የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነ
ይድረስ ለአቶ ኃይሉ አራጋው፡ -
ይህ አምዳችን በ06/13/2010 ባወጣው ላይ አንተን የሚመለከት አስተያየት ተሰንዝሮብሀልና መልካም ፈቃድህ ሆኖ መልስህን ለሚመለከታቸው ወይንም ለዚህ አምድ ትገልጽን ዘንድ በእግዚሐብሔር ስም በትህትና እንጠይቃልን?
እንኻን ለበረከት ተብሎ ግልጋሎት ለሚሰጥበት ሀይማኖታዊ ቦታ፣ በአለም ውስጥም ማንም በአገልግሎቱ ምክንያት በእጁ ያሉትን ለተተኪው ወይንም ለሚመለከትው አካል የማስረከብ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን በሕግም ግዴታ ጭምር እንዳለበት ለአንተ ማስረዳት ተገቢ አይመስለንምና ፤ ስምህ በዚህ ምክንያት ተነስቶ መጠቀስ ተገቢ አይደለም ። በተለያየ ምክንያት ሳይመችህ ቀርቶ ስለሚሆን ስለ ቅዱስ ሚካኤል ብልህ ባስቸክይ እልባት እንድታደርግለት በትህትና እንጠይቅሀለን። ባንተ ምክንያት ሰበብ እንዲሆን መልካም አይሆንም ። ቀድሞ የሰጠኸውን አገልግሎት እንዲቆጥርልህ አሁንም የቦርድ አባል ብቻ መሆን የለብህም በምትችለው ሁሉ የእግዚሐብሔርን ቤት ማገልገል የሁላችንም ግዴታ መሆኑን እያስገነዘብን፣ አንተም ያካበትከውን እውቀት በስራ በማዋል በአርያነት ማሳየት ይጠበቅብሀል። እልህ፣ ቂምና በቀል፣ ስምና ዝና ወይንም ንቀት ለማንኛውም ወገን በጌታ ቤት ቦታ የለውምና።
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment