ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
በቅርብ የምናውቀው ወዳጃችን ብዙም ለሀይማኖት ግድ የሌለው ነገር ግን የሚያውቀው ወዳጁ እናት አርፈው ለቀብር ስርዐት ሲል ወደ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ጎራ ብሎ በነበረበት ትምህርት ተነክቶ እንደእርሳቸው ሳልሆን በፊት ወይንም እንደጨቅላው ሳልቀደም ዛሬውኑ ንስሀ ገብቻለሁ ሲል በስልክ አጫውቶናል። እኛም ለጨቅላውም ሆነ ለአዛውንቷ ወይዘሮ የመንግስቱ ወራሽ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን እንላለን።
የዕለቱን ትምህርት ያስተማሩት አባት ሁላችሁንም እንዳላቀሱና እንድትገነዘቡ ማስጨበጣቸውን ከሚካኤል ሰይፍ የደረሰንም ዜና ያረጋግጣል። እንግዲህ ልብ ያለው ልብ ይበል እነዚህ እርሳቸው በህልማቸው ያዩትን እኛን ተንባይ ባያሰኘንም ቀደም ብለን ቤታችሁን ከተኩላና እባቦች ጠብቁ ብለናል። ከነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ወጥመድ አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ ፣ በስህተትም ሆነ በድፍረት የገባችሁ ከመጥፎ መንገድ ተመልሳችሁ ንስሐ ወስዳችሁ ከአምላካችሁና ከፈጣሪያችሁን እንድትታረቁልን ካህኑ በፈተቱበት ሰውነት መስቀሉን ይዘውና ተንበርክከው በመለመን ቃል አስገብተዋችኃል። እኛም ከዚህ በላይ የምንጨምረው የለንም። እንግዲህ ለካሳ የከሰሰችውም ባል ሀዘንተኛ ሆኖ በተቀመጠበት፣ የተቀሩትም ከሳሾችና አስከሳሾች ባሉበት ይህንን ያደረገ አምላክ አንበሳውን እንዳይለቅባቸው ሲል ሀዘኑን ገልጾልናል።
ከዚህ ጋር አብሮ የደረሰን ካስከሳሾች አካባቢ በቅርቡ በሌላው የደብሩ ተመራጭ ላይ በገጻቸው ሊለጥፉት ያቀዱትን የሀሰት ወሬ ነው። እኛም ንጹኃን ሲነኩ ዝም ማለት መልካም አይመስለንምና እንደ ካህኑ እነዚህ እንግዲህ እባቦች ያሏቸው ናቸውና መራራታችን በነፍሳችን ያስጠይቀናል። በእጃችን ያሉ እልቀ መሳፍርት መረጃ አለንና እንደ ቀድሞው ቆንጠጥ ለቀቅ አናደርግም።በጥርሳችን ከነከስን አብረን እንወድቃታለንን እንጂ አንላቀቅም። ሀይማኖታችንን ስንጠብቅ ቤተክርስትያናችንን መጠበቅ አለብን። ቤተክርስትያናችንን ስንጠብቅ ደግሞ አገልጋዮቻችንን መጠበቅ አለብን። ይህንን ስንል ደግሞ collateral damage ሰለባ ሆነው የሚወድቁትን ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ከግምት በማስገባትና ፈጣሪን በመፍራት ነው። ቁጥር 44 መሪ የነበርከውና የንጹሀን ደም በእጅህ ያለህ ስለፈጣሪ ብለህ ተወን አትነካካን፣ እኛ እዚህ ሀገር የገባነው እንዳንተ ቀዩ መሎዮዬ ሊለወጥብኝ ነው ብለን ሀገራችንንና የገባነውን ቃል ሰብረን ከሰራዊቱ አልከዳንም፣ ማንኛውንም የሰው ዘር አንግተን አላሰቃየንም ፣ ለሕይወታቸውም ተጠያቂ አይደለንም፣ ወዘተ………ወይንም እንደቀዳዳው አልቀደድንም፣ ከኃላ ሆነን ሌላው የኛን dirty ስራ ይስራልን አላልንም፣ በንዋይ አልተመካንም፣ ዝምብ እሽ ያላንን ካራቲስት አይደለንም፤ የትም ይሁን የት እያንዳንዷን ሳንቲም በጭቦ አልያዝንም፣ ነገር ግን የትኛውን ክር እንደምንስበው ስለምናውቅ domino effect ምን እንደሚሆን ከዚሁ በማስላት ስለሆነ የሚሻለው ወደ ፈጣሪ መንገድ ሁላችንም መመለስ እንጂ ቀናተኛ አምላክን መፈታተኑ ስህተት ነው። በአይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ መጀመሪያ እናውጣ ወይንም እስቲ ማናችን ነን ንጹህ የመጀመሪያውን ድንጋይ የምንወረውር? ምናምንቴ ከመሆን ይሰውረን። አሜን።
ሌላው የተጠቆምነው ሌላ የፖለቲካ ገጽ አለ። ነገር ግን ስለ ደብራችሁ የተጣፈውን ለማየት http://www.ethiodallas.blogspot.com/ ይህንን በመጫን ወይንም ኮፒ በማድረግ December ያወጡትን ይመልከቱላቸው የረባ አስተያየት ይዟልና። ሰንበቴንም ይመልከቱ።http://www.senbete.blogspot.com/
በተረፈ አዲስ መማክርት የምትመርጧቸውን ካሉት ጋር ተመሳስለው በሰላም የተጀመረውን እድገት ይቀጥላሉ የምትሏቸውን እንጂ እናንተን መልሰው ወደ አለፈው ወይንም ወደ ባሰው የሚስቧችሁ እንዳይመጡ ጸልዩ። ምንም ሆነ ማን አምሃ የሚል ስም ከያዘ እባብ ራቁ። ሌላው ሁለት ፀጉር ዕድሜ ይዘው ተርማቸውን ሳይጨርሱ የለቀቁና የነርሱ ወዳጆችን እንዳትጠቁሙ ፣ ከዚህ በፊት ገጻችን የኮነናቸውን ወደኃላ ሂዳችሁ ተመልከቱ ሊያጠፏችሁ እንጂ አይሆኗችሁምና ተጠንቀቁ። ሌላው መለከት ወደተባለው ገጽ በመግባት ጸረ ሀይማኖታችሁና አጽራረ ቤተክርስትያን የሆኑት ተመራርጠው ያቋቋሙት ኮሚቴ ስም ዝርዝር አለና ፈጽማችሁ የነዚህን ግለሰቦች ስም እንዳታስገቡ በሚካኤል ስም እንጠይቃለን፣ ንስሀ ወስደው ወደ ምንጩ መግባት ተስኗቸዋልና።
ባለፈው የቴኔሲው ብዙነህ የጀመሩት ዘግይቷልና የእርሳቸው ሳያልቅ በእጃችን ያለውን ማስረጃ መልቀቅ አልፈለግንምና አይጥፉብን እንላለን።
እርሶስ ምን ይላሉ?
2 comments:
ዳላሶች እንደምን ከረማችሁ!
መጣጥፎቻችሁን ወደኋላ ሄደን ስንመረምር ያየናቸውን አንዳንድ ጉድለቶች ልንጠቁማችሁ ወደድን። ቅር እንደማትሰኙ ተስፋ እናደርጋለን።
መድረኩን የመወያያ ማድረጋችሁና በዛ መልክ ማስተዋወቃችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከሁሉም ወገን የሚቀርቡትን ሃሳቦች የሚደግፍም ሆነ የሚነቅፍ አለመኖሩ የአንባቢያችሁን ቁጥር ውሱንነት ወይም ደግሞ ቢያነብም በተለያዩ ምክንያቶች ሃሳብም ሆነ አስተያየት ለመሰንዘር የተሳነው አንባቢ እንዳላችሁ እንገምታለን። ይህን ችግር ለማቃለል ምናልባት የበኩላችሁን ብታሻሽሉ በይበልጥ ብሎጉ ያቀዳችሁለትን የመወያያ መድረክነት ግብ ሊመታ ይችል ይሆናል የሚል እምነት አለን።
ለምሳሌ ፡ የሚካኤል ቤተክርስቲያንን የሚመለከቱ ወቅታዊ ጉዳዮችን (አወንታዊም ሆነ አሉታዊ) በወቀቱ ብትዘግቡና በዛ ርእስ ላይ ተሳታፊው ያለውን ሃሳብ እንዲሰጥ የተለያዩ ጥያቄዎችን አብራችሁ ብትከትቡ ምናልባት የብዙ ምሁራንን ተሳትፎ ታገኛላችሁ የሚል እምነት አለን።
ሌላው አንዳንድ ማስራጀዎችን እንቀርባለን ወይም ደግሞ ተከታዩን ወደፊት እንገልጻለን ተብለው የተረሱ ወይም ተከታይ ያልተዘገበላቸው ርእሶች ስላሉ እነዛን በቅርብ መከታተልና እርምጃ መውሰድ በጣም አስፈላጊ ነው እንላለን። ስለእነእንቶኔ ማስረጃ እናቀርባለን ወይም በሚቀጥለው ተከታዩን እናቀርባለን ወዘተ… ብዙዎቻችንን በእንጥልትል አስቀርቶናል።
ባለፈው ሳምንት በሚካኤል ቤተክርስቲያን ምን ምን ሁኔታዎች ተካሄዱ? በያዝነው ሳምንትስ? ወደፊትስ ምን ታስቧል? ጥቆማስ? ምርጫስ? ወዘተ…..
ከዚህ በላይ አስተያየት የሰጡን ተሳታፊያችንን እያመሰገን ተመሳሳይ በእንጥልጥልነት የተውናቸውና ያልቋጠርናቸው በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶችን ተቀብለናል። ያልቀጠልንባቸው ተጨማሪ መረጃዎችን በማጠናከር፣ ወቅታዊው ሁኔታን የሚያደናቅፍ፣ አንባቢዎችን ላለማሳዘን፣ በሕግ በመረጃነት በመያዙ፣ መንግሥታዊ አካል እጅ በምርመራ ላይ የሚገኝ ወይንም በመሳሰሉት ምክንያቶች እንጂ የጀመርነውን እንደምንቋጨው ከዚሁ እንገልጻለን። ተሳትፎቿችሁ ይቀጥሉ።
Post a Comment