Sunday, December 12, 2010

ቅጥረኝነት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እኛ የምንለው ምንም የለንም ነገርን ሁሉ የሚያስተካክል እግዚሀብሔር የተናቁትን የሚያስከብር፣ የወደቁትን የሚያነሳ፣የጠገበ የሚያስተነፍስ፣የተራበ የሚያበላ፣ወዘተ……ዛሬም ፈቃዱ ሆኖ መልሶ በዚች ገጽ ዳግመኛ በመገናኘታችን አሁንም ሆነ ወደፊት ክብርና ምስጋና ለፈጣሪያችን ይሁን። አሜን።

የዛሬውን ጥሁፋችን መነሻ ያደረገው የDFW ETHIOPIAN COMMUNITY  http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ ገጽ በሆነው ላይ ብዙ መረጃዎች ተመልክተናል። በግል ጥቅም የታወሩና የሕብረተሰቡ መዥገር እነማን እንደሆኑ በሚገባ ተቀምጦ ይገኛልእንግዲህ ጨው ላራስህ ስትል ጣፍጥ ነውና ዳላሶች እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦችን ከመካከላችሁ ማጽዳት ቅድሚያ የምትሰጡትና የሚያስፈልገውን እርምጃ መከወን ግዴታችሁ ነው
እንዚህም ግለሰቦች ምን ያህል ለትግሬ ነጻ አውጪ ለሚመራው ሁሉ ቅጥረኝነት ከዚህ በላይ ማስረጃዎች ለምትሹ ከተኛችሁበት መንቃት ያቃታችሁ ብቻ ናችሁ። እኛም በእጃችን በየጊዜው የሚገቡትን መረጃዎች ወደሚመለከታችቸው አካላት ከማካፈል ወደኃላ ባንልም፣ እንደአስፈላጊነቱ ለናንተም እንዲደርስ በገጻችን የምንለጥፍ መሆናችንን ከዚሁ እንጠቁማለን።

ሌላው በከተማችሁ ተከብሮ የጋሼና የአቶ ስም ተሰጥቶት በቸርነቱም ዝና የሚዳረግ በኑሮውም የተባረከ መስሎ ሲኖር አመታትን ያስቆጠረ ግለሰብ ከበስተዋላ ምን እንዳደናቀፈው ባናውቅም ወይም በውስጡ አብሮት የኖረ አግርሽቶበት ይሁን አሊያም ከቀን በኃላ ያገኘው መንፈስ በስህተት ጎዳና እየነዳው ይገኛል። በገዛ እራሱም ኃይል ተመጻድቆ ከታጋሹ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ጋር እየተላጋ ይገኛል። ህሊናውን በማሳሳቱም ግንዛቤውንና ማስታወሉንም አጥቷል።

በምሳሌ ከሚጠቀሱት የናይጀሪያና የፓኪስታን ሰዎች ጸባይ አንዱ ለንዋይ ሲሉ የወለዷዋቸውን ልጆች ሳይቀር የሚለውጡ እንደሚባለው ሁሉ አቻ የሚቆጠር የሆነ፤ እንደሚባለው የቀድሞ ወዳጁን ልጅ ባደራ እንዲያስተምር ወስዶ ያገባ፣ ቆይቶም በሚስቱ ላይ ጥቁር አሜሪካዊት የሆነች ደርቦ በመያዙ በዚያም ቢፋታ ሀብት እንዳያክፍል ሚስቱን በቄስ ይዞና ተማልዶ የቆረበ ፣ ለአሜሪካዊቷም ወዳጁ በገንዘብ የሸነገለ፣ ከዚሁ ትዳር ያፈራት ልጁ መጸነሷ ሲነገረው እንዴት ያውም ከጥቁር ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ የግድ ማስወረድና ምናምን ሲል በገዛ ልጁ አንደበት አንተስ በእናቴ ላይ ጥቁር ደርበህ አልነበርክምን? ጥቁርም ሰው ነው የጸነስኩትም ሰው ነውና አይሆንም በማለቷ ሀቅን በግድ ያስዋጠችው፣ ከሌላ የሚወልዳትን ትልቋን ልጁንም ያልተንከባከበና የመኖሪያ ፈቃድ እክል ያላትንና መጥቀስ በማንሻው የኑሮ ህይወት የምትገኘውን እንደመደገፍ፣አዲስ አበባ ላይ ያለመው ፕሮጄክቱ ይሳካለት ዘንድ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤልን ደብር በአባ ጳውሎስ ስር ለማድረግ ለዚሁም ውለታው የሚያስፈልገውን ትብብር ከትግሬ ነጻ አውጪ ከሚመራው መንግስት ለማግኘት ደብራችሁን ለሚከሱት ሁሉ የግንባር ቀደም ተባባሪና አስተባባሪ የሆነ፣ እነዚሁ ከሳሾች የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች በትግሬ ነጻ አውጪ ከሚመሩትና በውጪ አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ተወላጆች የአንድነት መድረኮች ሁሉ ያሰማሯቸው ለጥቅም ያደሩ ቅጥረኞች ለጠሩት ስብሰባ መተዳደሪያው የሆነውን የዳንስ ቤት ያመቻቸ አንዱ ጠላታችሁ ነው።

ይህ ዳንስ ቤት ለትግሬ ነጻ አውጪ አጀንዳ መማከሪያ በመሆን ለዳላስና አካባቢው የመረዳጃ ማህበር ስም የህገወጥ ስብስብ ማድረጊያና ለህብረተሰቡ አደጋኛ ዱለታ መድረክ በመሆን ማገልገል ከጀመረ አመታት እያስቆጠረ ነው። አሁን ደግሞ ሀይማኖት የሌላቸው ስለ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በማለት በየዳንኪራው ቤት መገናኘትና መዶለት መልሱን ለአንባቢያን እንተወዋለን
ይልቁንስ ባለዳንኪራው ቤት ባለቤት ቤቱን ወንጀል ለሰሩ ወይንም ደብር ለሚበጠብጡ ከማድረግ ይልቅ ከፈተኛ እርዳታን ለሚሹ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ የሚያገኙበት መድረክ ቢያደርገው

ሌላው ይኸው ባለዳንኪራው ቤት ግለሰብ ስሙንም ለመጥራት በድርጊቱ ምክንያት ስለተፀየፍነው ብናልፈውም፤ በሌሎች እንዳደረገው እርሱም በሌላ በኩል እየከፈለው ያለውን ልናካፍላችሁ እንወዳለን። በከተማችሁ በመልቲና በቀጣፊነቱ የሚታወቀው ሙላው aka ቀዳዳው የተባለውን ያለእኩያው ጓደኛው አድርጎ ጆሮውን ስለሚያቀላው፣ የአዲስ አበባውን ችግሩን በተስፋ አስደግፎ በsouth Dallas አዲስ በጀመረው ፕሮጀክት ማን አራጅና ማን ታራጅ እንደሚሆን ለማወቅ የጓጓው የዳላሱ ምንጫችን አካፍሎናል። እንደዚሁም ቀዳዳው የግል ጠበቃና ከዳኝነት በስነምግባር የተወገደውን በማምጣት ደብሩን ለሚታናኮሉ ተቀጥሮ ከሚያገኘው የጥብቅና ገቢ ሁሉ ኮሚሽን እንደሚከፈለው ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል። ባለዳንኪራ ቤቱም ጓደኛ ያደረገው ቀዳዳው በእጅ አዙር በገንዘብ እየጠበጠበው ይገኛል።

