Friday, June 4, 2010

የደንቆሮ ጩኽት መልሶ መልሶ……

የርሶ ብዕር አስተያየት ተሳትፎ ሕብረተሰባችንን ይጠቅማል ያሉትን አይንፈጉን ገንቢነቱ ቦታ ይኖረዋልና!ማሳሰቢያ፡ ይህ ገጽ የተዘጋጀው የተለያዩ የኅብረተሰባችንን ሀሳብ ለመለዋወጫ እንጂ ለሚሰጡት ማንኛውም አስታየቶች በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ አይደለም። ጉግል ድርጅትም ኃላፊነት አይወስድም። ኃላፊነቱ በሙሉ የአስታየት ሰጪው ብቻ ነው።


የደንቆሮ ጩኽት መልሶ መልሶ……

የኢትቶጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ደብር በዳላስ፤ የቆዩበት የውስጥ ችግሮቹ አደባብይ ከወጡ ከረም ብለዋል።

እንደተረዳነው ከሆነ ችግሮቹ የተፈጠሩት ከዕምነቱ ሳይሆን፤ ከልባቸው ዕምነቱን ከተቀበሉትና ከአንገት በላይ ዕምነታችን ነው ከሚሉት መካከል ነው። ይኽንን ለማለት ያበቃን፣ አንድ ዕምነት ይዞ የሚከተል የሀይማኖት ተከታይ ሀይማኖቱን መሰረት ያደረገ እንዴት ይለያያል? ከዚኽም በላይ ሀይማኖታዊ ችግሮች ሁሉ የሚፈቱት በሀይማኖታዊ መንፈስና መንገድ መሆኑ እየታወቀ ለምን ወደ ፍርድ ቤት መሄዱ አስፈለገ? የዕምነት ማነስ ወይስ ዕምነተቢስነት? የዕምነት ልዩነት ከሆነስ የእውነተኛ አማኝ ተግባር ለምን ዕምነቱን ለፈተና እንዲሁም ለአለም ፍርድ ይሰጣል? የትኛው የክርስትና ዕምነት ነው ወይስ በነቢያት ነውስ ወይ በሐዋርያት፣ በህግ፣ በቅዱስ መጻህፍት አሊያም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምናትና ህግ ልዩነታችሁን በፍርድ ቤት አድርጉት የሚል? በደብሩ የሀይማኖት ተግባር የተቃረኑ ከሆኑ ለምን እራሳቸውን እንደቃሉ አይለዩም? እራሳቸውንም ሐዋሪያት ወይስ የሀይማኖት አርበኛ እያደረጉ ነውን?

በዚህ ወቅትና ሀገር እየኖርን ያስገረመን ነገር ቢኖር፤ በፍርድ ቤት እራሳቸውን ሽማግሌ ብለው ለደብሩ ከሳሾችና ጸረ ሀይማኖቱ ምግባር ላይ ላሉ ግለሰቦች ዕማኝነት የቀረቡት ግለሰብ ቀደም ሲል ለደብሩ የከሸፈ አዲስ ሕግ አውጭ ብቻ ሳይሆኑ በፍርድ ቤት ላይ ተይዞ ባለ ጉዳይ ላይ ፤ ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ (ደብሩ) የሕግ ጠበቃ ይዘው እየተካሄደ ባለ ሂደት ውስጥ፣ ያለሁለቱም ወገን ጠበቃ እውቅና ውጭ፣ ተከሳሽ ክሱን ሳይሰርዝ፣ የሕግን መንፈስ በተቃረነ መንገድ ላስታርቅ እያሉ በተመሳሳይ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ጊዜን ማስቆጠራቸው ብቻ ሳይሆን ስራ ፈትተው ቦርዱንም ስራ እያስፈቱ ይገኛሉ። የዚህ እኩይ ምግባር ግምባር ቀድም ተሳታፊ ግለሰቦች ውስጥ የሚከተሉት ስሞች ይገኙበታል።

1ኛ፡ አቶ ተፈራወርቅ አሰፋ ሊቀመንበር
2ኛ፡ አቶ ግርማቸው አድማሴ ም/ሊቀመንበር
3ኛ፡ አቶ ብርሃነማርቆስ ታደሰ ፀሐፊ
4ኛ፡ አቶ ሳሙኤል ደንቢ ፈረጃ ቃለ ጉባኤና የእቅድ ሥራ
5ኛ፡ ዲ/ን አርአያ ኃይለመስቀል የኃይማኖት አማካሪ
6ኛ፡ አቶ ንጉሤ ጀንበሩ የፍትሕና የሕግ Aማካሪ
7ኛ፡ አቶ ቢራቱ ዎዳ የፍትሕና የሕግ አማካሪ
8ኛ፡ አቶ ደመላሽ ደበበ የሕዝብ ግንኙነት
9ኛ፡ ወ/ሮ በየነች መኮንን የሕዝብ ግንኙነት 2

እነዚህና መስሎቻቸው ያወጡት መግለጫና ውሳኔ ምግባርም ቢሆን ጸረ ሀይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን ጸረ ደብርም ጭምር ነው። በአውኑ ሰአት የደብሩ ቦርድ ተመዘበረ የተባለውን ገንዘብ በውጭ የሂሳብ መርማሪ እንዳይመረምር ለማደናቀፍ ፣ በአውኑ ሰአት ግምቱ ወደ መቶ ሺህ ዶላር ይጠጋል ተብሎ የ ሚገመተውን የህግ አማካሪ ወጭ በተፈረደባቸው መሰረት ከከሳሾች ላይ በሕግ ጠይቆ እንዳያስመልስ ለማድረግ፣ጠንካራና ጥሩ ስራዎችን በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ያሸነፋቸውን ቦርድ ለማፍረስ የሚካሄድ ብሎም ቤት ክርስትያኑን ካልቻሉ ማዘጋት መሆኑ በግልጽ ኣየታየ የመጣ ሀቅ ሆናል። ሙሉ ዝርዝሩን ከዚህ በከሳሽ ወገን ከሚዘጋጅ ገጽ ያንቡትና አስታየቶን ያካፍሉን።
http://merewametta.blogspot.com/
THURSDAY, MAY 27, 2010 ወደ መጨረሻው ላይ ይገኛል።

1 comment:

Anonymous said...

ይኽቺ ደግሞ አዲስ መጥ መሆና ነው ወይስ ሰንበቴ እንቅፋት መታት ወይ? ቸሩ ፈጣሪ ሁላችሁን ይጠብቃችሁ ።

ማለፊያና ትምህርት ሰጪ ስለሆነች እደጊ በርቺ ከጠላትና ከዓይን ይጠብቅሽ ተባረኪ ብዬ ኣመኝልሻለሁ።

ቸሩ ፈጣሪ ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን !
መሪዎቻንና ቀሳውስቶቻን ይጠብቅልን !
በክፋት የተነሱባትን ልቦና ሰብሮ ለንስሐ ያብቃልን !
በመካከላችን ሠላምና ፍቅር ያውርድልን !
አሜን!