Sunday, June 13, 2010

የመረዋው ጋሼ ተኮላ Looser

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ጋሼ ተኮላ (ሉዘር) የመረዋው ኸረ ለመሆኑ እንደምን ተርፈህ ከርመህ ነው አሁንም ያለስራህ ገብተህ የምትፈተፍትው? አንዴ ከምግባር ቢጤህ ጋር ሁነህ የሰው ቤተክርስትያን የከሰስክ፣ የምትደሰኩርልት መብት የሚመጣው ከግዴታ ጋር መሆኑ ያልገባህ ደንቆሮ በምን ቀንቀ ብናስረድህ ይገባህ ይሆን? ጉዳይ ሳይኖርህ ከሳሽ፣ አባል ሳትሆን መብት ጠያቂ፣ ኸረ ለመሆኑ አንተ ከየትኛው ፕላኔት ነህ ወይስ የምትጠጣው ቢራ አስክሮህ ነው እንዲህ የሚያደርግህ፣ በውትድርናህ ጊዜህ የሸተተህ ባሩድ ወይስ ያደክበት ቀዬ የለከፈህ ሰይጣን አሁንም ይጫወትብሀል?

አዎን በእውነት እንላለን አንድ ሰው ለአንድ ድርጅት አባል ሲሆን፤ ጠንቅቆ መብቱንና ግዴታውን አምኖ ይሆናል። ማንኛውንም እንቅስቃሴ በሕጉና በደንቡ ነው። አንተና መሰሎችህ ቤተክርስትያና ከሀይማኖት አገልግሎት ውጭም ያላትን ምግብም ሆነ መጠጥ ያለክፍያ አስተናገደቻችሁ፡ የአንተና የምግባርህ ተካፋዮች ግን የተመገባችሁበትን ወጪት ሰባሪዎች ናችው። አልፋችሁ ተርፋችሁ በስብሰባችሁም ኣኔ ሚካኤል የሚሄደው ለትዝብት እንጂ ለፀሎትማ ሌላ ቦታ ነው የሚሄደው፣ አንተም ራስህ ምዕመናን ወደ ሚካኤል እንድይሄዱ ገንዘብም እንዳይመፀውቱ የቅስቀሳ ዘመቻ እንዳደረክ እና እንደምትቅጥልበት ኃይሉ እጅጉና ሙላው ወራሽ የተባሉት ፀረ ኦርቶዶክሶች ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ፣ በኩራት እንደ ጀግና የተናገርከውና ማኅብር-ቅዱሳኑ መስፍን ኢሕአፓው የቀዳውን ቪዲዮ እንዳለ አላወክምን? ሚካኤልን በተመለከተ መናገር የሚችል የሚካኤል አባል እንጂ እንደ አንተ አይነት የርኩስ መንፈስ ማደሪያ አልተፈቀደለትምና። ይህ መልክት ላንተና ለብጤዎችህ ለነ ሰላም ተዋህዶ ጭምር ነው።

አንዳንድ ቃል የተገባላቸው ለሥልጣንም ሆነ ለስም ስትሉ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ ወይም ጋደኛ ላለማስቀየም ብላችሁ ለርኩስ መንፈስ መጠቀሚያ ፤ አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁ፣ በስህተትም ሆነ በግድፈት በየዋህንት የቀራችሁ ጥቂት ግለሰቦች ንስህ በመግባት አሁኑን ወደ ፈጣሪያችሁ ተመለሱ። የመዳን ሰአቱ አሁን ነውና።

ዕምነታችሁ የተፈተነባችሁ፣ ከቤተክርስትያን ራሳችሁን ለማራቅ የአሰባችሁ፡ ቤቱን በአሽዋ ላይ እንደሰራው አትሁኑ፡ በአለት ላይ ወደ ቆመው ቤተክርስትያን ተመለሱ። አልፎ አልፎ የክርስትናው መንገድ ይጎረብጣልና ጽኑ እርሱ አብሮአችሁ ነውና።

በዛሬው ዕለት አዲስ የመጡትን አባት አባ ምህረትን ይህ ግጽ እንካን ደህና መጡ ይሎታል። እንደስሞም ምህረት እንዲሆኑን ፀሎታችን ነው። በትውውቁ እንደተገለጸው ያልዎት ደረጃና ያካበቱት ዕውቀት ለከተማችን ተመሳሳይ አቻ የሎትምና የበግ ለምድ የለበሱ አንዳንድ ተኩላዎች ቀደም ብለው ሊያጠምዱዎት እንደሞከሩና እዚህም ከደረሱም ሰአት ጀምሮ የተለያዩና የረቀቁ ዘዴዎችን እያቀናበሩ ይገኛሉ። ሌላው በዛሬው ትውውቅና ትምህርቶ፡ ሴት ወንድ ሳይል ካሕናቱን ጭምር ዕንባችንን መቆጣጠር እስኪሳነን ድረስ ልብ የሚነካ ነበር። እንግዲህ እርሶም እኛም ንጹህ ልቦና ይዘን ከቀረብን እግዚሐብሔር ከኛ ጋር ይሆናልና፣ በዛ ፈጽሞ ሀዘን አይኖርም።

እርሶስ ምን ይላሉ?

1 comment:

Anonymous said...

ለመሆኑ እሁድ ያ ሁሉ ሰው የአባልነት ክፍያ ለመክፈል ተሰልፎ ለመክፈል ያልቻለው ለምንድን ነው? ብለን ባካባቢው የነበሩ ሁለት ሶስት ስዎች ብንጠይቅ ኮምፒተር ተበላሽቶ የሚል መልስ አግኝተናል። ብልሽቱ ምን ላይ ነው? የሚለውን ለማወቅ ግን አልቻልንም። ትዝ ይላችሁ እንደሆን ሌላው የጋሽ ተኮላ ወዳጅ የቀድሞው የቦርድ ጸሀፊ የኮምፒተር ሶፍትዌር አላስረክብም ብሎ እስካሁን እቤቱ ይዞ ቁጭ ብልዋል። ቦርድ በነበረበት ጊዜም በገንዘብ ተቀባይነትና ሶፍትዌሩን ከጻፈው ኒክ ከሚባል ከነፍስ ይማር አለማየሁ ጓደኛ ጋር በመሆን በከተማው ያለውን የወያኔ ተወካይ የአመትና የሁለት አመት ክፍያ እይተቀበለ በቤተክርስቲያናችን የሰገሰገ የቤተክርስቲያን ጠላት እንደነበር ልንዘነጋው አይገባም። ይህ ግለሰብ በዚች ቤተክርስቲያን ላይ የሰራው ብዙ ታሪክ ከመኖሩም በላይ ባለፈው ወያኔዎች በቤተክርስቲያናችን አመጽ ባካሄዱበት ስብሰባ ፖሊሶች እያሉ ፎቶግራፍ የሚያነሱትን አዛውንት በእርግጫ መምታቱ የድሮው የማጅራት መችነትና ኪስ አውላቂነቱ ትዝታ እንደገነፈለበት በይፋ ታይቷል። እንደጠላቱ በሚያየው በጎባ ልመና ያችን ማታ ከእስር ድኗል። ከዚህ ወንጀለኛ ተጠንቀቁ ከዚህ የባሰ ወደፊት የሚወጣ ጉድ ብዙ አለበትና። አሁንም የዚህ የኮምፒተር መበላሸት ሲጣራ ከሱና ከወንጀል ጓደኛው ከኒክና ወዘተ….ብዙ እንደማይርቅ እሙን ነው።