ከዚህ በፊት እኛም ሆንን ሌሎች በኢትዮጵያን ስም በዳላስና ፎርትዎርዝ አካባቢ የተቋቋመው መረዳጃ ማህበር በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች እጅ መውደቁን ስንገልጽ ቆይተናል። እድር የተባለውም ዛሬ መስራች የነበሩት አባላቱ ሳይቀር እውስጡ ያለውን ምዝበራና አጸያፊ ድርጊቶችን በማየት ላለማደስ በመወሰናቸው የአባላቱ ቁጥር እየመነመነ ይገኛል። ዕድሜውም በወራት ውስጥ እንደሚቆጠር ያገኘነው መረጃ ሲጠቁም ፣ በየሳምንቱ በእድሩ ስም የሚደረገው የስልክ ጥሪ እንደሰለቻቸው የሚናገሩ እንዳሉ ተነግሮናል። ከዚሁ ሳንርቅ የሬድዮ አገልግሎትም በዕሁድ አቅርቦቱ ካስታወቀው ውስጥ የደብሩ በጥባጮችን ጥሪ በዳንኪራ ቤትና የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞችን የበአል ጥሪን ያሰሙት የነሱ ቅጥረኛ ስለሆነ የነሱን ስራና የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያሳድድ በመሆኑ ፤ የሚስቱ ስራ ማጣትና የሱዋን 401ኬ የተባለውን የሂሳብ ቁጥራን እንዴት እንደሚበላ እንጂ ለህብረተሰቡ የሚረባ አንድም የለው ሲሉ ያዳመጡት ምንጮቻችን አካፍለውናል።

እኛም ጋሼ ተኮላ aka ተኩላውን ካስደሰተ ብለን የሚቀጥለውን ለናንተም ጭምር እንጋብዛለንና ካላዩት ይመልከቱት።
 http://www.youtube.com/watch?v=TWVSisi3N20&feature=player_embedded

እርሶስ ምን ይላሉ?

1 comment:

Anonymous said...

አላህ ይስጣችሁ አቦ ቪዲዮ ፈረቃ አስገራሚን በማቅረባችሁ። በቅርብ ጊዜ አገር ቢት ሄጄ ነው የተመለስኩት ከባለቤቴና ከልጆቼ ጋር። የአቶ መለስ ዜናዊ መንግስት እስኪሞት ድረስ ግን እየገደልዋት ያለችው አገሬና ሕዝብ መሃል ላለመገኘት ግዴታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የምችለውን ግን ዘመዶቼንና ጎረቤቶች መርዳት ግዴታ ነው። ልክ ፈረቃ በሚለው ቪዲዮ የተቀመጠው በተለይ ድሬደዋና ሃረር ንዋሪዎች በየቀኑ የሚኖሩት ችግር በመሆኑ ባትሄዱም በስልክ ዘመዶቻችሁ የነገሩዋችሁ እንዳሉ አምናለሁ። ቤተሰቤና እኔ ውሃና መብራት እየጠፋ ስንሰቃይ የከረምንበትን ሃረር ከተማ በቪዲዮው ሳየው በጣም ደስ አለኝ የህዝቡን ችግር በዚህ መልኩ ለሰሚና ለተመልካች መቅረቡ። በፓኬጅ ጉብኝት ወደ ሰሜን ሄደን ነበር። አንዱ ከሚጎበኘው ቦታ ትርግራይ ነው። የምን የውኋ በየቦታው እንደልብ ነው። ችግር የሚባል የምንም የለም በዛ ደስ ብሎናል። መቀሌ ተራራው ሳይቀር በገንዘብ ብዛት በተደረገው ጥረት አረንጉዋዴ ሆንዋል። መንገዱ የመቀሌ በሰው እጅ የተነጠፈ ድንጋይ ነው። ልክ ምንጣፍ ይመስላል የድንጋዩ ቅርጽና አነጣጠፍ። የህንጻዎች ማማርና የዩንቨርስቲው የኮሌጁ የሆቴሎች ብዛትና ቁንጅና ለመግለጽ ያስቸግራል። የሁዋ ችግር አይደለም የከብቱ ብዛት ሃረርጌ አስንቅዋል። እነዚህ የአቶ መለስ ደጋፊ ሁሉ ትግሬም ይሁን አማራ ወይም እንደኔ ሃረሪ ለምን ለሁሉም ከተማ ውሃ እንዲደርስ አይደረገም ፎቅና መንገድ ከመገጥገት በትግራይ ውስጥ ብቻ? እባካችሁ የአቶ መለሰ ደጋፊዎች ባለድሪምስ ክልብ ባለቤት ጭምር በቃው ትግራይ እሲ ውሃ ለሌለው ከተማና ህዝብ ገንዘቡን አካፍሉ በሉልን አማልዱን።
አላህ የሃረሪን ህዝብ ውሃ ያምጣለት።
አብደላ ሙሃመድ
እርቪንግ ቴክሳስ