችሁ blend አድርጎ

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች በእርሱ ፈቃድ መልሶ በዚህ ጦመር ለመገናኘትና በያለንበት ሆነንም ይህን ታላቅ የክርስትና   በዐል ለማክበር ጤና፣ እድሜ ከሰላማዊ ኑሮ ጋር አዋህዶ የፈቀደልን ለእርሱ ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን።አሜን።

ባለፈው ጥሁፋችን እንዳስነበብነው ሁሉ የመረዳጃ ማህበር አመራር ብቃትና ችሎታ የለሽነት አስመልክተን ያስረገጥናቸው ነጥቦች እንዳሉ ሆነው፤ በሌላ በኩል ይህንኑ የሚያሽከረክሩና ለትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪ የሆኑት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ የነሱን ተቀጣሪዎች አስርገው ለማስገባት በተጀመረው የአመራር ምርጫ ጥቆማ ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ቢፍጨረጨሩም ቅዱስ ሚካኤል እየከሰተባቸው ይገኛል። በእነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ቡድን ካዘጋጁዋቸው ግለሰቦች ውስጥ ብዙዎቹ መስፈርቱን የማያሟሉ ሲሆን፤ ተጠቋሚ ካደረጓቸው መኃል ማንኛቸውም በትምህርትም ሆነ በስራ ችሎታቸው አሊያም ስለሀይማኖቱ እውቀት የሌላቸውን ስም ይጨምራል። ጥቂቶች ከኃላቸው አክራሪና ከሀገሪቱ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም፣ ማሀበረ ቅዱሳን ለተባለው ቡድን ተቀጣሪና መልዕክተኛ ፣ የቡድን ተገዢ፣ በዘርና በጎሳ ለተቋቋመ ድርጅትና እድር ተገዢ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ወይንም እኔ ከሌለሁበት የሚል ትምክህተኝነት የተወጠሩ፣ ሚስቶቻቸው የሌላ ዕምነት ተከታይና በሚስቶቻቸው ተጽዕኖ የኖሩ፣ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ከምንጣፍ ስር በመደበቅ ባለፈው ለተከሰተው ችግሮች ተጠታቂና ዕድል አግኝተው በአገለገሉበት ወቅት አድርባይና አስመሳይ እንጂ ብቃትን ያላስመዘገቡ፣ የወሰዱትን ያልመለሱ የተበደሩትን ያልከፈሉና ልቦናቸውን ሳያጸዱ እያወቁ የሚቆርቡትንና የሚያቆርቡትንም ያካትታል። ስለድፍረታቸው ከእርሱ ዋጋ የሚጠብቁ እነዚህ ግለሰቦች መካከል ስለአንዱ ግለሰብ ቀደም ብሎ ከተኔሲ ነዋሪ በቅርቡ የቀረበውን እያስታወስናችሁ፣ ከዚህ በታች የቀረበውን የሕግ መረጃ በጽሞና እንድታነቡትና የራሳችሁን ግንዛቤ እንድትወስዱ እየጋበዝን ከግለሰቡ ሰለባዎች ከሆኑት ውስጥም የኢትዮጵያ ተውላጆችም ይገኛሉ።

በ90ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ተኔሲ ግዛት ውስጥ ነዋሪ በነበረበት ወቅት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ስም የገንዘብ ዕርዳታ አዲስ ለሚቋቋም ቤተ ክርስትያን ይደረጋል። ይኸው በመልቲ ሙያ ወይንም በማጭበርበር ከነሚሽቱ የተካነው ግለስብ ዳላስ ላይ ማነጣጠር የጀመረው። በቅጥፈቱ ከማያወጣው አዘቅትና ኪሳራ ለመውጣት ሲል ዳላስ ላይ ባሉ ዘመዶች መሰላልነት ወደ ከተማችሁ ሲዘልቅ በነዚሁ ግለሰቦች አመቻቺነት በቀላሉ በመኃላችሁ blend አድርጎ በስማችሁ እየነገደና ለግል ጥቅሙ ሲል እናንተንም እየከፋፈለና እያናቆረ ሲኖር አመታትን አስቆጥሯል። በስማችሁ ያልከፈተው የግብረ-ሰናይና የሙያ ድርጅት ስሞች የበዙ ብቻ ሳይሆን በደብራችሁም ስም ጭምር ያጭበረበረበትን ከ ሰንበቴ  ገጽ ላይ ታገኙታላችሁ።


የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

5 comments:

Anonymous said...

ተዉ ብለናል እዛም ቤት ያለው እሳት ይፋጃል!!
አሁን ሉዘር ተኩላ ነው ወይስ ጨለማ ኩነኔ/ጸህይ የጨለመበት ነው ወይስ ክፈተው ነጋ? ኧረ ማነው ከናንተ ከአርባዎቹ ታዋቂ ወንጀለኞች የመጀመሪያውን ድንጋይ መወርወር የሚችል? ደግሞስ በያንዳንዳችሁ አይን የተጋደመውን ግንድ መስታወት አይታችሁ ቀንድና ጅራት እንዳላችሁ ለማየት እንድትችሉ ታግላችሁ ማውጣት ይሻልችኋል ወይስ ገና በፍርድ ቤት ያልተጣራ የአበበን ጉድፍ ከሱ እይን መዝንቆል?
መቸምስ ወድሀገርና! ዝኾነ ኾይኑ ሽዋን አስመራ ኾይኑ ዝብሃል! ምፋለጥማ ተፋሊጥና!
አሁን ማንኛችሁ ናችሁ ስለሰው ሃጢአት መናገር የምትችሉት? ሁላችሁም ማንነታችሁና ምንነታችሁ የሚታወቅ በየቤታችሁ ከራስ ዳሸን ተራራ የሚበልጥ ጉድ ያለባችሁ ናችሁ። ግማሻችሁ የኢትዮጵያን ወጣት ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ እንደበግ እየነዳችሁ እቤተክርስቲያን በር ላይ እየረሸናችሁ ደሙን እንደጎርፍ ውሃ እንዳላፈስሳችሁ ሁሉ እዚህ መጥታችሁ ደግሞ የሚያውቀን የለም ብላችሁ እንናተ ሃይማኖተኛና ቤተክርስቲያን ሳሚ ሆናችሁ በሌላው ምእመን ላይ ጣታችሁን መቀሰራችሁ በጣም አስገርሞናል።
ግማሻችሁ በምድረ ኢትዮጵያ ጌይ (ወንዳገረድ) የሚባለውን ቃል በየፍልውሃውና በየሆቴሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመዘገባችሁ ናችሁ፤ ሌሎቻችሁ ደግሞ ከኪስ አውላቂነት እስከ ማጅራት መቺነት፤ ከቤት ሰርሳሪነት እስከ ባሪያ ፈንጋይነት፤ ወዘተርፈ በወንጀል ስራ ተሰማርታችሁ የኖራችሁ ቦዘኔዎች ስትሆኑ እዚህ መጥታችሁ ደግሞ የሰው ትዳር ከማፍረስ፤ ከጋለሞቶች ከመደራትና ኑሮውን ለማሸነፍ ሌት ተቀን የሚደክመውን ኢትዮጵያዊ እያደናችሁ ሚስቱን ከማባለግና ከመንጠቅ አልፎ ከዘረፋ እስከ ግድያ በተለያየ የወንጀል ስራ ተሰማርታችሁ እየኖራችሁ እንደው ለመሆኑ የትኛው ታሪካችሁ ነው እናንተን በሌላው ሰው ላይ ጣታችሁን የሚያስቀስራችሁ። ተዉ ብለናል በመስታወት ቤት የሚኖር ድንጋይ አይወረውርም ብለናል።
አትነካኩን አትኮርኩሩን ለናንተው ነው ጠንቁ! የብዙዎቻችሁን ዝጉርጉር ታሪክ በስም በቀይ ቀለም መጻፍ ይቻላል፤ ቢያሻንም ከነፎተግራፋችሁ። ሁልህም/ሽም በየቤትህ ጉድ (ስኬለተን) አለህ፤ አይታወቅብኝም ብለህ ከሆነ think again ያገር ቤቱ ቀርቶ እዚህ እንኳን ያለህ የእያንዳንድህ ግም ታሪክ ቢመዘገብ ክርፋቱ መላው የኢትዮጵያን ኮሙዩኒቲ በተስቦ በሽታ ይፈጃል። ተዉ! አርፋችሁ ተቀመጡ ብለናል። አላርፍ ያለች ጣት ኩስ ጠንቁላ ትወጣለች እንደተባለው የናንተ ጣት ጠንቁላለች ነገር ግን አልወጣ ብላ እየታገለቻችሁ እንጂ፤ ስታወጧት ሁላችሁንም ጠራርጋ ይዛችሁ መቀመቅ ትወርዳላችሁ። እግዚአብሄር በናፍቆት ለምትጠብቁት ለዛ ቀን ያብቃችሁ እንላለን።

Anonymous said...

ቤተክርስቲያናችን ያለው እቋፍ ላይ ነው።
ውድቀቱም ደህንነቱም ያለው በእናንተ በማህበርተኞቹ እጅ መሆኑን አትዘንጉ፤ ችላም አትበሉ። የሚመጣውን ምርጫ እንደቀላል ነገር ቆጥራችሁ ችላ ለምትሉ ግለሰቦች መልእክቴ፤-
አንድም ሆነ ሁለት ለቦርድ የምታስገቧቸው ግለሰቦች ለምንድነው ቦርድ ለመግባት የሚፈልጉት አንድ ለማጥፋትና ለመዝረፍ አለበለዚያም ቤተክርስቲያኑን ለመሸጥ ወይስ እዉነት ቤተክርስቲያን
በንጽህ ልቦና ለማገልገል የሚለውን ጥያቄ አውጥታችሁ አውርዳችሁ መሆን አለበት። የድሮ ሃጢያታቸው በዝርዝር በመረጃ እየቀረበላችሁ አይታችሁ እንዳላየ ሰምታችሁ እንዳልሰማ በመሆን የምትመርጡት ግለሰብ በዝምድናና በጓደኝነት ከሆነ ግን ቤተክርስቲያኑን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አትዘንጉ። ስላዚህ፡ ሚካኤል ቤቱን እየጠበቀ ነው? ወይስ እየተፈታተነ ነው?
ካሁን ቀደም የሚካኤል ምእመን እያወቀ እንደነ ኢዮኤልን አይነት ቁማር አጫዋችና ብር ባራጣ አበዳሪ መርጦ ደብሩን ሲያስበዘብዝ ኖረ። እንደነ ኪዳኔ ምስክርን አይነት መርጦ ከነ ዘመዶቻቸው
በማህበረ ቅዱሳን ስም ቤተክርስቲያኑን ሲያሟጥጡቱ ኖሩ። እንደነ ኪዳኔ አለማየሁ አይነት ጋር በመተባበር ማህበር ካህናት የሚባል የቀረጥ ነጻ (501.c) ያለው ድርጂት አቋቁመው የምእመኑን
ገንዘብ በጎን እያወጡ ሲከፋፈሉት ኖሩ። አሁን ደግሞ ይህ አልበቃ ብሏቸው አይን ያወጣ ሌባ የሰው ቤት የራሱን አስመስሎ የሚሸጥና በእርግጥ የተፈረደበት ሌባ ቤተክርስቲያኑ ዉስጥ አስገብተው ሊያስበዘብዙት ይሆን?
የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊና ጥቅም አባራሪ ሰሞኑን በ http://senbete.blogspot.com/
እንደተጠቀስው ግለ ሰብ ያሉና ስማቸውን እየቀያየሩ አንዴ በትሩ አምሳለ በሌላ ጊዜ በትሩ ገብረእግዚአብሄር ሌላው ደግሞ አንዴ ተፌ በሌላ ጊዜ ተፈራ ወርቅ እየሉ የአሜሪካንን መንግስትና ህዝብ የሚያታልሉ ግለሰቦችን ወደ ቤተክርስቲያኑ መሃል አስገብተው ሊያስበዘብዙ መሆናቸውን የማያውቅ ምእመን ይኖር ይሆን? ወይስ እየወቁ የአቶ ጌታቸው ትርፌ ዘመዶች እንደሚሉት ለስለት ክፈል ብለው ሲሰጡትና ሲበላው “ እኛ የሰጠነው ለሚካኤል ነው በእኛ ፊት
የሰጠነው ደርሶልናል እሱ ቢበላው የራሱ ሃጢአት ነው” እያሉ በመደጋገም የሚሰጡና ሌባ ሲመርጡ ቤተክርስቲያኑንም ሆነ አገልግሎቱን እንደሚጎዱ አልተረዱም ማለት ይሆን?።በእኔ አስተያየት የሚካኤልን ቤተክርስቲያን ቢሆንላቸው በክስ አዳክመው ባይሆንላቸው ሰርገውገብተው እንደገና በዝብዘው እራቁቱን ካስቀሩ በኋላ ቤቱን ሸጠው ለመከፋፈል እንጅ ለአማኙ ምእመን አዝነው አለመሆኑን የተገነዘበ ሁሉ መተባበርና እነዚህን ነቀዞች በቃችሁ ማለት አለበት ባይ
ነኝ።እዩኤል የተመረጠበትንና መቅደስ ላይ ቆሞ የማለበትን አገልግሎት ለምን ረግጦ ጠፋ ብላችሁላዘናችሁ ሁሉ፤ አይናችሁን ክፈቱ እባካችሁ። እየኤል ሚካኤልን ላባ ጳውሎስ ለመሸጥተስማምቶ አቡነ ቅወስጦስን አስመጥቶ ሊያስረክብ ሲል ተነቅቶበት ሃሳቡ ሲከሽፍ ምእመኑምተናዶ ከቦርድ እናስወጣ የሚል ክርክር በነበረበት ጊዜ የተናገረውን ትእቢት የረሳቸሁ ካላችሁላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ “ ከቦርድ ካወረዱኝ ይህን ቤተክርስቲያን አዘቅት ዉስጥ ከትቸው ነው
የምወጣው” ማለቱ ይፋ እንጅ ሚስጢር አልነበረም። ይሄም አባባል የንዴት ወይም የዛቻ ብቻ እንዳልነበረ የምትረዱት፤ ያን ጊዜ የቤተክርስቲያኑ ሂሳብ የሚመራው አንድ በሱ ሁለት በ
አለማየሁ ሶስት በሌላ ማህበር ቅዱስን ተወካይ የቦርድ አባል እንደነበረና ከነዚህ ሁለቱ ብቻ በሚፈርሙበት ሰነድ የቤተክርስቲያኑ ሃብት ባዶ መሆን ይችል ነበር። ሚካኤል በጥበቡ ግን እዚያ
ከመድረሱ በፊት ቀስ በቀስ ይሄን ሃይሉን እያመነመነ ምርጫ ደርሶ ደጋፊወች በማጣቱ የዛተበትን ተንኮል አቀዝቅዞ እንዲባረር አደረገው።
የሱ ጥሎ መጥፋት ገና ምርጫው መካሄድ እንደተጀመረ የተተነበየ እንደነበረ ለሁላችንም ግልጽ ነበር።
የሱ ብቻ መቅረት ከቤተክርስቲያኑ የሚያገኘው የስርቆት ገንዘብና ከኮንትራክተሮች ላይ የሚያገኘው የደላላነት ተግባር እንደተቋረጠ ሲያውቅ ካልሰረቅሁና ጥቅም ካጣሁ ለምንድነው በነጻ የማገለግለው በማለት መሆኑን ገና ሳይታወቅ የተፈታ ነበር። አሁንም መልሳችሁ እንደሱ የመሳሰለ ሰው ለመምረጥ የምትቃጡ ካላቸሁ ቤተክርስቲያኑን አደጋ ላይ መጣላችሁን እንድታውቁት ይሁን አላለሁ። ቤተክርስቲያናችንን የምንጠብቅበት አእምሮ ይለግሰን ዘንድ ሁላችንም ተንበርክከን እንጸልይ አሜን!

