Sunday, October 31, 2010

ጉድና ጅራት ከወደኃላ ነው እንዲሉ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ጉድና ጅራት ከወደኃላ ነው እንዲሉ!

የተወደዳችሁ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን አላችሁ? እኛ በእርሱ ጸጋ ለዚህ ላደረሰን እግዚሀብሔር ለገናናው ስሙ አሁንም እስከዘላለሙ ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።


ጋሼ ተኮላ (ተኩላው) ስለ ቀድሞው መሪያችን ቢል ክሊንተን መጽሀፍ በእርግጠኝነት አንብበህ በሚገባ ተረድተህ በራስህ የተረጎምከውን ስላካፈልከን እውነት ከሆነ በርታ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገበያልና። ነገር ግን እንግሊዘኛ ችሎታህ ተርጉሞ ለሌላ ለማካፈል ቀርቶ ለራስህም ለመረዳት ገና ዳዴ እያልክ ነህና የተሳሳተ ትርጉም ላለመጨበጥ የቋንቋ ዕውቀትህን ለማሳደግ የግድ ትምህርት ለመቁጠር ወደ ባለሙያዎቹ መዝለቅ እንደሚገባህ እያካፈልንህ፣ ይህ ባይቻልህ እውቀቱ ያላቸው በትርጉሙ ቢረዱህ መልካም ነው። ትርጉም እራሱን የቻለ ሙያ ነውና።  ባለፈው ወዳጅህ ቀዳዳው ከዳኛ አንደበት የሰማውን የእንግሊዘኛ ቃል “እስብሊት“ የሚለውን አብሮህ ሲጨፈላልቀው ከርሟልና። በተለይ እያንዳንዱ የቃላት ሕጋዊ ትርጉሙ ጥንቃቄ እንድናደርግ
ለማሳሰብ ነው። ከዚህ ሌላ ዛሬም መዋሸት ይብቃህ ፣ ዕድሜ አልመክርህ ብሎህ ሰው በጣፈው ከመናገር የራስህን ደግመህ ደጋግመህ በየጊዜው የጣፍከውን ወደ ኃላ ተመልሰህ አንበው። ከስህተትህም ተማር‘። ‘ሀሰት አድርጌ ጥፌ ተገኝቼ ስለጠቆማችሁኝ አመሰግናለሁ‘ ብቻ ብትጥፍ እኛም ከሰው ስህተት አሊያም የሚሰራ ሰው ብለን በዘለልነው ነበር። ከኛም ጥሁፍ ሀሰት ካገኘህበት ጠቁመን በደስታ ለማስተካከልና ካለፈው ለመማር ወደኃላ የማንል ለመሆናችን ካንተ በላይ ዋቢ አንፈልግምና።

ከዚህ በመቀጠል ወደ እርዕሳችን ስንመለስ “ጉድና ጅራት ከወደኃላ እንዲሉ“ በቅርቡ የተጀመረው “http://www.dfwethiopiancommunity.blogspot.com/ “ ገጽ ጥሁፍ አጣጣሉ ወደፊት እንደኛ በሂደት እያደገና ተወዳጅነትን እያተረፈ እንደሚመጣ ተስፋችን ከፍተኛ ነው። በውስጡ አልፎ አልፎ የሚላመጥ ፍሬ አለው፤ በትላንትናው ጥሁፉ ባስነበበው ግን “ እግዚኦ “ የሚያሰኝ ነውና ፤ ኽረ ዳላስ ላይ ምን አደንዛዥ በሽታ ነው በኢትዮጵያ ተወላጆች መካከል የገባው? ምን አይነት ጉድ ይዛችሁ ነው የምትኖሩት? ለመሆኑ በወገኑ ላይ ይህ አይነት በደል ሲፈጸም የሚችል አንጀት መቼ ተጀመረ? ምን አይነት ልቦና ይዛችሁ ነው አብራችሁና አቅፋችሁ የምትኖሩት? በከተማው ያላችሁ የተማራችሁም ሆነ ያልተማራችሁ ፤ ወጣቶችም ሆነ አዛውንት ነን የምትሉ ሁሉ ፤ የሀይማኖትም ሆነ የግብረ ሰናይ ድርጅት ወይም የሰብአዊ መብት አባላትም ሆነ የሕግ ሙያተኞች የሆናችሁ የኢትዮጵያ ተወላጅና ወዳጆች ሁሉ የሞራልና የሕግ ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ እያሳሰብን አስቸኳይ እርምጃ እንደምትወስዱ  ተስፋ እናደርጋለን። እኛም የሞራልና የህግ ግዴታ ስላለብን መረጃዎች በእጃችን እንደገቡ ለዳላስ ካውንቲ አቃቤ ጽ/ቤት በማስተላለፍ ጉዳዩ በዚያ ተመርምሮ የህግ መጣስ ካለበት አግባባዊ እርምጃ እንዲወሰድ የተቻለንን ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን።

እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

በመጀመሪያ በሀቅ ላይ ተመርኩዞ ለሚጥፍ ሁሉ ለተከፈተው ለዳላስ ኢኦቲሲ መድረክና ጠሀፊዎች ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ጉድና ጅራት ከወደኋላው ነው እንደሚባለው አንድ ወረሃና ወልሻሻ ተኩላ እበጎች መሀል ገብቶ ያለእኔ ሃቀኛና ሃይማኖተኛ የለም፤ ግድየለም እመኑኝ እያለ የሚዘባርቀውን የዶሮ ጭረትና በስኳር እየቀባ የሚነዛትን ስንክሳር ስንመለከት ይኸ የእፉኝት ልጅ አባቱ ዲያብሎስስ እግዚአብሔርን እየተንቀጠቀጠ የሚያምነው ከዚህ የተለየ ምን አለ? ብለናል። “እኔን ከይሲውን አርዮስን ሉሲፈርን እመኑኝ” አይደል ያለው። ታዲያ አንተስ ተኩላው ያላባታህ ከየት ታመጣው? እንደው አንዳንዴ ምላስህ ከጅራትህ እየቀደመ ላይዳህን እያደናቀፈ ባፍጢምህ እየደፋህ ችግር ገባህ እንጂ፤ ይኸ ተንኮልና ሃሲዊ መሲህነትማ የተጠናወተህና የተካንከው ካባትህ ከዲያብሎስ የወርስከው ቅርስህ መሆኑን ማንም አይስተውም።
ለመሆኑ ያ ከወያኔ የሚጣልልህ ድርጎ አሁንም አለ ወይስ ጌቶችህ ከተመረጡ በኋላ አፍንጫህን ላስ አሉህ? ከመቼ ወዲህስ ነው በየደርስክበት እንደሜዳ አህያ ማናፋትህን ትተህ ከኩንቢህ በላይ የተጋረጠውን የአጋሚዶ ግንድ ገለል ሳታደርግ ስለሌሎች አርባ ክንድ ምላስህን መዘርጋትና መርዝህን መርጨት የጀመርከው? እስከዛሬ ከከተብከው ክታብ አንድ እንኳን ክርፋት የሌለው ይገኛልን? እስቲ ወደኋላ መለስ በልና ካልቆፈነኑህና ካልሰነፈጡህ ቅብዥሮችህንና ቅዠቶችህን ተመልከታቸው። እነዚህ ዙሪያህን ከበው መጣፈ አጋሚዶ ወእኩይ ከሚለው 52 ገጽ መመሪያቸው ብስናቸውን እየጎበሱትብህ የጣፍካቸው ክርፋቶች መሆናቸውን ትረዳለህ። አልሳደብም? እንዴት፤ እንዴት? የአንተን የሚሰለ ዝጉርጉር ታሪክ ያለው ሸለምጥማጥ እንዴት አድርጎ ይሳደባል? ቅቤ ይቀባል እንጂ! እንደው እስቲ ተጠየቅ? በየሰንበቱ ጌቶችህን እየተከተልክ ሸንደል ሸንደል እያልክ ወደሚካኤል ሰይፍ ስትጠጋ ምንም አይሰማህም? እስቲ ስእሉን ልብ ብለህ ተመልከተው ምናልባት እንደበልዓም አህያ መልአኩና ሰይፉ ቢገለጥልህ! ምናልባትም እንደአህዩት መንገድህን ትቀይር እንደሁ፤ አልያ አንተም አጋሚዶዎችህም የሰይፉ እራት ናችሁና እሲኪበላችሁ አንዛርጡ አህያነት ለመቼ ነው?

Anonymous said...

ለ ዳላሰኦትሲ ብሎግ።
በትላንትናው ብሎግ የተጠቀሰውን “ በተለይም መለከት በተባለው ገጻቸው በሴብተምበር 25 የቃዡትን በትላንቱ ዕለት በተደረገው የውስጥ ስብሰባ ላይ ቅዠት ተብሎላቸው ተደምድሟል” ሳነብ የሚያስደንቅ ስሜት ተሰማኝ። እኔ የሰማሁት “ቦርዱን በጎን ረዳት መስለው ሰርገው እንዲገቡና ከሳሾች ጋር የሚደራደር ቦርድ የመረጠው ቡድን አቋቁመው ካስታረቁና ባይሆን እንኳን ቤተክርስቲያኑ ለክሱ ያወጣውን ገንዘብ እንዳይጠይቅ ካደርጉ የገንዘብ ጥገና እንደሚሰጣቸው በሻለቃው በኩል ቃል ተገብቶላቸው መቋቋማቸውን” ነው።
ለዚሁም ዋና አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ትርፌን እንዲያስገቡ መደረጉን ነበር። አቶ ጌታቸው ትርፌንም ባለፈው መስቀል ደመራ ላይ ተፍ ተፍ ሲል ሳያው የተወራው ወሬ እዉነት መሆኑን አረጋገጥሁኝ። የምጠይቀውም የቦርድ አባል ስላሌለኝና ነገሩም ቢያናድደኝ ያው አንዴ መርጫቸዋለሁ የሚመስላቸውን ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ይምራቸው ብየ ነበር። አሁን ግን ብዚህ ብሎግ እንዳነበብኩት ከሚካኤል ምንም ይሚሰወር ነገር ባለመኖሩ በቦርዱ በኩል የተከሰተው ሴራ መፍረሱን ስሰማ እምነቴ የባሰ እየጠነከረ ሄዷል።
በጣም የሚገርመው እነዚህ ሰይጣን የተጠናወታቸው አዛውንት በእድሜ የገፉ አንዳንዱም የሚካኤልን እርዳታ የሚጠይቅ የታመመ ወይም የተቸገረ ዘመድ ልጅ ወዳጅ ያለው ሁሉ ለ ተቸገረ ወንድሙና ዘመዱ በመጸለይ ፋንታ በቤተክርስቲያን ላይ ማደም እምን ቦታ ያደርሰን ይሆናል አለማለታቸው ነው።
ቸር ወሬ ዳላሰኢኦቲሲ ስላሰመኝ እግዜር ይስጥለኝ እላለሁ።