Thursday, June 3, 2010

የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ደብር እንደምን ከረመ?

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የዳላስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ደብር እንደምን ከረመ?

እንደምንሰማው ከሆነ ደብሩ ብዙም ባይሆን ያኮረፉበት ምእመናን አሁንም አሉት። አንዳንድ የቀድሞ የቦርድ አባላት ተመዘበረ ከሚባለው የደብሩ ገንዘብ ጋር ግንኙነት ስላላቸው፣ በቅርቡ ለሚጀመረው የውጭ የሒሳብ አጣሪ ስራ ለማስቆም የተቻላቸውን እየጣሩ ይገኛሉ። ከቶንኮሎቻቸው አንዱ የትውሶ አስተማሪ ለማሳጣት የሚያደርጉት ሴራ እየከሸፈባቸው ይታያል። ግብረ አበሮቻቸው አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን፣ መናፍቅ እያለ የስም ማጥፋቱን ቢቀጥልም ገና የቃላቱ ‘መናፍቅ‘ ትርጉም ያወቀው ሆኖ አልተገኘምና ዘመቻው ሁሉ አልሰራለትም። እንዲያውም በMAY 18, 2010 የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ሲሰማ፤ ይኽው ድርጅት አባላት በደብሩ ረብሻ ወቅት ከቤተክርስትያኑ ፎቅ ላይ የስው ልጅ ሊወረውሩ መዶለታቸው በምስክር ከተረጋገጠባቸው ወዲህ ቀልብ ስላጡ ያተረፉት ስም ታላባን፣ ከልት፣ አክራሪ ና ወንጀለኛ ነው።

ደብሩም የተሰለፉበትን የውስጥና የውጭ ጠላቶቹን አስመልክቶ በዚህ ሳምንት ምህላ ላይ ይገኛል። አዲስ መምህር ለመቅጠርም የመጨረሻ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ሲሆን ከዚህ በኃላ የሚቀጠሩ ሁሉ በኮንትራት ሆኖ በየጊዜው እየተገመገመ የሚታደስ በመሆኑ አባሎቻቸውን ሁሉ አስደስቶ ይገኛል።

የርሶን አስተያየት ያክሉበት ዘንድ እንጋብዞታለን።

1 comment:

Anonymous said...

ato eyoel nega bmercha teshenefeu
yatuten seletan bekodita lesemelesu
degafiwchachewon eyasebasbu mehonachewon andande mmenchuch ytkomalu semonun pitishn lebord yasegebut budenochem yezhu tegebar
tebbariwch endehono yminageru ena
endemiktelubetem sinagru tdemetal