Friday, December 31, 2010

እንኳንም ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እንደምን ሰንብታችኃል ? እንኳንም ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። ደግሞም በእርሱ ፈቃድ ደግመን በዚህ ገጽ ለመገናኘት ስለበቃን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ለእህታችን የወይዘሮ የሐረር(የኢትዮጵያ)ወርቅ ጋሻው የዳላስ ታክሲ አሽከርካሪዎችን በመደገፍ በዛሬው ምሽት ለጠሩት ሥራ ማቆም በኮሚኒቲው ልሳን እየሆነ የመጣውን ገጻቸውን  በማየት ድጋፋችሁ አይለያቸው።

ለጭቅጭም ሆነ ለሀዘን በሚል አጽራረ ቤተክርስትያን ከሆኑት ጎራ በገፃቸው የጣፉትን አንብበን ብዕራቸውን የቋጩ  አርገን ቸል ባልናቸው፤ የእናንት የሆኑትንና ለገጻችን ያቀረባችሁትን የአስተያየት ጥሁፎች ለመኮነን ከልጅነቱ ልክፍት የመታውና መዳኛ ያጣው ነፍሰ ገዳይ የሆነው ተኮላ መኮንን AKA ተኩላው በገጹ የለጠፈውን ብቻ ሳይሆን ያዘጋጀውትንም ጥሁፍ በአውደ ምህርቱ ፊት አላሰማሁም በማለት እሮሮውን ለጥፏል። እኛም ላንተ አይነቱ ቀርቶ ይህንን ያሰቡት ጭምር ንስሀ ሊገቡ ይገባል እንላለን። የእናንተን አስተያየት ባለቤትነታችሁን በመዳፈር ያለፈቃዳችሁ ከመለጠፉ አልፎ በመሀይም አእምሮው ሊኮንናችሁ ከጅሏል። በዚያው ጥሁፍም በሚገባ ያስረገጠው ቁምነገር ቢኖር ምንም የክርስትና እምነት እንደሌለውና ለእምነት ፈጽሞ ያልቆመ ፤ ጭቅጭቅን ሥራዬ ብሎ ሀይማኖታችንና ደብራችሁን እንደሚያውክ ነው።ባለፈው ስለ በትሩና አምሳለ ገ/እግዚሀብሔር ባልና ሚስት የለጠፍነው ጫፉን ብቻ እንጂ ሰለባ ከሆኑት ውስጥ አብዛኛው የኢትዮጵያ ተወላጆች ከዩጋንዳ ሀገር ይጀምራልና መቼም ይቅር የሚል ፈጣሪ በእውነት ንስሀ ገብተው ይሆን የቆረቡ?

እንግዲህ በቅዱስ ሚካኤል ደብር የቀብር ሥርዐት ላይ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የደብሩ ካህን መማጸን የቆየ ቢሆንም፤ በዚህ ሳምንት ውስጥ እነዚሁ አጽራረ ቤተክርስትያንና በትግራይ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች የተሰበሰቡት በ20 ውስጥ የሚቆጠሩት ግለሰቦች ያለ ፋይዳ ተበትኗል። ከነዚህ ውስጥ አንዱ ነፍሰ ገዳይ የሆነውና የብዙዎችን ወጣቶች ህይወት ተጠያቂ የሚባለው ተኮላ መኮንን AKA ተኩላው ነው።  ይህን ለማለት ያነሳሳን በመጀመሪያ ይኸው ግለሰብ ራሱን ኮሚኒስት አድርጎና ፈጣሪን ክዶ ለግል ጥቅሙ ብቻ እንጂ ሰብአዊነት የተለየው ሁኖ ኑሮ ዛሬ የሀይማኖት ካባ ለመልበስና የተላ ህይወቱን ለመደበቅ የሚጥር ነው።

በኢትዮጵያ ሠራዊት ውስጥ በአየር ወለድ የምድር  ስንቅ ማመላለሻ ትራንስፖርት አሽከርካሪነት ተመድቦ ሲሰራ የደርግ አስተዳደር በወቅቱ ለነበረው ሰራዊት በሙሉ የመለዮ ቀለም ሁሉ አንድ አይነት እንዲሆን ሊወስን ነው የሚል ወሬ ይሰራጫል። በወቅቱ የመልዮው ቀለም ቀይ በመሆኑ ፣ቀይ ቀለም ሁሉ የኮሚኒስት ምልክት የመሰለው ነፍሰ ገዳዩ ተኩላ ለመለዮ ቀለም ሲል 40 ከሚሆኑ የጦር አባላት በኮለኔል አለማየሁ AKA ኮለኔል አበጀ (ዲሲ ላይ የሞተ) መሪነት ከሠራዊቱ ተነጥለውና ሀገራቸውን ከድተው ሲኮበልሉ ነበር ኢሕ አፓ እጅ የወደቁት። በዚያን ጊዜም ቀደም ቀደም ማለትና እግዚሀብሔር የለም ብሎ እራሱን ቁሳዊ ያደረገው ተኩላው ደፋርና ጀግና እራሱን ማስመሰል እምነትና ተቀባይነትን ያስገኝልኛል በማለት እውቅናም ለማግኘትም ሲል መጣጥፍም ይጀምራል።

በትግራይ ነጻ አውጪና በኢሕ አፓ መካከል በተደረገው ውጊያ ኢሕ አፓ  ተሸንፎ ሽሽት ሲያደርግ አመራሩ በሁለት ይከፈላል። በፍቅሩ ታደሰና እነ ብርሃኑ ነጋ ብሎም ኢያሱ አለማየሁ በመሰሉት ከተማ እንግባና ቤተ መንግሥቱን እንያዝ በሚሉና፤ አንግባ ወጣቱንም አናስመታው ባሉት በኩል ብርሃነመስቀልና ተስፋየ ደበሳይ በአቋምይለያያሉ። በወቅቱ ከተማ ካሉትና አንግባ ያሉትን የነብርሃነመስቀል ቡድንን አንጃ በማለት ለማስመታት ከደርግ ሰራዊት የተዘረፈውን መሣሪያ በነክፍሉ ታደሰ ትእዛዝ አዲስ አበባ ላይ በብርሃነመስቀል የመኖሪያ ደጃፍ ላይ እንዲጣል ያስደርጋሉ። ይኸው ድርጊት ደርግ ዘንድ በመድረሱ ክትትል ተደርጎ አባሪው ነው በሚል ጦሱ ለተስፋዮ ደበሳይም ደርሶ የነሱ አሟሟትን ሁሉም የሚያውቀው የአዲስ አበባ ሚስጥር ነው

እንግዲህ ከታች ባሉትና ሜዳ በወጡት የተቋቋመው የዚሁ ሰራዊት ማዕከል በሆነው ሰንገዳ ሰፈር ውስጥ ማን ነው ጨካኝና ርህራዬ የሌለው ተብሎ የተመረጠው ተኮላ መኮንን AKA ተኩላው  ሲሆን እርሱ የሚመራው ጋንት 44 የተባለ አሳሪ፣ መርማሪና ነፍሰ ገዳይ ቡድን ይቋቋማል። በዚህ ጊዜ ነበር አንጃ ተብለው ቁጥራቸው የበዛ ወጣቶች ያለምንም ደንብና ሕግ ሥርዐት ያለፈቃዳቸው በሀሳብ ልዩነት ብቻ እጅና እግራቸው ታስረው በእስረኝነት በሚዘገንን ሁኔታ በተኩላው ተሳትፎና ትዕዛዝ ለመናገር በሚዘገንን ሁኔታ ምርመራ በማለት በሰይጣኑ ተኩላው መሪነት የተፈጸመባቸው።ከነዚህም ውስጥ 13 የሚሆኑት በግንቦት ወር 1978 እንደፈረንጆች አቆጣጠር እጃቸውና እግራቸው እንደታሰረ በነክፍሉ ታደሰ ትእዛዝ በጋንት 44 አዛዥና ነፍሰገዳይ ተገድለው አፈር እንኳ እንዳይለብሱ ከልክሎ ለአውሬ ተዳርገው ያለፉትን ነፍስ ተጠያቂ ነው። ለምናደርገው መረጃ አሰባሰብ በዲሲ አካባቢ ነዋሪ የሆነ ጆርጆ የሚሉት ከ13 የተኩላው ሰለባዎች ውስጥ የአንደኛው victim ወንድም ስለሆነ እንዲገናኘን በዚህ አጋጣሚ የአንባቢዎቻችንን ተሳትፎ እንጠይቃለን?

ይህ ጋንት 44 የተባለው ቡድን በመጨረሻ ከተጠያቂነት መረጃም ለመሰወር ሲባል ስሙን ወደ ጋንት አንድ (ጋንት # 1) እንዲለወጥ ተደርጓል። የነዚሁን የመጀመሪያዎቹን 13 ወጣቶችን የስም ዝርዝር በሚቀጥለው ጥሁፋችን ይዘን እንቀርባለን።

ማሳሰቢያ፡
1. ይህን ከዚህ በላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ወንጀል የምታውቁ በዚህ ሀገር በየትኛውም ግዛት ያላችሁ ሁሉ ሙሉ ስም ከcontact information ጋር አክላችሁ፣ የምታውቁትንም በአጭሩ ብቻ እንድትልኩልን ስንጠይቅ በኛ በኩል ምስጥርነቱ ተጠብቆ ለመረጃነት ለሚመለከትው መንግሥታዊ የምርመራ ክፍል ብቻ የምናቀርበው ይሆናል። የተፈጸመን ወንጀል እውቅና ያለው ሁሉ አውቆና ደብቆ መያዝ በሕግ ተጠያቂ ያደርገዋል።
2. በሚቀጥለው 30 ቀናት ውስጥ ከልብ ተጸጽቶ የእርሱ ሰላባ የሆኑትንና የዳላስን ቅዱስ ሚካኤል ደብርን ይቅርታ ካልጠየቀ፤ ቃል ሰማይና ምድርን በፈጠረ ስም ጉዳዩን ወደሚመለከተው ክፍል እናደርሳለን።
3. የኢትዮጵያን ተወላጆችን በተመለከተ በተለያየ መንገድ የምትዘግቡና የምትጥፉ ሁሉ ይህንን በተመለከተ በየአምዳችሁ እንድትዘግቡ በነዚህ 13 ነፍሳት ስም እንማጸናለን።
4. በአሁኑ ሰአት በዳላስ ውስጥ በትግሬ ነጻ አውጪ ለሚመራው የባዕድ መንግሥት 52 ገጽ አላማ ለማራመድና ቅጥረኛ በመሆን  በዳላስ ነዋሪ የኢትዮጵያ ተወላጅ በሆኑ ዜጎቻችን ላይ “አልማ“ በሚል ተቋቁሞ ዛቻና ሽብር ብሎም በጠርሙስ አስላጭሀለው የምትሉ ምናምንቴዎች ጉዳያችሁን በቅርቡ Homeland Security እንዳናስገባው ተጠንቀቁ! በደብሩ ላይም የምታደርጉትን ተንኮል በአስቸኳይ ግቱ! ዜጎቻችንን እንዲሁም እንደናንተ ያለን ባንዳ ለመመከትና ለመደምሰስ የገባነው ቃል ኪዳን አሁንም የጸና ነውና። Long Live US Marine.  

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, December 25, 2010

በመኃላችሁ blend አድርጎ

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች በእርሱ ፈቃድ መልሶ በዚህ ጦመር ለመገናኘትና በያለንበት ሆነንም ይህን ታላቅ የክርስትና   በዐል ለማክበር ጤና፣ እድሜ ከሰላማዊ ኑሮ ጋር አዋህዶ የፈቀደልን ለእርሱ ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን።አሜን።

ባለፈው ጥሁፋችን እንዳስነበብነው ሁሉ የመረዳጃ ማህበር አመራር ብቃትና ችሎታ የለሽነት አስመልክተን ያስረገጥናቸው ነጥቦች እንዳሉ ሆነው፤ በሌላ በኩል ይህንኑ የሚያሽከረክሩና ለትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪ የሆኑት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ የነሱን ተቀጣሪዎች አስርገው ለማስገባት በተጀመረው የአመራር ምርጫ ጥቆማ ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ቢፍጨረጨሩም ቅዱስ ሚካኤል እየከሰተባቸው ይገኛል። በእነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ቡድን ካዘጋጁዋቸው ግለሰቦች ውስጥ ብዙዎቹ መስፈርቱን የማያሟሉ ሲሆን፤ ተጠቋሚ ካደረጓቸው መኃል ማንኛቸውም በትምህርትም ሆነ በስራ ችሎታቸው አሊያም ስለሀይማኖቱ እውቀት የሌላቸውን ስም ይጨምራል። ጥቂቶች ከኃላቸው አክራሪና ከሀገሪቱ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም፣ ማሀበረ ቅዱሳን ለተባለው ቡድን ተቀጣሪና መልዕክተኛ ፣ የቡድን ተገዢ፣ በዘርና በጎሳ ለተቋቋመ ድርጅትና እድር ተገዢ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ካልሆነ ወይንም እኔ ከሌለሁበት የሚል ትምክህተኝነት የተወጠሩ፣ ሚስቶቻቸው የሌላ ዕምነት ተከታይና በሚስቶቻቸው ተጽዕኖ የኖሩ፣ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ከምንጣፍ ስር በመደበቅ ባለፈው ለተከሰተው ችግሮች ተጠታቂና ዕድል አግኝተው በአገለገሉበት ወቅት አድርባይና አስመሳይ እንጂ ብቃትን ያላስመዘገቡ፣ የወሰዱትን ያልመለሱ የተበደሩትን ያልከፈሉና ልቦናቸውን ሳያጸዱ እያወቁ የሚቆርቡትንና የሚያቆርቡትንም ያካትታል። ስለድፍረታቸው ከእርሱ ዋጋ የሚጠብቁ እነዚህ ግለሰቦች መካከል ስለአንዱ ግለሰብ ቀደም ብሎ ከተኔሲ ነዋሪ በቅርቡ የቀረበውን እያስታወስናችሁ፣ ከዚህ በታች የቀረበውን የሕግ መረጃ በጽሞና እንድታነቡትና የራሳችሁን ግንዛቤ እንድትወስዱ እየጋበዝን ከግለሰቡ ሰለባዎች ከሆኑት ውስጥም የኢትዮጵያ ተውላጆችም ይገኛሉ።

በ90ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ተኔሲ ግዛት ውስጥ ነዋሪ በነበረበት ወቅት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ስም የገንዘብ ዕርዳታ አዲስ ለሚቋቋም ቤተ ክርስትያን ይደረጋል። ይኸው በመልቲ ሙያ ወይንም በማጭበርበር ከነሚሽቱ የተካነው ግለስብ ዳላስ ላይ ማነጣጠር የጀመረው። በቅጥፈቱ ከማያወጣው አዘቅትና ኪሳራ ለመውጣት ሲል ዳላስ ላይ ባሉ ዘመዶች መሰላልነት ወደ ከተማችሁ ሲዘልቅ በነዚሁ ግለሰቦች አመቻቺነት በቀላሉ በመኃላችሁ blend አድርጎ በስማችሁ እየነገደና ለግል ጥቅሙ ሲል እናንተንም እየከፋፈለና እያናቆረ ሲኖር አመታትን አስቆጥሯል። በስማችሁ ያልከፈተው የግብረ-ሰናይና የሙያ ድርጅት ስሞች የበዙ ብቻ ሳይሆን በደብራችሁም ስም ጭምር ያጭበረበረበትን ከ ሰንበቴ  ገጽ ላይ ታገኙታላችሁ።


የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

Friday, December 24, 2010

የልደት በአል አደረስዎ

                እንኳን ለጌታችንና የመድሀኒታችን የኢየሱስክርስቶስን የልደት በአል አደረስዎ፤ 
   መጪውም አዲስ አመት የጤና፣ የፍሰሀና የስላም አመት ይሆንልዎ ዘንድ ምኞታችን ይድረስዎ!

Wednesday, December 22, 2010

እግዚኦ በመሀሪነትህ ይቅር ብለህ አድነን

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እግዚኦ በመሀሪነትህ ይቅር ብለህ አድነን

የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢዎች እንደምን ከርማችኃል? በፈጣሪ ጸጋ መልሰን ስለተገናኘን ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን። አሜን። ዛሬ ጠዋት መሪያችን "Obama signs bill ending 'don't ask, don't tell' ሕግ እንዲሆን። የሚያመጣው ጥቅምና ጉዳት ወደፊት የሚገመገም ቢሆንም ለሠራዊታችን አባሎች የስነ ልቦና ተጽዕኖው ይኖረው ይሆን? እኛ በአሁኑ ሰዐት በሠራዊቱ ውስጥ አገልግሎት ላይ ባንገኝም እምነታችንን በተመለከተ የምንወደው ሕግ አይደለም

ሰሞኑን በዳላስ ከተማ ነዋሪ በሆኑት ወገኖቻችን ውስጥ በሕይወት ለተለዩት ወገኖች ቤተሰቦች ፈጣሪ ሀዘነልቦናቸውን ያሳሳልን፤ የተለዩንንም በመንግሥቱ ይሰብስብልን፤ በትላንትናው ዕለት ለተለዩንም እናት እንዲሁ።

ከዳላስ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ እንደደረሰን በትላንት ዕለት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ከሳሾችም ሆነ ተወካዮቻቸው ባለመገኘታቸው ዳኛው ቅሬታቸውን መግለጻቸውን ሲገልጽልን፤ እኛም በሰሞኑ ሂደትና በካህኑ ጥያቄ ክሱን ለመተው አስበው እንደሆን ብንለው እየሳቀ ቀዳዳው ከሰልስቱ ቀድሞ ሕይወቱ ሳታልፍ ጠበቃው እንዲወክልና ከካሳ ምን ያህል የመድህን ኮሚሽኑን እንደሚበላ እያሰላ እንጂ ብሎ ከመጨረሱ በፊት እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ በማለት ንግግሩን አቋረጥነው። በእርግጥ የትምህርት ቤቱም ሆነ የመስኩ የመድህን ዋስትና ያለክርክርና ያለ ነገረ ፈጅ የሚገባውን ክፍያ የሚከፍል ሲሆን፣ ነገረ ፈጅ ከገባ ሲሶውን በነጻ እንደማካፈል ስለሆነ ይህን በመጠቆም ለባለጉዳዮቹ እንተወዋለን። ከዚሁ ጋር በማያያዝ ደብሩ በሩን ከፍቶ ሙሉ አገልግሎት የሰጠው ያለምንም ክፍያ ሲያገለግለው ላደገው ወጣት እንጂ አንዳቸውም የሟቹ ወጣት ወላጆች የቅዱስ ሚካኤል ደብር አባልነታቸውን ያልጠበቁ (የሌሉ) ከአጽራረ ቤተክርስትያን ጎራ የተሰለፉ ናቸው። የደብሩ አመራር ላሳየው ትብብር አድናቆታችንና ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን ቤተሰቡም ከዚሁ ተመክሮ ይወስዳል የሚል ግምት አለን።

በሌላ በኩል በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች እየተመራ የሚገኘው የዳላስ አካባቢ የመረዳጃ ማህበር (ኮሚኒቲ) ያለ አንዳች የቦርድ ስብስባ በጥቂት እባጭ አመራር አባላት የጎደፈና የዘቀጠ ምግባራቸውን አጋጣሚ አግኝተን እናድስ በማለት ይሁን ወይንም ወደ ነፈሰበት መዝመም አቋም አሊያም በሟችና በኮሚኒቲው እንደመቀለድና የነዋሪውንም የማስተዋል ችሎታን እንደማኮሰስ የሚደፈር ድርጊታቸውን ዛሬም ባደባባይ እየፈጸሙት ይገኛል። ይህንን ለማለት ያበቃን ለደንብና ስርዐት ሳይገዙ ፣ ሳይመክሩና ሳያማክሩ ፣ የነዋሪውን ወገኖቻችንን አሉታ ሳይጨምሩ በአንባ ገነንነትና በስሜት ተገፋፍቶ የወገንን መብት ገፎ በወገን ስም ለመነገድ የሚደረግ ሩጫ ፈጽሞ አግባብነት የሌለው ነው።


እኛ መጪው የኢትዮጵያ ቀን በማቲው ሥም ለምን ይሰየማል የሚል ጥያቄ ወይንም ተቋውሞ የለንም። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቀን ማለት ምንድን ነው? አላማውስ? በዐሉ በግለስቦች ሥም ለምን ይሰየማል? መሟላት ያለበት መስፈርት ምንድን ነው? ወዘተ…… የተባሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ማንሸርሸርና ወጥ የሆነ ሕግና ደንብ መሟላት የግድ ነው። አዎን የዚህ ታዳጊ አሟሟት ሁላችንም ነክቶናል። ነገር ግን ወጣቱ በሕይወቱ ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ያበረከተው  ወይንም ከሌላው ተነጥሎ አሊያም አወዳድሮ ይገባዋል የሚባልበት ውሳኔ በምን መንገድ ተጠንቶ እንደተመረጠ የሚደግፍ ምንም መረጃ ልንጨብጥ ቀርቶ አመራሩ የተነጋገረበት ቃለ ጉባኤ ማግኘት እንኳ አልቻልንም። ይኸው ተመሳሳይ ጥያቄ በሁሉም የዳላስ አካባቢ ነዋሪ ወገኖቻችን ውስጥ ያለና መልስ የሚገባው ነው።

አመራሩም ቀደም ባለው ጊዜ ደጋግመን ላቀረብንለት ጥያቄ ዳተኛ ቢሆንም እድሜውን አሳጠረ እንጂ አላራዘመም። በየጊዜው በህብረተሰቡ ተተፋ እንጂ ተቀባይነትን አላገኘም። በስሩ ያቀፈውም እድር እየከሰረና አባላቱ አናድስም እያለ ወጥቶ ቀረ እንጂ አላደገም። ለማዕከል ማሰሪያ ተብሎ ነጋሪት ተጎሸመ፣ ገንዘብም ተዋጣ ተባለ፤ እምነትን ከኮሚኒቲው ያጣ አመራር ቤሳ አላገኘም። እንዲያውም ባለፈው አዲስ ኮሚቴ ሲያዋቅሩ የቀድሞው ምን እንዳደረጉት ወይንም ገንዘብ ይሰብስብ አይሰብስብ ይፍረስ አይፍረስ ምንም መረጃ አላስጨበጡም። አንዳንዶቹ እንኳን ኮሚኒቲ ሊመሩ የባንክ ሂሳባቸውንም ማወራረድ የማይችሉ ናቸው ወይንም መዋያ ያጡ ጡረተኞች።

ከዚህ ወጣ ስንል ደግሞ ሰሞኑን በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ በጎደሉትና የሥራ ጊዜ በማጠናቀቅ በምትካቸው ለሚመረጡት 8 ተጠቋሚዎች የጊዜ ገደቡ የሚያልቀው የፊታችን እሁድ መሆኑን የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ገልጾልናል። መምረጥም ሆነ የመመረጡን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ እንድትሳተፉ እያስታወስን፣ የተጀመረው የደብሩ የመሻሻል እድገትና ሰላሙ እንዲጎለብትና አዲስ የሚመረጡትም በእምነትና በቅንነት የሚያገለግሉ እንዲሆኑ ሁላችንም በጸሎት እንድንተጋ ገጻችን በቅዱስ ሚካኤል ስም ይለምናል። ለምርጫ በፈቃደኝነት ከቀረቡት ውስጥ ከደረሱን ስሞች ወ/ ኤልሳ በቀለ ፤ አቶ ላቀው ደስታ፣ አብርሃም አሰፋ፣ ሰሎሞን ጋዲሳ፣ ዮሴፍ ረታ፣ ሙሉጌታ ወልደ ሚካኤል፣ ተስፉ በላቸው፤ ከፍተኛ ድምጽ ያገኛሉ ተብለው ይጠበቃሉ። ይሁን እንጂ እርሱ ቅዱስ ሚካኤል የሚበጁትን ይምረጥ። አሜን።

የእርሶስ አስተያየት ምን ይሆን? መጣጥፋችሁ ይቀጥል።

Sunday, December 19, 2010

በትምህርት ተነክቶ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


በቅርብ የምናውቀው ወዳጃችን ብዙም ለሀይማኖት ግድ የሌለው ነገር ግን የሚያውቀው ወዳጁ እናት አርፈው ለቀብር ስርዐት ሲል ወደ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ጎራ ብሎ በነበረበት ትምህርት ተነክቶ እንደእርሳቸው ሳልሆን በፊት ወይንም እንደጨቅላው ሳልቀደም ዛሬውኑ ንስሀ ገብቻለሁ ሲል በስልክ አጫውቶናል። እኛም ለጨቅላውም ሆነ ለአዛውንቷ ወይዘሮ የመንግስቱ ወራሽ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን እንላለን።

የዕለቱን ትምህርት ያስተማሩት አባት ሁላችሁንም እንዳላቀሱና እንድትገነዘቡ ማስጨበጣቸውን ከሚካኤል ሰይፍ የደረሰንም ዜና ያረጋግጣል። እንግዲህ ልብ ያለው ልብ ይበል እነዚህ እርሳቸው በህልማቸው ያዩትን እኛን ተንባይ ባያሰኘንም ቀደም ብለን ቤታችሁን ከተኩላና እባቦች ጠብቁ ብለናል። ከነዚህ አጽራረ ቤተክርስትያን ወጥመድ አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ ፣ በስህተትም ሆነ በድፍረት የገባችሁ ከመጥፎ መንገድ ተመልሳችሁ ንስሐ ወስዳችሁ ከአምላካችሁና ከፈጣሪያችሁን እንድትታረቁልን ካህኑ በፈተቱበት ሰውነት መስቀሉን ይዘውና ተንበርክከው በመለመን ቃል አስገብተዋችኃል። እኛም ከዚህ በላይ የምንጨምረው የለንም። እንግዲህ ለካሳ የከሰሰችውም ባል ሀዘንተኛ ሆኖ በተቀመጠበት፣ የተቀሩትም ከሳሾችና አስከሳሾች ባሉበት ይህንን ያደረገ አምላክ አንበሳውን እንዳይለቅባቸው ሲል ሀዘኑን ገልጾልናል።

ከዚህ ጋር አብሮ የደረሰን ካስከሳሾች አካባቢ በቅርቡ በሌላው የደብሩ ተመራጭ ላይ በገጻቸው ሊለጥፉት ያቀዱትን የሀሰት ወሬ ነው። እኛም ንጹኃን ሲነኩ ዝም ማለት መልካም አይመስለንምና እንደ ካህኑ እነዚህ እንግዲህ እባቦች  ያሏቸው ናቸውና መራራታችን በነፍሳችን ያስጠይቀናል። በእጃችን ያሉ እልቀ መሳፍርት መረጃ አለንና እንደ ቀድሞው ቆንጠጥ ለቀቅ አናደርግም።በጥርሳችን ከነከስን አብረን እንወድቃታለንን እንጂ አንላቀቅም። ሀይማኖታችንን ስንጠብቅ ቤተክርስትያናችንን መጠበቅ አለብን። ቤተክርስትያናችንን ስንጠብቅ ደግሞ አገልጋዮቻችንን መጠበቅ አለብን። ይህንን ስንል ደግሞ collateral damage ሰለባ ሆነው የሚወድቁትን ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ከግምት በማስገባትና ፈጣሪን በመፍራት ነው። ቁጥር 44 መሪ የነበርከውና የንጹሀን ደም በእጅህ ያለህ ስለፈጣሪ ብለህ ተወን አትነካካን፣ እኛ እዚህ ሀገር የገባነው እንዳንተ ቀዩ መሎዮዬ ሊለወጥብኝ ነው ብለን ሀገራችንንና የገባነውን ቃል ሰብረን ከሰራዊቱ አልከዳንም፣ ማንኛውንም የሰው ዘር አንግተን አላሰቃየንም ፣ ለሕይወታቸውም ተጠያቂ አይደለንም፣ ወዘተ………ወይንም እንደቀዳዳው አልቀደድንም፣ ከኃላ ሆነን ሌላው የኛን dirty ስራ ይስራልን አላልንም፣ በንዋይ አልተመካንም፣ ዝምብ እሽ ያላንን ካራቲስት አይደለንም፤ የትም ይሁን የት እያንዳንዷን ሳንቲም በጭቦ አልያዝንም፣ ነገር ግን የትኛውን ክር እንደምንስበው ስለምናውቅ domino effect  ምን እንደሚሆን ከዚሁ በማስላት ስለሆነ የሚሻለው ወደ ፈጣሪ መንገድ ሁላችንም መመለስ እንጂ ቀናተኛ አምላክን መፈታተኑ ስህተት ነው። በአይናችን ውስጥ ያለውን ግንድ መጀመሪያ እናውጣ ወይንም እስቲ ማናችን ነን ንጹህ የመጀመሪያውን ድንጋይ የምንወረውር? ምናምንቴ ከመሆን ይሰውረን። አሜን።

ሌላው የተጠቆምነው ሌላ የፖለቲካ ገጽ አለ። ነገር ግን ስለ ደብራችሁ የተጣፈውን ለማየት http://www.ethiodallas.blogspot.com/  ይህንን በመጫን ወይንም ኮፒ በማድረግ December ያወጡትን ይመልከቱላቸው የረባ አስተያየት ይዟልና። ሰንበቴንም ይመልከቱ።http://www.senbete.blogspot.com/

በተረፈ አዲስ መማክርት የምትመርጧቸውን ካሉት ጋር ተመሳስለው በሰላም የተጀመረውን እድገት ይቀጥላሉ የምትሏቸውን እንጂ እናንተን መልሰው ወደ አለፈው ወይንም ወደ ባሰው የሚስቧችሁ እንዳይመጡ ጸልዩ። ምንም ሆነ ማን አምሃ የሚል ስም ከያዘ እባብ ራቁሌላው ሁለት ፀጉር ዕድሜ ይዘው ተርማቸውን ሳይጨርሱ የለቀቁና የነርሱ ወዳጆችን እንዳትጠቁሙ ፣ ከዚህ በፊት ገጻችን የኮነናቸውን ወደኃላ ሂዳችሁ ተመልከቱ ሊያጠፏችሁ እንጂ አይሆኗችሁምና ተጠንቀቁ። ሌላው መለከት ወደተባለው ገጽ በመግባት ጸረ ሀይማኖታችሁና አጽራረ ቤተክርስትያን የሆኑት ተመራርጠው ያቋቋሙት ኮሚቴ ስም ዝርዝር አለና ፈጽማችሁ የነዚህን ግለሰቦች ስም እንዳታስገቡ በሚካኤል ስም እንጠይቃለንንስሀ ወስደው ወደ ምንጩ መግባት ተስኗቸዋልና

ባለፈው የቴኔሲው ብዙነህ የጀመሩት ዘግይቷልና የእርሳቸው ሳያልቅ በእጃችን ያለውን ማስረጃ መልቀቅ አልፈለግንምና አይጥፉብን እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?      

Friday, December 17, 2010

ማን ያውራ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

የሚቀጥለውን ጥሁፍ የላኩልንን የተኔሲው ብዙነህ ከልብ እያመሰገንን ጥሁፋቸው ይቀጥል እንላለን። እኛም እንዳለ ሁሉንም አውጥተነዋል። እንደዚህ አይነት ግለሰቦች የጎደፈ ታሪካቸውን መንካት ያልፈለግነውን ያህል መሰሪ ተግባራቸውን  ቸል ማለት አይገባም። ማን ያውራ? የነበረ እንዲሉ የሚቀጥለውን የምስክርነት ጥሁፍ ስናካፍላችሁ የታዳጊው የዳላሱ ጨቅላ ማቲዎስ ኃይሌ ድንገትኛ ዜና እረፍት በጣሙን የተነካን  መሆናችንን እንደዚሁም መጽናናትን ፈጣሪያችን ለቤተሰቡ  ይስጥልን ዘንድ እንለምናለን።
ሰንበቴ አስቸኳይ ማሳሰቢያ የለጠፈውን ይመልከቱ።

Anonymous Anonymous said...
ጋሻ ኢንሹራንስ ማናጀር ተፌ አሰፋ የቱ ናቸው ወይስ ሻለቃ ተፈራ ወርቅ አሰፋ ስማቸውን ቀይረው በተፌ ተመዝግበው ነው? አቶ በትሩ ገብረእግዚአብሔር ምንሰርተው ይሆን ለዳላስ ኢትዮጵያውያን? እረ እነዚህ ምርጫው ውስጥ እንዳይጠልቁ አደራ። የሚካኤል ሂሮ ሆነው ሌላ መቶሽህ እንዳይካፈሉ። አቶ በትሩ ሰዎችን ኢንሹራንስ ኤጀንትነት ያሰማሩና ከዚህ በታች ሴፍኮን እንደ ተጠቀሙበት እሳቸው ተሸላሚ የመለመሉት እንደ ሚስተር ተፌ አሸላሚና ገንዘቡን ተቃራጭ ሚስተር ተፌም ይሆናሉ። አይ በትሩ ቴኒሲ አክስረውን ቴክሳስን እያሙዋጠጡ ነው። ከመንፍስ ብዙነህ። Releases & ArchivesPress KitExecutive ProfilesConsumer TipsIndustry LinksMedia Contacts Safeco Media Relations Paul Hollie, 206-473-5745 pauhol@safeco.com Safeco Announces 34 Foundation Grants and 30 Community Hero Awards Totaling Nearly $2.3 Million Dollars Speaking about the Community Hero Awards, Anderson said, “Safeco knows every neighborhood has heroes and saw this opportunity to partner with our agents to identify individuals special to them and their home towns. Safeco’s Community Hero Awards are intended to recognize and celebrate those individuals who make a positive difference in their community and inspire others to do the same.” SEATTLE-(Feb. 14, 2008) - Safeco (NYSE: SAF) and the Safeco Insurance Foundation today jointly announced the recipients of two separate giving programs: the Safeco Insurance Foundation Community Grants and Safeco Insurance Community Hero Awards. Betru Gebregziabher of Dallas, Texas for his work with Mutual Assistance Association for the Ethiopian Community, nominated by Tefe Assefa, Manger Gasha Insurance Agency. Thirty-five non-profit organizations in six locations (Atlanta, Dallas, Indianapolis, Seattle/Puget Sound, Southern California and Spokane) received Community Grants from the Safeco Insurance Foundation, totaling $1,791,000. Awarded by Safeco Insurance through an agent driven program, the company also announced 30 Community Hero Awards. In this signature program, Safeco agents nominated individuals from across the country who demonstrate a tireless commitment to strengthening and enriching their communities. Each “hero” was presented with a $15,000 check for the non-profit organization at which they work or volunteer. In total, this program contributed $500,000 to various organizations nationwide.
December 16, 2010 11:09 PM

Thursday, December 16, 2010

የተጀመረው መሻሻል ከግቡ እንዲደርስ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


የተከበራችሁ ውድ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁልን? በእርሱ ፈቃድ ፣ ሁሉን አስተካክሎና ደግሞ በዚች ጦማር ደግመን ለመገናኘት ስለበቃን ለፈጠረን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ከምንግዜውም በላይ የበለጠ ተሳትፎ በገጻችን ላደረጋችሁትና ለሰጣችሁን አስተያየት ምስጋናችን የላቀ ነው። እንድናስተላልፍላችሁ የሰጣችሁን ምክር፣ ጥቅስ ፣  ማበረታቻዎች፣ ድጋፎች በሙሉ ለሚመለከተው ስናስተላልፍ፤ በሌላ በኩል ሀይማኖቱ የሚያዘው ስርዐት እንዲጠበቅ አመራሩ ከአባቶች ጋር በመመካከር የወሰዱትንም እርምጃ በናንተ በኩል ከፍተኛ ድጋፍና ተቀባይነት በማግኘቱ ይህንኑ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲደርስ የበኩላችንን እያደረግን እንገኛለን።

በሌላ በኩል ሰሞኑን ገጻችን ካወጣው መጣጥፍና ገጠመኝ ሁላችንም የግላችንን ግንዛቤ ወስደናል። በትውልድ ሀገራችንም ከተለያዩ ሀይማኖት ተወክለው በሀገሪቱ ውስጥ ይቅርታን ለማምጣትና ወደፊት ለመጓዝ ብሎም የመዘከሪያ ዕለት በመሰየም “የይሁንታ“ እየተዘጋጁ በሚገኙበት ተግባር ሁላችንም ከጎናቸው መቆም ይጠበቅብናል። የሀይማኖት አባቶችም ከዚህ መድረክ ተለምዶ ወደፊትም ጣልቃ ገብነታቸው ይቀጥል እንላለን። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደብራችሁ ሰሞኑን የሀይማኖት አባቶች ያሳለፉትን ተገቢ አስተያየት በመቀበል አስተዳደሩ የወሰደው ውሳኔ አማራጭ የሌለውና ተገቢ ነው በማለት አምዳችን በሙሉ ልብ ተቀብሎታል። አባል ምዕመናንም ከምትልኩልንና ከጎናችሁ ካሉት ምንጮቻችን  ከመረዳታችንም በላይ ይህ ውሳኔ የአባቶችንም ይሁንታ የጨመረ ነው። እኛ በምዕራቡ ዐለም ያለን ያመለካከታችንን አድማስ በማስፋት በትውልድ ሀገራችን ከሚተገበረው ተመክሮ መውሰድና የተሻለ አቀራረብ ማድረግ ይገባናል።

በሌላ በኩል ሰንበቴ እየተባለ የሚታወቀውና ከኛ ገጽ ቀደምተኛ የነበረው ጠፍቶ ከከረመበት  የሚላመጥ ፍሬ የጣፈው አለውና ጎራ ብላችሁ እንድታነቡት እየጋበዝን የነርሱ ጥሁፎቻቸው አይራቁን ነው የምንለው። እንደዚሁም የናንተው ኮሚኒቲ ልሳን የሆነው የዲኤፍ ደብልዮ ብሎግ አዲስ ያወጡትም አላቸውና አንብቡላቸው።

አሁን ያሉት የደብሩ አመራር አባላት በአጭር ጊዜ ውስጥ እያስመዘገቡ ያሉት ተግባራት መመስገን ብቻ ሳይሆን መኩሪያዎቻችሁ ናቸው።በተለያየ ደረጃና ስፍራ ላይ በተለያየ ጥበብ ተደራጅተው የመጡትን አጽራረ ቤተክርስትያን ድባቅ እያስገባችሁ የምትገኙና የነርሱን አካሄድ የተረዳችሁ ሁሉ ህብረታችሁንና አንድነታችሁን በማጠናከር የተጀመረው የደብራችሁ የለውጥ እድገትና አገልግሎት ላፍታ እንኳን እንዳይስተጓጎል ከዚሁ በመንጠንቀቅና በማስተውስል የምትመርጧቸውን የአመራር አባላት በንጹህ ልቦና እንድታደርጉት በጸሎት መትጋት አለባችሁ። ይህንን ለማለት ያበቃን በተለይ በ2009 ያገለገለው የአመራር ቡድን ከ1 እስከ 10 ደረጃ ስጡት ብንባልና 10 ከፍተኛ ውጤት ቢሆን የምንሰጠው 3 ነው። አለ ወይንም ሰራ የምንለው የለንምና። ተከፋፍሎ ያከፋፈለ ፣ የስድብና የጥላቻ ፣ የጎሰኝነትና የትምክህተኝነት ብቻ ሳይሆን የመተዳደሪያው ደንብ ይከበር በሚሉና የተሻለ የትምህርት ዕውቀት ባላቸው ጥቂት አባሎችና ትምህርቱም ሆነ እውቀታቸው የማይመጣጠንና ሀቅን መዋጥ የተሳናቸው ወገን መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነበር። 

በ2010 የተመረጡትና እያገለገሉ ያሉት አመራሮች በውስጣቸው ካቀፏቸው የቀድሞ አባላት የተረፉት ቢኖሩ የተመረጡበትን ሀላፊነት እንደዚሁም በመቅደሱ ቆመው የገቡትን ቃል አፍርሰው ተንጠባጠቡ። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት የሌላቸውና ያንኑ ጸጸት ለመሸፈን ለአጽራረ ቤተክርስትያን መሳሪያ በመሆናቸው ብናዝንም ከድርጊታቸው ተቆጥበው ቅዱስ ሚካኤልን አታስቀይሙ እንላለን። አሁን ያሉትም አመራሮች በአሁኑ ሰአት አንድ አይነት አቋም ይዘው በአጭር ጊዜ እያስመዘገቡ ያሉት ውጤት ከፍተኛ በመሆኑ፤ አዲስ የምትመርጧቸው ከነዚሁ ከሚቀሩት አመራሮች ጋር በዕውቀት ፣ በትምህርትና በእምነት የሚመስሉ ሲሆን የለጠቁ ቢሆን የተጀመረው ስራ ሁሉ ሳይስተጓጎል ግቡን ይመታል። የሚቀጥለውም 2011 አመት በአመራሩ መካከል በመከባበርና በመተሳሰብ መልካም ፍሬን ለማየት እንበቃለን።

ጥቂት አጽራረ ቤተክርስትያን የሆኑ ካሁኑ የነሱን ተቀጣሪዎች ለማስመረጥ እየተሯሯጡ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁሟሉ። እኛም እነዚህ ግለሰቦች ማንነት በሚገባ መረጃዎቻችንን የሰበሰብን ስለሆነ ፣ ጥቆማው እንደተጠናቀቀ ለናንተ የምንገልጥ መሆኑን ከዚሁ እንገልጣለን። ከብዙ አቅጣጫ በተለያየ ጥበብና ስልት አልፎ በአለም ፍርድ ቤት ሳይቀር ደብራችሁን ለመቀማት ካልሆነም ለማዘጋት ያልተፈነቀለ ድንጋይ ያልተወረወረ ጦር ፣ ያልተቆፈረ ጉርጓድ ፣ ያልተዋቀረ ኮሚቴ፣ ያልተደጎመ ንዋይ፣ ያልተደረገ ቅስቀሳና ዘመቻ የለም። ቅዱስ ሚካኤል ግን ከውስጥም ሆነ ከውጪ የተነሱትን እንሒን አጽራረ ቤተክርስትያን በየወቅቱ እያጸዳቸው እንዲሁም ክብሩንና ሀይሉን እያስመሰከረባቸው ይገኛልና ከብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።


እናንተም መራጮች የደብራችሁ ህልውናን ለመጠበቅና የተጀመረው መሻሻል ከግቡ እንዲደርስ አጥብቃችሁ መጸለይ ይገባችኃል። ከላይ እንዳስቀመጥነው ብቁ ያላችኃቸውን ግለሰቦች ስትጠቁሙም ሆነ ስትመርጡ ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ መሆን ይገባል። አንዳንድ በቤተሰብ፣ በጓደኝነት፣ በማህበር፣ በዝምድና፣ በጋብቻ፣በሰፈር፣ በሀገር ፣ በዘር፣ በጎሳና በመሳሰሉት ተመስጦ ወይንም ተገፍቶ የሚደረግ ድምጽ ፀፀት ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪም ያጋጫል። በተለይም እልህ ቂም በቀል ይዞ ምርጫ ማድረግ ከመንፈሳዊ መንገድ ፈጽሞ የራቀ ስለሆነ አስቀድሞ ንስሀ ወስዶ በንጹህ ልቦና በሱ ተመርቶ መከወን የክርስትና ግዴታ ነው። ይህንን ለመተግበር እግዚሀብሔር ያብቃችሁ። አሜን።

Tuesday, December 14, 2010

በጠዋቱ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


እንደምን አደራችሁ? የዕለት ተግባራችንን እያከናወንን ባለንበት ቢሮ አልፎ አልፎ ከስራ ሰአታችን እየተሻማን ከስራችን ውጪ  ሌላ ነገር መዳሰሳችን የተለመደ ነው። በዛሬው  ዕለት ግን ከወትሮ የሚለየው  የቀዳነው ቡና ቀዝቅዞ የምንመራው ስብሰባ በኛ አለመገኘት በመዠግየቱ ከስብሰባው  ታዳሚዎች አንዱ ወደ ቢሮአችን ዘልቆ በመግባቱ ነበር ሳናውቀው በፊታችን ይወርድ ከነበረው እንባ የነቃነው። በየዕለቱ ጠዋት የምናካሂደውን ስብሰባ ከጨረስን በኃላ ነው   ተመልሰን ገጠመኛችንን ከናንተ ጋር እንካፈለው ለፈቀደ አምላክ ምስጋና ይግባው ። አሜን።

እናንተም  የሚቀጥለውን በመጫን ወይንም  ኮፒ በማድረግ ወደ ድኅረ ገጹ  በመግባት ሙሉውን እንድታነቡት እንጋብዛችኃለን።
http://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article&id=4371:2010-12-12-08-21-48&catid=98:2009-11-13-13-41-10&Itemid=617


እርሶስ ምን ይላሉ?

Monday, December 13, 2010

ሁሉም ሀጢያትን ሰርተዋልና

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ምንም እርቀን ብንኖርም የናንተን ሀዘንም ሆነ ደስታችሁን ከመካፈል አላሰለስንም። ያጠፉ ቢኖሩ እንዲመከሩ ፣ የተሳሳቱም ቢኖር እንዲመለሱ ከመጠቆም አናቋርጥም። እንደመልካችን ሁሉ አስተሳሰባችን ይለያያል። በምንወስደውም እርምጃ ከተጠያቂነት አናመልጥም። ምንም እንኳ ከሰው ስህተት ከብረትም ዝገት አይጠፋም ቢባል የሕዝብን አደራ ተቀብለው በአመራር ላይ የሚቀመጡ ፤ ከሚጠበቅባቸው ዋነኛውና ተቀዳሚ መመዘኛ የስነ-ምግባር ሞዴልነታቸው ነው።

በምንኖርበት ሀገር ባሕሉም ሆነ ህጉ ከትውልድ ሀገራችን ጋር በጣሙን የተለየ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው። በተለያየ የዜና ማሰራጫ በየጊዜው እንደሚዘገበው  ኃይልና ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ከሕግ በላይ ራሳቸውን ያደረጉ እስኪከስትባቸው እንጂ ፣በለስ የቀናው ሲያመልጥ ሌላው ደግሞ ሕጉ ሲጎብጥለት እናያለን። ለዚሁም ደግሞ  ቀደም ያለ ስነ-ምግባራቸውን ከግምት በማስገባት አስተያየት ይደረግላቸዋል። ከትንሽ ከተማ እስከ ሀገር መሪነት ፣ ከተራ የሀይማኖት ተማሪ እስከ ከፍተኛ የክህነት ስልጣን፣ ከተቆጣጣሪ እስከ ዋናው የድርጅት መሪ እንደዚሁም የስራ ጠባያቸው ከሕብረተሰቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ሁሉ ከስህተት ለመጠንቀቅና የሚያደርጓቸውን ተግባራት ሁሉ የመጨረሻ ነጥባቸውን ከወዲሁ ማጤን ብልህነት ነው።

አንዳንድ ግልሰቦች ወይንም ምንጮች በህግ የተያዘን ጉዳይና እልባት ባልተደረሰበት የራሳቸውን እንዲሆን የሚመኙትን ብቻ አስተያየት በመስጠት የሌላውን አመለካከት ለሀሰት ግምገማ ሲዳርጉ በየጊዜው ተመልክተናል።በዚህ በምድረ አሜሪካ “innocent until proven guilty “  Constitution of the United States እንደተቀመጠው ሁሉ ይህንን በመዘንጋትም ሆነ አውቀው የግል አቋማቸውን ሲያንጸባርቁ ይታያሉ። ይህ በህግ የተያዘን ጉዳይ የራሱን Legal process ሳይጨርስ በግልጽ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም እንላለን። ይህ አሜሪካ ሆነና moral and ethical questions ከተለያየ viewpoint እየተገመገመና እየተሰነጣጠቀ በተለያየ መልኩ ቅርሱንና ይዘቱን ከዘመን ወደ ዘመን እየለዋወጠ ይገኛል። ነገርን ከስሩ ውኃን ከምንጩ እንዲሉ ጫፍ ይዞ መሮጥ ከግምት ይጥላልና። ይህን moral and ethical questions ጫንቃቸው መሸከም ያቃታቸው ራሳቸውን ከሀላፊነት ማግለልና ከሰፋ ጸጸት መዳን ይገባቸዋል።ነገር ግን ወደ ቃሉ ስንመለከት “ ሁሉም ሀጢያትን ሰርተዋልና……” ስለዚህ የጥፋትና የሀጢያት ትንሽ የለውምሁላችንም ሀጢያትን ሰርተናልናየይቅርታ አምላክ ግን ንስሀችንን ይቀበልልን። የድክመት ስህተታችን ለሌላው መውደቂያ አያድርግብንምንም ወርቅ በእሳት ቢፈተንም ፤ በቤተክርስትያን አገልጋዮች ላይና በቤተክርስትያን ላይ ፈተናው ይበዛል። አማኞችም በጾምና በጸሎት ይበልጡን በመጠንከር ፈተናዎችን ሁሉ በማሸነፍና ለመንግስቱ ወራሽነት ለመብቃት እግዚሀብሔር የበቃችሁ ያድርጋችሁ።

Sunday, December 12, 2010

ቅጥረኝነት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


እኛ የምንለው ምንም የለንም ነገርን ሁሉ የሚያስተካክል እግዚሀብሔር የተናቁትን የሚያስከብር፣ የወደቁትን የሚያነሳ፣የጠገበ የሚያስተነፍስ፣የተራበ የሚያበላ፣ወዘተ……ዛሬም ፈቃዱ ሆኖ መልሶ በዚች ገጽ ዳግመኛ በመገናኘታችን አሁንም ሆነ ወደፊት ክብርና ምስጋና ለፈጣሪያችን ይሁን። አሜን።

የዛሬውን ጥሁፋችን መነሻ ያደረገው የDFW ETHIOPIAN COMMUNITY  http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ ገጽ በሆነው ላይ ብዙ መረጃዎች ተመልክተናል። በግል ጥቅም የታወሩና የሕብረተሰቡ መዥገር እነማን እንደሆኑ በሚገባ ተቀምጦ ይገኛልእንግዲህ ጨው ላራስህ ስትል ጣፍጥ ነውና ዳላሶች እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦችን ከመካከላችሁ ማጽዳት ቅድሚያ የምትሰጡትና የሚያስፈልገውን እርምጃ መከወን ግዴታችሁ ነው
እንዚህም ግለሰቦች ምን ያህል ለትግሬ ነጻ አውጪ ለሚመራው ሁሉ ቅጥረኝነት ከዚህ በላይ ማስረጃዎች ለምትሹ ከተኛችሁበት መንቃት ያቃታችሁ ብቻ ናችሁ። እኛም በእጃችን በየጊዜው የሚገቡትን መረጃዎች ወደሚመለከታችቸው አካላት ከማካፈል ወደኃላ ባንልም፣ እንደአስፈላጊነቱ ለናንተም እንዲደርስ በገጻችን የምንለጥፍ መሆናችንን ከዚሁ እንጠቁማለን።

ሌላው በከተማችሁ ተከብሮ የጋሼና የአቶ ስም ተሰጥቶት በቸርነቱም ዝና የሚዳረግ በኑሮውም የተባረከ መስሎ ሲኖር አመታትን ያስቆጠረ ግለሰብ ከበስተዋላ ምን እንዳደናቀፈው ባናውቅም ወይም በውስጡ አብሮት የኖረ አግርሽቶበት ይሁን አሊያም ከቀን በኃላ ያገኘው መንፈስ በስህተት ጎዳና እየነዳው ይገኛል። በገዛ እራሱም ኃይል ተመጻድቆ ከታጋሹ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ጋር እየተላጋ ይገኛል። ህሊናውን በማሳሳቱም ግንዛቤውንና ማስታወሉንም አጥቷል።

በምሳሌ ከሚጠቀሱት የናይጀሪያና የፓኪስታን ሰዎች ጸባይ አንዱ ለንዋይ ሲሉ የወለዷዋቸውን ልጆች ሳይቀር የሚለውጡ እንደሚባለው ሁሉ አቻ የሚቆጠር የሆነ፤ እንደሚባለው የቀድሞ ወዳጁን ልጅ ባደራ እንዲያስተምር ወስዶ ያገባ፣ ቆይቶም በሚስቱ ላይ ጥቁር አሜሪካዊት የሆነች ደርቦ በመያዙ በዚያም ቢፋታ ሀብት እንዳያክፍል ሚስቱን በቄስ ይዞና ተማልዶ የቆረበ ፣ ለአሜሪካዊቷም ወዳጁ በገንዘብ የሸነገለ፣ ከዚሁ ትዳር ያፈራት ልጁ መጸነሷ ሲነገረው እንዴት ያውም ከጥቁር ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ የግድ ማስወረድና ምናምን ሲል በገዛ ልጁ አንደበት አንተስ በእናቴ ላይ ጥቁር ደርበህ አልነበርክምን? ጥቁርም ሰው ነው የጸነስኩትም ሰው ነውና አይሆንም በማለቷ ሀቅን በግድ ያስዋጠችው፣ ከሌላ የሚወልዳትን ትልቋን ልጁንም ያልተንከባከበና የመኖሪያ ፈቃድ እክል ያላትንና መጥቀስ በማንሻው የኑሮ ህይወት የምትገኘውን እንደመደገፍ፣አዲስ አበባ ላይ ያለመው ፕሮጄክቱ ይሳካለት ዘንድ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤልን ደብር በአባ ጳውሎስ ስር ለማድረግ ለዚሁም ውለታው የሚያስፈልገውን ትብብር ከትግሬ ነጻ አውጪ ከሚመራው መንግስት ለማግኘት ደብራችሁን ለሚከሱት ሁሉ የግንባር ቀደም ተባባሪና አስተባባሪ የሆነ፣ እነዚሁ ከሳሾች የሆኑ ጥቂት ግለሰቦች በትግሬ ነጻ አውጪ ከሚመሩትና በውጪ አለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ተወላጆች የአንድነት መድረኮች ሁሉ ያሰማሯቸው ለጥቅም ያደሩ ቅጥረኞች ለጠሩት ስብሰባ መተዳደሪያው የሆነውን የዳንስ ቤት ያመቻቸ አንዱ ጠላታችሁ ነው።

ይህ ዳንስ ቤት ለትግሬ ነጻ አውጪ አጀንዳ መማከሪያ በመሆን ለዳላስና አካባቢው የመረዳጃ ማህበር ስም የህገወጥ ስብስብ ማድረጊያና ለህብረተሰቡ አደጋኛ ዱለታ መድረክ በመሆን ማገልገል ከጀመረ አመታት እያስቆጠረ ነው። አሁን ደግሞ ሀይማኖት የሌላቸው ስለ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በማለት በየዳንኪራው ቤት መገናኘትና መዶለት መልሱን ለአንባቢያን እንተወዋለን
ይልቁንስ ባለዳንኪራው ቤት ባለቤት ቤቱን ወንጀል ለሰሩ ወይንም ደብር ለሚበጠብጡ ከማድረግ ይልቅ ከፈተኛ እርዳታን ለሚሹ ወገኖች ሰብአዊ እርዳታ የሚያገኙበት መድረክ ቢያደርገው

ሌላው ይኸው ባለዳንኪራው ቤት ግለሰብ ስሙንም ለመጥራት በድርጊቱ ምክንያት ስለተፀየፍነው ብናልፈውም፤ በሌሎች እንዳደረገው እርሱም በሌላ በኩል እየከፈለው ያለውን ልናካፍላችሁ እንወዳለን። በከተማችሁ በመልቲና በቀጣፊነቱ የሚታወቀው ሙላው aka ቀዳዳው የተባለውን ያለእኩያው ጓደኛው አድርጎ ጆሮውን ስለሚያቀላው፣ የአዲስ አበባውን ችግሩን በተስፋ አስደግፎ በsouth Dallas አዲስ በጀመረው ፕሮጀክት ማን አራጅና ማን ታራጅ እንደሚሆን ለማወቅ የጓጓው የዳላሱ ምንጫችን አካፍሎናል። እንደዚሁም ቀዳዳው የግል ጠበቃና ከዳኝነት በስነምግባር የተወገደውን በማምጣት ደብሩን ለሚታናኮሉ ተቀጥሮ ከሚያገኘው የጥብቅና ገቢ ሁሉ ኮሚሽን እንደሚከፈለው ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል። ባለዳንኪራ ቤቱም ጓደኛ ያደረገው ቀዳዳው በእጅ አዙር በገንዘብ እየጠበጠበው ይገኛል።

ከዚህ በፊት እኛም ሆንን ሌሎች በኢትዮጵያን ስም በዳላስና ፎርትዎርዝ አካባቢ የተቋቋመው መረዳጃ ማህበር በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች እጅ መውደቁን ስንገልጽ ቆይተናል። እድር የተባለውም ዛሬ መስራች የነበሩት አባላቱ ሳይቀር እውስጡ ያለውን ምዝበራና አጸያፊ ድርጊቶችን በማየት ላለማደስ በመወሰናቸው የአባላቱ ቁጥር እየመነመነ ይገኛል። ዕድሜውም በወራት ውስጥ እንደሚቆጠር ያገኘነው መረጃ ሲጠቁም ፣ በየሳምንቱ በእድሩ ስም የሚደረገው የስልክ ጥሪ እንደሰለቻቸው የሚናገሩ እንዳሉ ተነግሮናል። ከዚሁ ሳንርቅ የሬድዮ አገልግሎትም በዕሁድ አቅርቦቱ ካስታወቀው ውስጥ የደብሩ በጥባጮችን ጥሪ በዳንኪራ ቤትና የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞችን የበአል ጥሪን ያሰሙት የነሱ ቅጥረኛ ስለሆነ የነሱን ስራና የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያሳድድ በመሆኑ ፤ የሚስቱ ስራ ማጣትና የሱዋን 401ኬ የተባለውን የሂሳብ ቁጥራን እንዴት እንደሚበላ እንጂ ለህብረተሰቡ የሚረባ አንድም የለው ሲሉ ያዳመጡት ምንጮቻችን አካፍለውናል።

እኛም ጋሼ ተኮላ aka ተኩላውን ካስደሰተ ብለን የሚቀጥለውን ለናንተም ጭምር እንጋብዛለንና ካላዩት ይመልከቱት።
 http://www.youtube.com/watch?v=TWVSisi3N20&feature=player_embedded

እርሶስ ምን ይላሉ?

Tuesday, December 7, 2010

የመላእክትን ዝማሬ ያሰማልን!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የመላእክትን ዝማሬ ያሰማልን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር በጋርላንድ ከተማ በቴክሳስ ግዛት እያስመዝገበ ያለው መልካም አገልግሎቶች ከዳላስ አካባቢ አልፎ በሌሎች ግዛቶች እየተደነቀለት ይገኛል። የተወደዳችሁ የገጻችን አንባቢያን እንደምን ሰነበታችሁ? በሰላም ጠብቆና ተንከባክቦ ዳግመኛ በዚህ ጦመር እንድንገናኝ ፈቃዱ ለሆነው ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።

ደብራችሁ ተገኝተን አብረን የቅዱስ ሚካኤልን በዐለ ንግሥ ስናከብር ምስክር የሆንባቸው ታላቅ ለውጦች አሁንም ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን።ይህንኑ እውነት መቀበል ያቃታቸው ደብሩን ከመተናኮል ያላሰለሱትና ተዐምሩም ሆነ በረከቱ የጎደለባቸው፣ ልቦናቸውን እንዲያስገዙ እየጸለይንላቸው ወደ እርሱ መንገድ እስኪገቡ ድረስ ከወደቁበት ሁነው ቢፈረጋገጡ ለመላላጥ እንጂ ለመፈወስ አይሆንም። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ያደረባቸው የተለየ መንፈስ በመሆኑ የስነ ልቦና ብቻ ሳይሆን የኑሮ ቀውስም እየገጠማቸው መሆኑን ምንጮቻችን ይጠቁማሉ።

ሰሞኑን እነዚሁ ግለሰቦች በተለያዩ ገጾቻቸው አከታትለው ያወጡትን ተመልክተን ከወደቁ በኃላ መንፈራገጥ በማለት ችላ ብንልም በናንተ ጥያቄ፣ ለእነርሱም ትምህርት ለናንተም ማብራሪያ ይሆን ዘንድ በማለት እንጂ ። ቀደም ባለው ጥሁፎቻችን እንዳስነበብነውና ቅዠት እንዳልናቸው ሁሉ፤ በነርሱ እኛን ሀሰተኛ ጠሀፊ እንዳላሉን ፤ ይኸው ዛሬ መራራ መርዶ ሲቀምሱ ጣዕሙ ተናነቃቸውና እርማቸውን አወጡ ፣ ሀዘኑም ጠናባቸው። ለዚሁም ሰላማዊ የሆኑትንና ቅን የቤተ ክርስትያን አገልጋዮችን፣ በተለይም ከፖለቲካም ሆነ ከመሰለው ሁሉ እርቀው ኑሮዎቻቸውንና በሚችሉት ሁሉ ፈጣሪያቸውን የሚያገለግሉትን ለማደናቀፍ የማይፈነቅሉት ድንጋይና የማይሰጧቸው ስም የለም። የኛን ጥሁፍ በገጾቻቸው ደጋግመው ሲኮንኑ የነበሩት፣ እኛ ስም እየጠቀስን ግለሰቦችን እንደምንሳደብ ነበር። የኛ ጦመር ተፈጥሮ እስኪመታቸው ድረስ የጀመሩት እነርሱ ፣ አሁንም በቱልቱላቸው በ Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው የሚዘጋጀውና የሚቀርበው ገጽ ባለፈው ጥሁፉ ከደብሩ አመራር አባሎች ጀምሮ ሽማግሌ የተባሉትንና የአስተደሩ አዕምሮ ብሎ የሚላቸውን ቅን ምዕመናን ሁሉ ሳይቀር የሚፈልገውን መሰረተ ቢስ ምናምንቴውን ለጣጥፎባቸዋል።

ስለዚሁም ጉዳይ የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ የዘገበውን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

የሚካኤል ሰይፍ ተወካይ ካናገራቸው ውስጥ የአመራሩ አባላት ያሉት ነገር ቢኖር እኛንም ሆነ እነርሱን የፈጠረ አምላክ አንድ ነው ፣ እኛንም የመከረና የሚመራን እርሱ የእነርሱንም ልቦና ይግዛ፣ እኛ የተሰጠንን ሀላፊነት በቅን መወጣትና ይኸውም እንዲሳካ መጸለይ ነው። ማንም ከዚህ ቦታ ቋሚ የለም፣ ተርማችን ሲያበቃ ደግሞ እኛ ያገኘነውን በረከት ባለተራ እንዲደርሰው ነው። ይህ ቤተ እግዚሀብሔር ነው ፤ አባል በነበርንበት ወቅት በጊዜው የነበሩትን አመራሮች ብንመርጥም ሆነ ባንመርጥም ፤ ለተመራጮች የምንችለውን ድጋፍ በማድረግ ተባብረናልበኛ አመራር ቅሪታ ያለባቸው አባላቶች ካሉ በራችን ምን ጊዜም ክፍት ነው። ከኛ በፊትም ነበር ፣ አሁንም አለ እንደዚሁ ወደፊትም ይቀጥላል። ተጠሪነታችንም ለመረጡንና ላልመረጡን አባሎች ያለአንዳች አድሎ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ሽማግሌዎች የተባሉትን ግለስቦች blackmail  በማድረግ ደብሩ የማያውቀውን እውቅና ለማስገኘትና ቅደም ሲል በመረዳጃ ማህበሩ ውስጥ እንዳደረጉት አስርገው በማስገባት ጥረታቸው በመክሸፉ፣ እንደዚሁም ከደብሩ መተዳደሪያ ሕግ ውጪ በመሆኑ፣ በሚገባ አዛውንቶቹ በመረዳታቸው ተዳምሮ፤ እነዚሁን አዛውንቶች ስም በመጥቀስ ለማስፈራራትና ስማቸውን በከንቱ ለማጥፋት coercion በገጻቸው እንደተለመደው የከፈቱባቸው መሆኑን ቢታወቅም ከነዚሁ ውስጥ አንደኛው ሽማግሌ የደብሩ አባል ያልሆነና ከነርሱ ጋር አብሮ የወገነ ቢሆንም ሁለቱ ሽማግሌዎች አሁንም በቅን ለረዥም ጌዜ ( ከቆርቋሪዎች የሚደመሩ) እያገለገሉና ብዙ የደከሙ ሲሆን ለምናምንቴ የማያጎበድዱ መሆናቸውን ተወካዩ ገልጾልናል።

Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው በገጹ ካለው ውስጥ የመሸታ ቤቱ ግጭት እርሱ እንዳጋነነው ሳይሆን ሁለቱም ወገን በትግራይ ነጻ አውጪ ስር በአማራ ስም ከተጠራው ስብሰባ መልስ ለራት ባንድ ምግቤት ተገናኝተው  ሳሉ ዘግይቶ የደረሰው ግለሰብ ሰላምታ ካቀረበላቸው በኃላ ለምን ስብሰባችንን ረበሻችሁብን በማለት በተነሳው ቃል ልውውጥ ከተኩላው ጋር ተቀምጦ የነበረው የትግራይ ነጻ አውጪ በአጨብጫቢነት የሚታወቅውና ጎጃም በማደጉ ብቻ ጎጃሜ እራሱን በማድረግ የሚታወቀው ዘሩ ከትግሪ የሆነው መላኩ አቦዝን የሚሉት ግለሰብ ስድብ በመጀመሩ የወንድነት ጥያቄ ስለተጀመረ እንጂ የረባ ፍሬ የሌለው ነው። ተኩላውም ይህንን ይዞ ለግለሰቡ ሚስት ባልሽ ካልደበደብኳችሁ እያለን ብሎ ሰላማዊ ጋብቻ ውስጥ ቢያሞጠሙጥም፣ ታዲያ አንተስ ሱሪ ያጠለቅከው ወንድ ሆነ አይደለምን? እኔ ሴቷ ዘንድ የምን አማላጅ አመጣህ የተባለውን አፍረቱን መደበቂያ እንጂ ምንም ከጉዳዩ ጋር አይገናኝም፤ ስካርም ካለ እርሱም ሰክሮ ነበር ማለት ነው ተብለናል። ነገር ግን እኛም የምንጨምረው ቢኖር ተኩላው ስለጠመንጃ በሀገራችን በአሜሪካ ውስጥ ማንሳቱ እኛን ጠሀፊዎችን ባይነካካን ጥሩ ነው። እንደእርሱ አይነት ሽንታምና ፈሪ የጀግኖችን መሳሪያ ያለቦታው አትነካካ long live US Marine Corp ያለብቃትህና ያለቦታህ አትግባ ፣ ባለፈውም ጠቁመንሀል።

ሌላው ምንጫችን ያናገረው ስለስራው ሳይቀር ስሙ የተጠቀሰው ግለሰብ ያለውን ነው። ግለሰቡ ያለው ቢኖር የአገልጋይ እጥረት በነበረበት ወቅት ለደብሩ ባገኘሁት ሁሉ ከልቤ በቅን በማገልገሌ ተባርኬበታለሁ። ጤናንና ዕድሜ ቀጠለልኝ፣ሥራዬ ቀዝቅዞ የነበረው ተመለሰልኝ፣ ለ5 አምታት ያህል በአንድ የሆቴል ክፍል ተጣብቄ ስኖር ማገልገል ከጀመርኩኝ በኃላ የቤት ባለቤት ከማድረጉም በላይ ባለፈው ጥቂት ወራት ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር ያላነሰ በነበረኝ ሀብት ላይ ጨመረልኝ፤ ስለዚህ በመንበሩ ፊት በሁለት እግሬ ቆሜ አይደለም ብችል በጭንቅላቴ ተዘቅዝቄ ቆሜ ብዘምርለት ስላደረገልኝ ምክንያት ስላለኝ ነውና ለኔ የፈሰሰው በረከት ቀላል አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ ለማያውቁኝ ወገኖቻችን ሙያዬን ብቻ ሳይሆን እኔንም አስተዋወቁኝ። እኔ  ለመታወቅና ለዝና ያደርኩት ነገር ምንም የለኝም፣ ችሎታውም ሆነ ዕውቀቴ ለተከበሩት አዛውንቶችና ከደብሩ አመራር አባሎች ተሽሎ ተገኝቶ በኔ የሚመሩ ከሆነ ወደፊት ለፖለቲካ ቤሮ ለመወዳደር አሊያም በዳላስ የሚገኙትን ወገኖቻችንን በቅን ለመምራት የሚያስችል ልዩ ተሰጥዎ አለኝ ማለት ነው በማለት በቀልድ እንደመለሰለት ዘግቦልናል። እኛም ስለ ግለሰቡ አገልግሎት የመላዕክት ዝማሬ ያሰማለን፣ ስለአገኘው በረከት የሰጠውን ምስክርነት ከልባችን የገባ በመሆኑ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እንላለን።

በተረፈ በወይዘሮ ሐረር (ኢትዮጵያ) ወርቅ ጋሻው የሚቀርበው የዳላስ ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ብሎግ http://dfwethiopiancommunity.blogspot.com/
እያወጣው ያለው መረጃዎች በአካባቢያችሁ እናንተን እየከፋፈሉና በናንተ ስም እየነገዱ የሚገኙትን እያጋለጠ ያለ የሕብረተስባችሁ ድምጽ እየሆነ የመጣ ስለሆነ ቅኝታችሁ አይታጎል።

የክብር እንግዳ ሳይሆን እንደ ኢሕ አፓ አባል በቅርቡ በተደረገ የመገናኛ ዝግጅት ላይ ሙሉጌታ ወራሽ aka ቀዳዳው ሙላው  መገኘት ከነበሩት ደርሶናል። እኛም የትና መቼ በድርጅቱ መታቀፉን ባናውቅ በወቅቱ ጥብቆ ያጠለቀና ቁንጯም መሆኑን አብሮ የደረሰን መሆኑን ነው።

ሌላው Looser ተኮላ መኮንን aka ተኩላው በገጹ ካለው ውስጥ የደብሩ አመራር ልጆችን ተጠቀመ በማለት ፍሬቢስ አስተያየት፤ የተማረና የሚማር ሁሉ እንደሚያስፍራው መሆኑን ነበር የጠቆመው። እርሱም በየሳምንቱ አርብ ምሽት በሚሰጠው መንፈሳዊ ትምህርት ከቻለ በአካል ካልሆነ እንደኛው በኢንተርኔት በመማር ክርስትናውን ቢያጠብቅ፤ ለልጆቹም ከዕድሜ ብጤዎቻቸውና ከወገኖቻቸው ጋር ተቀላቅለው መንፈሳዊ ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ ሲገባ፤ ነገርግን እንደተበደለና እንደተገፋ ሀሰት fabricate የማድረጉን እሮሮ ቢያቆመው በተሻለው። ምናልባት የተጠናወተው እርኩስ መንፈስ ለቆት እንደ ምናምንቴ ሳይሆን እንደሰው
ቢያደርገው።

ከዚሀ በፊት በትግሬ ነጻ አውጪ ለተሾሙት አባ ጳውሎስ ያደረ ባንዳና ካድሬ እነ ኢዮኤል (ክፈተው) ነጋ የቀጠሩት ሲደልል የተባለውና በዲፕሎማት ፓስፖርት ወደ አሜሪካን የገባው፤ በአዲሱ አመት ለሹመተ ጵጵስና ወደ አዲስ አበባ የሚዘልቀውን የአትላንታ ቄስ ተክቶ መቀጠሩን ስለስማን፣ አትላንታዎች ከዚሁ አስቡበት እንላለን። እንደዚሁም ቀደም ብለን እንደዘገብነው ግለሰቡ ቅጥረኛነቱን በተግባር እያስመሰከረ መሆኑን እያስረገጥን አሁንም ተጠልሎ ያለው ዳላስ ላይ ባለው የትግሬ ነጻ አውጪ በሚተዳደር ቤተ ክርስትያን ነው።

እርሶስ ምን ይላሉ?