ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
የመላእክትን ዝማሬ ያሰማልን!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር በጋርላንድ ከተማ በቴክሳስ ግዛት እያስመዝገበ ያለው መልካም አገልግሎቶች ከዳላስ አካባቢ አልፎ በሌሎች ግዛቶች እየተደነቀለት ይገኛል። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢያን እንደምን ሰነበታችሁ? በሰላም ጠብቆና ተንከባክቦ ዳግመኛ በዚህ ጦመር እንድንገናኝ ፈቃዱ ለሆነው ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።
ደብራችሁ ተገኝተን አብረን የቅዱስ ሚካኤልን በዐለ ንግሥ ስናከብር ምስክር የሆንባቸው ታላቅ ለውጦች አሁንም ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን።ይህንኑ እውነት መቀበል ያቃታቸው ደብሩን ከመተናኮል ያላሰለሱትና ተዐምሩም ሆነ በረከቱ የጎደለባቸው፣ ልቦናቸውን እንዲያስገዙ እየጸለይንላቸው ወደ እርሱ መንገድ እስኪገቡ ድረስ ከወደቁበት ሁነው ቢፈረጋገጡ ለመላላጥ እንጂ ለመፈወስ አይሆንም። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ያደረባቸው የተለየ መንፈስ በመሆኑ የስነ ልቦና ብቻ ሳይሆን የኑሮ ቀውስም እየገጠማቸው መሆኑን ምንጮቻችን ይጠቁማሉ።
ሰሞኑን እነዚሁ ግለሰቦች በተለያዩ ገጾቻቸው አከታትለው ያወጡትን ተመልክተን ከወደቁ በኃላ መንፈራገጥ በማለት ችላ ብንልም በናንተ ጥያቄ፣ ለእነርሱም ትምህርት ለናንተም ማብራሪያ ይሆን ዘንድ በማለት እንጂ ። ቀደም ባለው ጥሁፎቻችን እንዳስነበብነውና ቅዠት እንዳልናቸው ሁሉ፤ በነርሱ እኛን ሀሰተኛ ጠሀፊ እንዳላሉን ፤ ይኸው ዛሬ መራራ መርዶ ሲቀምሱ ጣዕሙ ተናነቃቸውና እርማቸውን አወጡ ፣ ሀዘኑም ጠናባቸው። ለዚሁም ሰላማዊ የሆኑትንና ቅን የቤተ ክርስትያን አገልጋዮችን፣ በተለይም ከፖለቲካም ሆነ ከመሰለው ሁሉ እርቀው ኑሮዎቻቸውንና በሚችሉት ሁሉ ፈጣሪያቸውን የሚያገለግሉትን ለማደናቀፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይና የማይሰጧቸው ስም የለም። የኛን ጥሁፍ በገጾቻቸው ደጋግመው ሲኮንኑ የነበሩት፣ እኛ ስም እየጠቀስን ግለሰቦችን እንደምንሳደብ ነበር። የኛ ጦመር ተፈጥሮ እስኪመታቸው ድረስ የጀመሩት እነርሱ ፣ አሁንም በቱልቱላቸው በ Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው የሚዘጋጀውና የሚቀርበው ገጽ ባለፈው ጥሁፉ ከደብሩ አመራር አባሎች ጀምሮ ሽማግሌ የተባሉትንና የአስተደሩ አዕምሮ ብሎ የሚላቸውን ቅን ምዕመናን ሁሉ ሳይቀር የሚፈልገውን መሰረተ ቢስ ምናምንቴውን ለጣጥፎባቸዋል።
ስለዚሁም ጉዳይ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ የዘገበውን እንደሚከተለው እናቀርባለን።
የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ካናገራቸው ውስጥ የአመራሩ አባላት ያሉት ነገር ቢኖር እኛንም ሆነ እነርሱን የፈጠረ አምላክ አንድ ነው ፣ እኛንም የመከረና የሚመራን እርሱ የእነርሱንም ልቦና ይግዛ፣ እኛ የተሰጠንን ሀላፊነት በቅን መወጣትና ይኸውም እንዲሳካ መጸለይ ነው። ማንም ከዚህ ቦታ ቋሚ የለም፣ ተርማችን ሲያበቃ ደግሞ እኛ ያገኘነውን በረከት ባለተራ እንዲደርሰው ነው። ይህ ቤተ እግዚሀብሔር ነው ፤ አባል በነበርንበት ወቅት በጊዜው የነበሩትን አመራሮች ብንመርጥም ሆነ ባንመርጥም ፤ ለተመራጮች የምንችለውን ድጋፍ በማድረግ ተባብረናል። በኛ አመራር ቅሪታ ያለባቸው አባላቶች ካሉ በራችን ምን ጊዜም ክፍት ነው። ከኛ በፊትም ነበር ፣ አሁንም አለ እንደዚሁ ወደፊትም ይቀጥላል። ተጠሪነታችንም ለመረጡንና ላልመረጡን አባሎች ያለአንዳች አድሎ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ሽማግሌዎች የተባሉትን ግለስቦች blackmail በማድረግ ደብሩ የማያውቀውን እውቅና ለማስገኘትና ቅደም ሲል በመረዳጃ ማህበሩ ውስጥ እንዳደረጉት አስርገው በማስገባት ጥረታቸው በመክሸፉ፣ እንደዚሁም ከደብሩ መተዳደሪያ ሕግ ውጪ በመሆኑ፣ በሚገባ አዛውንቶቹ በመረዳታቸው ተዳምሮ፤ እነዚሁን አዛውንቶች ስም በመጥቀስ ለማስፈራራትና ስማቸውን በከንቱ ለማጥፋት coercion በገጻቸው እንደተለመደው የከፈቱባቸው መሆኑን ቢታወቅም ከነዚሁ ውስጥ አንደኛው ሽማግሌ የደብሩ አባል ያልሆነና ከነርሱ ጋር አብሮ የወገነ ቢሆንም ሁለቱ ሽማግሌዎች አሁንም በቅን ለረዥም ጌዜ ( ከቆርቋሪዎች የሚደመሩ) እያገለገሉና ብዙ የደከሙ ሲሆን ለምናምንቴ የማያጎበድዱ መሆናቸውን ተወካዩ ገልጾልናል።
Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው በገጹ ካለው ውስጥ የመሸታ ቤቱ ግጭት እርሱ እንዳጋነነው ሳይሆን ሁለቱም ወገን በትግራይ ነጻ አውጪ ስር በአማራ ስም ከተጠራው ስብሰባ መልስ ለራት ባንድ ምግቤት ተገናኝተው ሳሉ ዘግይቶ የደረሰው ግለሰብ ሰላምታ ካቀረበላቸው በኃላ ለምን ስብሰባችንን ረበሻችሁብን በማለት በተነሳው ቃል ልውውጥ ከተኩላው ጋር ተቀምጦ የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ በአጨብጫቢነት የሚታወቅውና ጎጃም በማደጉ ብቻ ጎጃሜ እራሱን በማድረግ የሚታወቀው ዘሩ ከትግሪ የሆነው መላኩ አቦዝን የሚሉት ግለሰብ ስድብ በመጀመሩ የወንድነት ጥያቄ ስለተጀመረ እንጂ የረባ ፍሬ የሌለው ነው። ተኩላውም ይህንን ይዞ ለግለሰቡ ሚስት ባልሽ ካልደበደብኳችሁ እያለን ብሎ ሰላማዊ ጋብቻ ውስጥ ቢያሞጠሙጥም፣ ታዲያ አንተስ ሱሪ ያጠለቅከው ወንድ ሆነ አይደለምን? እኔ ሴቷ ዘንድ የምን አማላጅ አመጣህ የተባለውን አፍረቱን መደበቂያ እንጂ ምንም ከጉዳዩ ጋር አይገናኝም፤ ስካርም ካለ እርሱም ሰክሮ ነበር ማለት ነው ተብለናል። ነገር ግን እኛም የምንጨምረው ቢኖር ተኩላው ስለጠመንጃ በሀገራችን በአሜሪካ ውስጥ ማንሳቱ እኛን ጠሀፊዎችን ባይነካካን ጥሩ ነው። እንደእርሱ አይነት ሽንታምና ፈሪ የጀግኖችን መሳሪያ ያለቦታው አትነካካ long live US Marine Corp ያለብቃትህና ያለቦታህ አትግባ ፣ ባለፈውም ጠቁመንሀል።
ሌላው ምንጫችን ያናገረው ስለስራው ሳይቀር ስሙ የተጠቀሰው ግለሰብ ያለውን ነው። ግለሰቡ ያለው ቢኖር የአገልጋይ እጥረት በነበረበት ወቅት ለደብሩ ባገኘሁት ሁሉ ከልቤ በቅን በማገልገሌ ተባርኬበታለሁ። ጤናንና ዕድሜ ቀጠለልኝ፣ሥራዬ ቀዝቅዞ የነበረው ተመለሰልኝ፣ ለ5 አምታት ያህል በአንድ የሆቴል ክፍል ተጣብቄ ስኖር ማገልገል ከጀመርኩኝ በኃላ የቤት ባለቤት ከማድረጉም በላይ ባለፈው ጥቂት ወራት ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ በነበረኝ ሀብት ላይ ጨመረልኝ፤ ስለዚህ በመንበሩ ፊት በሁለት እግሬ ቆሜ አይደለም ብችል በጭንቅላቴ ተዘቅዝቄ ቆሜ ብዘምርለት ስላደረገልኝ ምክንያት ስላለኝ ነውና ለኔ የፈሰሰው በረከት ቀላል አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ለማያውቁኝ ወገኖቻችን ሙያዬን ብቻ ሳይሆን እኔንም አስተዋወቁኝ። እኔ ለመታወቅና ለዝና ያደርኩት ነገር ምንም የለኝም፣ ችሎታውም ሆነ ዕውቀቴ ለተከበሩት አዛውንቶችና ከደብሩ አመራር አባሎች ተሽሎ ተገኝቶ በኔ የሚመሩ ከሆነ ወደፊት ለፖለቲካ ቤሮ ለመወዳደር አሊያም በዳላስ የሚገኙትን ወገኖቻችንን በቅን ለመምራት የሚያስችል ልዩ ተሰጥዎ አለኝ ማለት ነው በማለት በቀልድ እንደመለሰለት ዘግቦልናል። እኛም ስለ ግለሰቡ አገልግሎት የመላዕክት ዝማሬ ያሰማለን፣ ስለአገኘው በረከት የሰጠውን ምስክርነት ከልባችን የገባ በመሆኑ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እንላለን።
በተረፈ በወይዘሮ ሐረር (ኢትዮጵያ) ወርቅ ጋሻው የሚቀርበው የዳላስ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ብሎግ http://dfwethiopiancommunity.blogspot.com/
እያወጣው ያለው መረጃዎች በአካባቢያችሁ እናንተን እየከፋፈሉና በናንተ ስም እየነገዱ የሚገኙትን እያጋለጠ ያለ የሕብረተስባችሁ ድምጽ እየሆነ የመጣ ስለሆነ ቅኝታችሁ አይታጎል።
የክብር እንግዳ ሳይሆን እንደ ኢሕ አፓ አባል በቅርቡ በተደረገ የመገናኛ ዝግጅት ላይ ሙሉጌታ ወራሽ aka ቀዳዳው ሙላው መገኘት ከነበሩት ደርሶናል። እኛም የትና መቼ በድርጅቱ መታቀፉን ባናውቅ በወቅቱ ጥብቆ ያጠለቀና ቁንጯም መሆኑን አብሮ የደረሰን መሆኑን ነው።
ሌላው Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው በገጹ ካለው ውስጥ የደብሩ አመራር ልጆችን ተጠቀመ በማለት ፍሬቢስ አስተያየት፤ የተማረና የሚማር ሁሉ እንደሚያስፍራው መሆኑን ነበር የጠቆመው። እርሱም በየሳምንቱ አርብ ምሽት በሚሰጠው መንፈሳዊ ትምህርት ከቻለ በአካል ካልሆነ እንደኛው በኢንተርኔት በመማር ክርስትናውን ቢያጠብቅ፤ ለልጆቹም ከዕድሜ ብጤዎቻቸውና ከወገኖቻቸው ጋር ተቀላቅለው መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ ሲገባ፤ ነገርግን እንደተበደለና እንደተገፋ ሀሰት fabricate የማድረጉን እሮሮ ቢያቆመው በተሻለው። ምናልባት የተጠናወተው እርኩስ መንፈስ ለቆት እንደ ምናምንቴ ሳይሆን እንደሰው
ቢያደርገው።
ከዚሀ በፊት በትግሬ ነጻ አውጪ ለተሾሙት አባ ጳውሎስ ያደረ ባንዳና ካድሬ እነ ኢዮኤል (ክፈተው) ነጋ የቀጠሩት ሲደልል የተባለውና በዲፕሎማት ፓስፖርት ወደ አሜሪካን የገባው፤ በአዲሱ አመት ለሹመተ ጵጵስና ወደ አዲስ አበባ የሚዘልቀውን የአትላንታ ቄስ ተክቶ መቀጠሩን ስለስማን፣ አትላንታዎች ከዚሁ አስቡበት እንላለን። እንደዚሁም ቀደም ብለን እንደዘገብነው ግለሰቡ ቅጥረኛነቱን በተግባር እያስመሰከረ መሆኑን እያስረገጥን አሁንም ተጠልሎ ያለው ዳላስ ላይ ባለው የትግሬ ነጻ አውጪ በሚተዳደር ቤተ ክርስትያን ነው።
እርሶስ ምን ይላሉ?
5 comments:
ዳላስ ኢኦቲሲ እንዴት ከረማችሁ። ስለአገልግሎታችሁ እግዚአብሔር ይስጥልን፤ እድሜና በረከቱን ያብዛላችሁ።
መቸም ሜካኤል ለቤቱ ያውቃልና! እናንተን የመወያያ መድረክ እንድታዘጋጁና እውነት እንድትፈነጥቅ ሲያደርግ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት እንጂ የሌቦች መታጎሪያ አለመሆኗን የማያውቁ እንዲያውቁ የሚያውቁ ደግሞ ከእውቀታቸው ለማያውቁ እንዲያካፍሉ እንደሆነ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ችለናል።
ትናንት የእግዚአብሔርን ቤት እንደራሳቸው ቤት እንኳን ያላከበሩ የድሪያና የመነገጃ ቤት አድርገዋት የነበሩና እንደላም ጥገት ሲያልቧት የኖሩ ሁሉ ማርና ወተቷ ቢጓደልባቸው እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዙ ያዩትን ሁሉ የሚነክሱ የቀን ጅቦች ዛሬ ጮማ መቁረጥ ቀርቶ ያ ሁሉ ወዝ ጠፍቶ አመድ ነዝቶባቸው እንደ ጎስት ከየምናምኑ ብቅ ጥልቅ ሲሉ የታዘቡ አዛውንት በግምባራቸው ተደፍተው አይ አንተ አምላክ ምን ይሳንሃል ምንስ ይከፈልሃል የልጆቻችን ደስታ ዝማሬ ምስጋና ምን ያውጣ ይሄን አይቼ ነገ ብሞትስ ምን ቅር ይለኛል፤ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ለዘለዓለም ይሁን ብለዋል የደስታ እንባ እያፈሰሱ።
ቤተክርስቲያን ለእንደነዚህ ላሉ አምላካቸውን ለሚያውቁ፤ ለታላቅነቱና ለገናነቱ እራሳቸውን ለሚያስገዙ፤ ለሚያክብሩትና ለሚያመሰግኑት፤ ምን ትልቅ ቢሆኑ እራሳቸውን ከሁሉ በታች ዝቅ አድርገው በቅንነት ለሚያገልግሉት እንጂ በትምክህት ተወጥረው እዩን ያለእኛ ሃይማኖተኛ የለም ለሚሉ፤ የነጠላ ክርስቲያኖች ወይም ደግሞ በሃይማኖት ለሚነግዱ የክርስቶስ ጠላቶች አይደለችም።
የዘረፋ ዘመን እንዳለፈ በምን ቋንቋ ቢነገራቸው እነግሪን ፌስ (ክፈተው ነጋ) የፍልውሃው ጀግና እንደሚገባቸው፤ የጳውሎስ ነጋዴዎች አንዴ የካህናት ማህበር አንዴ የምእመናን ጉባኤ እያሉ ቤተክርስቲያናችንን ለጳውሎስ ሊያስረክቡ ሲሯሯጡ የከረሙት እነ ኪዳኔ አለማየሁ የሚባሉ ወረበሎች እውነት እውነት ናትና ይኸው ጊዜዋን ጠብቃ ወጣች እነሱም እርቃናቸውን ቀሩ። ሲደልልም ተልእኮውን እንዲወጣ ያሰማሩት ሌቦች በሚካኤል ሲመቱ መግቢያ ጠፍቶት ሲደናበር የአወናባጆች መሪ ወታደር ጸባቴ ብርሃን የአምሳ አለቃ ሲደልልን ተክቶ ለጵጵስና ወደ ዋናው አዘቅት ወርዷል። መስፍን ወልደየስ የሚባል ወሮበላ የሚካኤልን ካዝና እየመዘበረ በበጎ አድራጎት ስም የማህበረ ሰይጣንን ካዝና ሲያዳብር ከነጅሪዎቹ ሲነቃበት ከነቤተሰቡ ቤተክርስቲያናችንን እስከዛሬ ሲበጠብጡ ኖሩ፤ አሁን በቃ መግቢያችሁን ፈልጉ ሊባሉ ይገባቸዋል። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቼ ልፈትፍት ይላል እንዲሉ ሉዘር ተኮላን ቆማጣ ነህ ወግድ የሚለው ስላጣ እኮ ነው እንዲህ ጥሬ ኩሱን በየሄደበት የሚረጨው።
የአባታችን የአቡነ ይስሐቅን የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘብና ምን ሆነው እንደሞቱ ሊጠየቁ የሚገባቸው ሻምበል ግዛው፤ ኢዩኤል ነጋና ኪዳኔ ምስክር የሚባሉ የውስጥ አርበኞች የሚካኤል ጠላቶች ሲሆኑ በስላጣን መባለግ የሰሯቸው ብዙ ግፍና ማጭበርበር እንዲሁም ዘረፋ ስላለ በከፍተኛ ደረጃ ምርመራ እንዲካሄድ ህዝቡ ጉዳዩ የሚመለከተውን የህግ ክፍል በማሳወቅ ምርመራ እንዲደረግ መነሳሳት ይኖርበታል። ካልሆነ ግን ማስረጃዎቹ አንድ ባንድ እየወጡ ስለሚለጠፉ እነዚህ ወንጀለኞች ከመፈርጠጣቸው በፊት ጉዳዩ ባስቸኳይ ይጣራ እንላለን።
እንግዲህ ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል ነውና በየመሸታ ቤቱ ተገናኝተው ሲዶልቱ የሚታያቸው ያ እንደፈለጉ በሁለት እጃቸው አፍሰው በየመንገዱ እየተንጠባጠበ በየኪሳቸው የሚሞሉት ለሚካኤል የገባው ስለት ትዝ እያላቸው እኮ ነው ያ እርኩስ ዶክተር በምን አይነት መተት ነው እመሃላችን የገባብን እያሉ እንባ በእንባ የሚራጩት። እኛ ዶክተሩ ምንም ያደረጓቸው ነገር እንደሌለ ደርሰንበታል። ነገር ግን ሚካኤል የራሱን ወታደሮች ከየስርቻው ለቃቅሞ አምጥቶ ዘብ አቁሞ መድረሻ እንዳሳጣቸው እያንዳንዱ ለእውነት የቆመ ክርስቲያን የሚሰጠው ምስክርነት ነው። ያለፍንበት ሁለት አመት ሲጻፍ ከሶስት ያላነሰ መጽሀፍ እንደሚወጣው ጥርጥር የለንም።
በአንድ ወቅት ለከሳሾች አስር ሺ ብር አበዳሪ የሆነች ስሟን ቄስ ይጥራውና አንዲት ስሟ የማይጠራ ባልቴት ስድስት ሺ ብር እያስከፈሉ ከኢትዮጵያ በማጭበርበር ስው የሚያስመጡ (HUMAN TRAFFICKERS) በዚህ ቤተክርስቲያን ዘረፋ ላይ መሰማራታቸውን ብታጋልጥ ሊደበድቧት መጋበዛቸው ትዝ ሲለን በአሁኑ ወቅት ብዙ ደጋፊዎች በቁጥር ከአስር የማያንሱ ከማግኘቷም ሌላ እኔም ስድስት ሺዬን ተበልቼ እያስፈራሩኝ ቁጭ ብያለሁ የሚሉም አልታጡም። በድሮ ዘመን ቤተክርስቲያን ለተገፉ፤ ለተቸገሩና ለእግዚአብሔር ላደሩ መጠጊያ መሸሸግያ ነበረች። ዛሬ ደግሞ በግፍ የወደቁ አባቶች እርግማን ነውና ከአቦይ ገ/መድህን ጳውሎስ ጀምሮ የሽፍታ፤ የወንበዴና የተራ ሌባ መሸሸጊያ ሆናለች።
ከሁሉ የሚያሳዝነን ነገር ቢኖር የእድሜ ድሀ የሆኑት ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ሌት ተቀን ሲሯሯጡ ማየቱ ነው። እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ወቅት ንስሃ ገብተው ከቤተክርስቲያን ተጠግተው ሌት ተቀን ለነፍሳቸው ማገልገል ይገባቸው ነበር። ነገር ግን አልታደሉምና ለሰይጣን አድረው የእግዚአብሔርን ቤት ሲያፈርሱ ይታያሉ። እግዚአብሔር በምህርቱ ይጎብኛቸው ከማለት ሌላ ለነኪዳኔ አለማየሁ እና እሱን ለሚመስሉ የዲያብሎስ ልጆች ስንጸልይ አንገኝም። እዛው አባታቸው ሉሲፈር ይወሰዳቸው እንጂ።
እብድ ቢጨምት አስተ እኩለ ቀን!
እነሆ መረዋ የተባለው ብሎግ እራሱ የጀመረውን የስም ማጥፋት ዘመቻና ስም እየጠሩ ቀሳውስትን
ጭምር ያለ እፍረት ሲያዋርድ የነበረ ብሎግ በተለይም በስደት ያሉትን ቅዱሳዊ ጳጳስ አንተ እያለ
ሲለፋደድ የነበረ ብሎግ ሰሞኑን ራሱን እንደ መልካም እውነት ተናጋሪና ፈሪኅ እግዚአብሄር
የሌላውን ብሎግ እንደበዳይና ባለጌ ለማስመሰል ሲዘባርቅ ቆይቶ አሁን ወደ እውነተኛ ብልግናው
መመለሱን በርግጥ እያሳየ ነው።
እባካችሁ አንብቡለትና እውነቱን ተረዱ።
በ እኔ አስተያየት ከ ዳላስ ብሎግ ደራሲዎች ጋር የማልስማማበት ነገር ቢኖር፤ የመረዋ ደራሲ
ትኩላው አለመሆኑን ነው።
ብሎግ የሚያጽፍም እውቀት ያለው አይመስለኝም።
ለዚህም ማስረጃየ እንደሚከተለው ነው።
የመጀመሪያውን የመወረዋን አጻጻፍ ልብ ብላችሁ ያነበባችሁ ካላችሁ አንዲት ነጥብ ለመጣል
ይተረክ የነበርው ታሪክ የተኩላው እንዳልነበረ ተረዱ።
በ እኔ አስተያየት መረዋ የተጀመረው ገና ለገና እነ ክፈተው ተሸንፈው የኛ የሚሏቸው
ተመራጮች ካልተመረጡ፤ ቤተክርስቲያኑን ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ እንዳይወስዱት ለመከላከል
የተጀመረ ብሎግ እንደነበረ ነው። ጀማሪዎቹም እንደሚመስለኝ የሆለታው ሻለቃና ጡረተኛው
ዶክተር ናቸው። ተባባሪዎቹ እነ አቶ አለማየሁና የቦርዱን ወሬ አቀባይ እነ ክፈተው ለመሆናቸው
ለ አዲስ አበባው ሲኖዶስና ኢትዮጵያ ላለው አሜሪካዊ ጳጳስ የጻፉትን ደብዳቤ መልሶ ማንበቡ
ተገቢ ይማስለኛል። በዚሁም ብሎግ ሌላው ተካፋይ አሁንም በቤተክርስቲያኑ ተቀጥሮ የውስጥ
ስለላውንና ዶሴዎችን የማጥፋት ተንኮል እያደረሰ ምሆኑን አትጠራጠሩ።
በዚሁም አኳያ እንድታነቡልኝና ቤተክርስቲያናችን ከምን አይነት ችግር ውስጥ ሊያስገባ መረዋ
ሲሯሯጥ እንደነበር ለመረዳት http://www.dejeselam.org/2010/11/blog-post_27.html
November 27,2010 “የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የገንዘብና
የንብረት ቆጠራ ላይ ጥብቅ መመሪያ ሰጠ” የሚለውን በጥሞና እስተመጨረሻው አንብቡ እላለሁ።
ምዕመኑ ከልጁ አፍ አውጥቶ ለቤተክርስቲያን ከሚሰጠው ትሙኒና ድንቡል እነማን እንደሚጋሩት
ተመልከቱ። በተለይም “የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ለተለያዩ ክዋኔዎች ማስፈጸሚያ፣ የካህናት
አስተዳደር መምሪያው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በየጊዜው ለሚደረገው አቀባበል ጥንግ ድርብ
ለብሰው ለሚሰለፉ ካህናት አበል እንዲከፈል በማዘዝ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለመስቀል
ደመራ እና ለመሳሰሉት ክብረ በዓላት ጥናት ለሚያደርጉ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች(ማህበረ ቅዱሳኖች)
አበል እንዲከፈል በማዘዝ፣ ሀገረ ስብከቱ ለሽልማት እና ለመሳሰሉት አጥቢያዎች በተሰጣቸው ደረጃ
መጠን እንዲያዋጡበማዘዝ በየአቅጣጫው አቅምን የሚያዳክሙየግዳጅ አስተዋጽዖ በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ ለመፈጸም የሚገደዱበት የወጥ አሠራር ጉድለት “
“(ለገቢው) መዳከም በምክንያትነት መጠቀስ ይገባውእንደነበር አስረድተዋል፡፡ በቅጥርም ረገድ ከላይ
በሚሰጥ ትእዛዝ ብቻ ያለአቅማቸው በርካታ አገልጋይ ካህናትን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን የሚቀበሉ
አጥቢያዎች ከገቢያቸው ጋራ በማይመጣጠን አኳኋን ደመወዝ ለመክፈል መገደዳቸው፣ በዝውውርም
በኩል በገቢ አሰባሰብ እና በሌሎች የተግባር አፈጻጸማቸው መመሪያን ጠብቀው በሐቅ የሚሠሩ
የአስተዳደር ሠራተኞች ከቦታቸውእንዲነሡ እየተደረገ በምትኩ ለመጠቃቀም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ
ሙሰኞች እንዲተኩ መደረጋቸውም በተጨማሪ መንሥዔነት መታየት እንደሚገባው ተሳታፊዎቹ
አስገንዝበዋል፡፡”
በተጨማሪም ከዚቹ ስሙኒና ድንቡል ለመካፈል፤ ሙዳይ በጎን ማን እንደሚያስቀምጥ ተረዱ
እላለሁ።
መጥፎውን ክድጉ የምንለይበት ልቦና ይሰጠን ዘንድ አምላኬን እለምናለሁ።
አሜን!.
እብድ ቢጨምት አስተ እኩለ ቀን!
