Sunday, June 6, 2010

ሰላም ተዋሕዶ Selam - Tewahedo

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


ሰላም ተዋሕዶ Selam - Tewahedo


ሰላም ተዋሕዶ - በዳላሰ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ አባላት ችሎታ እጦት ምክንያት በቤተ ክርስቲያኑዋ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጥፋትና ይህንኑ ለማስተካከል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለአጥቢያውና ለአካባቢው ምእመናን የሚያስገነዝብ ፤ በእውነት ላይ የተመረኮዘ ጊዚያዊ ብሎግ ነው፡፡Blogging Since October 2009


‹ከዚህ የመጨረሻ ዕድል በኋላ ግን እጃችንን አጣምረን አንቀመጥም ! መረጃዎቻችንን ይዘን የ I.R.S ን በር እናኳኳለን ! ሕዝቡ ግን ያን ጊዜ ይህ ለምን ሆነ እንዳይለን !

FRIDAY, JUNE 4, 2010
የስብሰባ ጥሪ !

TUESDAY, JUNE 1, 2010
ማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔውን በመልካም ሁኔታ ጀምሮ አጠናቀቀ !

ዛሬ የምናካፍላቹህና የናንተን የአስትያየት ተሳትፎ የምንጠይቀው ከዚህ በላይ ከሰላም ተዋሕዶ ገጽ ያገኘነውን ነው።

ይህ ገጽ የሚታወቀው የዳላስ ማኅበረ ቅዱሳን እየተባለ የሚጠራው ከልት ድምጽ ሆኖ ነው። ከመጀመሪያው አላማውን ሲገልጽ ያነጣጠረው በዳላስ ቅዱስ ሚካ ኤል ላይ ነው። ሌላው ደግሞ ከመንፈቅ በላይ ማስፈራሪያው የግብር ሰብሳቢውን መስሪያቤት ነው። የተሰነጽው ተወልዶ አድጎ እንዳያነብባችሁና እንዳይሰቅባችሁ ፣ ዕውነተ ቢስ ናችሁና በማኅበረ ቅዱሳን ስም የተዘረፈው እያነቃችሁና ሃባዜው እያስለፈለፋቸው ነው።

በFRIDAY, JUNE 4, 2010 የስብሰባ ጥሪ ! በሚል በገጻቸው ያወ ጡት ደግሞ ብጤዎቻቸው ከሌላ ቡድን ሆነው አንዴ በክስ ሌላ ጊዜ ደግሞ እናስታርቅ ወይንም ቦርድ እንገልብጥ እያሉ ጀንበር ለጠለቀችባቸው ጸረ ሀይማኖትና ጸረ ቤተክርስትያኖች ቱልቱላ መሆኑን በግልጽ ያስረዳል። ከዚሁ ሳንወጣ ፣ ከአሁን አሁን ንስሀ ይወስዳሉ ብለን ከምንጠብቃቸው መካከል ኢዮኤል ነጋ ፤ ሀይሉ አራጋው ፤ እንደዚሁም ፈትለወርቅ የቀድሞ ቦርድ አባላትና ሌላ የ11 ግለሰቦች ስም ዝርዝር የያዘ የስብሰባ ፈቃድ ጥያቄ ለቦርዱ ገብቶ ተከለከለባቸው። የዚሁ ኮሚቴ ተወካይና መሪ ደግሞ አዜብ ኃይለማሪያም ስትሆን ያቀፈችው ከወልቃይት ተውላጆችና የባለቤቶቻቸውን ስም ዝርዝር ያካተተ ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ እነ አዜብ የወያኔ ደጋፊ ብቻ ሳይሆኑ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ሚስት የቀረበ ዝምድና ያላቸው ናቸው። ለዚሀም ነው እነ ጌታቸው ትርፌ ወደ ወልቃይት ሲወርዱ በመንግስት ወጪ የመንግስት ወታደሮች 24 ሰአት በአደጉበት ቀዬ ጥበቃ እንደሚያደርጉላቸው በኩራት የሚናገሩት። ሌላው ደግሞ ሳይሆን ወያኔ ነኝ የሚለውና በዋሾነቱ አቻ ያጣው ፣ በምግባሩ ለአመታት ሲጠጣ ከቆየው ጽዋና ዕቁብ የተባረረው ፣ ለአዲሱ የቤተክርስትያን ክስ አስተባባሪ ብቻ ሳይሆን የራሱን ጠበቃ የቸረው ሙላው ወራሽ ከነሚስቱ ፣ ይኼንኑ ክስ የገንዘብ ድጋፍ የማደርገው እኔ ነኝ እያለ የሚኩራራው ሀይሉ እጅጉ ከነ ሚስቱ የመሰሉ ይገኙበታል። የሚገርመው እነኢዮኤል ጥሩ የሰሩትን ስናስታውስ የመጥፎ ስራቸው ውጤት አብረው ማሻሻል ሲገባቸው ለምን አዋኪ ይሆናሉ? እስከምናውቀው ድረስ ለቤተክርስትያን ማገልገል ለዘር የሚተርፍ በረከት ለማግኛ እንጂ ለዝና ወይንም ለክብር አይደለም። ከዚህስ የተለየ ምን ይኖራቸው ይሆን?

