Saturday, June 19, 2010

አይ ሜይ 2

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።







አይ ሜይ 2

እንደምን ከረማችሁ? አንዳንዴም በመካከላችን ሆነ ብለው ይሁን ወይ ዘግቶባቸው ነገር የተማታባቸው ፤ ተነፈስ ብለውም ጤና የማይሰጣቸው ፤ ከመጥፎ  ተግባርም የማይለዩና ድንግርግር ያለባቸው አልፎ አልፎ በሕብረተሰባችን ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለታቸው አይቀርም። ለዚህ መነሻ የሆነን ደግሞ ጋሼ ተኮላ (ተኩላ) Looser  በገጹ እንደለመደው ጫፍ ይዞ መሮጡን አላቃረጠም።

እሱና የሱ የተግባር ቢጤው በከሰሱት ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል ፍርድ ቤት ዳኛው በጊዜአዊነት በሰጠው ትእዛዝ ላይ የዳኛው ውሳኔ ያለአግባብ በኃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብታል፣ ይህም ጉዳይ ጊዛዊነቱ ይጎዳኛል ስለዚህም ሕግ ከሆነ ቁዋሚ አልያም ይሰረዝ በማለት ያመለከተው በውቅቱም ጉዳዩን ለተመለከተው ዳኛም ያሳወቀ ሲሆን፤ እስካሁንም ያልፈጸመው የተባለው ጊዛዊ ትእዛዝ በዳኛው እስኪፈረም ጠብቆ ነው። ምንም ኣዲስ ነገር የለውም። መቸም አይገባህምና እናስረዳህ። በየደረስክበት የተናገርከውና የፈጸምከው ማስረጃ እያሳደደ ያባንንሀል መሰለኝ ከታቦት መጣላት እንዲ ያደርጋል።
ሊያው ይኼ አንተን አይመለከትም፣ ጉዳዩ የሚታየው በይግባኝ ሰሚው አካልና በቤተክርስትያኑ መካከል ብቻ ነው።

2ኛ/ ከዚህ በፊት ስላለው ክስም ቢሆን በከሳሽ ለተከፈተው የብይን ይግባኝ፣ ከሳሽ ሲያጛትተው ከቆየ በኃላ በመጨረሻው የይግባኝ ማኅደር ያስገባውን ዝርዝር በተመለከተ የቤተክርስትያኑ የሕግ አማካሪዎች ቡድን ተመልክቶ ጉድፍ አግኝቼበታለሁና ለዚህ መልስ የመስጠት መብቴ ይጠበቅልኝ ባለው አንቀጽ መሰረት ይግብኝ ሰሚው ስለፈቀደለትና ይህንኑ የገደብ ቀን የሰጠው መሆኑን በስተቀር እንደ Looser ገጽ ተአምር የተፈጠረ አይደለም። የተረፈው የተለመደው የአዞ እንባ ለቅሶ ብለን እናልፈዋለን።

እንደዚህም በሜይ 2ቱ ሁከት ቀንደኞችና ከዚሁ ደብር ቀደም ብሎ ያለብቃቴ ቄስ ሆንኩኝ ብሎ ከማስተማር የአገለግሎት መድረክ በመኮብለል ቅስናውን ያፈረሰው መስፍን ከደብራችን አጥር ሥር  ካልጠፋ ቦታ ነገር ፍለጋ በመጽሀፍ ቅዱስ ስም መንቀሳቀሱን ልሳናቸው በሆነ የከልት ገጻቸው ይናገራል። ከዚሁም ጋር ከካድሬው ሲደልል ጋር እንደልተለያዩም ሊያስተባብል ሞክሮአል።

ሌላው ሳንነካ የማናልፈው ቢኖር ባለፈው ስላቀረብነው የኢትዮጵያን ቀን ቅድመ ዝግጅት ስብሰባ ጥሪ በተመለከተ ሕብረተሰባችን እየተወያየበት ሲሆን ከኮሚኒቲው ጽ/ቤት እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።
እኛም በቅርቡ በአምዳችን ግምባር ላይ ብቻ ሳይሆን ዘመቻችን አድማሱን እናሰፋዋለን።

በሌላ በኩል ጸረ ኦርቶዶክሶች ሆነው የቀሩት ጥቂት የሕብረተሰባችን ግለስቦች ተልኮዎቻቸው ሁሉ እየፈረሰባቸው በመምጣቱ ያጠፉት ጊዜና ገንዘብ እየቆጠቆጣቸው የስነልቦና ችግር  እንደዚሁም ጸጸት ውስጥ ገብተው ይገኛሉ። አንዳንዶችም ይህ አምዳችን የመነዠጋቸው ሲቅበዘበዙና ጣታቸውን በአላፊ አግዳሚው ላይ ሲቀስሩ ይታያሉ። ስማቸውን ጠቅሰን በመተቸታችን፣ ስማቸው ከእምነታቸው ብለውም የተቀበሉት ስጋዎደም በላይ፣ አድርገው መቁጠራቸውን እያስመሰከሩ ይታያሉ። ይህ አምድም ምን እንደሆነም ምንም ሊገባቸውም ስላልቻለ፣ በጭንቅላታችሁ የያዛችሁትን እምነት ወደ ልባችሁ አስገቡ፣ እንደ ቃሉ ማንም ፍጹም የለምና ሁላችንም በደለኞች ነን ነገር ግን ምህረት በሱ ብቻ ነውና ወደ ዕውነት መንገድ እንግባ እንላለን። ይህን ደብር ስናቁዋቅም በወቅቱ ከፖለቲካ ጋር ሳንለየው ቀርተናል። ነገር ግን ጊዜውን ጠብቆ የፖለቲካው ስራ መለያየት ሲጀምር፣ ከስራችን ሳናውቀው የበቀሉ ከልቶች ሲያብቡ፣ በሙያቸው የሚቀጠሩት የሀይማኖት አባቶች (ባለሙያዎች) ካለንበት ጊዜና አጠቃላይ ሁኔታዎች ጋር ያለመጣጠምና የአቀጣጠር ሂደት፣ በየጊዜው የሚፈጠሩትን ችግሮች በወቅቱ እንደመፍታት ስናለባብስ ከአንድ ቦርድ ወደሌላው ስናሸጋግር፣ ጉልቻው ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ አስተዳደሩ በተመሳስይ አስተሳሰብ ባላቸው የተወሰኑ አባላት እጅ ብቻ በመሽከርከሩ የተወሳሰቡ ችግሮች ይዘን ለዚህ በቃን።

የቀደሙትንና በየጊዜው ተመርጠው በአስተዳደር ቦርድ አባልነት አገልግሎት ሁሉ  ባላቸው እውቀትን ጊዜ ከፍተኛ መስውዕት ከፍለው እስካሁን ደብሩን ለዚህ በማድረሳቸው ምን ጊዜም  በደብሩም ሆነ በምዕመናንም ጭምር ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። በአንጻሩም ደብሩን እኛ ብቻ ብለው በመያዛቸው፣ የሚቀርብላቸውንም የምዕመናን ቅን ጥያቄ ብሎም ምዕመናንም ጭምር መናቅ ጀመሩ። እየተሰሩ ያሉትን ስህተቶች ማየት ተሳናቸው፣ አገልግሎታቸው ለበረከት መሆኑ ቀርቶ ለግል ስም መጠሪያ፡ እርስ በርስ  የስልጣን ጸብ፣ አለመግባባት፤ እርስ በርስ መወነጃጀል አልፈው ደብሩንም ለአለም ፍርድ ቤት አበቁት፤ አንዳንዶችም ከከሳሽ ጀርባ በስውር ቆሙ ፤ ከመከፋፈላቸውም የተነሳ  እንካን ምዕመናን ሊመሩ ምዕመናኑ እነሱን ሸምጋይ ሆነ ፤ ቢሰለቸው በምርጫ ለወጣቸው ፣ ይህንንም ውጤት ለመለወጥ እስከ አሁን ተስፋ አልቆረጡም፣ ድምጸ አናሳ ብቻ ሲቀሩና እንደ ድሮው ሳይሆንላቸው ሲቀር ራስቸውን ከቦርድ አባልነት አወጡ።

ሁላችንም እንደምናውቀው ለአገግሎት መመረጥ ለበረከት ነው። የቦርድ  ወይንም የቤተክርስትያን አባል ብቻ ያገልግል የሚል ሕግ በኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን  የለም። ማንኛውም የዕምነቱ ተከታይ የሆነና ግብረ ገብ ያለው ሁሉ ትሕትና ብቻ ሳይሆን ለደረሰበትና ላጋጠመው ቤትክርስትያን እንግዳ መሆን የለበትም ፣ አቅሙና ጊዜው በፈቀደለት ሁሉ መስክ ማገልገል ይገባዋል።

ቀደም ብለው የተመረጡት አዲስ ቦርድ አባላት ያሉትን ችግሮች በአንክሮ ተመልክተው እንዲስተካከል ለመንቀሳቀስ ባደረጉት ጥረት መጀመሪያ በቦርዱ ውስጥ ብሎም በምዕመናን መካከል  ጥላቻ እንዲነሳ ዘመቻ ተከፈተባቸው፣ በመቀጠልም በመጨረሻ የተመረጡትም ከዚህ በፊት በቦርድነት ያላገለገሉ በመሆናቸው ገና ስማቸው ይፋ ሳይሆን የተለያየ ስም ወጣላቸው ፣ ገና ለገና የሰራነው ስህተት ይወጣብናል፣ ሳይቀድሙን እንቅደም ሩጫ ከፈቱባቸው። አንዳንዶችም አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፣ ፈጣሪን የማመን ይሁን የክህደት በሁሉም አቅጣጫ በፍርድ ቤትም ጭምር የተለያዩ ጸረ ኦርቶዶክስና ጸረ ቤትክርስትያን ቡድኖች የከፈቱትን ዘመቻ ለመግታት ብሎም ለመጣል ክእግዚሐብሔር ጋር የተስለፉት ያላሰለሰ ጥረት በጾም በጸሎት ምልጃ ላይ ናቸው። ምልጃቸውንም እየተቀበለ ያለ ፈጣሪም የተሳሳቱት ቁጥራቸው በየቀኑ እያነሰ ፣ ወደ ቤትክርስትያን ልጅነታቸውም እየተመለሱ ይገኛል።

በመጨረሻም በሜይ 2 ቀደም ሲል እንዲያስተምሩ ተጋብዘው በመጨረሻው አልችልም ያሉት የሁስተኑ ቄስ መኮንን ፣ ከዚያም ያንኑ ክፍተት እንዲሸፍኑ ተጠይቀው ሲያበቁ ከጥቂት ሰዐታት በፊት ያስያወቁት የአርቪንግ ማርያም መምህር ሰይፉ በቅዱስ ሚካኤል በአለ ንግስ ከተገኙት ካሕናት መካከል ይግኙበታል።  በእለቱም አጭር ትምህርት የስጡት የሁስተኑ ሲሆኑ በ ሜይ 2ቱ ሁከት የተሰማቸውን ሀዘን በጠቃሚ ትምህርት ቢገልጹም ለምን በእለቱ እንዳልተገኙ ማናቸውም አልገለጹምና በምዕመኑ አሉታን ፈጥሮ አልፋል።


እርሶስ ምን ይላሉ?

1 comment:

Anonymous said...

እንዴት የሚገርም ነው እናንተ!! ይኸ ሚካኤል የሚባል መልአክ እንዴት ተአምረኛ ነው!! በዛሬው ቀን የሚካኤልን ንግሥ ያልተሳተፋችሁ ካላችሁ ብዙ ስላመለጣችሁ ከነበሩ ጠይቃችሁ ተረዱ።
ሚካኤል ወዳጆቹን ከያሉበት ስብስቦ ሌሊት ሙሉና ግማሽ ቀን እግዚአብሔርን በማህሌት፤ በቅዳሴ፤ በመዝሙር፤ በጸሎት፤ በደስታ ልቅሶ፤ ወዘተ… ሲያመሰግኑና ስሙን ሲያወድሱ አድረው ውለዋል። ይህን ላደረግልን አምልክ ከሁላችንም ከልብ የመንጨ ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋልና ክብርና ምስጋና ለስሙ ይሁንልን እንላለን። ባንጻሩ ደግሞ የሚካኤል ጠላቶች ከየተቀበሩበት ጉድጓድ ብቅ ብቅ ብለው በሰው መሀል በመሽሎክሎክ የተለመደ ደባቸውን እንዴት እንደሚያራምዱ ሲመካከሩ ሲጠቃቀሱና ሲቀራመቱ የታዘቡ ሁሉ አስደናቂ ቲያትር እንደተመለከቱ ይተርካሉ። በቀድሞው ጸኃፊ የተንኮል መረብ ረዳት በመምሰል የኦዲዮ ሲስተም እንዳይሰራ ለማድረግ ከተሞከረው ደባ ባሻገር፤ ንጹሃንን በሀሰት ከሶ ቁልፍ አልተሰጠኝም በሚል ሰበብ ሁለተኛ የሚካኤልን ደጅ አልረግጥም ብሎ በህዝብ ፊት እራሱን አዋርዶ ከሄደ በኋላ ከከሳሾች ጋር በመቆም ሚካኤልን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ያለው የቀድሞው ሊቀመንበር ሽር ጉድ ማለት፤ እንዲሁም ከተክለሃይማኖትና አቡነ አረጋዊ የመጡ ቀንደኛ የሚካኤል ጠላቶች ስለላ ማካሄድ፤ ተስፋ የቆረጡ የማህበረ ሰይጣን አባላትም አንታወቅም ብለው በየቦታው ሲቅነዘነዙ መታየት እውነትም ፊልም የሚታይ ሊመስል ይችላል እውነቱ ግን እነዚህ ሁሉ ግብስብሶች በእውነት እግዚአብሔርን ለማምለክና ለማመስገን ሳይሆን ለስለላ መምጣታቸው በግልጽ ታይቷል ምን ሲሰሩ እንደነበረም ሰሞኑን ከሚወጡት የቪዲዮና የፎተግራፍ ምስሎች መመልከት ይቻላል። ከእግዚአብሔር ጋር አትታገሉ ትመላለጣላችሁ ቢባሉ በሃብታቸውና በጉልበታቸው የሚመኩትና ግብረአበሮቻቸው ጭራሽ የሚካኤልን ቤተክርስቲያን ካላጠፋነው አናርፍም በማለት ከማይቋቋሙት ባለጋራ ጋር ትግል ገጥመዋል። ምከረው፤ ምከረው እንቢ ካለህ መከራ ይምከረው እንዲሉ፤ እንግዲህ ካልሰሙ ከሚካኤል ስይፍ ይማሩ እንጂ ምን ይደረጋል!!