እነሆ መረዋ የተባለው ብሎግ እራሱ የጀመረውን የስም ማጥፋት ዘመቻና ስም እየጠሩ ቀሳውስትን
ጭምር ያለ እፍረት ሲያዋርድ የነበረ ብሎግ በተለይም በስደት ያሉትን ቅዱሳዊ ጳጳስ አንተ እያለ
ሲለፋደድ የነበረ ብሎግ ሰሞኑን ራሱን እንደ መልካም እውነት ተናጋሪና ፈሪኅ እግዚአብሄር
የሌላውን ብሎግ እንደበዳይና ባለጌ ለማስመሰል ሲዘባርቅ ቆይቶ አሁን ወደ እውነተኛ ብልግናው
መመለሱን በርግጥ እያሳየ ነው።
እባካችሁ አንብቡለትና እውነቱን ተረዱ።
በ እኔ አስተያየት ከ ዳላስ ብሎግ ደራሲዎች ጋር የማልስማማበት ነገር ቢኖር፤ የመረዋ ደራሲ
ትኩላው አለመሆኑን ነው።
ብሎግ የሚያጽፍም እውቀት ያለው አይመስለኝም።
ለዚህም ማስረጃየ እንደሚከተለው ነው።
የመጀመሪያውን የመወረዋን አጻጻፍ ልብ ብላችሁ ያነበባችሁ ካላችሁ አንዲት ነጥብ ለመጣል
ይተረክ የነበርው ታሪክ የተኩላው እንዳልነበረ ተረዱ።
በ እኔ አስተያየት መረዋ የተጀመረው ገና ለገና እነ ክፈተው ተሸንፈው የኛ የሚሏቸው
ተመራጮች ካልተመረጡ፤ ቤተክርስቲያኑን ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ እንዳይወስዱት ለመከላከል
የተጀመረ ብሎግ እንደነበረ ነው። ጀማሪዎቹም እንደሚመስለኝ የሆለታው ሻለቃና ጡረተኛው
ዶክተር ናቸው። ተባባሪዎቹ እነ አቶ አለማየሁና የቦርዱን ወሬ አቀባይ እነ ክፈተው ለመሆናቸው
ለ አዲስ አበባው ሲኖዶስና ኢትዮጵያ ላለው አሜሪካዊ ጳጳስ የጻፉትን ደብዳቤ መልሶ ማንበቡ
ተገቢ ይማስለኛል። በዚሁም ብሎግ ሌላው ተካፋይ አሁንም በቤተክርስቲያኑ ተቀጥሮ የውስጥ
ስለላውንና ዶሴዎችን የማጥፋት ተንኮል እያደረሰ ምሆኑን አትጠራጠሩ።
በዚሁም አኳያ እንድታነቡልኝና ቤተክርስቲያናችን ከምን አይነት ችግር ውስጥ ሊያስገባ መረዋ
ሲሯሯጥ እንደነበር ለመረዳት http://www.dejeselam.org/2010/11/blog-post_27.html
November 27,2010 “የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የገንዘብና
የንብረት ቆጠራ ላይ ጥብቅ መመሪያ ሰጠ” የሚለውን በጥሞና እስተመጨረሻው አንብቡ እላለሁ።
ምዕመኑ ከልጁ አፍ አውጥቶ ለቤተክርስቲያን ከሚሰጠው ትሙኒና ድንቡል እነማን እንደሚጋሩት
ተመልከቱ። በተለይም “የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ለተለያዩ ክዋኔዎች ማስፈጸሚያ፣ የካህናት
አስተዳደር መምሪያው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በየጊዜው ለሚደረገው አቀባበል ጥንግ ድርብ
ለብሰው ለሚሰለፉ ካህናት አበል እንዲከፈል በማዘዝ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለመስቀል
ደመራ እና ለመሳሰሉት ክብረ በዓላት ጥናት ለሚያደርጉ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች(ማህበረ ቅዱሳኖች)
አበል እንዲከፈል በማዘዝ፣ ሀገረ ስብከቱ ለሽልማት እና ለመሳሰሉት አጥቢያዎች በተሰጣቸው ደረጃ
መጠን እንዲያዋጡበማዘዝ በየአቅጣጫው አቅምን የሚያዳክሙየግዳጅ አስተዋጽዖ በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ ለመፈጸም የሚገደዱበት የወጥ አሠራር ጉድለት “
“(ለገቢው) መዳከም በምክንያትነት መጠቀስ ይገባውእንደነበር አስረድተዋል፡፡ በቅጥርም ረገድ ከላይ
በሚሰጥ ትእዛዝ ብቻ ያለአቅማቸው በርካታ አገልጋይ ካህናትን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን የሚቀበሉ
አጥቢያዎች ከገቢያቸው ጋራ በማይመጣጠን አኳኋን ደመወዝ ለመክፈል መገደዳቸው፣ በዝውውርም
በኩል በገቢ አሰባሰብ እና በሌሎች የተግባር አፈጻጸማቸው መመሪያን ጠብቀው በሐቅ የሚሠሩ
የአስተዳደር ሠራተኞች ከቦታቸውእንዲነሡ እየተደረገ በምትኩ ለመጠቃቀም ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ
ሙሰኞች እንዲተኩ መደረጋቸውም በተጨማሪ መንሥዔነት መታየት እንደሚገባው ተሳታፊዎቹ
አስገንዝበዋል፡፡”
በተጨማሪም ከዚቹ ስሙኒና ድንቡል ለመካፈል፤ ሙዳይ በጎን ማን እንደሚያስቀምጥ ተረዱ
እላለሁ።
መጥፎውን ክድጉ የምንለይበት ልቦና ይሰጠን ዘንድ አምላኬን እለምናለሁ።
አሜን!.
