ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
እግዚኦ በመሀሪነትህ ይቅር ብለህ አድነን
የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን ከርማችኃል? በፈጣሪ ጸጋ መልሰን ስለተገናኘን ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን። ዛሬ ጠዋት መሪያችን "Obama signs bill ending 'don't ask, don't tell' ሕግ እንዲሆን። የሚያመጣው ጥቅምና ጉዳት ወደፊት የሚገመገም ቢሆንም ለሠራዊታችን አባሎች የስነ ልቦና ተጽዕኖው ይኖረው ይሆን? እኛ በአሁኑ ሰዐት በሠራዊቱ ውስጥ አገልግሎት ላይ ባንገኝም እምነታችንን በተመለከተ የምንወደው ሕግ አይደለም።
ሰሞኑን በዳላስ ከተማ ነዋሪ በሆኑት ወገኖቻችን ውስጥ በሕይወት ለተለዩት ወገኖች ቤተሰቦች ፈጣሪ ሀዘነልቦናቸውን ያሳሳልን፤ የተለዩንንም በመንግሥቱ ይሰብስብልን፤ በትላንትናው ዕለት ለተለዩንም እናት እንዲሁ።
ከዳላስ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ እንደደረሰን በትላንት ዕለት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከሳሾችም ሆነ ተወካዮቻቸው ባለመገኘታቸው ዳኛው ቅሬታቸውን መግለጻቸውን ሲገልጽልን፤ እኛም በሰሞኑ ሂደትና በካህኑ ጥያቄ ክሱን ለመተው አስበው እንደሆን ብንለው እየሳቀ ቀዳዳው ከሰልስቱ ቀድሞ ሕይወቱ ሳታልፍ ጠበቃው እንዲወክልና ከካሳ ምን ያህል የመድህን ኮሚሽኑን እንደሚበላ እያሰላ እንጂ ብሎ ከመጨረሱ በፊት እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ በማለት ንግግሩን አቋረጥነው። በእርግጥ የትምህርት ቤቱም ሆነ የመስኩ የመድህን ዋስትና ያለክርክርና ያለ ነገረ ፈጅ የሚገባውን ክፍያ የሚከፍል ሲሆን፣ ነገረ ፈጅ ከገባ ሲሶውን በነጻ እንደማካፈል ስለሆነ ይህን በመጠቆም ለባለጉዳዮቹ እንተወዋለን። ከዚሁ ጋር በማያያዝ ደብሩ በሩን ከፍቶ ሙሉ አገልግሎት የሰጠው ያለምንም ክፍያ ሲያገለግለው ላደገው ወጣት እንጂ አንዳቸውም የሟቹ ወጣት ወላጆች የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባልነታቸውን ያልጠበቁ (የሌሉ) ከአጽራረ ቤተክርስትያን ጎራ የተሰለፉ ናቸው። የደብሩ አመራር ላሳየው ትብብር አድናቆታችንና ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን ቤተሰቡም ከዚሁ ተመክሮ ይወስዳል የሚል ግምት አለን።
በሌላ በኩል በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች እየተመራ የሚገኘው የዳላስ አካባቢ የመረዳጃ ማህበር (ኮሚኒቲ) ያለ አንዳች የቦርድ ስብስባ በጥቂት እባጭ አመራር አባላት የጎደፈና የዘቀጠ ምግባራቸውን አጋጣሚ አግኝተን እናድስ በማለት ይሁን ወይንም ወደ ነፈሰበት መዝመም አቋም አሊያም በሟችና በኮሚኒቲው እንደመቀለድና የነዋሪውንም የማስተዋል ችሎታን እንደማኮሰስ የሚደፈር ድርጊታቸውን ዛሬም ባደባባይ እየፈጸሙት ይገኛል። ይህንን ለማለት ያበቃን ለደንብና ስርዐት ሳይገዙ ፣ ሳይመክሩና ሳያማክሩ ፣ የነዋሪውን ወገኖቻችንን አሉታ ሳይጨምሩ በአንባ ገነንነትና በስሜት ተገፋፍቶ የወገንን መብት ገፎ በወገን ስም ለመነገድ የሚደረግ ሩጫ ፈጽሞ አግባብነት የሌለው ነው።
እኛ መጪው የኢትዮጵያ ቀን በማቲው ሥም ለምን ይሰየማል የሚል ጥያቄ ወይንም ተቋውሞ የለንም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቀን ማለት ምንድን ነው? አላማውስ? በዐሉ በግለስቦች ሥም ለምን ይሰየማል? መሟላት ያለበት መስፈርት ምንድን ነው? ወዘተ…… የተባሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ማንሸርሸርና ወጥ የሆነ ሕግና ደንብ መሟላት የግድ ነው። አዎን የዚህ ታዳጊ አሟሟት ሁላችንም ነክቶናል። ነገር ግን ወጣቱ በሕይወቱ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ያበረከተው ወይንም ከሌላው ተነጥሎ አሊያም አወዳድሮ ይገባዋል የሚባልበት ውሳኔ በምን መንገድ ተጠንቶ እንደተመረጠ የሚደግፍ ምንም መረጃ ልንጨብጥ ቀርቶ አመራሩ የተነጋገረበት ቃለ ጉባኤ ማግኘት እንኳ አልቻልንም። ይኸው ተመሳሳይ ጥያቄ በሁሉም የዳላስ አካባቢ ነዋሪ ወገኖቻችን ውስጥ ያለና መልስ የሚገባው ነው።
አመራሩም ቀደም ባለው ጊዜ ደጋግመን ላቀረብንለት ጥያቄ ዳተኛ ቢሆንም እድሜውን አሳጠረ እንጂ አላራዘመም። በየጊዜው በህብረተሰቡ ተተፋ እንጂ ተቀባይነትን አላገኘም። በስሩ ያቀፈውም እድር እየከሰረና አባላቱ አናድስም እያለ ወጥቶ ቀረ እንጂ አላደገም። ለማዕከል ማሰሪያ ተብሎ ነጋሪት ተጎሸመ፣ ገንዘብም ተዋጣ ተባለ፤ እምነትን ከኮሚኒቲው ያጣ አመራር ቤሳ አላገኘም። እንዲያውም ባለፈው አዲስ ኮሚቴ ሲያዋቅሩ የቀድሞው ምን እንዳደረጉት ወይንም ገንዘብ ይሰብስብ አይሰብስብ ይፍረስ አይፍረስ ምንም መረጃ አላስጨበጡም። አንዳንዶቹ እንኳን ኮሚኒቲ ሊመሩ የባንክ ሂሳባቸውንም ማወራረድ የማይችሉ ናቸው ወይንም መዋያ ያጡ ጡረተኞች።
ከዚህ ወጣ ስንል ደግሞ ሰሞኑን በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ በጎደሉትና የሥራ ጊዜ በማጠናቀቅ በምትካቸው ለሚመረጡት 8 ተጠቋሚዎች የጊዜ ገደቡ የሚያልቀው የፊታችን እሁድ መሆኑን የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ገልጾልናል። መምረጥም ሆነ የመመረጡን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ እንድትሳተፉ እያስታወስን፣ የተጀመረው የደብሩ የመሻሻል እድገትና ሰላሙ እንዲጎለብትና አዲስ የሚመረጡትም በእምነትና በቅንነት የሚያገለግሉ እንዲሆኑ ሁላችንም በጸሎት እንድንተጋ ገጻችን በቅዱስ ሚካኤል ስም ይለምናል። ለምርጫ በፈቃደኝነት ከቀረቡት ውስጥ ከደረሱን ስሞች ወ/ ኤልሳ በቀለ ፤ አቶ ላቀው ደስታ፣ አብርሃም አሰፋ፣ ሰሎሞን ጋዲሳ፣ ዮሴፍ ረታ፣ ሙሉጌታ ወልደ ሚካኤል፣ ተስፉ በላቸው፤ ከፍተኛ ድምጽ ያገኛሉ ተብለው ይጠበቃሉ። ይሁን እንጂ እርሱ ቅዱስ ሚካኤል የሚበጁትን ይምረጥ። አሜን።
የእርሶስ አስተያየት ምን ይሆን? መጣጥፋችሁ ይቀጥል።
No comments:
Post a Comment