ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
ሰላም ዳላስ
ብዙዎቻችሁን በዚች አምድ አጭር ቆይታ ለተሳትፍዎቻችሁ ከልብ እናመሰግናለን። መወያየት ካልተቻለ መተቸት እንደአጸያፊ ተደርጎ በባሕላችን ይቆጠራል ። ብዙውን መጣጥፍ የመጣው ከናንተው ተሳትፎ ነው።
በጥቂት አመት የዳላስ ቆይታችን ብዙም ከሕብረተስቡ ጋር ሳንቀላቀል በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ለመተዋወቅ ቢያበቃንም ለኮሚኒቲው እንግዳ ሆነን ነበር። በኛ ግንዛቤ ሕብረተሰቡ እርስ በራሱ ተጠራጣሪ፣ ለማወቅ ከመፈለግ ይልቅ እንደሚያውቅ ራሱን ማድረግ፣ ከስህተት አለመማርን፣ ችግሮችን በቀና መንፈስ ተወያይቶ መፍትሔ አለመፈለግን፣ በተለየ ዩልኝታ የሚባለው ነገር ፣ አስመስሎ ማደር፣ ሀቅን አለመቀበል፣ በሰሩት ስማቸው በነቀፋ መውጣቱ የሚቆጫቸውን፣ ወዘተ…… ከሚደርሱን መልዕክቶች ተረድተነዋል።
እኛ ደግሞ በተለያየ የአሜርካን ግዛት በስራ ምክንያት በቆየንበት ቦታ በብዛት የኢትዮጵያ ተወላጆችን ሳናይ አመት የቆጠርንበትን ጊዜ ፣ ፈጣሪ ምስጋና ይግባውና የእንጀራ ናፍቆታችንን አሁንማ በፌዴክስ እየተወጣን፣ ቅዳሴ በድሕረ ገጽ እያካሄድን ፣ ኸረ ስንቱን ቆጥረን…….እናንተ ግን ፈጣሪ በብዙ የሰጣችሁ ፤ መቻቻል የሚባለውን መተግበር ያቃታችሁ ፣ እስቲ ወደ ኃላ ዞር ብላችሁ የመጣችሁበትን ቀዬ ወይንም መንደር በዐይነ ህሊናችሁ ቃኙ? ሕብረተሰቡ እንዴት ነው የሚገኘው? በሰው ሀገር መጥታችሁ በሕብረት ያከናወናችሁትን ለምን በመናናቅና ባለመስማማት ታጠፉታላችሁ? ተረጋጉ ፣ ተደማመጡ ፣ በቅንነት ተወያዩ ፣ ለአዲስ አመለካከት ሕሊናችሁን አዘጋጁ ፣ በየጊዜው የሚነሱትን የጋራ ችግሮች ሁሉ በወቅቱ አስተናግዱ ለወደፊቱም ቅድሚያ ዝግጅት አድርጉ፣ በኃላፊነት የምትመርጡትን የተከታታይ አገልግሎት ዘመኑን ከሁለት ጊዜ በላይና ቢያንስ የአምስት አመት ዕገዳ ዳግመኛ ለመመረጥ ቢሆን የበለጠ ፍሬ ይኖረዋል የሚል ግምት አለን። በተለይም ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕውቀት ጋር የሚራመዱትና ዘመናዊ ትምህርት ያላቸውን መቀላቀሉ ጥቅሙ ከፍ ያል ይሆናል ብለን እናምናለን።
ይህቺ አምዳችን በአንባቢዎቻ ድጋፍና በሚሰጡት ጽሁፎች የተመታችሁ፣ የቆሰላችሁ ፣ ያዘናችሁ ሁሉ በሰጣችሁን አስተያየት ስለተሰማችሁ ሁሉ አምዳ ከልብ ይቅርታ ትጠይቃለች። ያለ አግባብ በዚህ አምድ ምክንያት የታማችሁ፣ ጣት የተጠነቆለባችሁ ፣ ንጹህነታችሁና መብታችሁ የተነካባችሁ ሁሉ ይቅርታ እየጠየቅን በዳላስ አካባቢ የእንደዚህ አይነት መወያያ መድረክ አስፈላጊነቱ በሚገባ የምናምንበት ስለሆነ ሌሎችም እንዲቀጥሉበት እናሳስባለን!
በመጨረሻም የውቂያኖስ ሳይንስ፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ሳይንስ፣ የውቂያኖስ ጥበቃና መከላከል ምርምር ሳይንስ፣ የዘይት ሀብት ልማትና ጥበቃ ምህንድስና፣ በውቂያኖስ ውስጥ ጥልቅ የዘይት ፍለጋ ምርምርና በመሳሰሉት ሙያ ዕውቀት ያላችሁ ወገኖች በአማካኝ የ36 ወራት የስራ ዕድል በደቡብ ምስራቅ የባሕር ሰላጤያችን በጥብቅ ይፈለጋልና ይህ መልክት ይድረሳችሁ። በተረፈ በዚህ የመጨረሻ የዳላስ አካባቢ ምሽታችን ስንብት ስናደርግ ፤ ከገልፉ አሳ ተርፈን የሄድንበትን አጠናቀን የት እንደምንሰፍር ባናውቅም በቆይታችን ከጎበኘናቸው የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች በንጽህና ፣ በዋጋ እንደዚሁም በአገልግሎት ለአዲሱ አይቤክስ ብናደላም ገና ብዙ ይቀረዋል ፣ የሚቀጥለው አዲስ አበባ ሲሆን የተቀሩትም በሚገባ ደረጃ የሚመዘኑበትና የሚሻሻሉበት መንገድ እንዲወስዱ ከዚሁ እንጠቁማለን። በተረፈ በመካከላችሁ ሰላም ወርዶ በፍቅርና በመተሳሰብ ለጋራ እድገት እንድትቆሙ ከልብ እንመኛለን።
ሰላም ዳላስ
No comments:
Post a Comment