Anonymous said...

ዳላስ ኢኦቲሲ እንዴት ሰነበታችሁ።
መቸም እግዚአብሔር ለቤቱ ያውቀበታልና እናንተን የመሰለ መቅሰፍት ከባህር ሆድ እንደ ዮናስ በአሰነባሪ ሆድ ሄዶ እግዚአብሔር በነነዌ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን መአት እንዲነግር በታዘዘው መሰረት ሳይወድ በግዱ እንዲጠፉ እየፈለገ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቁና በማወጁ ከጥፋት መንገዳቸው ተመልሰው ሊድኑ ችለዋል። እናንተ ግን በፈቃደኝነት የእግዚአብሔርን ስራ ብትሰሩም የሚሰማችሁ ስላላገኛችሁ እኩያን የዲያብሎስ ልጆች ከጥፋት ላለመዳን ቆርጠው "የዳላስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጥፋት ወይም ሞት የሚል መፈክር አንግበው ከሚካኤል ጋር በብርቱ እየተፈታተኑ ነው። አዲሱ ካህን እንደሚሉት ሚካኤል ታጋሽ መልአክ መሆን አለበት እስካሁን ዝም ብሎ ታግሷል። እንደ ዮናስ ትእዛዙ ከላይ ከመጣለት ጋውት የለ ስኳር፤ ደም ብዛት የለ ልብ ምታት፤ ካህን የለ ምእመን ሁሉን በአንድ ሌሊት አጥቦት ነው ቁጭ የሚለው። ንገረው ምከረው እሚቢ ካለህ መከራ ይምከረው” እንደተባለው መከራችሁ ዘከራችሁ እምቢኝ አሻፈረኝ ሲሉ ምን ታደርጋላችሁ። እግዚአብሔር በመራችሁ ግዳጃችሁን እየተወጣችሁ ሀቁን ለህዝቡ በመግለጣችሁ ስለሆነ አውቆ የተኛው ሁሉ መኝታው ሲቆረቁረው እየተገላበጠ ተው ማነህ? የተኛ ሰው አለ ትቀሰቅሳለህ። እንዴት? ለመሆኑ ይኸን ያህል አመት የት ሄጄ ኖርዋል ቤተክርስቲያኔን ሲዘርፉ?
እነ ኢዩኤል የቁማር መደብር ከፍተው ህዝቡን ሲዘርፉና ከሚስቱ ሲያፋቱ የኖሩና ለብልግናቸው ገደብ የሌላቸው ለመሆኑ ምስክር የሚያስፈልግ አይመሰለንም የምናውቀው እናውቃለን። የመደብሯን ሽንት ቤት እየታነቁ በግዳጅ የጎበኟት ብዙዎቹ ሊመሰክሩ የሚችሉት መሆኑን ዘንግተው በወዳጃቸው በአቶ ጤፉ ላይ ወረቀት አባዝተው ሲበትኑ ያየ ሁሉ ጉድ ነው! ይኸን ሰው ሲሞት መሬት ትቀበለው ይሆን በማለት አዝነው ተገርመዋል። የሚያስደንቅ ነገር ያለ አይመስለንም እኒህ ሁሉ ተራ ሌቦች አንቱ ስንላቸው በአንቀልባ አዝለን እሹሩሩ እያልን ዝረፉን ግድየለም ሚካኤል እንደየስራችሁ ይክፍላችኋል እያልን ዝም ባንል ዛሬ እነሱንም እዚህ ሁሉ ወንጀል ውስጥ ባላስገባን ሚካኤልንም ባላዘረፍን ነበር።
ይቀጥላል

Anonymous said...

ባለጌን አንዴ ስደበው ዘላለም እንደተሰደበ ይኖራልና፤
ይላሉ ያገራችን አዋቂዎች። ይሄውላችሁ ባለፈው ጊዜ በጎረቤታችን ላይ የተንኮል ተግባር ከመፈጻማችን በፊት በሚል መልእክት የደረስኩትን ዘገባ ውስጥ ውስጡን የነካው የመረዋ ደራሲ የሱም ተከታዮች እንዲያነቡለት መልእክቱን በሱ ብሎግ ማውጣቱ በጣም ደስ ያሰኛል።
በኔ አስተያየት መልእክቱ የገባው ይመስለኛል፤ መልእክቱን ከተቀበለ ጓደኞቹን ሁሉ ሰብስቦ ቤተክርስቲያን፤- መምህራችን እንዳለው የሁላችንም እናት ናት፤ እናት ደግሞ አትከሰስም
አትወቀስም። ይህ ነው የክርስቲያን ሁሉ እምነት ብሎ ክሱን ሁሉ አስቁሞ ምእመኑን ይቅርታ ጠይቆ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። የዚህ ግለ ሰብና የጓደኞቹ ሃይማኖት ግን በክርስትና ስም ገብተው ቤተክርስቲያን መዝረፍ፤ ሲነቃባቸው ደግሞ ድሮ የዘረፍነው በቃን ሳይሉ ዘረፋውን ለመቀጠል ወደ ክስ ሄደው
ቢፈርድላቸው እንደገና ቤተክርስቲያኑን ለማራቆትና ድምጥማጡን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ናቸው።
የክርስትና ትምህርት የተቀበለ ክርስቲያን ከሆነ! ለምን ብሎ ነው የራሱን ሃጢአት ደብቆ የሰው ሃጢአት የሚያራግበው
“በወንድምህም አይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፤በአይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?-----“
በማቴወስ ወንጌል ምእራፍ 7 ቁጥር 3 ጌታችን እንዳስተማረን የሰውን ሃጢአት አባዝቶ በየታክሲያችን ውስጥ ማደል ክርስቲያናዊ ስራ ነው ብለህ የምታምን ከሆነ ገና የእግዚአብሄር ቁጣ አንተንም ይጠብቅሃል ማለት ነው።
አሁንም ወዳጀ በእግዚአብሄር እጅ የተያዝክ በሽተኛ ስለሆንክ ሁሉንም መጥፎ ተግባር ወደ ኋላህ አድርግና ፊትህን ወደ ፈጣሪ መልስ፤ ብዙ ጊዜ ስለሌለህም ባስቸኳይ ወደ ቤተክርስቲያኑ
መጥተህ አምላኬ ፈጣሬየ በድየሃለሁና ይቅር በለኝ ብትል ለነፍስህም ለስጋህም ትሆናለህ፤ ክርስቲያን ማለት በአፍ በክርስቶስ አምናለሁ ማለት ብቻ አይደለም በትምህርቱም በትእዛዙም
መተዳደር ጭምር ነውና፡ ልቦናህን ክፍቶ ክጥፋት መንገድህ እንዲመልስህ እኛም አብረን ካንተ ጋር ሆነን እንጸልያለን፤
ብርታቱን አምላካቸን ይለግሰን፤
አሜን።

Anonymous said...

በተደጋጋሚ የምናነባቸው መጣጥፎች የሚያስገርም ታሪክ ያላቸውን ውስጡን ሳናውቅ የኮሚኒቲና የቤተክርስቲያን መሪ ብለን ስንኮራባቸው የኖርነውን በአሁኑ ጊዜ ግን ስማቸውን ለመጥራት የሚቀፈንን ተራ ሌቦች ታሪካቸው በማስረጃ እየተደገፈ እየወጣ እነርሱ ግን የሰው አይን ቀቅለው የበሉ ስለሆኑ ምንም ሳይሰማቸውና ቅር ሳይላቸው እንደውም የጥጋባቸው ብዛት የሚካኤል ነጻ አውጪ ኮሚቲ አቋቁመናልና ተከተሉን በማለት እንደበግ ሲነዷቸው የኖሩትን ጀሌዎች ይዘው በሚካኤል ላይ ለመዝመት ከበፊቱ ሰፋ ያለ መቃብር በመቆፈር ላይ ይገኛሉ። ለሀጥአን የመጣ ለጻቃድን ይተርፋል እንደሚባለው ወንድሞች፤ እህቶች፤ አባቶች፤ እናቶች የሚካኤልን ሃብት ንብረት ያልዘረፍን ሁሉ እግዚኦ እንበል! ለነዚህ የአርዮስ ልጆች የሚመጣው መአት ለእኛም እንዳይተርፈን።
እግዚአብሔር አለ ምክንያት እንዚህን ተኩላዎች አላንቀዠቀዣቸውም ከእሳቱ ወደረመጡ ከዛም የተረፉ ቢኖሩ ወደእቶነ እሳት ሊጥላቸው እየነዳቸው ስለሆነ አለሀጢአታችን ከወላፈኑ እንዳይደርሰን እግዚኦ እንበል። ምን ጉድ ነው እናንተ ሚካኤል ታግሶ የኖረው? ምንስ ያህል እግዚአብሔር ቢጣላን ነው ፊቱንስ ከኛ ቢያዞር ነው ሀያ አመት ሙሉ እንዲህ ያሉ እኩያን ቤቱን ሲመዘብሩት፤ ሲዳሩበት፤ ሲነግዱበት ዝም ያላቸው? ኧረ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ እግዚአብሔር ቅርባችሁ ነውና እግዚኦ በሉ! ቤተክርስቲያኑን ከተኩላዎች ነጻ እንዲያወጣ። የአሜሪካን ህግ ምን ያህል ለወንጀለኞች የቆመ መሆኑን የምትረዱት ወንጀለኞች ቤተክርስቲያንን የሚያክል የሃይማኖት ድርጅት ከሰው ሲሞግቱ ለቃቅሞ እስር ቤት በማስገባት ፋንታ መብት ሰጥቶ እያሟገተ ይገኛል። ፍርዱ ከላይ ሲመጣ የሚገቡት የት ይሆን?