Monday, June 21, 2010

ከድጡ ወደ ማጡ

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!

ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።




ከድጡ  ወደ ማጡ
ጠንካራ ዲፕሎማቶችና ኤምባሲዎች ያስፈልጋሉ
SUNDAY, 20 JUNE 2010

ይህ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ቀንና ጥቅስ የወሰድነው ‘ሪፓርተር‘ እየተባለ በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት እየተረዳ የሚወጣ ገጽ ነው። ይኸው ገጽ በርዕሰ አንቀጹ እንደጠቀሰው ያሉትን የዲፕሎማቲክ ሕብረተሰቦችን በበለጠ ዘመቻቸውን እንዲያጠናክሩ ለመግፋት ሲሆን ፣ በዚህ ባለንበት ከተማም ወኪሎቻቸው ያነጣጠሩት በራሳቸው ዜጎች ላይ ብቻ ነው።

እነዚህ ወኪሎቻቸው ከእውነተኛው የዲፕሎማቲክ ስራ አልፈው በከተማችን ውስጥ የተቆቃሙትን የሀይማኖትና የሲቭክ ድርጅቶች ውስጥ ሰርገው በመግባት ሕብረተሰባችንን በመከፋፈል ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ፍለሚያ ውስጥ ይገኛሉ። ከዚህም በቅርቡ በዳላስ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በሜይ 2 የተፈጠረው ሁከት በግምባር ቀደምትነት ያስተባበሩና ተሳታፊ የነበሩት ውስጥ ሶፍያ ዘሪሁንና እህታ የሺ ዘሪሁን የተባሉት ወያኔዎች ወንድማቸው የቀድሞ የዚሁ ከተማ ነዋሪ የነበረና አጎታቸውም ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ቤተሰብ ፤ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም ለመንጠቅ ወይም ለማፍረስ የፈጸሙት ተግባር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የቤተክርስትያኑ ለጊዜው ቢከሽፍም በወኪሎቻቸው አማካኝነት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ከዚህ ባሻገር በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መረዳጃ ማኅበር ውስጥ እንደ አሸን ፈልተው ድርጅቱን ተቆጣጥረው ይገኛሉ። ይኸው የማሕበረሰቡ ድርጅት ሁልጊዜም አንገቱን ቀና ማድረግ ያልቻለው በየጊዜው በአመራር ላይ የሚጠላጠሉት የሚፈጽሙት ተግባር በግል ለሚያምኑበት ርዮተ አለም እንጂ ለኮሚኒታችን አንድነትና እድገት ያደረጉት አስተዋጽዎ በጣም ውስን ነው።

በአሁኑ ሰአት ሁለት አመት ያስቆጠረው እድርም ቢሆን በጥበብ የተዋቀረ ቅርንጫፍ የአባላትን ቁጥር ለመጨመር ሆኖ ከዚሁም በሚገኘው ገቢ፣ ድርጅቱን እድሜ ለማራዘም በዚያም የኢትዮጵያን ተወላጆች አንድነትና ሕብረትን ለመበታተን ከፍተኛ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሚያ ለማድረግ ነው። ምክንያቱም ይህ እድር የተባለው ቅርንጫፍ አካል የሚያስከፍለው ገንዘብና የሚሰጠው ግልጋሎት በፍጹም የማይገናኝ ነው። ምክንያቱም በዚህ ክፍለ ንግዱ ዘርፍ የተሰማሩት የኢንሹራንስ ድርጅቶች የሚሰጡት ግልጋሎትና ክፍያ እጅግ በጣም የበለጠ ብቻ ሳይሆን ኮሚኒቲውን ከሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ በጣም ያነሰና በሕግም ቀጥተኛና ተቀባይነት ያለው ነው። በዚህ አይነት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ የሆናችሁ ወጎኖች በተለይ በዚሁ ዙርያ አስተያየታችሁን በዚህ አጋጣሚ እንድታካፍሉን እንጋብዛለን? እኛም ወደፊት የምናገኛቸውን የዚሁን ንግድ ዘርፍ ጥቅምና ክፍያውን በተመለከት ልናካፍላችሁ እንፈልጋለን።

