Monday, January 24, 2011

አዲሱ ዘመቻ በራዲዮ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!


ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



አዲሱ ዘመቻ በራዲዮ

ፖለቲከኛም አይደለን ወይንም ተንታኝ ነገር ግን ነገርን ነገር አነሳውና ለዚህ ጥሁፍ በቃን። የተወደዳችሁ ተከታታዮቻችን እንደምን ከርማችኃል? ለልዑል እግዚሀብሔር አሁንም በቸርነቱ ጠብቆ መልሶ በዚህ ገጽ ለመገናኘት ፈቃዱ ለሆነው ለእርሱ አሁንም ክብር ምሥጋና ይሁንልን። ገናናው ስሙ ለዘለዓለም ይባረክልን። አሜን።

እኛ በገለልተኛነት በቀደምት ጥሁፎቻችን ኢሕአፓ የተባለውን የፖለቲካ ድርጅትን መተቸታችን የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ቀደምት ታዳሚዎቻቸው ውስጥ ቀደምት የኮሚኒዝሙን ርዕዮተ ዓለም የሆነውን ቁሳዊ እምነትና አመለካከት የሻሩና ወደ መንፈሳዊነት ወይንም ሀሳባዊነት የተቀበሉ አያሌ አባሎችን ያቀፈ ድርጅት መሆኑና የአሰላለፍ ለውጥ ማድረጉ በሚገባ የተረጋገጠ ነው። ይህ ትውልደ ኢትዮጵያን አቅፎ የተነሳ ድርጅት ዛሬ የተለያዩ የሀይማኖት ተከታዮችን አቅፎ የያዘና በአለም ዙሪያ የተበተኑ ሺህዎች አባላት ያሉት ጎራ ነው። በትላንቱ የእሁድ ከሰአት በኃላ የዳላሱ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማሕበር በአማርኛ ቋንቋ በሚያሰራጨው የሬዲዮ ፕሮግራም ስርጭቱ እንዳስደመጠው ከሆነ ኢሕአፓን ለዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደብር ቀደም ሲል አጽራረ ቤተ ክርስትያን በሆኑ ጥቂት ግለሰቦች ለፈጠሩት ሴራ በተጠያቂነት ሊያስቀምጠው ሲቀባው እንደነበር ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ችለናል።

በመሰረቱ በትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ተቀጣሪ የሆኑት ግለሰቦች ተይዞ የሚመራው የዳላስና ፎርት ዎርዝ የኢትዮጵያ መረዳጃ ማኅበር ማንነት ቀደም ሲል በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ዘገባዎችን በአምዳችን ስናስነብባችሁ መክረማችን እሙን ነው። የዚህን መረዳጃ ማኅበር በወገኖቻችን ቸልተኝነትና የዋህነት አሊያም ድክመትም ሆነ አለማወቅ በሩንም ከፍተው ካስገቧቸው ውስጥ የኢሕአፓ አባላትንም ይጨምራል። ኢሕአፓና የትግሬ ነጻ አውጪ ድርጅት በአሁኑ ሰአት ከመገዳደል የማይመለሱ ለመጠፋፋት የቆሙ የራሳችን ወገኖች ናቸው (ልዩነታቸው ውስጥ በዝርዝር ሳንገባ)።

በሌላ በኩል የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳደርም ሆነ ምዕመን አንዴም ጣቱን በኢሕአፓ ላይ አልጠቆመም። በተለያየ ጊዜም እነዚሁ ተቀጣሪ የሆኑና ለትግሬ ነጻ አውጪ ያደሩ፣ አንዳንድ ከኢሕአፓ የከዱና አሁን ቅጥረኛ የሆኑ፣ ለይቶላቸው አጽራረ ቤተ ክርስትያን ጎራ የገቡ በመተባበር በደብሩ ላይ የከፈቱት ጥቃት በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ፣ በቤተ ክርስትያን ልጆችና በምዕመናን ፀሎት በመክሸፉ፤ ባላቸውና በጨበጡት በትር መወናጨፋቸውን የሚያሳይ የዚሁ የሬዲዮ ስርጭቱ ያስደመጠው ነው። በሬዲዮ ስርጭት የሙያው ብቃትም ሆነ መረጃ የሌላቸውና የስርጭት ደንብና ሕግ በጣሰ፣ የመረዳጃ ማሕበሩን ሕግና ደንብ ባልተከተለ መልኩ የሀይማኖትና የፖለቲካ ድርጅቶችን ለማጋጨትና በሕብረተሰቡ መካከል የመከፋፈልንና የመጠላላትን ነቀርሳ ለመትከል የታቀደና ከደብሩ አካባቢ ያጡትን አጸፋ ለመውሰድ ቆርጠው መነሳታቸውን ያረጋገጠ ስርጭት ነበር።
የዳላስና አካባቢው ሕብረተሰብ ቸልተኝነትና ተሳትፎ ማጣት የፈጠረው ክፍተት ምክንያት ሆኖ፤ ዛሬ ተሰግስገውበት የሚገኙት የትግሬ ነጻ አውጪ ተቀጣሪዎች ባላቸው ተልዕኮ ቀሎ ያገኙትን ይህንን የመረዳጃ ማኅበርን መቆጣጠርን ነበር።  ከዚያ በኃላ የተለያዩ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን ማቋቋምና በዚያ ስም በመታገዝ የህብረተሰቡን ስም በመጠቀም የተለያየ የገንዘብ ማግኛ ምንጭ ማድረግ ነው። አንዳንዶቹንም ቀድሞ ከነበሩበት ከተማ ሳይቀር እንዴት ሲያጭበረብሩ እንደነበር ከፍርድ ቤት መርጃ ጋር ማስነበባችን የሚታወስ ነው። ከዚህም አልፎ የሌለ የኮሚቴ ስም በመፍጠር በደብሩ ስምና በታቦቱ ሳይቀር እየቆመሩ ያሉ ግለሰቦች ናቸው። እንግዲህ ቅደም ብለው መረዳጃ ማህበሩን ከተቆጣጠሩ በኃላ ያመሩት ወደ ቅዱስ ሚካኤል ደብር ነበር። በዚያ ግን አልጋ በአልጋ ስላልገጠማቸው የተለያየ ስልት በማውጣት በደብሩ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ መግባትን፣ በፈጠራ ምዕመናኑን መከፋፈልን፣ ብለው ሁከት መፍጠርን፤ አጽራረ ቤተ ክርስትያን ቡድንን ማደራጀትን ብሎም መክሰስን አደረጉ። ይህ ሁላ ሴራቸው በተዋህዶ ልጆችና በደብሩ አመራር ከሸፈባቸው።

የተዋህዶ ልጆችም ተሰባስበው የነገሩን አመጣጥ ገመገሙ። በሕብረተሰቡም ውስጥ ያለውን የየግል ድርሻቸውን መረመሩ። መረዳጃ ማህበሩም የበለጠ መጠናከር እንዳለበት አመኑ። በዚህም ምክንያት መረዳጃ ማህበሩን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ከጀመረው የወጣቶች ቡድን ጋር የጠለቀ ውይይትና መግባባት ላይ ደርሰው መንቀሳቀስ በጀመሩ ማግስት፤ የሬዲዮ ፕሮግራሙ አንዴም በደብሩ ውስጥ የነበረውን እክል ጆሮ ዳባ ብሎ እንዳልኖረ ዛሬ ተቆርቋሪ መስሎና አዲስ ካባ ለብሶ ብቅ በማለት በማር የተጠቀለለ መርዙን በራዲዮ ፕሮግራሙ በማሰራጨት በኢሕአፓና ወጣቱን ለመርዳት በቆሙ የተዋህዶ ልጆች መካከል ቅራኔን ለመፍጠርና እኔ በደብራችሁ ጉዳይ ውስጥ የለሁበትም ለማለት ከፋፋይ መርዙን ጀምሯል። ኢሕአፓንንም ዋና ተዋናይና የደብሩ ጠላት በማድረግ ኮንኖታል። ዘጋቢዎቹም ሆነ የበላዮቻቸው መጡብን በማለት ለተተኪው ትውልድም ላለመስተላለፍ ሲሉ የቀደም ፊውዳላዊ ሥርዐት ቢጤ የዕድሜ ልክ በትረ-ሥልጣን ጨብጦ ለመቆየት ሲሉ ትረስቲ ለመሆን የጀመሩትን የመተዳደሪያ ደንብ የብወዛ ጨዋታ ባለፈው ጥሁፋችን ማስነበባችን ይታወሳል። የዚሁ ዘመቻቸው አካል የሆነው ሌላው ተልዕኮ ኢሕአፓን ያለቦታው መኮነን ተገቢ አለመሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሀቅ ነው። ከዚህ ከፋፋይ ከሆነ መሰረተ-ቢስ ዘመቻ ባስቸካይ መገታት እንዳለበትና ሕብረተሰቡም ጠንከር ያለ ግንዛቤና እርምጃ ሊወስድበት ይገባል እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, January 22, 2011

ዛሬም እንደትላንቱ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ዛሬም እንደትላንቱ

መቼም የት ተደበቃችሁ? ምንስ አገኘኛችሁ? ምንድን ነው ድምጻችሁ የጠፋው? አበቃላችሁ? ወያኔ ሆኑ እንዴ? ለምንስ ከድርጅት ጋር ተላጋችሁ? ኢሕአፓን ለምን ነካችሁብን? ወዘተረፈ የተባለውን ሁሉ ከምንጮቻችን ሰማነው።

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ከርማችኃል? እንኳንም ለጥምቀቱ በአል በሰላም አደረሳችሁ? መልካም ፈቃዱ ሆኖ ደግሞ ላገናኘን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን። አሁንም ጸሎታችንን ተቀብሎ ለመለሰልን ፈጣሪ ክብር ምስጋና አሁንም ለእርሱ ይሁን። አሜን።

የከተማችሁም ፖለቲከኞች ገጻችን ላበረከተው አስተዋጾ አክብሮት ቢኖራቸውም ለማጥላላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበረ ያምናሉ። አሁንም ከሚፈሩት ጦመር የመጀመሪያው ብንሆንም፣ እኛ የማንም ጠላት ወይንም ማንንም አንጠላም። ሁላችንም የኢትዮጵያ ተወላጅ ብቻ ሳንሆን በእያንዳችን ልብ የየግላችንን አመለካከት ቀርጸንና ይዘን የምንጓዝ እንደ መልካችን የተለያየን ነን። ነገር ግን ግለኝነትና በተለይም በሌላው ላይ ተንሰራፍቶ እኔን ብቻ አንግሡኝ፣ እኔ ብቻ ነኝ የማውቅላችሁ፣ እኔ ካልመራሁ እናንተ አታውቁም የሚሉና ነባራዊ ሁኔታን የማይረዱ ፣ ከጊዜው ጋር ግንዛቤ ለመውሰድ ዝግ የሆነ አእምሮ ለተሸከሙና ከፊውዳላዊው ሥርዐት ባፈጀ ዕድሜ በምዕራቡ ሀገር ለመጨበጥ የሚያልሙ በትሩና ካምፓኒው ትላንት በቅዱስ ሚካኤል ደብር ውስጥ የተደረገውን ታሪካዊ ምርጫ የመገንዘብ ብቃቱ የጎደላቸው ፣ እራሳቸውን ለራሳቸው ብቻ ጠቁመው ለመመረጥ ያቃታቸው ፣ የምዕመኑን ለውጥ መፈለግ ሊረዱ የተሳናቸው ግለሰቦች ዛሬም እንደ ትላንቱ በመረዳጃ ማሕበራችሁ ላይ የመጨረሻ የሞት ሽረት እርምጃ ላይ ይገኛሉ።

የመረዳጃው ማሕበር አባልና ያለመረጃ የዶክተርነት ማዕረግ የተሰጠው የወዳጃችን ወዳጅ እንዳካፈለው ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ገንዘብ ዘርፈው ለመሮጥ የጠነሰሱት በቅርቡ የገንዘብ መዋጮ (fund raising) ለማድረግ መወሰናቸውን ነው። በተጨማርም ሚሽቱ ከንቱ ከሚባለው ግርማቸው ጋር በመሆን በትሩና ካምፓኒውን የዕድሜ ልክ (life time) የሚጨብጡበትን ትረስቲ የሚባለውን ሕግ እያረቀቀች ለመሆኗ በኩራት አውግቶለታል። እንግዲህ 30 ቀን እንኳን እድሜ የሌለው የመረዳጃ ማሕበር ለምን አዲስ አመራር በመመረጫው ሰአት ይህንን 2 አበይት ተግባራትን ለመከወን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄ የመንኮራኩር ጠበብት መሆን አስፈላጊ አይደለም። ያለ ውዴታ የግዴታ በእድሩ ምክንያት አባል እንዲሆኑ የተገደዱት አባላት ለማሳደስ የተደጋገመ ጥሪ ቢቀርብላቸውም እምቢተኝነታቸውን አጽንተው የቆዩት ዋነኛው ምክንያት ያለአግባብ እየተመዘበረ ያለውን ጠቅላላ ምዝበራን በሚገባ ስለደረሱበትና የጠቅላላው ስብሰባ ተጠርቶ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ መሆኑን በሚገባ ያስረዳሉ። ለዚህም አጠቃላይ ስብሰባ ተደርጎ፣ ሪፖርትም ተሰምቶ፣ ገቢና ወጪው ታውቆ፣ አዲስ አመራር ተመርጦ ለማየትና ያለባቸውንም ውዝፍ በመክፈል መልሰው በአዲስ መንፈስ ለመሳተፍ እንደተዘጋጁ አስታውቀውናል። ነገር ግን በትሩና ካምፓኒው ያለባችሁን ውዝፍ ካልከፈላችሁ ድምጽ አታደርጉም በማለት ለዘረፉትና ላዘረፉት ገንዘብ ተጠያቂ እንዳይሆኑ መምከራቸውን ከዚሁ ዶክተር ተብዬው መደመጡን ምንጫችን አውግቶናል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለጽሕፈት ቤቱ ተቀጣሪ የሆነችው ግለሰብ ያላት ብቃትና ግልጋሎት፣ አቀጣጠሯንም ጨምሮ ይከፈላታል የተባለው ከ26 ሺ ዶላር በላይ መሆኑ ከፍተኛ ጥያቄ ነው። ለመሆኑ ድርጅቱ ይህን ያህል ከፍሎ የቀጠራት ሰራተኛ ከአባላት ውጪ ምን ያህል አዲስ የገንዘብን ምንጭ ፈጥራለች? ምን ያህሉንስ ገቢ አስደርጋለች? ምን ያህል የተቸገሩ ወገኖቻችንን ከችግር አውጥታለች? ስንቱንስ አስፈላጊ እርዳታን እንዲያገኝ አመቻችታለች? በመቶ እጅ ሲሰላ ስንት እጅ የሚሆነውን ነበር ካሰባሰበችው የውጪ እርዳታ ለእርሷ ደሞዝ የዋለው? ወዘተ የሚለውን ጥያቄ ይዞ የሚጠብቅ ተሰብሳቢ ይገኛል። እንግዲህ በትሩና ካምፓኔው እረፍት መውጣትን ካልከጀሉ፣ ለመጪው ስብሰባ እንቅፋትን ቢደረድሩ ውርድ ከራሳቸው እንጂ የተቀጣጠለውን ለውጥ ሊገቱት እንደማይችሉ አውቀውና ተቀብለው ራሳቸውንና የጥቅም አጋራቸውን ከሀዲዱ ባሻገር ያቆዩ ብለን ምክራችንን እንለግሳለን። ዛሬም እንደትላንቱ ሊቀጥል አይችልምና።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, January 15, 2011

ይድረስ ለኢሕአፓና ለሎሌዎቹ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ይድረስ ለኢሕአፓና ለሎሌዎቹ

ከሁሉ በላይ ፈቃዱ ሆኖ ለታላቁ የጥምቀት በዐል ሁላችንን ጠብቆ በሰላም ላደረሰን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን። እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

ባለፈው ‘እናንተን ምን እንበላችሁ?’ በሚል እርእስ ላቀረብነው ጥሁፋችን በአለም ደረጃውን የጠበቀ አቅርቦት መሆኑንና በየትኛውም ወገን የቆሙት በሙሉ የግላቸውን ግንዛቤ ወስደዋል። በእርግጥ በድርጅቱ ሥር ለታቀፉት ወይንም ዳይሀርድ ከሆኑት ጎራ ቅሬታን ብናስመዘግብም፤ ከትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች ጎራ ልባቸውን ለጊዜው አሞቀው እንጂ እነርሱም የሰው ልጅ በልተው ለዚህ መድረሳቸው መረጃ እኛን መጠየቅ ማለት ከሌላ ፕላኔት የወረደ ብቻ ስለሆነ ባንድ እንመትራቸዋለን።

ከጥቂቶች በስተቀር አብዛኛው ቃታ የሳበ የኢሕአፓ ጀሌ ሁሉ ባለሁለት ስም መጠሪያ ያለውና እስከ ሁለት ፓስፓርትም የያዘ እንዳለ የሚታወቅ ነው። በትግሬ ነጻ አውጪ ውስጥ ይህ ድርጊት ተመሳሳይነት አለው።የዳላሱ ወንድሞቻችን በethiodallas ገጽ ላይ በብዕር ስም ሳሙኤል ሽፈራው የተባሉት “ኢሕአፓን ለቀቅ“ ብለው ያጣፉትን በትህትና ተቀብለን በማፈግፈግ ላይ እያለን በፓርቲያቸው ልሳን በሆነው አሲምባ.ኦርግ ላይ እንደዚሁም በቢጤዎቹ ድኅረ ገጽ በተመሳሳይ ያስነበቡን እርእስ “ የቀድሞው ፕሬዝዳንት መንሥቱ ኃ/ማርያምን “ አስመልክቶ በኪዳኔ አለማየሁ የቀረበውን ማስተናገዱ ፍጹም ስህተት ነው። ይሀው ጠሀፊ በብሄራዊ ደርጃ ሊያስተዋውቃቸው የሚቃጣውን የግለሰቦችን ስም ማንነትና ምንነት የዳላስና የቴኔሲ ወገኖቻችን የተፏቸው መሆናቸው እሙን ነው። እነዚህ በትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኝነት የሚተዳደሩ ግለስቦችን ከቀይ ምንጣፍ እኩል ያነጠፈላቸው ለምን እንደሆነ ለናንተው ዳላስ ላይ ላላችሁትና የፓርቲያችሁ ክንፍ ለሆናችሁት ስንተው መልሱን ለአንባቢዎቻችን እንደምታቀርቡ በመተማመን ነው። ድኅረ ገጾችም ባስቸኳይ ያነሱታል የሚልም እምነት አለን። በተለይም የመንግሥቱን ፊርማ ተብሎ የቀረበው በኛ በኩል እውነተኛነቱን ለመቀበል አዳግቶናልና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይተቹበት እያልን በጥያቄ እናልፈዋለን። ምንአልባትም ኮለኔሉ ወይንም በዚህ አካባቢ ያሉ ሊመልሱ ይችላሉ። እኛ ከማስረጃው እውነተኛነት እንጂ ድርጊቱ አልተፈጸመም ብለን እንዳልሆነ ከዚሁ ለማስጨበጥ እንወዳለን።

ባለፈው በገጻችን ላይ“ከምቾት“ ለቀረበውና እኛም ለወሰድነው እርምጃ ለልቡ ሙቀት የተሰማው የመሰለው ባንዳ ምቾትን ጥሩ በሰራለት መልሶ ሊነክሰው ሞክሯልና እንግዲህ ባንድ ቀዬ ያደጋችሁ ከሆነና አብራችሁ ጓዴ ተባብላችሁ መሳሪያ በደርግ ላይ ያነሳችሁና የኢሕአፓ ሠራዊት የነበራችሁ ስለሆነ ክንብንባችሁን አውርዱት ነው የምንል። አሁንም ከጊዮርጊስ ያመለጠህ የተባልከው ምቾትም ካልሆንክ አንተ ማነህ? ወይ ከተኩላው ወይ ካንዳችሁ አንድ በሉን እያልን ለዛሬው በዚህ እንሰናበታለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

Thursday, January 13, 2011

አዲስ በሰንበቴ ብሎግ የወጣውን አንብበውታል? እርሶስ ምን ይላሉ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


አዲስ በሰንበቴ ብሎግ የወጣውን አንብበውታል? እርሶስ ምን ይላሉ?

Wednesday, January 12, 2011

ገጻችሁን መሰረተቢስ አታድርጉ!

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ገጻችሁን መሰረተቢስ አታድርጉ!

ብዙ ጊዜ ካሰብኩበት በኃላ በመወሰኔ የሚቀጥለውን ለመጻፍ ተነሳሁ። እናንተም ያለቅሬታ በብሎጋችሁ ላይ እንደምትለጥፉት እርግጠኛ በመሆን ነው። ካደረጋችሁት ጥሩ ከቆሻሻም ካስገባችሁት የናንተ ውሳኔ ነው። ነገርግን ለዛችሁን የባሰ ነው እያጠፋችሁ የምትሄዱ። የምትነኩትንም ወዳጅ ጠላታችሁን የለያችሁ አትመስሉኝምና ብሎጋችሁ ሲያደርግ የነበረውንና ያበረከተውን ሚና እያጨለማችሁትና እያጠባባችሁት ትገኛላችሁ።

እኔ እንደደረስኩበትና እንደተረዳውት የጨበጥኩት ግንዛቤ ቢኖር የዚህ ገጽ አዘጋጅ ምንም አይነት ስለ ኢሕ አፓ እውቀት የሌላችሁ ነገር ግን ግለሰብን ለመኮነን ስትሉ ድርጅቱን ያለአግባብ ወነጀላችሁ። ይህንን ለማለት ያበቃኝና የዚሁ ጽሁፍ መነሻ የሆነው አቶ ተኮላ መኮንን የተባለውን ግለሰብ አስመልክቶ የቀረበውን በማንበቤ ነው። እኔ አቶ ተኮላን ከልጅነቱ አውቀዋለው። በእርግጥ ከናንተ የሚያስማማኝ በትምህርቱ እንደናንተ የገፋ አይደለም። ነገር ግን እድሜው ደርሶ ወደ ውትድርና የገባው ወደ አየር ወለድ መሆኑንን አልክድም ነገር ግን በአየር ወለድ ውስጥ ሾፌር እንዳልነበርና ከዚያ ጋር የተያያዘው ዘገባ የተሳሳተ ነው። በአየር ወለድም የቆየበት አመት እርግጠኛ ባልሆንም 2 አመት የሞላው አይመስለኝም። ከዚያ ጦር ክዶ የሚለውን ቃል ባልስማማበትም በትክክል የተወሰኑ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን ኢሕ አፓን ተቀላቅሎ መሰለፉ ሀቅ ነው።

የናንተ ምንጭ የሆነው/የሆነችው ግለሰብ ከእውነት የራቀ ዘገባ ነውና የሰጡት ይህንን እንዲታረም ስጠይቅ ሁላችንም የተለያየ አመራር ስር በኢሕ አፓ ማገልገላችንና የሚጠበቅብንን መስዋዕት መክፈላችን እሙን ቢሆንም አቶ ተኮላ በጋንታ አዛዥነት አላገለገለም። በእርግጥ በቦታውና በሰአቱ ባልኖርም በአንጃነት እርምጃ የተወሰደባቸው እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እኔ በአይኔ አቶ ተኮላ ሲገድል ስላላየሁኝ የምንጫችሁን እውነተኛነት ማረጋገጡ ተገቢ ነው። በግል ጥላቻ ከሆነም ሀሰት ማድረግ ተገቢ አይደለም። በእርግጥ ሚስጥር እንዳይወጣ የተያዙ ነጥቦች ቢኖሩም ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን ተባብለን የተውነውን የእናንተ መቀስቀስ ይሆናልና መተው ይመረጣል። ጥቅምም አይኖረውም። በተረፈ አቶ ተኮላ ዛሬ ለወያኔ ያደረ ለመሆኑ የዘገባችሁት ላይ ብስማማም መብትና ነጻነት እንዳለው እንደምንስማማ እርግጠኛ ነኝ። በተረፈ በአቶ ተኮላ ላይ የተሳሳተና የተዛባ ዘገባ የሚሰጧችሁ ምንጮቻችሁ በቦታው የሌሉና ወደቀ ሲሉ ተሰበረ የሚሉ አይነቶች እንጂ ያላቸውን እውነታ ይዘው ቢሞግቱኝ ደስታዬ የላቀ ነው።

እናንተም እዚህ ውስጥ የገባችሁት በእውነት ለሀይማኖት ከሆነ ሆዴን ነክታችኃልና አቶ ተኮላን ይቅርታ ልትጠይቁት ይገባል። በእርግጥ እርሱም ቢሆን ሀይማኖት ያለው ከሆነ ከቤተ ክርስትያን ጋር ግጭቱን አቁሞ ቢበደልና ቢገፋም ለፈጣሪ ብሎ እንዲተውና የበደሉትን ሁሉ ይቅር እንዲል በዚህ አጋጣሚ በእግዚሀብሔር ስም እጠይቃለሁ። ለተሰጠኝም እድል አመሰግናለሁ።

ምቾት ከዳላስ


ከብሎግ አዘጋጅ

ከዚህ በላይ ያለውን የላኩልን አንባቢያችንን ጥሁፍ እንዳለ ስናቀርብ የተለያዩ ተመሳሳይ ጥሁፎችም ደርሰውናልና እንድ ሀገሩ አባባል’ we can not agree more’ እንደሚሉት እንደዚሁም አቅራቢ የነበረው ወንድማችን በዚህ ጉዳይ ላይ የነበረውን contact ለአስተያየት ልንገናኘው ሞክረን ባለመቻላችን ይህንን ለማውጣት ተገደናል። በእርግጥ የተዛባ ዘገባ ከሆነ ለአቶ ተኮላ ገጻችን ከልብ ይቅርታን ትጠይቃለች። እንደግመዋለን አሁንም ከልብ ይቅርታን እንጠይቃለን። ማንኛውንም ነቀፌታና ትችት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በአስተያየት መስጫችን ላይ እናስተናግዳለን። ይህ ገጽ የሁላችሁም ነውና አስተያየት ስጡበት ነገር ግን ከላይ ጠሀፊው እንዳሉት ከአቶ ተኮላ ጋር ልዪነታችን ሀይማኖታችንና ደብሩን መክሰሱ ዋናው ነጥብ ስለሆነ የጠሀፊውን ጥያቄ ይቀበላል እንላለን።


በሌላ በኩል በተጠየቅነው አስተያየት መሰረትና ከሚካኤል ሠይፍ ባገኘነው መርጃ ለደብሩ አዲስ አስተዳደር ምርጫ ያለፉት ተጠቋሚዎች ስም
1. ሙሉጌታ ው/ሚካኤል  በኛ አስተየት ብዙም መርጃ የለንም
2.ሰሎሞን ጋዲሳ                                ጥሩ ምርጫ
3.ኤልሳ በቀለ                                    መልካምና ጥሩ
4.አብርሃም አሰፋ                                  ?
5.ዮሴፍ ረታ                                     የእረፍት ጊዜ
6.ተስፉ በላቸው                                    ?
7.መሠለ ከልል                                  ጥሩ
8.አምሃ ገ/አማኑኤል                           መጥፎ ምርጫ


 በማለት እንደመድመዋለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Monday, January 10, 2011

የሰደዱት መልዕክት

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



በቅድሚያ ሰላምታችን ይድረስዎ! በእውነት ሃማ ቱማ ቢሆኑም ባይሆኑም የሰደዱት መልዕክት ለጥያቄያችን መልስ አድርገን ተቀብለናል። እኛም ስለተሳትፎዎ እያመሰገንን መልዕክቶን እንዳለ በፊት ገጻችንም እነሆ እንለጥፋለንና ግንዛቤውንም ለአንባቢያን እንተዋለን።

ነገር ግን የሰጡትን መልስ በእርግጥ መልሰው አንብበውት ካልሆነ ደግመው ያነቡት ዘንድ እየጠቆምን ከአንድ የላይላይ አመራር የማይጠበቅ ቃላትን በኛ ላይ መሰንዘር እኛን ሳይሆን የሚመሩትን ኢሕ አፓ ድርጅትን ብቻ ሳይሆን በሕይወት የተረፉትንና አሁንም አምነው የሚከተሉትን የድርጅቶን አባላት አንገት የሚያስደፋ ቃላትን መምረጥዎ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ከተራ ጎራ በታች ዝቅ ያደርገዋል። በሀሳብ መለያየት፣ መወያየትም ሆነ መሞገት ሲገባ ራስን በተራ ቃላት ማዋረድ ማንነትን ያስገምታልና የሂስ ኪኒን ካላቃሮት ቢውጡ መልካም ይመስለናል።

ኢሕ አፓ በጨቅላነቷ ባሀገር ቤት ያስነበበችንን በቀይ ቀለም የደመቀው ዲሞክራሲያ የተባለው በራሪ ወርቀትን ያስታወሰችን በምላሾ ጥሁፍ የጠቆሙትን ገጽ አንብበን ላላዩትም ለጥፈናል። ከዚህ ጥሁፍ ልንጠይቆ ከፈቀዱልን የማጭድ መዶሻ አርማችሁን ተነጥቃችሁ ነው? ወይንስ የ strategy ማፈግፈግ ይሆን? መቼስ ተጀመረ? የሚለውንና ለምንስ ለውጥ አስፈለገ? የሚለውን እንዲያስረዱን እየጠየቅን ምላሾን እንደሚከተለው ለጥፈናል።


Emama Ethiopia First has left a new comment on your post "ኸረ ማን እንበላችሁ?":

በባዶ ሜዳ መንጨርጨር፥
አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል።

ይህን ሊንክ ተከትለህ ብታነበው ትንሽ ትማራለህ፥ ያም ንፍጥ ብቻ ካልሞላህ http://www.ethiomedia.com/augur/democracia_no36.pdf 



ሰው የጁን ያገኛል የሚለውን አባባል እያየነውና ምስክር ያደረገን አምላክ አሁንም ምስጋና ይግባው።አሜን።በዳላስ እየተደረገ ያለው የአጽራረ ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴ ለትልቁም ለትንሹም እየደረሰ ስለሆነ አቤቱ ፈጣሪ በመሀሪነትህ ማረን ከቁጣህ ሰይፍ አድነን። እግዚኦ እግዚኦ እግዚኦ…..።

አንዳንዱ አውቆም ይሁን በስህተት የደብሩን መተዳደሪያ ሕግ ለማስለወጥ ፊርማ አሰባስበው አስገብተዋል። ሌላው ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው ደብሩን የያዙት ስለዚህ እነሱን ለመክሰስ ገንዘብ አዋጡ ይላል። አንዳንዱም የፈለገው ስላልተጠቆመ ምርጫው እንዲለወጥ ይፈልጋል። እንግዲህ ሌላው ደግሞ ወደ ፈጣሪው ስለደብሩ ጸንቶ በመጸለይና ምላሹን እያገኘ ለመሆኑ ገጻችን በየወቅቱ እያስረገጠ ነው። ማየትና መረዳት ያቃታቸውና ዕምነተ ጎዶሎ የሆኑት ግን የፈጣሪን ሥልጣን እየተጋፉ የአለምንም ሕግ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እየጫኑ እየፈተኑት ስለሆነ ልብ ያለው ልብ ይበል ወደ ፈጠረው አምላኩ በጊዜ ይመለስ እንላለን።

ከዚህ ደግሞ ወጣ ስንል ወደ መረዳጃው ማህበር ነው ጎራ የምንል። በድብቅ የተጀመረውና በትግሬ ነጻ አውጪ ወኪሎች ለቁማር የበቃው መረዳጃ ማህበር አዲስ መተዳደሪያ ሕግ እየተፈጠረለት ነው። ይኸውም ደብሩ ትረስቲ ያስፈልገዋል ብለው የከሸፈባቸው ይህንን ድርጅት ወደዚያ ለማሸጋገርና የትግሬ ነጻ አውጪ እጅ ስር እንዲቀር ለመተግበር ነው። ከአርክቴክቸሩ አንዱ ከንቱ የሆነው ግርማቸው ሲሆን ከዚህ በፊትም በደብሩ ተመሳሳይ ሙከራው የተጋለጠበትና የከሸፈበት ውርደታም ነው።

ሌላዋም ከዚህ በፊት በማህበር አደራጂነት ምንም ልምድ የሌላትና ድርጅቱን ለረዙሜ ማመቻቻ ለማድረግ የተነሳችው፣ ቀደም ሲል ተመራጭ ነኝ በሚለው ባሏ አማካኝነት ዘ ላየን ራይደር የተባለውን የወጣቶች ድርጅት እኔ ካልመራውት በማለት ከመረዳጃው ማህበር እንዲሸሹት ያደረገችው፣ ወዘተ… ትገኝበታለች።

ሰፊው የዳላስና አካባቢው የኢትዮጵያ ተወላጅ ሆይ! ይህንን ሴራ ዛሬውኑ ምላሽ ካልሰጠኸው ነገ የምትነካው ላይሆን ስለሚችል ጉዳይህ የማድረግ የአንተና  የአንተ ብቻ ነው።

ባለፈው እንዳስነበብናችሁ የእድሩም ጉዳይ ውኃ እየበላው ነውና ከከፈላችሁት ገንዘብ የተረፈውን ወይ በጊዜ መካፈል አሊያም በስማችሁ ለበጎ አድራጎት ለሚከውኑ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ብትዶሉት እርባና ይኖረዋልና ከዚሁ ትኩረትን ስጡት። ከኪሳራ ያልወጣና ሊወጣ ያልቻለ ማህበር ነው። ይህን እድር መደጎም ማለት የተቀደደ በርሜልን ውኃ ሲሞሉ መኖር ምርጫ የናንተው ነው እንላለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?  

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ!
ለአሲምባው ደመላሽ መልስ።
አሁን የምትለኝ አቶ ተኮላ ወደ አሲምባ የመጣው መንግስቱ ሃይለማርያምን ተቃውሞ ነው?
ሰው አንዳይስቅብህ። እኔ አቶ ተኮላ ጋር ቅራኔ የነበረኝ ቤተክርስቲያን ስለከሰሰ እንጅ ወታደር ስለነበረ አለነበረም።አንተም ቤተክርስቲያን የሚከስ የምትደግፍ ከሆነ ከከሳሾቹ ውስጥ አንተም አለህበት ማለት ነው። ልጠይቅህም የምፈልገው ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው?
የሃይማኖቱ ጥላቻ! ወይስ ከቤተክርስቲያኑ ካሳ ለመብላት?አሁን ወደ ዋናው ድንቢጥነት እንመለስና፡ አንተው የረዳህ መስሎህ አጋለጥከው። የአየር ወለድ ወታደሮች፤ በእድሜያቸው የገፉ በወታደርነት የሰለጠኑ እንደመሆናቸው መጠን እንኳን አንድ ወታደር ቀርቶ በስሜት የተገፋፋ መረን (Mob) የማይፈጽመውን መሳርያ ባልያዙ ገና ሙሉ አቅመ አዳም ባልደረሱ የአየር ሃይል ካዴቶች ላይ የፈጸሙት ድብደባና ባዶ ካምፕ በመትረየስና በታንክ መክበብ ሙያ መስሏቸው በጊዜው የነበረውን የእንዳልካቸው መኮንንን መንግስት ለመደገፍና ንቅናቄውን ለማፍረስ ያቀዱት ተግባር እንዳልሆነ ሲያውቁና እውነተኛው የኢትዮጵያ ወታደር ሲጥጋቸው የለበሱትን መለዮና ያደረጉትን ጫማ ሳይቀር ወርውረው የሴት ልብስና ለምድ ለብሰው ባዶ እግራቸውን ነፍሴ አውጭኝ ያሉ ናቸው። በዚያን ጊዜ መንግስቱ ሃይለ ማርያም የሚባልም ስም እንዳልነበረም አረጋግጥልሃለሁ። በዚያን ሰአት ገዥውም ጃነሆይ ጠቅላይ ሚኒስተሩም እንዳልካቸው መኮንን ነበሩ። ንደዚህ ያለውን ሰው ነው እንደዝነኛ አድርገህ አሲምባ መጥቶ መንግስቱን ተዋጋ የምትለን። መንግስቱ ሃይለ ማርያም ህጻናትን አልገደለም ህጻናትን ያስፈጀ ኢህአፓ ነው። አትሳሳት መንግስቱ ሃይለ ማርያምን መደገፌ አይደለም እውነቱን ለመናገር ነው። የሃይሌ ፊዳን አቋም ተመቃዋሚ በማስመሰል እንድ የማይረባ ያልተማረ የቀበሌ ዘበኛ ገድላችሁ የሰፈሩን ህጻናት እንዲረሸኑ ማድረግ ተገቢ ነበረን? ወይስ ጠጅ ቤት ገብቶ መፎከርና መጥፋት ምን ለማትረፍ ነበር ድሃ ለማሳሰርና ለማሰቃየት ካልሆነ በስተቀር። ተኮላ እናንተ ጋ አሲምባ መምጣቱ ነፍሱን ለማዳን እንጅ መንግስቱን ለመቃወም ነበር እንዴ?። እስቲ ምን ምን ተግባር ምን ጀብዱ የሚያሰኘው ነገር መስራቱን በሚቀጥለው ጽሁፍህ አብራራልን። እሱን የሚያክል ወታደር በእድሜም ሆነ ባሰለጣጠን ከማይወዳደሩት ህጻናት ስር ወድቆ በናንተ መመራቱ ውርደትን እንጅ ጀብዱነትን መስራት ከሆነ ይሁንልህ፤ በርታ ስሙን አጥፋለት። በ እኔ አስተያየት አንድ ወታደር ለቆመበት እምነቱ መጋደልና ማሸነፍ አለበለዚያም መሞት እንጅ እንደናንተ ያሉ እንኳን ፖለቲካ ቀርቶ አቋም እንኳ የሌለው የኢትዮጵያን ህጻናት ማስጨረስና አገር ለማስከበር የዘመተው ወታደር ስንቅ ላይ ጠርሙስ ፈጭቶ የሚከት ደካማ ወጠጢወች ውስጥ መደበቅ አሳፋሪና ገመና አጋላጭ ነው።
እንደዚህ ያለ ግለ ሰብ ጋር መነጋገር ቀርቶ እውቀዋለሁ ማለት እንኳ አሳፋሪ ነው። የዚህ አይነቱ ግለ ሰብ እንኳን ቤተ ክርስቲያን መክሰስ ቀርቶ ሌላም ብዙ ነገር ቢያደርግ የሚያስገርም አይደለም። በሌላው በኩል ክርስቲያን ለመምሰል ታላቁ ገታችንን መጥቀስህ ምና ይባላል። በተአምሩ ያማታምን ከሆነ ምን የሱን ስም አስጠራህ። አበበን ጌታ መላኩን በ ፓሊስ ምስል የላከለት መልካም አገልጋዩ ስለሆነ ነው። ለ እንዳንተ አይነቱ ቤተክርስቲያን ከሳሽና የሰው ሃጢአት በየ
ታክሲው ላይ በታኝ መልአኩን ልኮ ከመጥፎ ተግባርህ እንድትመለስ ከማድረግ ይልቅ ተገቢህን ይልክልሃል። መልእክቱንም ባይናችን አይተናል። አንተና ጓደኞችህ እነተኮላ አወን በእግዚብሄር አታምኑም፤ አንዴ ማርክሲስት ሲመች ክርስቲያን በሊላ ጊዜ የትግራይ ነጻ አውጭ እያላችሁ ባልኖራችሁ ነበር። ቤተክርስቲያን መክሰስ ምን ለማትረፍ ነው? ቤተክርስቲያን መበጥበጥ፤ ቀሳውስት መሳደብን ምን አመጣው? ከቀሳውስት አልፎ ጳጳስ መሳደብ “ አገር ጥሎ የሸሸ
እያላችሁ “ መዝለፍ ማንን ለማስደሰት ነው? እውነት አእምሮ ካለህ! አስበው ለምን መልአኩን ላከለት? ለምን መጥፎ ተግባር ከመፈጸም አዳነው? ለምን ያሰበውን በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርስበት ይችል ከነበረው አደጋ ሁሉ አዳነው?
መልሰህ መላልሰህ አስበው።

ዮናስን ለምን አሳ ነባሪ ላከለት? እግዚአብሄር ለሚወደውና ለሚያገለግለው ብዙ ክጥፋት መዳኛ መንገድ ይከፍትለታል።
ፖሊስዋ ባትላክለትኖሮ አንዷን (Drug addict) አግኝቶ ግብረ ስጋ ቢፈጽም፤
1፤- የአምላኩን ተእዛዝ አፈረሰ ማለት ነው ምክንያቱም ዝሙት አሰበ ከማለት ይልቅ ዝሙት ፈጸመ ማለት ነው።
2፤- ከዚሁ ዝሙት ጋር የሚመጣው ኤይድስ በሽታ ቢይዘው ምናልባት ያልተጠራጠረችውን ባለቤቱን የልጆቹን እናት በከለ ማለት ነው።
3፤- ይህን ዝሙት በሚፈጽምበት ጊዜ ሊደርሱ ከሚችሉ አደጋዎች አንዱ የሴተኛ አዳሪዋ በላቤት (Pimp) ሊዘርፈው ይችላል በዚያውም አኳያ ሊገድለው የችላል፤ባይገድለውም አንድ አካሉንም የማጣት አደጋ ሊገጥመው ይችላል። ከዚህ ሁሉ አደጋና ሃጢአት ውስጥ ከመግባቱ በፊት በቀላሉ ምናልባት በገንዘብ ክፍያና
በማስጠንቀቂያ ብቻ መመለስ ለ እንዳንት ላለው በሃጢአት ለተዋጠ ምንም አይመስለው ይሆናል። በእግዚአብሄር ማመንና እግዚብሔርን ማገልገል ግን ይህን አይነት ውጤት ያመጣልና አንተም ክስህን ትተህ አንዱ ጓደኛችሁ እንዳለው “እባካችሁ ሃጢአት በዛ” ብላችሁ ፊታችሁን ወደ አምላካችሁ አዙራችሁ ጸልዩና ምን አይነት መልካም ውጤት አንደምታገኙ ታያላችሁ።
በዛውም አገር ቤት ላስጨረሳችኋቸው ልጆች አምላክን ተንበርክካችሁ ይቅር በለን ብትሉ መሃሪው ፈጣሪያችን ይቀር ይላችኋልና።
አምላካችን ሆይ! ልቦናችንን ወደ ደጉ ተግባር ምራን! እነሱንም እባክህ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እባክህ፤
አሜን!
January 8, 2011 10:27 AM
Delete

ከዚህ በላይ ያስነበቡን ተሳታፊያችንን ከልብ እያመሰገንን፣ ከመመካከላችን መስራችና ረዳት አዘጋጃችን የሆነው ወንድማችን ላልተወሰነ ጊዜ ለግዳጅ ስለተለየን በሔደበት ሁሉ ቸሩ ፈጣሪያችን መሪና ጠባቂ እንዲሁም ደጋፊ ሆኖ በድል እንዲመልሰው የዘወትር ጸሎታችን ነው። የተወደዳችሁ የገጻችን ታዳሚዎችም በጸሎታችሁ ታስቡት ዘንድ እንጠይቃለን?

Semper fi!!

Wednesday, January 5, 2011

We request your patience while fixing the security compromise on this page. Thanks

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና! ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።

Tuesday, January 4, 2011

ኸረ ማን እንበላችሁ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የኢትዮጵያ ሕዝብ የልቡን የሚገልጽበት እድል ሲያገኝ የኢሕአፓን እውነተኛ ታሪክና መስዋእትነትን ይናገራል!

ከዚህ በላይ ያለውን ጥቅስ የወሰድነው ከአሲምባ ድኅረገጽ ሲሆን እኛ በጥያቄ ምልክት የምናልፈው ይሆናል፤ አንባቢዎቻችን ደግሞ የእራሳቸውን ግንዛቤ ይወስዳሉ እንላለን።ሃማ ቱማ የተባሉት የገጻችን ተከታታይ የታወቁ የኢሕአፓ ገጣሚና ቀንደኛ ዘካሪ ለኛ የሚጥፉት ይኖር ይሆን? ጥሁፋችንን አምነው ነው ዝምታን የመረጡት ወይስ ብዕራቸው ነጠፈ?

እኛ ተኩላው በገጹ ከሚያለቃቅስ እውነቱን ይዞ በብዕሩ ቢሟገት፣ ገጻችን እርሱንና ቢጤዎቹን ያለ አድሎ እንደምታስተናግድ ዛሬም መልሳ ታረጋግጣለች። በሀሳብ መለያየትና መሞገት አዋቂነት ነው። ሲነገረን የኖርነው ድርጅቱ ለሀሳብ ነጻነትና ለውይይት ያመቸ ነበር የተባልነው፣ ዛሬ ግን የተቃራኒ አቋም የሚጓዝ ጭፍንና ለሥልጣን  ብቻ ያነጣጣረ ነው። ኢሕአፓ ሥልጣን ያዘ ማለት መንግሥቱ ኃ/ማሪያምን መመለስ ማለት ነው። ከላይ ወደጀመርነው ጥቅስ ስንመለስ በሀገር ውስጥ ያለውን ዘለን በምዕራቡ አለም ያለው ኢትዮጵያዊ ያለምንም ሥጋት ስለ ኢሕአፓ በስፋት እየደለቀው እንደሆነ ገጻችን የመረጃ ምሳሌ ነው። የእኛ ገጽ በሚገባ ማንነታችሁን አስቀምጦ ይገኛል።

በኮምኒዝም እምነትና አላማ በወጣትነት እድሜው ጭንቅላቱን በርዛችሁ፣ ከወላጆቹ ነጥላችሁ፣ ቡቃያ እድሜውን አበላሽታችሁ፣ ለሰቆቃ ዳርጋችሁ፣ በየአደባባዩ አስረግፋችሁ፣ ሌላውንም ከቄው አስኮብልላችሁ፣ ለናንተ ሎሌ አድርጋችሁ፣ ጋሻና መከታ ሽፋናችሁ ሆኖ እንዲሰዋ ያደረጋችሁ፣ እናንተ ምርጥ በልታችሁና ጠጥታችሁ እርሱንና እርሷን በጥሬ አውላችሁ ያሳደራችሁ፣ ያለፍላጎቷ የደፈራችሁ፣ ጥያቄ ያቀረበን አንጃ እያላችሁ መራራ ስቃይ ብሎም ሕይወቱን የቀጫችሁ፣ የጫካ ንጉሥ የነበራችሁ፣ ኸረ እናንተን ማን ብለን እንጥራችሁ? የትኛው ነው የናንተ ጀብዱ የሚወሳላችሁ? የትኛው ታሪክና መስዋዕት ነው የሚዘከርላችሁ? ኸረ እናንተን ምን ብለን ከምን እንጀምርላችሁ? ዛሬም የትላንት ኮሚኒስቶች የሀይማኖት ካባ ለባሾች፣ የፈጸማችሁት በደል ጸጽቶ በንስሀ ያልተመለሳችሁ፣ አሁንም ካለፈው ያልተማራችሁ፣ ዛሬም ለሥልጣን የቋመጣችሁ፣ በካህናት መካከል ሳይቀር ገብታችሁ የከፋፈላችሁ፣ ከደርግ ሸሽታችሁ በገዳም ተሰውራችሁ፣ የተቀበላችሁትን ክህነት ያላከበራችሁ፣ ዛሬም ለሥልጣን ጥመኛ ሀይማኖት ከፋፋይ ቂመኛ፣ሰርጎ ገብ ሸረኛ፣በምዕራቡም ሀገር በሽታኛ፣ ደብር በጥባጭ ሱሰኛ፣ እምነት የሌለው መጋኛ፣ ኸረ እናንተን ማን ብለን እንጥራችሁ? ምንስ ማዕጸን አወጣችሁ፣ ከአንድ ትውልድ አልፋችሁ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ትውልድ እንዲጠፋ የቆማችሁ፣ የሀገር ጥፋት ነው ወይስ የትውልድ ነቀርሳ፣ መርግም ናችሁ ወይስ አበሳ? ኸረ ማን እንበላችሁ? ዘመንም ሆነ እድሜ ያለወጣችሁ፣ የሰው ሰቆቃ የመይሰማችሁ፣ ጨካኝና እርጉም የሆናችሁ፣ ኸረ ምን እንበላችሁ? እውነትና ሀቅ የማትቀበሉ እናንተ ማናችሁ? ጊዜም የማይሽረው ልክፍት የያዛችሁ፣ በሽታችሁን ሲነግሯችሁ የምትክዱ፣ የሀሰት ስም የምትለጥፉ፣ሴሬኛ ትውልድ አንገት የምታስደፉ፣ኸረ እናንተ እነማን ናችሁ? ማን ብለን እንጥራችሁ? ለቅጣትና ለመከራ የተፈጠራችሁ፣ አምላካችን ይቅር ይበላችሁ፣ ከአጽራረ ቤተክርስትያን  ሕይወት ያውጣችሁ፣ መልካሙን ልቦና ይስጣችሁ፣ ለንስሀ ሞት ያብቃችሁ።

እርሶስ ምን ይላሉ?

የህን መለክት እፊት ላይ እንዲለጥፉልን እንማጠናለን።

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


Anonymous Anonymous said...

ጸሃይ ጽድቅ ተተባለ ግለሰብ ካሁን ቀደም በኢትዮጵያ ውስጥ የድሮው የደርጉ የግፍ ዝነኛ የነበረው የ አምሳለቃ ለገሰ አስፋው የግል አንጋች ወታደር የነበረ ብዙ ህጻን ልጃገረዶችን ክናታቸው ጉያ ውስጥ እየጠለፈ ለአለቃውና ለግብረ አበሮቹ ከማቅረብም ሌላ እናቶቻቸውን
በግድ “Rape” ያደርግ የነበር። ብዙ አቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች በመትረየስ የፈጀና ያስፈጀ የደርግ ወታደር እንዴት እንዳመለጠ ሳይታወቅ ወደ አሜሪካ መጥቶ አሁን የቅዱስ ሚካኤልን
ቤተክርስቲያን ከከሰሱት ውስጥ አንዱ መሆኑን የሚያውቁ፤ሰሞኑን በነበረው የሟችቱን ወ/ሮ ሃዘን ለመካፈል የተሰበሰቡትን ሃዘንተኞች ሳይፈራና ሳያከብር በወንድማችን በ አቶ አበበ ላይ የለመደውን አደጋ ላይ የመጣል ተንኮል በማናለብኝነት ለጓደኞቹ ለማህበር ቅዱስን ሲያስተምር ማምሸቱን ሰምተናል። በጣም የሚገርመው! ሃዘን ላይ የተቀመጡትን አዛኞች እንኳ ሳይፈራ አካኪ ዘራፍ ሲል አብረውት የነበሩት ማህበር ቅዱሳናት ሲያወድሱትና ሲያደፋፍሩት ማምሸታቸውን የተመለከቱ ሁሉ እየታዘቡ ምን ቤት ነው የመጣነው እያሉ ውልቅ ውልቅ እያሉ መሄዳቸው ታውቋል።
ይህ በብዙ ኢትዮጵያውያን ደም የታጠበ ፍርድ ሸንጎ እንደ አለቆቹ መቅረብ ሲገባው እንዴት አምልጦ አሜሪካ እንደገባና እየደጋገመም ወደ አዲስ አበባ ሲመላለስ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንዴት እንዳልያዘው ባይገባንም! በኢትዮጵያዊነታችን የወንድሞቻችንን፣
የእህቶቻችንን፤ያባቶቻችንን፤ የናቶቻችንንና የጓደኞቻንን ደም በከንቱ ፈሶ እንዳይቀር ማድረግ መብታችን ስለሆነ! የዚህኑ የደርግ ወታደር ጸሃይ ጽድቅን ቢቻል የድሮ በዩኒፎርም ያለ ፎቶግራፍ ባይቻልም አሁን ያለ ፎቶግራፍ “ Name and Shame”
http://www.march4freedom.org/warcriminalsupporters/register.php በሚለው ብታወጡልን እኛም በበኩላችን ለሚታወቁት ጋዜጦች ሁሉ አባዝተን በዚሁ ግለሰብ (አናት፤ አባት፤ እህት፤ ወንድም፤ልጅ፤አጎት አክስት፤ ጎረቤት) የተገደለበት፤ ራፐ የተደረበበት፤ የታሰረበትን ሁሉ ፈልገን ወደ ፍርድ ሸንጎ ለማቅረብ እንዲቻለን እንድትተባበሩን ይህን መልእክት እናስተላልፋለን።
ሰሞኑንም አዲስ ብሎግ ከፍተን የሄን ግለ ሰብ ብቻ ሳይሆን ብዙ የሱ አይነት መታሰርና መገደልም ሲገባቸው አሁን ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ወደ አሜሪካና አውሮፓ ሸሽተው እንዲኖሩ ዲ.ቪ እየገዛ የላካቸው ብዙ ስላሉ፤ እንሱን እየተከታተልን አንድ ምስክር እስካለን ድረስ በፍርድ ቤት የአሜሪካንም ሆነ የአውሮፓን ነዋሪነት አስፍቀን ቢቻል ማሳሰር ባይቻል ካገር ማባረር መብታችን መሆኑንና ለዚሁም የተቋቋመ ብዙ ድርጂት ስላለ የምንፈልገውን
እርዳታ ሁሉ በቀላሉ ማግኘት ስለምንችል፤ልትተባበሩን የምትፈልጉ ሁሉ በዙሁ በዳላስ ኢኦትሲ ብሎግ ድጋፋችሁንና አሳባችሁን ብትለግሱን በጣም ደስ ይለናል። ሰሞኑን እያከታተልን የደረስንበትን እናስታውቃችኋለን። የዳላስ ኢኦቲሲ ደራሲወችንም እባካችሁ የህን መለክት እፊት ላይ እንዲለጥፉልን እንማጠናለን።
ጥላቶቻችንና ተንኮል አሳቢዎች ሁሉ እንዲጠፉልንና ሚካኤል የሰይፍ ቁጣ እንዲያሳይልን
እንለምናለን።
አሚን።
January 3, 2011 8:12 AM

Monday, January 3, 2011

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንድምን አላችሁ? በእርሱ ፈቃድና ፀጋ መልሰን በዚህ ጦመራችን ላገናኘን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብርና ምስጋና ይሁን። አሜን።

ባሳለፍነው የአመቱ መጀመርያ ዕለተ ሰንበት በደብራችሁ ለሚደረገው የአመራር አዲስ ተጠቋሚ መጠናቀቁን ከሚካኤል ሠይፍ ተወካይ ቢደርሰንም የተጠቋሚዎች ሥም ወደፊት ይወጣል። እኛም አስተያየታችን ወደፊት ይታከልበታል። ቅዱስ ሚካኤል የሚበጁትን ይምረጥ።

ምሽቱንም እንዳለፈው የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ ያልናቸው የኢሕ አፓ አባላት መልሰው ተሰብስበው እንደነበር ቢገለጽልንም፤ እውነትን ከመደበቅና ለመሸፋፈን ከመራሯጥ በገሀድ ከወገኖቻቸው ጋር ተቀምጠው በመወያየት በወቅቱ በመካከላቸው በአንጃነት ለተገደሉት ወገኖቻችን ቤተሰቦችና ለተቀሩትም በምክንያት ላለፉት ጭምር የልጆቻቸውን ማለፍ በማስታወቅና እልባት እንዲያደርጉ መንገድ መፈለጉ አማራጭ የሌለው ለሁለቱም ወገን የሚጠቅም እንጂ ገዳዮችን ………መፍትሄ አያመጣም እንላለን። እርቅና 
 ለአማኝም ንስሀ የሚገባ ነው።

በሰንበቱ የዳላስ መረዳጃ ሬዲዮ እንደ አዲስ አበባው መብራት ብልጭና ድርግም እያለ ያስተላለፈውን ቅጂ ከዳላስ ወዳጃችን ደርሶናል። የመቆራረጡ ችግር የሙያ ብቃት የጎደላቸውና ራሳቸውን ለማሻሻል የማይቃጡ ግለሰቦች መሆናቸውን አስመስክሯል። በተለይም ለረዥም ጊዜ ስርጭቱን አንቀው የያዙት ግለሰቦች የግል ፍላጎትንና ማን አለብኝነት ትምክህት በገሀድ እያስመዘገቡ መቆየታቸውን ዛሬም እየደገሙት ይገኛል። የበላይ ታዛቢም ሆነ ተቆጣጣሪ የሌለው እንዲሁም አላማውን የሳተ መሆኑን በሚገባ አረጋግጧል። ይህን ለማለት ያነሳሳን ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ፣ አድጎና ተምሮባት፣ አለም ያየበትን ሀገር ክዶ በመኮብለል አልፎ ሲወጋት የኖረውን ግለሰብና ግባተ መሬቱንም አስመራ ላይ ያደረገውን ሲያወድስበት ተደምጦበታል። እኛ ሟቹ ለዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አበረከተ ብለን ምሳሌነቱን የሚያስመዘግብ ነጥብ ስላጣን የሬዲዮናችሁ ዝከራ ጥያቄን ማን ይመልስ? ወይንም ለኮሚኒቲው የሚጠቅም መልዕክት ጠፍቶ ነውን? በማለት ይህ አይነቱ በኢትዮጵያ ተወላጆች ላይ የሚደረግ ንቀትና መብት ዘረፋ ብቻ ሳይሆን በኮሚኒቲው ሀብት የሚደገፈውን የራዲዮ ስርጭት ለንግድና ለትርፍነት ብሎም ለጠላት መሳሪያነት እየተቸበቸበበት ይገኛል። ባለፈው የመረዳጃ ማህበር የኢትዮጵያ ቀን አሰያየም አስመልክቶ በአመራሩ ላይ ላቀረብነው ዘገባ ጥፋቱን አምኖም ሆነ ክዶ አልያም ለምን ያን አቋም እንደወሰደ ምላሽን ከመስጠት ማፈግፈግ ማንነቱን እንዲሁም የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛነቱ አረጋገጠ። ዛሬም በራዲዮ ስርጭቱ ደግሞ አስረገጠ። ይህ አጠቃላይ አመራር የቅጥረኛ ስራው የወጣቶችን መደራጀት በመዳፉ ለመጨበጥ ቢከሽፍበት፣ ድርጅቱን ለማጥፋት በግልጽና በስውር እልቀመሳፍርት እንቅፋትና ፈተና አሁንም እየደነቀረባቸው ቢሆንም፤ ድርጅታቸው ከቅዱስ ሚካኤል ደብር ጋር በመተባበር በ2011 ሊጀምሩ ያቀዱትን tutorial program እንዳይሳካ፤ በመካከላቸው መከፋፈል እንዲፈጠርና እንዲበተን ጥረቱ የከሸፈበትን አመራር ፈጽመን መለወጥ ለነገ የማይባልና የማይዘለል ግዴታን መወጣት የዛሬ ግዴታ ነው። የመረዳጃ ማህበሩም ሆነ የሬዲዮው ስርጭት የናንተውና ለናንተው በናንተው እንጂ በከሀዲና በአጭበርባሪ ቅጥረኞች መነጠቅ የለበትም።

ስለታክሲ አሽከርካሪዎች የቀረበው ዘገባ የሚገባውን ያህል ያልተዘገበ ነው። ምክንያቱም አሽከርካሪዎቹንም ወክለው ከተደመጡት ውስጥ ሱራፌል የተባለው ግለሰብ የለየለት የትግሬ ነጻ አውጪ ቅጥረኛ ነው። ከዚህ በፊት በወዘሮ የሐረር(የኢትዮጵያ) ወርቅ ጋሻው ላይ የመረዳጃ ማህበራችሁን ወክለው ተመርጠናል በማለት “የካንጋሩ ኮርት“ ፍርድ ቤት  አርክቴክተር ውስጥ አንዱ የነበረ፣ ይህንኑ ፍርድም በዚሁ የሬዲዮ ስርጭት ሪዞልሽን ብሎ የተረከ፣ በቅርቡም ከ60 ሺህ ዶላር በላይ ከእነዚሁ አሽከርካሪዎች የተሰበሰበ ገንዘብ ምዝበራ ተጠያቂ የሆነ። ይህን የዘመን መለወጫ ሥራ ማቆም አርክቴክት የሆነችውንና የተዘጋባቸውን የብረት መዝጊያ ያስከፈተችላቸውን ወይዘሮ የሐረርን አንዴም በሬዲዮ ምስጋና ከመጥቀስ ይልቅ የሬዲዮ ዝግጅቱን ብቻ የሚያወድስ ሲሆን ፤ መንገሻ የተባለውም ተጠሪ አንድም አላለም።


ግለሰቧ ያላትን ችሎታ ዛሬም ደግማ ብቃቷን ያስመዘገበችውን እህት ጊዜዋን፣ ዕውቀቷን ያለአንዳች ክፍያ የሰጠችውንና ጠበቃቸው ያቃተውን የከወነች የአደባባይ ጀግናን ለአገልግሎቷ እውቅና መንፈግ የሚቀጥለውን የትግል ደረጃ የእርሷን መሪነት እንዳያሳጣት እያሳሰብን አስቸኳይ እርምጃና ማስተካከያ ከተረጂ ወገኖቻችን ይጠበቃል እንላለን። ከዚህ ቀደም ሲኮንናትና ሲፈርድባት የቆየውና በተልኮ ዳላስ የገባው ሱራፌል የተባለውን የጥፋት መልክተኛ፣ የረባ ትምህርት የሌለው ከወይዘሮዋ ማራቅና በትምህርት፣ በዕድሜ፣ በእውቀት፤ እዚህም ሀገር ለራዥም ጊዜው በመቆየት social culture and good English language skill ያካበተና ያለውን ነባራዊ ችግር አጉልቶ የማስረዳትና ጥሩ communicator በመሆን ያለባችሁን ችግር አስወጋጅ አምባሳደራችሁ መሆን የሚችል መሆን ይገባዋል። ለወይዘሮ ሐረርም የምትመካበትና በdisposes ያለ arsenal በመሆን ያለማችሁትን በቅርቡ ድልን ያጎናጽፍላችኃል።

የአካባቢን ብክለት በተመለከተ ባለሙያዎች ብንሆንም የታክሲ መኪና አሽከርካሪዎችን ባለ 4 ነጥብ አቀራረብ ጠለቅ ያለ ድርድርን የሚጠይቅ ሆኖ፣ ሕግ አውጪውም ሆነ አስፈጻሚ ወገን በመረጃ የተደገፈና በብሔራዊ ደርጃ ተቀባይነት ያለው መሆን ይገባዋል ። CNG compressed natural gas vehicle ከ200 ማይል እርቀት በላይ የማይጓዙ፣ ውስን የመቅጃ ጣቢያዎችና አብዛኛዎቹ ጋዙን የመልቀቅ ችግር፣ እንዲሁም ሕግ አውጪው ክፍል እራሱ የራሱ የሆኑትን በሙሉ ለውጣልን? ግለስቦቹ Owner operator በመሆናቸውና ከአንድ በላይ ስለማችሉ አቅም ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከመንግሥት የሚያገኙት ሪቤት መጠን እንዲሁም መኪናውን ያመረተው ፋብሪካ Warranty be voided case of tampering እና ማን ሀላፊነትን ይወስዳል? አሁን የጋዝ መኪናዎች እድሜ ለአምስት አመት ከሆነ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የአገልግሎት ዘመን ዕድሜ፣ የአካባቢን ብከላን ለመቀነስ  በእህት ከተሞች ልምድ መውሰድ፣ ይህን የመሳሰሉትን ጥያቄዎችን ከድርድሩ ውስጥ ለማስገባት መሞከር ተገቢ ነው።

ሌላው ያስደመጡን ቢኖር ስንጥፍበት የነበረው በመረዳጃ ማህበሩ ጥገኛ የሆነው የእድር ሊቀ መንበር ተብዮው ያቀረበው ትምህርት አይሉት ልመና ነበር። እስከ አሁን 80 ሺህ ከፍያለሁ የሚለው እድር ከተጀመረ እስካሁን ይሁን ያለፈው አመት ብቻ አላብራራም። እስካሁንም ጥንካሬውን ለመገምገም በባንክ ምን ያህል ጥሬ ገንዝብ እንዳለውና የአባላቱንም ቁጥር ያላካተተ አሀዝ ጥርጣሬን ያመጣል እንላለን። በኛ መረጃ ግን 400 አካባቢ ደርሶ የነበረው የአባላት ቁጥር ክፉኛ አዘቅዝቆ ይገኛል። ቢወተወቱም መስራች አባሎችን ጨምሮ እምቢኝ ብለዋል። ጥያቄዎቻቸውም አይስተናገዱም። አንዳንዶች እንደሚሉት በትግራይ ነጻ አውጪ ቅጥረኞች አመራር፣ ለኮሚኒቲው የሚከፈለው 40 ዶላር ጥያቄ፣ ኮሚኒቲው እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን በእኩልነት አለማስተናገድ፣ በአመራር አካባቢ ያለግለስብ ሚሽት መቀጠር፣ ሌላም ሌላም ተጨምሮበት መሆኑን የሚደርሱን አስተያየቶች ይጠቁማሉ

እርሶስ ምን ይላሉ?

በጸለምት የደረሰው መበታተን በዳላስ ተደገመ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።



ተኩላና ብዕሩ በከፊል ይህንን ይመስላል። የእንቅቡ መንጣጣት በትላንትናው ምሽት በዳላስ ተሰብስበው  ነበር። በጸለምት የደረሰው  መበታተን በዳላስ ተደገመ። ዛሬ የሚረሽኑበት የትግራይ ጫካ የለ ። የገዳዮች ለምድ ሲከፈት እንዲህ ይጀምራል።


ምነው ዳግም ጦ ርነት?
ተኮላ መ ኮንን
02/28/1999
የሳባ ጉዞ ምላሽ ምንሊህን ይዞ ሲተም ፣
ከፖርቹጊስ የጦር አጋር ከአሌክሳንደርያ ሥ ጋወደም ።
ከቱርክ ከድርቡሽ ወረራ ከግራኝ መ ሐመ ድ ስግደት ፣
ከቴዎድሮስ መ ቅደላ ከዮሐንስ የአንገት ስልበት፣
በሮም የዘርዓይ ድረስ ጎራዴ የሰላቶ ደም እልበት።
ለጣሊያን ነፍጥ በጋሻ ምትሽ፣
ጀግናሽ ከግራ ቀኝ ሲመ ክትልሽ።
ድል በድል ሆኖ አድዋ ላይ እልል ተብሎ ሲፎከር፣
ምነው ምኒልህ ፈረሱ ባሕር አጠገብ አድሮ በነበር።
ውጫ ሌ የተሻረው ውል አድዋ መፍረሱ ቀርቶ፣
አዶሊስ ላይ በነበረ ግጫ ነቅሎ ቄጤ ማ አንጥፎ ውኃ ነክቶ።
ፈረንጅ በገባበት ሁሉ የተከለው ተንኮል ሴራ ፣
ለዓመታት እኛም ላይ ሊያደራ?
እንደቆላ ቁስል ሊነፈርቅ እንደነቀርሳ ሊያንሰራራ?
ከከፋሽማ ተገንጠ ይ ካልጣ መ ሽ ቤታችን ቤትሽ ባልን፣
ለትግሉ እንዳልደማ ን ለነሱ ትላንት እንዳልሞትን፣
ይቅር መቼስ ተብሎ የሆነ ያልሆነውን እንዳልቻልን፣
የሕዝቡን ቁጣ እንዳልገታን እሮሮውን እንዳልዋጥን፣
ሚስት እንደነጠ ቀ አጉራ ዘለል ጣውንትነት ሊከጅሉን?
በጥይት ሊለበልቡን ባውርፕላን ሊያቃጥሉን?
በሞርተር ሊጨ ፈጭፉን በታንካቸው ሊዳምጡ ን?
ተው ሲሏቸው ካልሰሙ አውራው ከሆነ ንጉሳቸው ፣
ሠላም ማለት አቅሯቸው ጦር ከሆነ ዳንኪራቸው ፣
ወንድሞቼ ምርጫ ም የለ ክንዳቸሁን አሳዩአቸው ።
የተወጠ ረን ፊኛ እፍታ መ ች ይጎዳዋል፣
እስትንፋስማ ጌጡ ነው ወደ ሰማይ ይወስደዋል ።
ሲነኩት ነው እንጅ በመ ርፌ በቢለዋ በጉጠ ቱ ፣
የማያምረው አወዳደቁ መ ሽመ ድመ ዱ አሟ ሟ ቱ።
ተዋቸው ሲባሉ ከነገሱ ይብቃ ሲሏቸው ካበጡ ፣
ምንም ልመ ና አያሻም ወንድሞ ች የጠመ ቁትን ይጠ ጡ ።
ሰሚ ካለ ግን ጦ ር ይብቃ በሏቸው ዘፈናቸውን ይቀይሩ፣
«አደየ ጀጋኑ» ይቅርና ስለፈቅር ይዘም ሩ፣
ስለሰላም ተወያዩ በሏቸው መ ሃይሙ ን ያስተምሩ።
ከእጅ ወዳፍ የሚ ኖረው ን ያንን ጭ ቁን አርሶአደር፣
ዛሬም ያላለፈለትን የከተማ ው ን ላብ አደር፣
በግዴታ ተሰባስቦ የተከማ ቸውን ወታደር።
ምን አለ ሀሁ ቢያስተምሩት ሀ ግእዝ ለ ግዕዝ ፣
የጦር ከበሮ ከመ ምታት የትም ክህት ክራር ከመ ጠ ረዝ ፥
ምን አለበት «አሶ» ላይ ቢረባረቡ ፣
ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ ቢያቀርቡ ፣
ሚግ እየገዙ በየሜዳው ከሚ ከስሩ።
ሰውን የሚጎዳው ፍቅር እንጂ ጠብማ መ ዝጊያ በር ነው ፣
ትእግስት ሰላም ያዋቂ ፥ ጡ ጫ ብትር የመ ሃይም ነው ።
መ ሪዎች ትላንት ነበሩ አልፈዋል፥ የዛሬዎቹም ያልፋሉ፣
ምንም ነገር ቢፈጠ ር ሕዝቦች ግን ይኖራሉ።
እናም ለማያልፈው ሕዝብ እትብቱን ለበጠ ሰ ሰው ፣
ሠላምን እንስጠ ው እንጂ ጠ ላትነትን አናውርሰው ።
ለምነን ለምነን እንቢ ካላችሁ ፣
ከእውነት ይልቅ የዳንዴ ውሸት ከጣማችሁ፣
ለሃገር ሳይሆን ለግለሰብ ከቆማችሁ፣
የአማባ ገነኑ ደንገጡ ሮች ኩርኩማችን ያውላችሁ።


 ደህና ሰንብት አበጀ
ተፈጥሮም: የራሱን: ሂደት: እድግቱን: እየጠ በቀ፣
ያልታሰበ: እየፈጠ ረ: ገና: በጉዞ: ላይ: ያለውን: በድንገት: እየነጠ ቀ።
ያልተጠ ራበት: እየገባ: የማያውቀውን: ቤት: እየከፈተ፣
ዛሬ: ገና: ድል: መታ: ጀግናውን: ይዞ: ተካተተ።
ምንድነው: ሞት? ወንድሞች: መ ተንፈስ: ማቆም: ሕ ይወት: ማጣት!!!!!
ከመ ሃል: ጠ ፍቶ: መ ቅረት: መ ሰወር: ለዘላለም: መ ረሳሳት?
እንዲያ: ከሆነስ: አልሰመረም ፣
በጭ ራሽ; ግቡን: አልመታም ።
እጁን: ቢይዘው: ብቻውን: አግኝቶት: ከመንገድ: ላይ፣
ስሙ ንስ: አይቀብረውም: ታሪኩ: ሕያው: ነው ከሞት በላይ።
እናም: አንቀበልም: ሞትህን: የሞ ተስ: ታሪክ: ያልሰራ፣
እኛ: አናወራም: መ ቀበርህን: የሚ ቀበር: በተግባሩ: የማይኮራ።
በምግባሩ: የማይተማመን: ባደረገው: ሁሉ: የሚ ያፍር ፣
በተናገረው: የሚ ጸጸት: አንገቱን: የሚያቀረቅር፣
ያንተ: የሚያኮራ: ነው: አበጀ: በሕይወት: ሳለህ: ሳንናግር: በሞትህ: ሳልስት: እንመ ስክር።
ለሕዝብ: መ ቆምን: መ ርጠ ህ: የግል: ጥቅምህን: ኌላ: ብለህ፣
ከላብ: አደሩ: አብረህ: ከአርሶ: አደሩ: ተቀላቅለህ ፣
እንደሌላው: ሳትመ ጻደቅ: እንዲህ: እኮ: ነበርኩ: ብለህ፣
በአላማህ: ሳትዋዥ ቅ: በእምነትህ: ሳትደራደር፣
ባልመ ሰለህ: ፍርድ: ላይ: ባለመ ስማማትህ: ሳታፍር።
ም ነው? ዛሬ: ታዲያ: ጔድ: አበጀ: ገና: ድፍርሱ: ሳይጠራ፣
የተንከራተትክበት: ሜዳ: አቀበት: አንተን: መ ሰል: ሳያፈራ፣
ወገብህ: ገና: ሳይጠ ና: መንገድ: የጎዳው: እግርህ: ሳያገግም ፣
በሩጫ : ላይ: እንዳለህ: በድንገት: እንዲህ: ታዘግም ።
በሰላሙ ም: በትግሉም: ሁሌ: ታጥቀህ: እንዳልነበር፣
ዛሬ: ትጥቅህን: ትፈታው: መንገድ: ጥለኸ ው: ትቀበር።
እኔ: አላምንም: ይኸንን: ለሰውም: እንዳትነግሩ፤
ሞቷል: ሲባል: የኖረ: ሰው: አለ: ሲባል: ልትቀብሩ?
አብረን: ስንኖር: እስከ: ዛሬ: ያላወቅሁት: ቅር: ያሰኘኝ፤
ኢትዮጵያዊነትህን: እንጂ: አማራ: መ ሆንክን: ሳትነግረኝ።
ደህና: ሰንብት: ኮሎኔል: አለማ የሁ: እንዳለቃ: ሰላምታ: ልስጥህ፣
ደህና: ክረም: ጔድ: አበጀ: እንደታጋይ: ልሰናበትህ፣
ለታጋይ: አያለቅሱማ: ይላሉና: እኔም: አላለቅስልህ፣
እንደጔደኛ: ሆኜ: ግን: መ ጎዳቴን: ልግለጽልህ።
ተኮላ: መ ኮንን
November 10th 2000


 ለብርሃኑ ነጋ
ተኮላ መኮንን
ዳላስ ቴክሳስ
05/15/2006
የልጅነት ዘመ ን አንደዋዛ ሳይጫ ወቱበት እያለፈ፤
ሰኞ ማ ክሰኞ ሳይባል አስፋልት ላይ፤ እድሜ እንደ ቀልድ እየከነፈ።
በጊዜው የነበረ የትግል ግዳጅ ወጣ ትነትን እየበላ፤
ለግላጋ ጣቱን ለቃታ ሰጥቶ ፦ ለስላሳ እግሩን በፈንገስ እያቀላ።
«መ ዝሙር ዘፈኑን ተክቶት» ኮረዳ ማየት ቀርቶ፣
ባክስት ባጎት በወንድም ምትክ፦ ጔድ መባል ተተክቶ፣
አባት እናት ተረስተው ፦ቤት ንብረት ባገር ተሞልቴ፤
ትምሕርት ቤት በገባር ጎጆ ፦ ህክምናው በአኩምፓቸር ተቀይሮ፤
በእንጀራ ምትክ በቆሎ ተበልቶ፦ሆድ በበለስ ተወጥሮ።
ለቅንጦት ሲባል ተልባ፦ ለጉዝጔዝ ሲባል ሃምሊ ተበልቶ፣
ካልጋ ወርዶ ካንሶላ ቁራጭ ላይ ተኝቶ፣
ባልጠና ወገብ ዝናር ታጥቆ፦ በልጅነት ጫንቃ ብረት አንግቶ።
ገና ከትግሉ ሲቀላቀል መስዋእትነቱን ተቀብ ሎ፣
ኑዛዜውን ለጔዶቹ ትግሉን ቀጥሉ ብቻ ብሎ ።
አገር ለራስ ቅንጦ ት ሳይሆን፦ ለሕዝብ እኩልነት መ ሆኑን አምኖ፤
ላብ አደሩን ነፃ ሊያወጣ ከአፈር ገፊው እኩል አፈር ዘግኖ፤
ከቤት ከቀየው እርቆ በዱር በገደል ፈንኖ።
ለዓላማ መሞት ክብር እንደሆነ ያመነ፦ እህት ወንድሙን ለትግሉ የገበረ፣
ካላመነበት የሚናገር፦ የተሰለፈበት ድርጅት ሲዛነፍ እንኴን፦
አንገቱን ያልሰበረ፣
ትግል ብሎ ህይወቱን እንዳልገፋ በትግሉ እንዳላደገ፤ ዛሬ ዘብ ጥያ ተወረወረ????
ሲሆን ምስጋና ምርቃት እውቅና ይገባው ነበረ።
ወጣቱ ታጋይ ብርሃኑ ነጋ እግሩ በእግረ ሙቅ ታሰረ፣
እጁ በፌሮ አበጠ ዓይኑ በጨለማ ታወረ።
እኔ እንደትላንቱ «ጔድ »አይደለሁ አቌምህን አልገመግም ፥
ካጠገብህ አልተሰለፍኩ ብሩሕ ጨረር ዛሬ አላልም ።
እኔ እንዳንተ «ልብ ም »የለኝ ሁሉን ነገር ትቼዋለሁ ፣
ታገሉ ብየም አልሰብክ ዳግም በስደት ተወጥሬአለሁ ፣
በግለኝነት ተሳስሬ በሕይወት እጣ ወድቄአለሁ፣
ያም ቢባል የቆረጡ ትን ግን አደንቃለሁ፣
ለክቡር ሥራቸው ም እሰግዳለሁ፣
ብርሃኑ ምንም ባቌምህ ባልስማማ ቆራጥንትህን ግን አወድሳለሁ ።
ዝም በል ወንድሜ
ትላንት ወንጀል የነበር ፥ዛሬ ገድል ሆኖ አይተናል፣
«አንጃ» ብ ለን ዛሬ አንጠራህ፦ ተጋዳይ መ ሆንክን አም ነናል፣
በገንዘብ አልታለልክ፦ ኖሮህም ስትፋለም አስተው ለናል።
ድሮስ መች ታማ ህ በድህነት፦ በወጣ ትነትህ እንጂ፣
ጔዶችህን ጠ ላት ሳይሆን ሲያስተኛቸው የወገን ፈንጂ፤
ድሮስ መች ታሰርክ በሙ ስና፥ ተናገረ ተቃወመ ብ ለው ፣
ድክመ ታቸው ን አወላግደው ፥ አላማ ቸው ን ደበላልቀው ፣
ነፍጠኛ አይሉህ ነገር ዛሬ፥ የትላንቶቹም አልቀናቸው ፣
እዉ ነት እየፈካ እንደመ ጣ እነዚህንም አይለቃቸው ፣
ተዋግተህ ጦርነት ያክትም ደም ማ ፍሰስ ይብቃ ባልካቸው ፣
ከትግራይ አባረው ህ መ ርካቶ ብ ትጠ ብቃቸው ፣
የመ ብ ት ነገር ብታነሳ በኩልነት ብትገጥማ ቸው ፣
ዲሞክራሲው ተረሳና እስራት ሆነ ምላሻቸው፣
አባይ ኢ ትዮጵያ ያሉበት እሬት ሆነ ምላሳቸው ፣
ሕ ዝ ብ ሆነ ፈራጁ ም ርጫ ሆነ ጠ ላታቸው ።
ብ ርሃኑ የትላንት ወጣ ት ብ ርሃኑ ያሁንም ታጋይ፣
በርታ እንጂI አንሞት እኛ፦ መፈታትህን ገና ሳናይ።
አንሞት አንሞት አንሞት
አትሞት ያመንክበትን ፈጽመህ ሕልምህን እውን ሳታደግ፤
አምልጠህ የለ ከድርጅት ግርፊያ እስራት እንኴን ከዚህ ከትላንቱ ፋሽስት ደርግ።
አትሞት እኛም አንሞት


የብርሀኑን መጸሀፍ ባናነብም ተመሳሳይ ታሪክ አለውና ያሳደዱህና ሊገድሉህ የነበሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ወለድና ከድተው ከኢሕ አፓ ተቀላቅለው ገዳይ ቡድን (እስኳድ) የነበሩት ዳላስ እንደሚገኙ ከዚህ በላይ መረጃ የሚያስፈልገው አይመስለንም።

እርሶስ ምን ይላሉ?

Saturday, January 1, 2011

የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ

እንኳን ለዚህ የአዲስ አመት አዲስ ቀን በሰላም አደረሰን፣ ፈቃዱን ለሞላልን ለልዑል እግዚሀብሔር ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።

ባለፈው ጥሁፋችን ፍቅሩ ታደሰ ላልነው ግድፈት ይቅርታ እየጠየቅን ክፍሉ ታደሰ ተብሎ እንዲነበብልን በአክብሮት እንጠይቃለን። ሌላው ጋንት ሳይሆን ጋንታ በሉት ስንባል የጦር ሰፈሩ ስም ሰንገዴ መሆኑን ስፍራውም በአሲምባ ተራራ አካባቢ ነው። እኛ የዚያ አካል ስላልሆንን እየቀሰምንበት ነው። ስለዘግብነውም ምላሽ በገጻቸው ሊሰነዝሩ ቢሞክሩም እውነትን  መሸከም የተሳነው አእምሮ እራሱን በራሱ በቃላቱ ሲቃረን አስነብቧል።  እኛ እንደነርሱ ሕግ ወጥ አለመሆናችን በሕግ ውስጥ ያለንና የሚያስፈልገውን ማስረጃ ለሚመለከተው ማቅረብና ሕጉ የራሱን አቅጣጫ እንዲይዝ እንጂ እንደ ደንቆሮው ተኩላ የሰውን ሕጋዊ ነጻነት አንወስድም። እርሱ በቅርቡ አልማ በሚል በመተባበር በዳላስ ውስጥ በአዘጋጁት ስብሰባ ላይ በተፈጠረው ማደፍረስ ኮንነን የጣፍነውን ማንበብ በቂ ምላሽ ይሆናል። ይህ ሀገርን እንደ አፍሪካ ጫካ ማመሳሰል ትክክል አይደለምና የሳትከውን አስተካክል ነው የምንል። ጊዜ ገደቡም የተሰጠህ ከጸጸት ተመልሰህ ትክክለኛውን መንገድ እንድትገባና ለንስሀ እንድትበቃ እንጂ ለእንኪ ሰላምታ አታድርገው ፤ በጊዜህ ተጠቀም።

ሌላው የምጣዱ ሳለ ያሰኘን 2 ነጥብ አለን። አንደኛው ከተኩላው ጥሁፍ በላይ የሰፈረው በወቅቱ ጥጃ የነበረችና በኢሕ አፓ ውስጥ ብዙ ሚስጥር የማይነገራት ከደንቆሮ ጎራ የምትቆጠር፤ ባለፈው የአመቱ መዝጊያ ሳምንት ውስጥ ላለፉት እናት በደብራችሁ ሥርዐትና ሽኝት በኃላ የተናገረችውን ብንጠቅስ “ከዚያ ዕንቁላል እራስ ጋር ምን ታወራለህ ብሏ ለሌላው ከንቱ ግርማቸው ስትል እርሱም ተቀብሎ ደደብ ነው“ ያሉት አቶ መሰረት እርሷን የትምህር ቤት በሩን ያሳያት መሆኑን እንዴት ዘንግታ እንቁላል እራስ ትላለች? እርሷስ ሰሼንቶ ቢጤ ነጂ አይደለችም ወይ? ወይስ በየትኛው ትልቅ ትምህርት ሊቅነት ኖሯት ነው? ገና ሳይደርሱብሽ? ያንቺም ጉድ ከፈለግሽ ትን እስኪልሽ ብቻ ሳይሆን የስነ-ልቦና ሀኪም በጊዜ እንድታመቻቺ ገበያ እንዳትወጪ? እውነትን የያዘ ቀጠሮ ምን ያስፈልገዋል? የኢሕ አፓ code of silence had been broken. የንጹሀን ደም በፊታቸው የፈሰሰ ከሰው ቢሸሽጉት ከፈጣሪ ይደበቃልን?  ምን አይነት ህሊናን ይዘሽ ነው እንዲ ባደባባይ ክህደት? የቀድሞ ሚሽቱ ለምን ፈታቺው? በፍርድ ቤት ላይ አይደለምን እርሱ የነገራትንና ያረጋገጠችውን murderer ነው ያለችው። ደምመላሽ ደበበ ማን ነበር የሜዳ ስምሽ? ሌላውን ዋሾ ከማለትና ከባሰ ትዝብት ተሰብሰቢ። እንደ ወይዘሪት ያሳደገሽን ክፍሉ ታደሰን አሁን ከማምለክ ያልወጣሽ ደንቆሮ ቆርቆሮ።

ሌላው ከዳላስ በስልክ የደረሰን ብርሀኑ ኃይሌ AKA አምዴ ቀኑን በሙሉ በስልክ እየደዋወለ ስብሰባ የጠራው በሙሉ አጽራረ ቤተ ክርስትያን የሆኑትን ብቻ መሆኑን ሲደርሰን decent human being የሆነ እንደማይገኝ ሆኖ ካለፈው ሳምንት በትግሬ ነጻ አውጪ ከሞከሩት እንደማይለይ ነው። እኛ ግን ምናልባት አምዴን ያስጨነቀው ያለፈው ጥሁፋችን ከሆነና ካህናትን ይዞ ሰላምን ያመጣ ይሆን? ብንል የስልኩ ወዳጃችን ስቆ ተወን። እኛም ይህንኑ ጥፈን እያወጣን አምዴም በስብሰባው ምን እንደሚደርስ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።

እርሶስ ምን ይላሉ?