Thursday, June 10, 2010

ጋሼ ተኮላ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ሰላምታችን ለሁላችሁም ይሁን። በተለይ የመረዋው ጋሼ ተኮላ አዲሱ ሥራህ እንደምን ይዞኃል? ለምርጫ ማዋከቢያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ለአንተና ብጤዎችህ ለዳላስ የተመደበው ድርጎ የዘላለም መስሎህ ከሻትል መባረርህ፣ ቤተክርስትያንና ጸረ ሀይማኖት ሥራህን የተጸየፉብህም ወገኖች ፊት መንሳታቸው፣ አሽሽቶህ አሁን ዳረጎቱ በመቆሙም ሌላ Looser (ይህ ቃል ያምሀልና)እንዳትሆንብን ለስሚዝ ኩባንያ እድሜ ለማኝ ለመሆን እንካን አበቃህ።

ይቺ ገጻችን በጣም ስላስቆጣችህ ልትቀባት ያልሞከርከው የቀለም አይነት የለም። ሊያው ያንተ ጎራ ብቻ ሳይሆን ያንተው ኣኩይ የተግባር ወዳጆችህ ኣነ ሰላም ተዋህዶዎችም (ሽኮኮው በቀለና መስፍን ኢሕአፓው) እርር ብግን ብለውብናል። ከሁለታችሁም ጎራ እውነቱን እየተረዱ የራቁዋችሁ በየቀኑ በዝተዋልና በቅርቡ ብቻችሁን የንስህ እድል እንካን ሳታገኙ እንዳታልፉ እንሰጋላችኃለን። እኛና እናንተ በዚህ ገጽ ያቀራረብ ችሎታ እንደናንተ አገማገም ሙያውም ሆነ ችሎታውም የለንም። እኛ ተራ፣ በሙያችንም ሆነ በኑራችንም ቀጥተኞች፣ የማንንም መውደቅ የማንሻ፣ ፈጽመንም ንጽህና የሌለን ነገር ግን በሱ አምነን በመጠመቃችን ብቻ እንደዳንን ያመንና፣ ባልንጀራችንን እንደራሳችን ፣ ወንድማችንንም የምንወድና እውነትን የያዝን ብቻ እንጄ እናንተ ኣንደምታስቡት የፖለቲካም ሆነ የሌላ ድህረ-ገጽ ወይንም የቦርድ አፈ ቀላጤ አለመሆናችንን በፈጣሪ ስም እውነት ብለን እንናገራለን። ለዚህም ነው ብዙ አንባቢያን ከቀን ወደ ቀን በአጭር ጊዜ ውስጥ መጨመር ብቻ ሳይሆን አንባቢዎቻችንም ወደ ትክክል አቅዋም እይተመለሱ ያሉት። ከሁሉም በላይ ይህ ገጽ ምን ጊዜም ቤሆን በሩን ለእናንተም ጭምር ክፍት ያደረገ ገጽ ነው። የሁሉንም አስተያየት እያስተናገደ ይገኛል።

የኛ ገጽ ባይገርማችሁ ከኢትዮጵያው ኤምባሲ አልፎ የቤተክሕነትና የመንግሥትን ቀልብ እንደሳበ ከኤምባሲው ውስጥ ያሉት ወዳጆቻችን አካፍለውናል። ስለ ጠላታችሁ ሰንበቴም ከናንተ አልፋ ለጳጳሱ ደብዛዋን እንዲጠፉላቸው የቅርብ ዘመዳቸውና ሚስጥረኛቸውን የእንግሊዝ ዜጋ ነገር ግን በኢትዮጵያ ዲፕሎማት ፓስፖርት አለምን የሚዞረውን ሰላይ በለንደን 3 አባላት ያለው ቡድን አቃቁሞ ስራውን እየሰራ የሚገኘውን ተመድቦበታል። ይኸው ቡድን ያቀፈው የኮምፒተር ባለሙያዎች ሲሆን፣ እነሱም ከኤዥያ በተለይ ከቻይና እንደዚሁም ከአውሮፓ ዕውቀት ያላቸውን እየተኮናተሩ የሳይበር ዘመቻ ያካሂዳሉ። ቡድኑም ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስተርና ለአገር ውስጥ ደህንነት ጉዳይ ስር የሚገኝ የጸረ-ስለላ መምሪያ ቢሮ ነው። ሰንበቴም እንደ ሌሎቹ የዚህ ቡድን ሰለባ ሆኖም እንደሆነ ገና አላረጋገጥንም፣ ነገር ግን የሚያወጣው የጽሁፍ መረጃዎች ግን አዲስ አበባን እየረበሻቸው ይገኛል። እኛም በተጠንቀቅ እንጠብቃለን።

በርግጥ እስካሁን ይህ ቦርድ አጠፋ የምንለው ባይኖረንም በሜይ 2ቱ ረብሻ ሳቢያ ለጊዜው በቁጥጥር ሥር የነበረችውን ግለሰብ አንደኛው አባል ጣልቃ ገብቶ ማስለቀቁ (በቅን ልቦና) ትክክል አለመሆሁን ሲቀበል፣ የሕግን ሂደት አደናቅፋል እንላለን። ከዚህ ውጭ ግን ለቦርዱ እንዲ ብሎ ገብቶ እንድህ ብሎ መለሰባቸው ብሎ የናንተ ትችት ፍሬ ቢስ ብቻ ሳይሆን የከፋ ስም ያስከትልባችኃል። መረጃ መረጃ አሁንም መረጃ አምጡ ኣንላለን። እንደ ትችታችሁ ከሆን መናገር ያሻችሁት ስለ አዜብ ኃይለማሪያም ነው። ገና ውሳኔው ሳይወጣ የናንተ ገጾች ዜናውን ለማብሰር ኣሽቅድድም ያዛችሁ። እኛ ደግሞ የምንጠይቃችሁ ያን ያህል ለጉዳዩ ቅርበት ብቻ ሳይሆን ቁጭት የጨመራችሁን ጉዳይ ለምን በአምዳችሁ አውጥታችሁ እኛም የራሳችንን ግንዛቤ እንድንጨብጥበት አታበቁንም?

አዜብን ካነሳን ከምንለው በጥቂቱ፡- በቁርባን ባላን አስራ ከተባረረው በናንት መላክ ሳህል ለኛ ድብተራ ወይንም ካድሬ ሲደልል ጋር ያላትን፣ ብቁነታን ሳትመዝን (ሊያው እሳ ብቻ ሳትሆን አበሮችዋን ጨምሮ) የተቀበለችውን የሥጋ ዎደሙ ይዛ በሜይ 2ቱ ረብሻ ልጃን ደብቃ መጥታ ጩሁ እያለች ስታስጮህ የነበረች፣ ይኸው ሲከሽፍ ከከሳሶችና አስከሳሾች ጋር ተባብሪ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን በሚሰጣት መመሪያ ከአበሮችዋ ጋር በመሆን የስብሰባ ቦታ ጥያቄዋ ውድቅ የሆነባትእያልን ብዙ ማለትም እንችላለን። ለርሳም ሆነ ለቢጤዎቻ የምንለው ንስሀ ግቡ፣ በስጋ ወደሙ ተጠብቁ፣ ከቂም በቀል ራቁ፣ በጾም ጸሎት ትጉ እርሱ ቤቱንና በጎቹን ይጠብቃልና። ስለዚህ ለአዜብ የምንለው ፡- ስለስጋወደሙ ፣ እንዴትስ ተወስኖ እንደሚኖር ፣ ክርስትና ህይወቱ እንዴት እንደሚኖር አስፈላጊውን ትምህርት በቶሎ መውሰድ ይገባሻል። አንቺም ያስፈረምሻቸውም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ የማድረግም ግዴታ አለብሽ። ሌላው ወዳጅሽ ዋሾውና የሕብረተሰባችን ዝቃጭ ሙላው ወራሽ የሚሉት ወደ አገር ቤት ይሄዳል ማለትን ሰማንና፣ተሹሞ ከመጣም እነ ታደሰ ጸሀይን እጅ እንዳያስነሳ ቀድመውትም ከሆነ ከቦሌ ወደ ከርቼሌ እንዳይገጥመው ሹክ በይው።