ሌላው የዚሁ ኮሚኒቲ ልሳን ነኝ የሚለው የራድዮ ክፍል በሁለት ቢላዋ የሚበላ ክፍል ነው። አዘጋጁም ቢሆን ለረዥም ጊዜ በዚሁ ዘርፍ ከመቆየቱ የተነሳ ይመስላል አስተዋጽዎ ለኮሚኒቲው አስመዝጊቤአለሁ የሚለው የረባ የለውም፣ የግል ጥቅሙን አካበተበት እንጂ። በተለይም ለብዙ ግዜ ጸረ- ወያኔ አስመሳይ ዘመቻ ያደርግ በነበረበት አንደበቱ ዛሬ ተቀልብሶ እነዚህ የወያኔና ወኪሎቻቸው በከፈቱት ጸረ- ኦርቶዶክስ ፣ ጸረ-ሀይማኖት ፣ ጸረ-አንድነት ግብር ተካፋይነቱን በዚሁ ራዲዮ ፕሮግራም እያስመሰከረ ይገኛል። በማንኛውም የነሱ ስብስባ በመገኘት እንደ ሪፖርተር ሳይሆን እንደአማካሪና እንደ ሕዝብ ግኑኝነት ተጠሪም እያደረገው ከመሆኑ በላይ በያዘው የራዲዮ ፕሮግራም ጭምር የነሱን ሰይጣናዊ ተልዕኮ ማስታወቂያ አድርጎት ይገኛል። እርሱም ሆነ የድርጅቱ ተመራጮች ከቀን ወደ ቀን የሚወስዱት ጸረ- ሚካኤል ምግባር በሁለቱም መካከል ቆይቶ የነበረውን መተባበር ከመጉዳት አልፎ በከፍተኛ ፍጥነት እየገታው ይገኛል። ድርጊታቸው ሁ ሉ ከድጥ ወደ ማጡ እንዲሉ ሆናል።

የኮሚኒቲው መሪዎችም ቢሆኑ እስከ ዛሬ ድረስ በቤተክርስትያን ውስጥ ተፈጥሮ ስለነበረው ችግር ለኮሚኒቲው አቁዋም ያልገለጠ ሲሆን እንደዚሁም በወቅቱ ሜይ 2 የድርጅቱ ሊቀ መንበር በቤተክርስትያኑ ውስጥ መገኘቱ ብቻ ሳይሆን የሰጠውም አስተያየት በሙሉ ሁካታ ፈጣሪዎቹን ደጋፊነቱን ያረጋገጠ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ተጠናቀቀ ለተባለውና በአይነቱ አቻ ያላስመዘገበው የመንግስት ሕዝባዊ ምርጫ ውጤትን አስመልክቶ ለምን መግላጫ አላወጣም፣ ለኮሚኒቲው አባሎች በትውልድ አገራቸው ውስጥ ስላለው ሶሲዎፖለቲክም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ወይንም ስላለንበት ሀገር አስመልክቶ የሕብረተሰባችንን ግንዛቤ ለምን ሊያጎለብትና ካለው የሌላው መጤ ሊያስተካክል አልቻለም ተብሎ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ እስከ ዛሬ መልስ ያልሰጠ ድርጅት ነው።

ከጥቂት አመታት በፊትም ለግል ጥቅማ ጥቅም ሆነ ለወያኔ ባደሩ ቅጥረኞች፣ የጡረታ ዕድሜ የደረሱና ወደ ትውልድ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ፣ እንደዚሁም ወያኔ ባንዳዎችን ቁጥራቸው በዚሁ ድርጅት ውስጥ ከመቸውም በላይ ጨምሮና አመራሩን ተቆጣጥሮ ይገኛል። በየአመቱ መከበር የተጀመረውንና በቅርቡም የኢትዮጵያ ቀን
ተብሎ የሚከበረውን አመታዊ በአል የወያኔ ኢትዮጵያዊ ቀን ለማድረግ የቅድሚያ ዝግጅቱን ጀምሮ ይገኛል። ለዚሁም መነሻ መድረክ ያደረገው ድሪምስ የምሽት መጨፈሪያ ቤትን ነው። የዚሁ ምሽት ቤት ባለቤት ደግሞ ለወያኔ የሚሰራ  ፤ በከተማችን ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም የኢትዮጵያ ተወላጆችን ያቀፈ የሀይማኖትና የሕብረተሰቦች አገልግሎት ሰጪ የሆኑትን ድርጅቶችን ለወያኔ ማስረከብ ወይንም ማጥፋት ስራዬ ብሎ የተነሳው ሀይሉ እጅጉ (ቀዩ ሰይጣን) የሚባለው ነው። በቅርቡም  ዳላስ ደብረ ምህረት ካቴድራልን ለዚሁ አላማው ሰለባ ለማድረግ ከግብር ቢጤዎቹ ጋር በማበር የተለያዩ ስብሰባዎችን በማዘጋጀት ፣ በመቀስቀስ፣ በማሳደም ፣ ሁከቶች እንዲቀሰቀሱ ፣ የሀስት ክሶች በቤተክርስትያን ላይ እንዲመሰረቱና ሲረቱም ይግባኝ እንዲሉ፤ ከዚህም አልፎ አባል ያልሆኑ ደግሞ አዲስ ክስ እንዲመሰርቱና መሳይ ተግባራትን በቀንዳምነት የሚያካሂድ የሕብረተሰባችን ጸር የሆነ ግለሰብ ነው።

በዚህ መልኩ ለተዋቀረ ድርጅትና ተግባር መሳተፍ አሉታ ብቻ ሳይሆን ሕሊናን እንደ መሽጥ ያስቆጥራል። እንደ ኢትዮጵያ ተወላጅነታችን የማንነታችን መታወቂያ የሆኑትና ብርቅዬ ክብራችንን ማስደፈር ልንፋለመው የሚገባን አበይት ምግባር ነው።


እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: