Monday, December 13, 2010

ሁሉም ሀጢያትን ሰርተዋልና

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ምንም እርቀን ብንኖርም የናንተን ሀዘንም ሆነ ደስታችሁን ከመካፈል አላሰለስንም። ያጠፉ ቢኖሩ እንዲመከሩ ፣ የተሳሳቱም ቢኖር እንዲመለሱ ከመጠቆም አናቋርጥም። እንደመልካችን ሁሉ አስተሳሰባችን ይለያያል። በምንወስደውም እርምጃ ከተጠያቂነት አናመልጥም። ምንም እንኳ ከሰው ስህተት ከብረትም ዝገት አይጠፋም ቢባል የሕዝብን አደራ ተቀብለው በአመራር ላይ የሚቀመጡ ፤ ከሚጠበቅባቸው ዋነኛውና ተቀዳሚ መመዘኛ የስነ-ምግባር ሞዴልነታቸው ነው።

በምንኖርበት ሀገር ባሕሉም ሆነ ህጉ ከትውልድ ሀገራችን ጋር በጣሙን የተለየ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። በተለያየ የዜና ማሰራጫ በየጊዜው እንደሚዘገበው  ኃይልና ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ከሕግ በላይ ራሳቸውን ያደረጉ እስኪከስትባቸው እንጂ ፣በለስ የቀናው ሲያመልጥ ሌላው ደግሞ ሕጉ ሲጎብጥለት እናያለን። ለዚሁም ደግሞ  ቀደም ያለ ስነ-ምግባራቸውን ከግምት በማስገባት አስተያየት ይደረግላቸዋል። ከትንሽ ከተማ እስከ ሀገር መሪነት ፣ ከተራ የሀይማኖት ተማሪ እስከ ከፍተኛ የክህነት ስልጣን፣ ከተቆጣጣሪ እስከ ዋናው የድርጅት መሪ እንደዚሁም የስራ ጠባያቸው ከሕብረተሰቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሁሉ ከስህተት ለመጠንቀቅና የሚያደርጓቸውን ተግባራት ሁሉ የመጨረሻ ነጥባቸውን ከወዲሁ ማጤን ብልህነት ነው።

አንዳንድ ግልሰቦች ወይንም ምንጮች በህግ የተያዘን ጉዳይና እልባት ባልተደረሰበት የራሳቸውን እንዲሆን የሚመኙትን ብቻ አስተያየት በመስጠት የሌላውን አመለካከት ለሀሰት ግምገማ ሲዳርጉ በየጊዜው ተመልክተናል።በዚህ በምድረ አሜሪካ “innocent until proven guilty “  Constitution of the United States እንደተቀመጠው ሁሉ ይህንን በመዘንጋትም ሆነ አውቀው የግል አቋማቸውን ሲያንጸባርቁ ይታያሉ። ይህ በህግ የተያዘን ጉዳይ የራሱን Legal process ሳይጨርስ በግልጽ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም እንላለን። ይህ አሜሪካ ሆነና moral and ethical questions ከተለያየ viewpoint እየተገመገመና እየተሰነጣጠቀ በተለያየ መልኩ ቅርሱንና ይዘቱን ከዘመን ወደ ዘመን እየለዋወጠ ይገኛል። ነገርን ከስሩ ውኃን ከምንጩ እንዲሉ ጫፍ ይዞ መሮጥ ከግምት ይጥላልና። ይህን moral and ethical questions ጫንቃቸው መሸከም ያቃታቸው ራሳቸውን ከሀላፊነት ማግለልና ከሰፋ ጸጸት መዳን ይገባቸዋል።ነገር ግን ወደ ቃሉ ስንመለከት “ ሁሉም ሀጢያትን ሰርተዋልና……” ስለዚህ የጥፋትና የሀጢያት ትንሽ የለውምሁላችንም ሀጢያትን ሰርተናልናየይቅርታ አምላክ ግን ንስሀችንን ይቀበልልን። የድክመት ስህተታችን ለሌላው መውደቂያ አያድርግብንምንም ወርቅ በእሳት ቢፈተንም ፤ በቤተክርስትያን አገልጋዮች ላይና በቤተክርስትያን ላይ ፈተናው ይበዛል። አማኞችም በጾምና በጸሎት ይበልጡን በመጠንከር ፈተናዎችን ሁሉ በማሸነፍና ለመንግስቱ ወራሽነት ለመብቃት እግዚሀብሔር የበቃችሁ ያድርጋችሁ።

3 comments:

Anonymous said...

ተዉ …. ተዉ እናንት ዳላሶች…
ተዉ… በእግዚአብሔር፤ በቅዱስ ቃሉ አትቀልዱ’
ተዉ…
ሰው ይለምናችኋል፤ እግዚአብሔር ግን….
እባካቹሁ … ተዉ … ተጸጸቱ/ እንጸጸት።

Anonymous said...

ተዉ ብለናል እዛም ቤት ያለው እሳት ይፋጃል!!
አሁን ሉዘር ተኩላ ነው ወይስ ጨለማ ኩነኔ/ጸህይ የጨለመበት ነው ወይስ ክፈተው ነጋ? ኧረ ማነው ከናንተ ከአርባዎቹ ታዋቂ ወንጀለኞች የመጀመሪያውን ድንጋይ መወርወር የሚችል? ደግሞስ በያንዳንዳችሁ አይን የተጋደመውን ግንድ መስታወት አይታችሁ ቀንድና ጅራት እንዳላችሁ ለማየት እንድትችሉ ታግላችሁ ማውጣት ይሻልችኋል ወይስ ገና በፍርድ ቤት ያልተጣራ የአበበን ጉድፍ ከሱ እይን መዝንቆል?
መቸምስ ወድሀገርና! ዝኾነ ኾይኑ ሽዋን አስመራ ኾይኑ ዝብሃል! ምፋለጥማ ተፋሊጥና!
አሁን ማንኛችሁ ናችሁ ስለሰው ሃጢአት መናገር የምትችሉት? ሁላችሁም ማንነታችሁና ምንነታችሁ የሚታወቅ በየቤታችሁ ከራስ ዳሸን ተራራ የሚበልጥ ጉድ ያለባችሁ ናችሁ። ግማሻችሁ የኢትዮጵያን ወጣት ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ እንደበግ እየነዳችሁ እቤተክርስቲያን በር ላይ እየረሸናችሁ ደሙን እንደጎርፍ ውሃ እንዳላፈስሳችሁ ሁሉ እዚህ መጥታችሁ ደግሞ የሚያውቀን የለም ብላችሁ እንናተ ሃይማኖተኛና ቤተክርስቲያን ሳሚ ሆናችሁ በሌላው ምእመን ላይ ጣታችሁን መቀሰራችሁ በጣም አስገርሞናል።
ግማሻችሁ በምድረ ኢትዮጵያ ጌይ (ወንዳገረድ) የሚባለውን ቃል በየፍልውሃውና በየሆቴሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመዘገባችሁ ናችሁ፤ ሌሎቻችሁ ደግሞ ከኪስ አውላቂነት እስከ ማጅራት መቺነት፤ ከቤት ሰርሳሪነት እስከ ባሪያ ፈንጋይነት፤ ወዘተርፈ በወንጀል ስራ ተሰማርታችሁ የኖራችሁ ቦዘኔዎች ስትሆኑ እዚህ መጥታችሁ ደግሞ የሰው ትዳር ከማፍረስ፤ ከጋለሞቶች ከመደራትና ኑሮውን ለማሸነፍ ሌት ተቀን የሚደክመውን ኢትዮጵያዊ እያደናችሁ ሚስቱን ከማባለግና ከመንጠቅ አልፎ ከዘረፋ እስከ ግድያ በተለያየ የወንጀል ስራ ተሰማርታችሁ እየኖራችሁ እንደው ለመሆኑ የትኛው ታሪካችሁ ነው እናንተን በሌላው ሰው ላይ ጣታችሁን የሚያስቀስራችሁ። ተዉ ብለናል በመስታወት ቤት የሚኖር ድንጋይ አይወረውርም ብለናል።
አትነካኩን አትኮርኩሩን ለናንተው ነው ጠንቁ! የብዙዎቻችሁን ዝጉርጉር ታሪክ በስም በቀይ ቀለም መጻፍ ይቻላል፤ ቢያሻንም ከነፎተግራፋችሁ። ሁልህም/ሽም በየቤትህ ጉድ (ስኬለተን) አለህ፤ አይታወቅብኝም ብለህ ከሆነ think again ያገር ቤቱ ቀርቶ እዚህ እንኳን ያለህ የእያንዳንድህ ግም ታሪክ ቢመዘገብ ክርፋቱ መላው የኢትዮጵያን ኮሙዩኒቲ በተስቦ በሽታ ይፈጃል። ተዉ! አርፋችሁ ተቀመጡ ብለናል። አላርፍ ያለች ጣት ኩስ ጠንቁላ ትወጣለች እንደተባለው የናንተ ጣት ጠንቁላለች ነገር ግን አልወጣ ብላ እየታገለቻችሁ እንጂ፤ ስታወጧት ሁላችሁንም ጠራርጋ ይዛችሁ መቀመቅ ትወርዳላችሁ። እግዚአብሄር በናፍቆት ለምትጠብቁት ለዛ ቀን ያብቃችሁ እንላለን።

Anonymous said...

"If you go to hell, don't blame it on Jesus" Tekula Chapter 51:0. We say if you don't love Jesus go to hell. This is a fact Tekula, that is your everlasting home!! after you draw your last breath, ofcourse. which might be between now and the next heart blow up. When you say you will continue the fight against the Church, don't you know Jesus is the Head of the Church and your fight is against God. You think you will win the fight? dream on, suckerrrr!! You realy are dragging down all these criminals to the depth of the pit you call Hell your home. ya'll belong there anyway!! Good riddddddeeeennnnns!!