ማንም ቢሆን ምንም ሕግም ቢባል ያለውን ቦርድ መለወጥ የሚቻለው ቦርዱ ፈቃደኛ ሆኖ ወይም በሰላም ጊዜውን ሲጨርስ ብቻ ነው። በሌላ መንገድ ለማፍረስም ሆነ ለመለወጥ የሚደረገው ትግል ፍሬ ቢስ መሆኑን ከዚሁ ልናስገነዝብ እንወዳለን ፣ ታገሱም እንላለን። ምክንያቱም የመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ያለው እየተገበረ መሆኑን አልገባ ያላቸውና ፤ ወደ መሰሪ መንገድ የገቡት እንዲሁም አብረው ከኖሩ ወገኖቻቸው የተቀያየሙትን ስላየን ነው።

TUESDAY, JUNE 1, 2010 ማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔውን በመልካም ሁኔታ ጀምሮ አጠናቀቀ ! ይህ የዳላስ ድርጅት አንደበት የሆነ ገጽ ምግባሩና ስሙ ለየቅል ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ አቡነ ጳውሎስን ብሎም የወያኔን መንግስት ከመገልበጥ ወደ ኃላ እንደማይል ባለፈው አመት አዲስ አበባ ላይ ጳውሎስንና መንግስትን አስደንግጣል። ይኽ ድርጅት በቀድሞ ኢሀአፓዎች አሁን ሀይማኖተኞች መሪነት የሚንቀሳቀስ ነው። የተማሩትንና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይዞ ጥሩ ስራ ሲሰራ በሌላ ጎኑ ደግሞ ፖለቲካና ጸረ ክርስትና ስራ የሚያራምድ ቡድን ከሀገር ቤት አልፎ በየትኛውም ክፍለ ዐለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ተ ሰራጭቶ ይገኛል። በዳላስ ሚካኤልና በሌሎቹም ውስጥ ነጠላ ለብሰው ሲያስቀድሱ፣
በመዘምራንነት፡፣ በትምህርት ክፍል፣ በበጎ አድራጎት፣ በህጻናት ክፍልና በሌሎችም ውስጥ በመሳተፍ ቤተ ክርስትያንን የሚያደሙ፣ በጣባብነት የተወጠሩ፣ ወዘተ……. ናቸው። ሚካኤል ውስጥ በመዘበሩት ሊጋለጡ ሲሉ፤ ከተራ ምዕመን ቀሳውስትና ቦርዱንም ጭምር ለመለያየት የረጩት መርዝ ያልዳኑት ዛሬም ቤተ ክርስትያንን ሲጣሉዋት ይታያሉ።

እርሶስ ምን ይላሉ?

No comments: