የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
ሰላም ተዋሕዶ Selam - Tewahedo said...
ሰንበቴ ብሎገ ከሠረ ፡፡ የሥራቤቶችንም አሉባልታ ጀመረ ፡፡ ከትንሽ ቀን በኋላ ደግሞ ይሄም ይቆምና በሌላ ብሎግ ስም ወጥቶ እናገኘዋለን፡፡ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም ፡፡አቀራረቡ የሥነ ጽሑፍ ሕግን የተከተለ ሳይሆን ተራ ስድብ ስለሆነ ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንደ ሰንበቴ ብሎግ በሕዝብ የተናቀ ይሆናል፡፡ሰላም ተዋሕዶም ከዚህ በኋላ ጊዜዋን ይህን ትራሽ በማንበብ አታጠፋም ፡፡
June 7, 2010 10:34 PM
ውድ የሰላም ተዋህዶ ገጽ አዘጋጆች፣ እንደምን ሰንብታችኃል? እናንተም እንደኛው እግዚሐብሔር በአምሳሉ የፈጠራችሁ በሰውነታችሁ የምንወዳችሁ ነገር ግን ስራችሁን የምንጸየፍባችሁ፣ ከዚህ በላይ ለሰጣችሁን አስተያየት እናመሰግናለን። ይህቺ ገጻችን ከመቆንጠጥ አልፋ በሽታችሁን እየዳበሰች በቀላሉ የሚድኑትን ወገኖቻችንን ከአጠገባችሁ እየነጠቀች ይገኛል። የተቀሩትም እውንቱን ሲያዩ ሁላችሁም በንስሐ ትመለሳላችሁ።
ይህቺን ገጽ የሚያዘጋጀው፣ እናንተ እንደምታስቡት ሳይሆን ወይንም ሰንበቴ አለመሆኑን ከዚሁ እናረጋግጥላችዋለን፣ አላማውም ከሕብረተሰባችን ውስጥ ያለውን ችግር መቅረፍ ባይቻል ዕውነተኛ ግንዛቤ ለማስጨበት እንዲረዳ የተዘጋጀ ገጽ ነው። የሚመስላችሁን ግለጹበት እናንተም የሕብረተሰባችን አካሎች ናችሁ፣ የኛ ችግር የናንተ፣ የናንተ ደግሞ የኛ የሚያደርጋቸው ሒደቶች ብዙ ናቸውና። ሥለሥራቤቶች አሉባልታም ነካ አድርጋችኃል፣ በተረት ካልሆነ የምታውቁት ግንዛቤ ትንሽ እንስጣችሁ። የዐጼ ኃይለሥላሴ ቤተመንግትስት የምግብ ክፍል ባለሙያዎች ሲሆኑ እንደናንተ አገላልጽ አሉባልተኞች ሳይሆኑ የነሱን አስተያየት ለማጣጣልና ገንቢነት የሌለው የደረጃ ማሳነሻ የቀድሞ አስተዳደር ስልት መሆኑን ተማሩ እንላለን። ሌላው ጥቅሳችሁ ደግሞ መልሶ እዛው ማዕድ ቤት ከተታችሁ። አንድ እውነት ያላችሁት ቢኖር የዚህ ገጽ አዘጋጆች የሥነ ጽሁፍ ችሎታ የላቸውም ከናንተም ሆነ ከሌላ ለመማር ዝግጁ ናቸው፣ ነገር ግን የሚያቀርቡት ሁሉ መጣጥፍ የእውነት ነውና አትጠራጠሩ። እድሜ ሰጥቶን እናንተም ወደ እውነት መንገድ ገብታችሁ፣ ያስቀየማችሁትን ፈጣሪ ንስሀ ተቀብላችሁ፣ ልታፈርሱት የተነሳችሁትን ቤተክርስትያን በአገልግሎት ክሳችሁ፣ ያቀያየማችሁትን አስታርቃችሁ፣ የተቀየማችሁትን ይቅርታ ጠይቃችሁ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመልሳችሁ ለማየት የዚህ ገጽ ጸሎትና ፍላጎት እንጂ በቶሎ በኖ አይጠፋም።
ስለሰጣችሁት አስተያየት ይኽን ያኽል ካልን በኃላ ለመሆኑ በአዲሱ አቅርቦታችሁ ላይ ‘ሠበር ዜና‘ በሚል የጣፋችሁትን ስናይ፣ እናንተን እንደምን እንበላችሁ ! እንድንማማር ከፈቀዳችሁ “ በቅርቡ ወይንም ትኩስ ዜና“ ብትሉት ፣ የባዕድ ቃል ቀጥታ ትርጉም መጠቀሙ የራስን ሀብትና ባሕል ማጥፋት ይሆናልና ይታሰብብት እንላለን። ከዚሁ አርስት ሳንወጣ የሰጣችሁት ዜና ሳይሆን አስነዋሪ ምግባራችሁን ነው የገለጻችሁት፣ እናንተን ካልመሰለ ጥላቻን መንዛት የክርስትና ተግባር አይደለም፣ ከራሱና ከቤተስቡ አልፎ ሌላውንም ቀጥሮ የሚያስተዳርን ወገን ማበረታት ሲገባ የዚሁን ግለሰብ ምርት በሚያቀርብበት መደብር እየሄዱ ምርቱ ላይ ተንኮል ማድርግ በህግ ያስወነጅላል! ይኽ አይነት በቀል እናንተና ብጤዎቻችሁ መቆጠብ ይገባችኃል። ስለናንተ በአበስኩ ገበርኩ ብቻ አያቆምምና !
ለመሆኑ ራሱን “ማኅበረ ቅዱሳን“ እያለ የሚጠራው ድርጅት እንዴት እንደተፈጠረ ለአንባቢዎቻችን ትንሽ ማስጨበት እንወዳለንና በሚቀጥለው ጽሁፋችን ይጠብቁን። ከቻልንም በተቀጣይ ለምን ጌታቸው ትርፌ በማኅበረ ቅዱሳን ከተሰጠው የኮሚቴ መሪነት ወደ ሌላ ተዘዋወረ? የትላንት ማታው የወያኔ ራት ግብዣ ላይ ጸህይጽድቅና የተኮላ ድርሻ ምን ነበር? እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment