የተከበራችሁ ውድ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁልን? በእርሱ ፈቃድ ፣ ሁሉን አስተካክሎና ደግሞ በዚች ጦማር ደግመን ለመገናኘት ስለበቃን ለፈጠረን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።
ከምንግዜውም በላይ የበለጠ ተሳትፎ በገጻችን ላደረጋችሁትና ለሰጣችሁን አስተያየት ምስጋናችን የላቀ ነው። እንድናስተላልፍላችሁ የሰጣችሁን ምክር፣ ጥቅስ ፣ ማበረታቻዎች፣ ድጋፎች በሙሉ ለሚመለከተው ስናስተላልፍ፤ በሌላ በኩል ሀይማኖቱ የሚያዘው ስርዐት እንዲጠበቅ አመራሩ ከአባቶች ጋር በመመካከር የወሰዱትንም እርምጃ በናንተ በኩል ከፍተኛ ድጋፍና ተቀባይነት በማግኘቱ ይህንኑ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲደርስ የበኩላችንን እያደረግን እንገኛለን።
በሌላ በኩል ሰሞኑን ገጻችን ካወጣው መጣጥፍና ገጠመኝ ሁላችንም የግላችንን ግንዛቤ ወስደናል። በትውልድ ሀገራችንም ከተለያዩ ሀይማኖት ተወክለው በሀገሪቱ ውስጥ ይቅርታን ለማምጣትና ወደፊት ለመጓዝ ብሎም የመዘከሪያ ዕለት በመሰየም “የይሁንታ“ እየተዘጋጁ በሚገኙበት ተግባር ሁላችንም ከጎናቸው መቆም ይጠበቅብናል። የሀይማኖት አባቶችም ከዚህ መድረክ ተለምዶ ወደፊትም ጣልቃ ገብነታቸው ይቀጥል እንላለን። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደብራችሁ ሰሞኑን የሀይማኖት አባቶች ያሳለፉትን ተገቢ አስተያየት በመቀበል አስተዳደሩ የወሰደው ውሳኔ አማራጭ የሌለውና ተገቢ ነው በማለት አምዳችን በሙሉ ልብ ተቀብሎታል። አባል ምዕመናንም ከምትልኩልንና ከጎናችሁ ካሉት ምንጮቻችን ከመረዳታችንም በላይ ይህ ውሳኔ የአባቶችንም ይሁንታ የጨመረ ነው። እኛ በምዕራቡ ዐለም ያለን ያመለካከታችንን አድማስ በማስፋት በትውልድ ሀገራችን ከሚተገበረው ተመክሮ መውሰድና የተሻለ አቀራረብ ማድረግ ይገባናል።
በሌላ በኩል ሰንበቴ እየተባለ የሚታወቀውና ከኛ ገጽ ቀደምተኛ የነበረው ጠፍቶ ከከረመበት የሚላመጥ ፍሬ የጣፈው አለውና ጎራ ብላችሁ እንድታነቡት እየጋበዝን የነርሱ ጥሁፎቻቸው አይራቁን ነው የምንለው። እንደዚሁም የናንተው ኮሚኒቲ ልሳን የሆነው የዲኤፍ ደብልዮ ብሎግ አዲስ ያወጡትም አላቸውና አንብቡላቸው።
አሁን ያሉት የደብሩ አመራር አባላት በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስመዘገቡ ያሉት ተግባራት መመስገን ብቻ ሳይሆን መኩሪያዎቻችሁ ናቸው።በተለያየ ደረጃና ስፍራ ላይ በተለያየ ጥበብ ተደራጅተው የመጡትን አጽራረ ቤተክርስትያን ድባቅ እያስገባችሁ የምትገኙና የነርሱን አካሄድ የተረዳችሁ ሁሉ ህብረታችሁንና አንድነታችሁን በማጠናከር የተጀመረው የደብራችሁ የለውጥ እድገትና አገልግሎት ላፍታ እንኳን እንዳይስተጓጎል ከዚሁ በመንጠንቀቅና በማስተውስል የምትመርጧቸውን የአመራር አባላት በንጹህ ልቦና እንድታደርጉት በጸሎት መትጋት አለባችሁ። ይህንን ለማለት ያበቃን በተለይ በ2009 ያገለገለው የአመራር ቡድን ከ1 እስከ 10 ደረጃ ስጡት ብንባልና 10 ከፍተኛ ውጤት ቢሆን የምንሰጠው 3 ነው። አለ ወይንም ሰራ የምንለው የለንምና። ተከፋፍሎ ያከፋፈለ ፣ የስድብና የጥላቻ ፣ የጎሰኝነትና የትምክህተኝነት ብቻ ሳይሆን የመተዳደሪያው ደንብ ይከበር በሚሉና የተሻለ የትምህርት ዕውቀት ባላቸው ጥቂት አባሎችና ትምህርቱም ሆነ እውቀታቸው የማይመጣጠንና ሀቅን መዋጥ የተሳናቸው ወገን መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነበር።
በ2010 የተመረጡትና እያገለገሉ ያሉት አመራሮች በውስጣቸው ካቀፏቸው የቀድሞ አባላት የተረፉት ቢኖሩ የተመረጡበትን ሀላፊነት እንደዚሁም በመቅደሱ ቆመው የገቡትን ቃል አፍርሰው ተንጠባጠቡ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት የሌላቸውና ያንኑ ጸጸት ለመሸፈን ለአጽራረ ቤተክርስትያን መሳሪያ በመሆናቸው ብናዝንም ከድርጊታቸው ተቆጥበው ቅዱስ ሚካኤልን አታስቀይሙ እንላለን። አሁን ያሉትም አመራሮች በአሁኑ ሰአት አንድ አይነት አቋም ይዘው በአጭር ጊዜ እያስመዘገቡ ያሉት ውጤት ከፍተኛ በመሆኑ፤ አዲስ የምትመርጧቸው ከነዚሁ ከሚቀሩት አመራሮች ጋር በዕውቀት ፣ በትምህርትና በእምነት የሚመስሉ ሲሆን የለጠቁ ቢሆን የተጀመረው ስራ ሁሉ ሳይስተጓጎል ግቡን ይመታል። የሚቀጥለውም 2011 አመት በአመራሩ መካከል በመከባበርና በመተሳሰብ መልካም ፍሬን ለማየት እንበቃለን።
ጥቂት አጽራረ ቤተክርስትያን የሆኑ ካሁኑ የነሱን ተቀጣሪዎች ለማስመረጥ እየተሯሯጡ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁሟሉ። እኛም እነዚህ ግለሰቦች ማንነት በሚገባ መረጃዎቻችንን የሰበሰብን ስለሆነ ፣ ጥቆማው እንደተጠናቀቀ ለናንተ የምንገልጥ መሆኑን ከዚሁ እንገልጣለን። ከብዙ አቅጣጫ በተለያየ ጥበብና ስልት አልፎ በአለም ፍርድ ቤት ሳይቀር ደብራችሁን ለመቀማት ካልሆነም ለማዘጋት ያልተፈነቀለ ድንጋይ ያልተወረወረ ጦር ፣ ያልተቆፈረ ጉርጓድ ፣ ያልተዋቀረ ኮሚቴ፣ ያልተደጎመ ንዋይ፣ ያልተደረገ ቅስቀሳና ዘመቻ የለም። ቅዱስ ሚካኤል ግን ከውስጥም ሆነ ከውጪ የተነሱትን እንሒን አጽራረ ቤተክርስትያን በየወቅቱ እያጸዳቸው እንዲሁም ክብሩንና ሀይሉን እያስመሰከረባቸው ይገኛልና ከብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።
እናንተም መራጮች የደብራችሁ ህልውናን ለመጠበቅና የተጀመረው መሻሻል ከግቡ እንዲደርስ አጥብቃችሁ መጸለይ ይገባችኃል። ከላይ እንዳስቀመጥነው ብቁ ያላችኃቸውን ግለሰቦች ስትጠቁሙም ሆነ ስትመርጡ ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ መሆን ይገባል። አንዳንድ በቤተሰብ፣ በጓደኝነት፣ በማህበር፣ በዝምድና፣ በጋብቻ፣በሰፈር፣ በሀገር ፣ በዘር፣ በጎሳና በመሳሰሉት ተመስጦ ወይንም ተገፍቶ የሚደረግ ድምጽ ፀፀት ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪም ያጋጫል። በተለይም እልህ ቂም በቀል ይዞ ምርጫ ማድረግ ከመንፈሳዊ መንገድ ፈጽሞ የራቀ ስለሆነ አስቀድሞ ንስሀ ወስዶ በንጹህ ልቦና በሱ ተመርቶ መከወን የክርስትና ግዴታ ነው። ይህንን ለመተግበር እግዚሀብሔር ያብቃችሁ። አሜን።
2 comments:
ጋሻ ኢንሹራንስ ማናጀር ተፌ አሰፋ የቱ ናቸው ወይስ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋ ስማቸውን ቀይረው በተፌ ተመዝግበው ነው? አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር ምንሰርተው ይሆን ለዳላስ ኢትዮጵያውያን? እረ እነዚህ ምርጫው ውስጥ እንዳይጠልቁ አደራ። የሚካኤል ሂሮ ሆነው ሌላ መቶሽህ እንዳይካፈሉ። አቶ በትሩ ሰዎችን ኢንሹራንስ ኤጀንትነት ያሰማሩና ከዚህ በታች ሴፍኮን እንደ ተጠቀሙበት እሳቸው ተሸላሚ የመለመሉት እንደ ሚስተር ተፌ አሸላሚና ገንዘቡን ተቃራጭ ሚስተር ተፌም ይሆናሉ። አይ በትሩ ቴኒሲ አክስረውን ቴክሳስን እያሙዋጠጡ ነው።
ከመንፍስ
ብዙነህ።
Releases & ArchivesPress KitExecutive ProfilesConsumer TipsIndustry LinksMedia Contacts
Safeco Media Relations
Paul Hollie, 206-473-5745
pauhol@safeco.com
Safeco Announces 34 Foundation Grants and 30 Community Hero Awards Totaling Nearly $2.3 Million Dollars
Speaking about the Community Hero Awards, Anderson said, “Safeco knows every neighborhood has heroes and saw this opportunity to partner with our agents to identify individuals special to them and their home towns. Safeco’s Community Hero Awards are intended to recognize and celebrate those individuals who make a positive difference in their community and inspire others to do the same.”
SEATTLE-(Feb. 14, 2008) - Safeco (NYSE: SAF) and the Safeco Insurance Foundation today jointly announced the recipients of two separate giving programs: the Safeco Insurance Foundation Community Grants and Safeco Insurance Community Hero Awards.
Betru Gebregziabher of Dallas, Texas for his work with Mutual Assistance Association for the Ethiopian Community, nominated by Tefe Assefa, Manger Gasha Insurance Agency.
Thirty-five non-profit organizations in six locations (Atlanta, Dallas, Indianapolis, Seattle/Puget Sound, Southern California and Spokane) received Community Grants from the Safeco Insurance Foundation, totaling $1,791,000.
Awarded by Safeco Insurance through an agent driven program, the company also announced 30 Community Hero Awards. In this signature program, Safeco agents nominated individuals from across the country who demonstrate a tireless commitment to strengthening and enriching their communities. Each “hero” was presented with a $15,000 check for the non-profit organization at which they work or volunteer. In total, this program contributed $500,000 to various organizations nationwide.
በጎረቤታችን ላይ የተንኮል ተግባር ከመፈጸማችን በፊት በአምላክ ፊት ምን እንደሚጠብቀን አስቀድመን ብናውቅ ሁላችንም የመጀመሪያውን ድንጋይ ለመወርወር ባልቃጣን ነበር። በዚህ በያዝነው ሳምንት ውስጥ ፈጣሪያችን አምላካችን ለ ዳላስ አካባቢ የክርስቶስ አማኞችና የቅዱስ ሚካኤል ምእመን ብዙ ተአምር አሳይቶናል። እንድንጠነቀቅም ፊታችንንም ወደ ፈጣሪያችን እንድንመልስ ሊያደርገን ሁለት ተአምር አሳይቶናል። አንደኛው የቤተክርስቲያናችን አባል የሆነው ጸሃፊያችን የልቡን አይቶ ሃጢአት ውስጥ እንዳይገባና እንዳይረክስ መልአኩን በ ፖሊስ መልክ ልኮ ከ መጥፎ ተግባር እንዲድን አድርጎታል።
ባኳያውም የዚህን ግለሰብ ኅጢአት ከ ፖሊስ ሰነድ ውስጥ አውጥቶ በየ ታክሲያችን ላይ ሲበትንና ያገሩን ልጅ ስም ሲያጠፋ የነበረው ( ስሙን በደረሰበት አደጋ ምክንያት ለመጥቀስ በማንፈልገው ግለሰብ ) ላይ በደረሰው የአባት ሃጢአት ለልጅ በተላለፈ አደጋ ልጁን ያጣው ሰው የቅዱስ ሚካኤልን ደጀ ሰላም መጥናኛ እንዲሆን ያውም በትምህርት ቀን ያስፈቀደለት ማን ይመስላችኋል!
መድረኩን ማስፈቀድ ብቻ ሳይሆን ቀሳውስቱና ዲያቆናት እንዲተባበሩ ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረገው ሰው ነው። አሱም ፤በ እኔ ላይ የራሱን ጉድ ደብቆ ልጆቹን በትኖ ብህግ ያገባት ሚስቱን የልጆቹን እናት
ጥሎ ወደ ሴተኛ አዳሪ ቤት የገባ ሰው የኔን ሃጢአት እያጋነነ ለጠላት ስለሰጠብኝ ብሎ አልተቀየመውም። ይሄን ያልነው እኛ ጉዱን የምናውቅ ነን። ይልቅስ በማያውቀው ሓጢአት ዉስጥ ገብቶ ልጁን ማጣቱ አሳዝኖት እንደማንኛችንም ሲያለቅስ አምሽቷል። ታዲያ እኛ እን ማን ሆነን ነው የቅዱስ ሚካኤልን ሥራ ነገ በኛ ላይ የሚደርሰውን አዉቀን የሰው ስም ለማጥፋትና በሃሰት ሰው ለመክሰስ እምንመኘው።
ለዚህ ነው ነገ የሚደርስብንን ብናውቅ ዛሬ እማጥ ውስጥ አንገባም ነበር ያልኩት። በሰው ላይ ተንኮል ለመስራት አንሯሯጥ ሰው ባያውቅብን እግዚአቤሔር ያውቀዋልና፤ ከሱ የሚሸሸግ ነገር እንደሌለ እንወቅ።
አሜን;
Post a Comment