የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።
እናስተዋውቃችሁ፡-
ዛሬ የምናስተዋውቃችህ እነዚህ ሁለት ግለሰቦች ስማቸው፡-
1ኛ/ ዶ. ሰለሞን አበበ
2ኛ/ ኪዳኔ አለማየሁ በቀንደኝነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ሰሎሞን አበበ ማለት ቀደም ብሎ በንጉሡ ስርዐት ለማባበያነት እድል ከተሰጣቸው ወገኖች ውስጥ ለትምህርት በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ወደውጭ ሀገር ተልኮ ከተመለሰም በኃላ ይህን ለሀገሬ አድርጌ ብሎ ያስመዘገበው የሌለው የከተማ አውደልዳይ፣ ሀገራችን የተማረ ያለህ ብላ በምትማጸንበት ወቅት ክዶ ለተባበሩት መንግስታት በመቀጠርና ጡረታ እስኪወጣ ድረስ፣ ከዚያም የልጆቹን እናት ክዶ ወደ አሜሪካን በመምጣት ከሀገሩንና ከወገኑን ይልቅ የራሱን የግል ጥቅም የሚያስቀድም፣ ከሁሉም በላይ የተባበሩት መንግሥታትና የኢትዮጵያ መንግስት ጡረተኛ ፣ የራሱ ቤት በጋርላንድ ከተማ ያለው፣ የተለያይ ጥቅማጥቅሞችን ከአሜሪካ መንግስት የሚወስድ፣ በወር 30 ዶላር መክፈል ማለት በቀን አንድ ዶላር ለቤተክርስትያን የአባልነት ክፍያ ላለመክፈል ያመለከተ በጣሙን እርካሽ የሆነ ግለሰብ ነው።
ይኸው ግለሰብ ወደ ዳላስ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሕብረተሰባችን ጋር ተመሳስሎ ከመኖሩም በላይ የቀድሞ የሚካኤል አስተዳደር ቦርድና በፈቃዱ ከምዕመናንና ከፈጣሪ የተሰጠውን አገልግሎት ጥሎ የኮበለለው የኢዮኤል ነጋ ቀኝ እጅ የነበረና አሁንም የሆነ ግለሰብ ነው። ሰሎሞን አበበ ወያኔ ያሰረው የበደለው አርጎ ሲኮንን በሌላ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ያለ ችግር ይመላለሳል እንደውም የነሱ ነውም ይባላል። እኛም እስከምናውቀው ድረስ ኢዮኤል ሊቀመንበር በነበረበት ወቅት የሱ ምስጥረኛ ብቻ ሳይሆን የደብሩም እቡዕ ዋና ጸሐፊ በመሆን አብዛኛውን የኢዮኤል ፊርማ ያለበትን ሰነዶች የተላላከና በግሉም የወሰደውን ውሳኔም በሊቀመንበሩም ሆነ በቢጤዎቻቸው ጥያቄ ያላጋጠመው፣ ኣስካሁን ሰአት ድረስ ኮምፒተር መሀይሙ ኢዮኤል ኢሜል ተቀባይና መላሽ ፣ አማካሪውና ልዩ ሚስጥርኛ ብቻ ሳይሆን ኢዮኤልን ከጀርባ ሆነው ከሚያሽከረክሩት ከነ ጌታቸው ትርፌ የበለጠ ቦታ ያለው ነው። ከርሱም ጋር ከገጠመ በኃላ ኢዮኤል ራሱን ከሌላ ፕላኔት የመጣ ወይም ራሱን እንደ አምላክ ማየት የከጀለው።
ሰሎሞን አሁንም በቤተክርስትያኑ በሚሰጡት የምሽት ትምህርቶች ላይ በመምጣት ስለላን ማካኼድ፣ ከየቦታው የሚሰበስባቸውን መጻሕፍቶችን እንድ ሱቅ በደረቴ በውድ መሸጥ ብቻ ሳይሆን፣ የሚጋበዙትንም አስተማሪዎችን በጎ ስራቸውን ለማደናቀፍ ስውር ደባ ፈጻሚ ነው። ከጥቂቱ በትንሹ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቃቸውንም ሆነ እነርሱን በመጠቀም በመተዋወቅ ከደብራችን ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖራቸው መጥፎ መርዝ በመርጨት ከነኢዮኤል ጋር እየሰራ ያለ ፣አዛውንት መባል የማይገባው አስነዋሪ ስራው ቢቆጠብ፣ የሚቀበለው የስጋወደሞ ባያስቆጣ እንላለን። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ትውውቁን ምክንያት በማድረግ አዲስ የተቀጠሩትን መነኩሴ ከጥቂት ሳምንት በፊት ታጋብዘው በመጡበት ወቅት ወደኢዮኤል ቤት ድረስ ወስዶ ያስተዋወቀና በትላንትናው እለትም ወደዚሁ መነኩሴ አባርትመንት ድረስ በመውሰድ ያገናኘ ነው። እኛ በግላቸው ላላቸው ጉዳይ ባያገባንም ቂመኛው ኢዮኤልና የሰሎሞን መርዝ ለደብራችን እንዳይተርፍ ለማሳሰብ ነው።
ባለፈው እሁድ ገጻችን እንዳስነበብነው ‘ የበግ ለምድ የለበሱ……….’ ያልናቸው እነዚህንና ቢጤዎቻቸውን ነው። ሎላው ደግሞ ኪዳኔ አለማየሁ የተባለው እንደ ሰሎሞን አበበ ተመሳሳይነት ያለውና ያስተማረውን ወገን ከድቶ እንደቢጤው ለተባበሩት መንግሥታት ከዚያም ለዐረብ አገር የሰራ፣ ጡረተኛ ነኝ ብሎ ወደ ዳላስ ከመጣ ጀምሮ ሳይሳካለት ቀረ እንጂ ያልሞከረው የለም። ሀይማኖተኛም ነኝ ብሎም ከቀድሞ የትምህርት ቤት ጋደኞቹ ጋር በመሆን በኢዮኤል አጋፋሪነት የተወጋገዙትን ጳጳሶችን እናስታርቅ ብሎ ለጳውሎስ ሎሌ የሆነ፣ በቤተክርስትያናችንም ውስጥ ለነበሩት ችግሮች ሁሉ በእጅ አዙር የሚመርዝ ብቻ ሳይሆን ምዝበራ ውስጥም እጁን የዶለ ግለሰብ ነው። ገናም መቀጠራቸው ይፋ ሳይሆን አዲሱን መነኩሴ ያሉበት ከተማ ድረስ እጅጉን ስራዬ ብሎ በሰው አፈላልጎ ለመተዋወቅ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም።
የመጡ ዕለትም ቤተክርስትያን ድረስ በመሄድ የተዋውቀ የመጥፎ ምግባር ማደሪያ የሆነ ግለስብ ነው። ስለ እርሱም ሆነ ስለሌሎቹ ጸረ-ኦርቶዶክስ በሰፊው ከነ መረጃው ሰንበቴ በተባለው ገጽ በተለያየ ጊዜ በሰፊው የውጣ ስለሆነ ያንን ገጽ እንድትመለከቱ እንጋብዛለን።
ከሁሉም በላይ እኛን የሚገርመን ቢኖር ‘ አንድ ህይማኖትና አንድ ዕምነት ‘ ያለው ምዕመን ለምን ጥላችና ጠብ ውስጥ እርስ በራሱ ይገባል? የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ምንድን ነው? እስቲ ሁላችንም ወደ መልካም መስመር ፣ ወደ ፈሪሀ እግዚሐብሒር እንመለስና እኛም ጣታችንን በመጥፎው ልይ ከመጠንቆል ፣ እከሌ እንዲህ መልካም አደረጉ ብለን ለመዘገብ እንዲያበቃን መልካም ፈቃዱ እንዲሆንለን እንጸልይ፣ ከልባችን ካደረግነው የሱ ማደሪያ እንሆናለንና።
እርሶስ ምን ይላሉ?
No comments:
Post a Comment