ከዚህ በላይ ለተሰጡት አስተያየቶች እያመሰገንን፤ ተሳትፎዎቻችሁ ይቀጥሉ ዘንድ ምኞታችን ነው።
ጉድ ሳይሰሙ መስከረም አይጠባም እንዲሉ ቀስ… እያለ ጉድ ይወጣ ጀመር! ኪሮስ በሰራው ወንጀል ተጋለጠ ገባ። ነገር ግን ኪሮስ ቤተክርስቲያንን አልዘረፈም፤ አልከሰሰም፤ ውድቀት አላደረሰም።
እኛ እኮ በቤተክርስቲያን ላይ ስለሚደርስ በደል ብቻ አወራን እንጂ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውጭ ስለሚደርገው ብንጽፍማ የአካባቢው እስር ቤቶች ሞልተው በቦታ ጥበት አዳዲስ እስር ቤቶች ለመስራት መንግስት በተገደደ ነበር። “Human trafficking” ነው ያላችሁት?? ዋአ…ውው ከማን ልታጣሉን ይሆን ይኸን ምስጢር ያወጣችሁት። የተባለችው ባልቴትና ወይዘሮ/አቶ ቀጮ ይኸንን ዘመቻ ከዚህ በፊት ጀምረው ብርቱ ማስጠንቀቂያ ተስጥቷቸው ነው ደብዛቸው ጠፍቶ እስተዛሬ የቆዩት። አሁን ደግሞ አላርፍ ብለው እንደገና ከጀመሩ “አብዮት ልጇን ትበላለች እንዳለው” እንግዲህ እርስ በርሳቸው….። የቦርድ ጸኃፊ የነበረውን ኪስ አውላቂንስ ምን ልትሉት ይሆን። የሚካኤልን ማህተምና ደብዳቤ እየተጠቀመ አይደለም እንዴ ከአስር ያለነሱ ዘርማንዘሩን ያስገባው፤ እንኳን ዳላስ በሚካኤል ማህተም እየገቡ በየስቴቱ የተበተኑት ስንትና ስንት ናቸው። የቀረውንማ ቤቱ ይቁጠረው ከዚህ በላይ ትራፊኪንግ ምን ልታመጡ ነው። በአጠቃላይ ስብሰባ እንደተነገረን ከሆነ የዘረፈውን የቤተክርስቲያን ንብረት የሚታወቀውን እንኳን መልስ ቢባል እስከዛሬ እንዳልመለሰ ነው የምንሰማው። ይኸ ሁሉ ትምክህትና ድፍረት ከምን የመጣ ይመስላችኋል? ጋንግስተርስ የሚባለው ግሩፕ ስሙን ቄስ ይጥራው እንደተባለው ሲፈጽመው ለቆየው ወንጀል እስር በቂ ነው ብላችሁ ትገምታላችሁ? ኧረ የእግዚአብሔሩ ይበልጣል! በሰማይም በምድርም ክፍያው ብዙ ነውና።
የሚካኤልን ተአምር እስተዛሬ ተመልክታችኋል፤ ገና ተጀመረ እንጂ አላበቃም! ከሚካኤል የተወሰደች ሰባራ ሳንቲም ሳትቀር ከነወለዷ በእጥፍ ድርብ እንደምትመልስ እምነታችን ነው። ለሚጠራጠሩ ሁሉ የእምነታቸው ማረጋገጫው ወቅት አሁን ነውና አይናቸውን ከፍተው ይመልከቱ። የእግዚአብሔር መአት ለእንደነዚህ ላሉ አመጸኞች ነውና። የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሱ! የሚለውን 3ኛውን ትእዛዝ በማፍረስ በእግዚአብሔር ስም በሃሰት እየማሉ ህዝቡን በአንድ በኩል የእግዚአብሔርን ቤት በሌላ ሲያደኸዩ ኖሩ አሁን ደግሞ እንደእባብ በደረታቸው እየተሳቡ ቀዳዳ ባገኙበት ሁሉ ለመሽሎክ እያደቡ ስለሆነ የሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ ሁሉ ነቅታችሁ ቤተክርስቲያናችሁን ጠብቁ። እንደመዥገር ተለጥፈው ስታገኟቸው መደፍጠጥ፤ እንደእባብ ሲሽለኮለኩ ስታገኙ መደምጠጥ፤ መርዛቸውን ሲረጩ ስታገኙ የሚካኤልን ስእል እንዲመለከቱ በማድረግ በሩን ማሳየት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነውና አንዘናጋ። የእንቅልፍ ዘመን አልፏል!! እስከዛሬ ሲጠሉን ስንወዳቸው፤ ሲንቁን ስናከብራቸው፤ ሲስድቡን ስናወድሳቸው፤ ሲረግሙን ስንባርካቸው፤ ቤተክርስቲያናችንን ሲያረክሱ እያየን እያወቅን እንታገስ እያልን አሁን ያለንበት አረንቃ ደርሰናል። እኛም ቸል ብንላቸው ሚካኤል አልተዋቸውም ይህችን አመት አንዳቸውም በእግዚአብሔር የቀለዱ አያልፏትም በምንም ሆነ በምንም የእጃቸውን ዋጋ ከሚካኤል ይቀበላሉ።
ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ። መዝ 37፡9
ለአፍታ እንጂ፤ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ ስፍራውንም ብታስስ፤ አታገኘውም። መዝ 37፡10
እግዚአብሔር ጻድቅ በመሆኑ፤ መከራን ለሚያመጡባችሁ፤ መከራን ይከፍላቸዋል። 2 ተሰሎንቄ 1፡6
Post a Comment