ከዚሁ ሳንርቅ ጌታቸው ትርፌ ለማኅበረ ቅዱስን የህልም ቦርድ ሊቀ መንበር ምክትሉ ደግሞ ተፈራወርቅ አሰፋ ገና ሳይደርሱ ሹም ሽር አድርገው ጌታቸውን ወደሌላ አዞሩት፣ የተሰጠውም ምክንያት ሆዱ የማይታወቅ ፣ ሰልል ተብሎ ወደ ቤተክርስትያን የማታ ትምህርት ቢላክ ወደ መጨረሻው ላይ ምዳየ ምጽዋት ገንዘብ ለምን እንዲዞር አደረክ፣ በትምህርቱ ልቦናው ተነክቶ በማብቂያው ላይ ቆሞ በሰጠው አስተያየት ፤ ይኽንኑ ሰምተውት ከነበሩት ምዕመናን መካከል ለመወያየት ለሰኞ በመቃጠሩ፣ ሲሆን ቀጠሮውንም እንዳይገኝ አድርገውታል። ሚስቱም ከዚሁ ጎራ የተሰጣት የናቶች መዘምራንና የሴቶችን ክፍል እንድትሰልልላቸው ነው።

ሌላው ጋሼ ተኮላ የተገኘበት የራት ግብዣ በአዲስ አበባ ምግብ ቤት በወያኔ ደጋፌዎች ቁጥራቸው ከ30 የማይበልጡ የተገኙበት ሲሆን፣ አላማው እንደቀዳዳውና መሀይሙ ሙላው ወሬ የምርጫ ማሸነፍ ሳይሆን፣ ኤች አር ለተባለው ጉዳይ የአሜርካን ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ያለውን በተመለከተ ነበር። በዚህ ምሽት ጋሼ ተኮላ ከወትሮ የተለየና በጣም የቀዘቀዘ ሆኖ በመገኘቱ አፉ እንደታሰረበት ቸኩሎ ወጥቶ ሄዳል። ሌላው የሱ ቢጤ ጸረ-ሀይማኖትና ጸረ-ቤተክርስትያኑ፣ የቤተክርስትያኑ አጋር ከሳሹ ፀሐይጽድቅ ቤተማርያም ግን ፉከራና ቀረርቶ ቀረሽ በደርግ ላይ እንደለመደው ሁሉ የወያኔን መንግሥት ሲያወድስና ሲያመሰግን ነበር።
ይህ አድርባይ በደርግ ጊዜ የተደበቀ ጉዱን እንዳይወጣ ወይንም ቢወጣም ለይቅርታ ይሆን? ወይስ እዚ በመንግሥት ድጋፍ የሚኖርበት ቤት፣ ታክስ ግዴታውን ያላማላ እንደጋደኞቹ፣ ኢምግሬሽንን ዋሽቶ ያገኘውን፣ ወዘተ… ሲወጣበት መሸሸጊያ ፍለጋ ነውን?

ጋሼ ተኮላን የተተናኮለው መጥፎ መንፈስ ዛሬ አይደለም ከልጅነቱ ነው። ነፍሱን ፈጣሪ ይቀበልና ከደጋጎቹ ይጨምርልን የምንለው ወንድሙና ወዳጃችን መስፍንን የምታውቁ ሁሉ ፤ ከዳዊት ያልተለየ ቤተክርስትያን ወዳጅ፣ ሰው አክባሪና ትሁት፣ የማይጠገብ የነበረው ወንድምህ አሁን በሕይወት ኖሮ ቢሆን እንዴት አዝኖ ባፈረብህ። ትልቅ ስህተትና ጥፋት በዚህ እድሜህ ለፕለቲካ ብለህ መስመር የለቀክ። ይኼ የኢሕአፓ ፖለቲካ ቦታ አይደለም የዚያንም ተለምዶህን ከዚህ ቅዱስ ቦታ አርቅ። ከምዕመናን አልፈህ ከታቦት ጋር ግጭትህን አቁም ብትችል ንስህ ግባ፡ ቅዱስ ሚካኤልን ቦርድ ካልወደድክ ሌላ ቦታ ሂድ። የሌሎቹን ዘመዶች ተነኩ ብለህ አትፎክር አሁን አንተም ዘር ማንዘርህን እንዳታስቆጥረን። ለመሆኑ ባለቤትህና ዘመዶቻ ምን ይበሉ? ለልጆችህስ ምን እያወረሳችሁ ነው?

ሌሎቻችሁም ስለ ፈጣሪ ብላችሁ ቤተ ክርስትያንና ምዕመናን አታውኩ፤ ለሰላምና ለፍቅር ተነሱ!

እርሶስ ምን ይላሉ?

2 comments:

Anonymous said...

አየ ጉድ! አዬ ጉድ! ጉድ እስተወዲያኛው!! ይኸ ሁሉ ሌባ፤ ይኸ ሁሉ ወንጀለኛ እቤተክርስቲያን ምን ያደርጋል?? ጉድ እኮ ነው እናንተ! እንዴ! መቼ ነው ይኸ እሚካኤል ካዝና እጁን የዶለ ሁሉ ከኮሌራ ወይም ከስዋይን ፍሉ ወይም ከሚካኤል ሰይፍ ጋር የሚገናኘው? እስከ ዛሬ ሰው እያጭበረበርክ እንደጀርመን ኮክሮች ባደባባይ ተደብቀህ ከረምክ። አሁን ደግሞ ሚካኤል እየመነቀረ ሲጥልህ ጌታህን ወያኔን ተገን አርግህ ላትህን ውጭ ማሳደር ፈለግህ?የሚካኤል ሰይፍ አይቆርጥ መስሎህ! ይጎማምድህ!! ምን አይተህ ገና! የሚካኤልን ፈተናና ሰይፍ ሁልህም ትቀምሳለህ!! የዋሁን ምእመን አይኑን ሸብበህ ስትዘርፈው ኖርክ። የአፍ ሌባ፤ የእጅ ሌባ፤ የአይን ሌባ፤ ስንት ጉድ ታየ? ስድብ፤ ዘረፋ፤ ማጭበርበር፤ ክስ፤ ክስ፤ ክስ፤ ክስ!!!!፤ ደወል፤ መረዋ፤ ሰላም ተዋህዶ፤ ሰንበቴ፤ ትዝብት፤ ዳላስ....አረ ስንቱ? አይነጋ መስሏት በቋት ... እንዲሉ፤ ነጋ!! የት ይግባ ይኸ ሁሉ ኮክሮች!! አዛኙ ካህን ሲያስተምሩ የመዳን ቀን አሁን ነው! ንሥኃ ግቡ አሉ፤ እነ ተኩኩኩላ እና ግብረአበሮቹ ለንስኅ ይበቁ ይሆን? እግዚአብሔርን ስለማያውቁት አምላካቸው ... ይርዳቸው። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ቤተክርስቲያንን አይከስም፤ ትእዛዛቱን ይጠብቃል፤ እግዚአብሔርን አይደፍርም! በቤቱም ሁከትንና ጩኸትን አያደርግም፤ ለሀጥአን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል ነውና ቅዱስ ሚካኤል የአምላኩን ትእዛዝ ሲፈጽም እንክርዳዱን ከስንዴው ለይቶ እንደየስራው ለሁሉም እንዲከፍለው የእግዚአብሔር ባሪያዎች የሆንን ሁሉ በርትተን እንጸልይ!! እግዚአብሔር ይርዳን፤ አሜን።

Bekalu said...

I am so glad that we have this site to express our views and concerns about the Dallas D.M.St. Michael Orthodox Church. I am sure many of us ,who have followed the Mehabere kidusan and those of the bugs' hidden agenda have come to our mind. There are still a lot of people remained confused. There are also many people who are working with the ASMESAYOCH with out knowing their intended goals.We should call on those friends and use every means available to tell them the truth about these enemies of our church. Please. Please, let's come together and defend our church from these Asafari Yeken Jiboch and Bandas.let them play their dirty political game somewhere outside, not in our church.By the way , I would suggest our Board to take some time after Kidase and brief the people about the current situation, "the reason why they are fighting and what step they are taking to protect the church. At least give them a hint what the interests of those stupids.
That is how we create solidarity and defend our church.It is when we get a full picture and understanding of their intention that we can clear our church from insurgents.
Egziabeher Hailina Birtatun Yisten. Amen.